Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
92.2K subscribers
3.88K photos
146 videos
2 files
416 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ ለኢትዮጵያ) ስርዓቶቻቸውን በማቀናጀት ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሰነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን ምዝገባ ከመያዝ ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያለውን የመንገደኞች አገልግሎት ባዮ ሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ ይሰራል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፋይዳ
October 29, 2024
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትህትና በተላበሰ ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ሊያገለግልዎ ሁሌም ዝግጁ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
October 29, 2024
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” ሽልማት መቀዳጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
October 30, 2024
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሲሸልስ “አንድ ትኬት ይግዙ አንድ በነፃ ይሸለሙ” የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል:: የዚህ ልዩ ቅናሽ ሽያጭ ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 6፣ 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ጉዞዎን ከህዳር 1፣ 2017 እስከ ታህሳስ 22፣ 2017 ያድርጉ። ደንብና እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሲሸልስ
October 31, 2024
መግለጫ
በዛሬው ዕለት አንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚል መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራን አየር ክልል እንዲጠቀም ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የተሰጠው እና የኤርትራ አየር ክልልን ለመደበኛ በረራ እየተጠቀመ መሆኑን እያረጋገጥን በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገለፀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
October 31, 2024
በአፍሪካ የመጀመሪያው ኤርባስ ኤ350-1000 ላይ ምቹ እና አይረሴ የበረራ ጊዜ የሚያሳልፉባቸውን ጊዜያት ለመፍጠር ዝግጅታችንን በማጠናቀቅ ላይ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #A350-1000
November 1, 2024
ለአፍሪካ አሕጉር የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ልንረከብ እነሆ ሶስት ቀናት ብቻ ቀርተውናል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኤርባስA350-1000 #በአፍሪካቀዳሚ
November 2, 2024
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር የሚያቀርበውን ሳምንታዊ “የኢትዮጵያ” የተሰኘ በአየር መንገዳችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ፕሮግራም እንድትከታተሉ ጋብዘናችሗል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
November 2, 2024
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንግላዴሽ ዳካ የሚያደርገውን አዲስ በረራ ዛሬ ምሽት ጀመረ። የበረራውን መጀመር በማስመልከት በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ሲክደር ቦዲሩዛማን፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ክፍል ዋና ሀላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ደማቅ የበረራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተከናውኗል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
November 2, 2024