የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ አቡጃ በተካሄደው የቱሪዝምና ትራንስፖርት ኤክስፖ ለናይጄሪያ የቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት በዓየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ "Outstanding Onboarding Experience Achievements” ሽልማት ተበረከተለት። ይህ ዓመታዊ የቱሪዝም ኤክስፖ የትራንስፖርት ትስስር ለቱሪዝም ዕድገት በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ወሳኝ ሚና ያላቸው የተለያዩ ተቋማት ተሳትፈውበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገፆች የአክሱም ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል የአየር ትራንስፖርት ትኬት ዋጋ ላይ ከውድ ደንበኞቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስቱዲዮ ተገኝተው የሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ እንድትከታተሉ ጋብዘናችሗል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ @FanaBroadcastingCorporate https://www.youtube.com/watch?v=2bc7FovnJvw
#የኢትዮጵያአየርመንገድ @FanaBroadcastingCorporate https://www.youtube.com/watch?v=2bc7FovnJvw
YouTube
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ ማብራሪያ።
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገፆች የአክሱም ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል የአየር ትራንስፖርት ትኬት ዋጋ ላይ ከውድ ደንበኞቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስቱዲዮ ተገኝተው የሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ እንድትከታተሉ ጋብዘናችሗል።#የኢትዮጵያአየርመንገድ @FanaBroadcastingCorporate
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአቪዬሽን መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአቪዬሽን ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ከ460 በላይ ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ መካከል ከ10 የአፍሪካ ሀገራት መጥተው ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች ይገኙበታል። ዩቪቨስርቲው በዛሬው ዕለት132 በአብራሪነት፣ 123 በበረራ ላይ መስተንግዶ፣ 128 በማርኬቲንግ እና ሽያጭ እንዲሁም 84 በአውሮፕላን ጥገና ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን አስመርቋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ