Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በቻይና ዢያሜን እና በብራዚል ሳኦፖሎ መካከል እየሰጠ ያለውን የዕቃ ጭነት አገልግሎት ሁለተኛ ዓመት አከበረ። ይህ በሁለቱ ከተሞች መካከል በሚደረገው የዕቃ ጭነት አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለቱን አህጉራት ንግድ ትስስር ይበልጥ ያጠናከረ ሲሆን እስካሁን በሁለት ዓመታት ውስጥ በተደረጉ 474 በረራዎች ወደ 33,226 ቶን ያህል የዕቃ ጭነት ማጓጓዝ ተችሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ባለው አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት አለም ዓቀፍ የዕቃ ጭነት አገልግሎት ላይ የላቀ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ፓን አፍሪካዊው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተካፈሉ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ክብር ይሰማዋል!
በዛሬው ዕለት የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ጆሴፍ ቦካይ፣ ክቡር ኤቭራስቴ ንዳሺሚዬ የብሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት፣ ክቡር ፎውስቲን ታውዴራ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እንዲሁም ክቡር ሙሃማድ ጃሎው የጋምቢያ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ምርጫቸው በማድረግ ወደየሀገሮቻቸው ተመልሰዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠውን የላቀ አገልግሎት በማጠናከር አፍሪካውያንን እርስበርስና ከተቀረው ዓለም ጋር የማገናኘት ተልዕኮውን በትጋት ይወጣል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ ፤ ከ140 በላይ መዳረሻዎቻችን የማይረሱ ትዝታዎችን ያሳልፉ! ለስራ አሊያም ለመዝናናት የሚመርጧቸው መዳረሻዎቻችንን ያጋሩን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ትሶኮአኔ ሳሙኤል እንዲሁም የካሜሩን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ጆሴፍ ንጎቴ የኢትዮጵያ አየር መንገድን መርጠው ከእኛ ጋር ስለተጓዙ ክብር ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም ጉዞ ልዩ የሚያደርገው የራሱ ማስታወሻ አለው። ቀጣዩ ጉዞዎን ከእኛ ጋር በማድረግ አዲስ ትውስታን ይፍጠሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአስደናቂ የተፈጥሮ ውበቷ እና በመዝናኛ ስፍራዎቿ ወደምትታወቀው ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የማይረሳ ጉዞ ያድርጉ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ አንጌላ ራይነር እና የልዑክ ቡድናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመጎብኘት በመምጣታቸው ላቅ ያለ ክብር ተሰምቶናል!
ክብርት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የልዑክ ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በነበራቸው ቆይታ የአየር መንገዱ የሥራ ክፍሎች የሆኑትን የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል እና የተግባራዊ በረራ ማሰልጠኛ ምስለ በረራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በመቀጠልም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከአቶ መስፍን ጣሰው እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘመናዊ አውሮፕላኖቹ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ሂትሮው፣ ለንደን ጋትዊክ እና ማንችስተር ከተሞች አሥራ ስድስት ሳምንታዊ በረራ በማድረግ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ