Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኝት ውይይት እና የስራ ጉብኝት አደረገ።

የተለያዩ የሚዲያ ሃላፊዎች በተገኙበት በዚህ መርሃግብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃገር ውስጥ ካሉ የሚዲያ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ገለፃ እና ጉብኝት ተደርጓል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ ቀዳሚ በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በልዩ ምቾት እና መስተንግዶ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለእያንዳንዱ በረራ ስኬታማነት የበረራ ክፍል ባልደረቦቻችን በጠንካራ የስራ መንፈስና በጋራ መስራት ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረክታል ።

https://www.youtube.com/watch?v=IrSvv4ALWsc

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፋናብሮድካስቲንግኮርፖሬት
ብሔራዊ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች አለም አቀፍ ሙያ በሆነው አቪዬሽን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ አመልካቾች የጽሁፍ ፈተና እየሰጠ ይገኛል።

የመግቢያ ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በአዳማ ፣ አምቦ ፣ አርባ ምንጭ ፣ አሶሳ ፣ ባህር ዳር ፣ ደሴ ፣ ድሬዳዋ ፣ ጋምቤላ ፣ ጎንደር ፣ ሀዋሳ ፣ ጂግጂጋ ፣ ጅማ ፣ መቀለ ፣ ነቀምት ፣ ሮቤ ፣ ሰመራ ፣ ወልቂጤና አዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨስርቲዎችና የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት አመቺ ትራንስፖርት በሌለባቸው ቦታዎች ጭምር በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራዎ ቹ በመጓዝ በሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ያሉ ወጣቶች ብሔራዊ ሀብት የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀላቅለው ራሳቸውን አየር መንገዱንና ሀገርን እንዲጠቅሙ ለማስቻል ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ