ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርሻለር ከአውሮፕላን ፓይለት ጋር ምን እየተነጋገሩ ያለ ይመስልዎታል? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Anonymous Quiz
15%
ሀ. ለመብረር ተዘጋጅ
80%
ለ. ቁም
2%
ሐ. ወደ ግራ ታጠፍ
1%
መ. ወደ ቀኝ ታጠፍ
2%
ሠ. ወደ ኋላ ተመለስ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መንደር (ET-Village) ሕፃናት እና ታዳጊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝታቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ልቆ እንዲቀጥል ያስቻሉትን የተለያዩ የስራ ክፍሎች እና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሕፃናትና ታዳጊዎቹ በተለያዩ የአየር መንገዱ ባልደረቦች ገለፃና ማብራሪያ የተደረገላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዙሪያ የተዘጋጀ ጥያቄና መልስ ውድድርና መሰል አስተማሪና አዝናኝ መርሐግብሮች ተሳትፈው የተዘጋጀላቸውን የማስታወሻ ሽልማቶች ተቀብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መኖሪያ መንደር (ET- Village) አየር መንገዱ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ለ5ሺህ ሰራተኞች የምዕራፍ ሁለት የመኖሪያ መንደር ግንባታ እያካሄደ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ