ስቱዲዮ ውስጥ በሚኖር መቀላለድ፣በሚያመልጥ ሳቅ... ጋዜጠኛዋ መባረሯ ገርሞኛል። ይህ በታላላቅ ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ውስጥ በሚሰሩ ጋዜጠኞች ዘንድም የሚያጋጥም ነው።
በእኛ እና በእህታችን መካከል ያለው ልዩነት፤የእኛ ሳቅ ወደ አደባባይ አለመውጣቱ ብቻ ነው። በተለይ ከእህቴ ከገሊላ ጋር ማዕደ ኢሳትን ስንሰራ የቀለድናቸው ቀልዶች እና የሳቅናቸው ሳቆች ፤መቼም የምረሳቸው አይደሉም። "ስቱዲዮኮ ሰይጣን ነው"ይላሉ አንዳንድ ጋዜጠኞች የማያስቀው ነገር ስቱዲዮ ውስጥ ሳቅቸውን ስለሚያመጣው። ደግሞ ተኮራርፎ ከመስራት፤ እየተሳሳቁ መስራት ሥራን ያሳምራል።የሥራ መንፈስን ያነሳሳል።
ምናልባት እኛ ጋር ነገሩ የከረረው ፤ሁሉን ነገር ከብሔር ጋር ስለምናገናኘው ይሆን?
ግዴለም ተረጋጉ።ቀለል አርጉት።

"ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ምርጫ ቅንጦት ነው። አንድ ተረት አለ። ጭንቅላት ካለ ነው ጥምጣም የምትጠመጥምበት። ጭንቅላቱ ከሌለ ግን ምኑ ላይ ትጠመጥመዋለህ? ምርጫ ሊካሄድ የሚችለው መንግሥት የሚቆጣጠረው ቦታ ሲኖር ነው።
ዛሬ አማራ ክልል ውስጥ መንግሥት ባህር ዳር እና የተወሰኑ ጥቂት ቦታዎች እንጂ ክልሉ በቁጥጥሩ ስር አይደለም። በኦሮሚያ ክልል ውስጥም ከተወሰኑ ዋና ዋና ከተሞች ውጪ ሌላው የአማፂያን መፈንጫ ነው። ኢትዮጵያ ካላት 547 የፓርላማ የምርጫ መቀመጫዎች ውስጥስንቱ ቦታ ውስጥ ነው ምርጫ ሊካሄድ የሚችለው? ኢትዮጵያ ካላት 547 የፓርላማ ወንበሮች ውስጥ ቢያንስ በ2/3ኛው በትንሹ ምርጫ ካልተካሄደ ያ ምርጫ ተቀባይነት አይኖረውም።
ስለዚህ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ስለ ምርጫ ማውራት ዋጋ የለውም። መጀመርያ አገራችንን ወደ ሠላም መመለስ መቻል አለብን። አንጻራዊ ሰላም ከመጣ ስለ ምርጫ ማውራት እንችላለን። አንጻራዊ ሠላም መጥቶ የምርጫ እድል ከመጣ የመጀመርያው ረድፍ ላይ እሰለፋለሁ።"
ጃዋር መሐመደ ከቢቢሲ "በቀጣዩ ምርጫ ላይ ትሳተፋለህ?" በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ከሰጠው ምላሽ

የብልጽግና መንደር በጃዋር "ኢንተርቪው" ታውኳል። ፖለቲካ ማለት ባለበት መርገጥ የሚመስላቸው አንዳንዶችማ፤ "ጃዋር ፦"አማራ.አማራ ማለት የጀመረው፤ የሚያስፈራራባቸው የሼኔ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ አብይ ስለገቡበት ነው" በማለትም እየጻፉ ናቸው።
ጃዋር ጋር ያሉን የሀሳብ ልዩነትና ያለፉ ክስተቶች ፤ ሀቁን እንዳልናገር አያንቁኝም።
ስለዚህ አሁን ያ ሁሉ ወጣት ታጣቂ ሆኗል ብላችሁ ካልተቀዳዳችሁ በስተቀር፤ ወትሮም አብዛኛው የጃዋር ድጋፍ የሚመነጨው፦ ከአብዛኛው የኦሮሞ ወጣት እንጂ ከታጠቁ የኦነግ ወታደሮች አይደለም።
በእርግጥ አሁን ያለው ፖለቲካዊ አሰላለፍ ከባለፈው ጊዜ በእጅጉ ተለይቷል። በተለይ በአማራ ክልል በፋኖ የተቀሰቀሰውና በአጭር ጊዜ ውስጥ መላ ክልሉን ያዳረሰው ትግል ፤ፖለቲካዊ አሰላለፉን ሙሉ በሙሉ ለውጦታል። ይህን እውነታ ተገንዝቦ አዲስ አቅጣጫ የማይተልም ፖለቲከኛ ደግሞ-ፖለቲከኛ ሊባል አይችልም።
እያወራን ያለነው ፤ በባለፈው ነገር እየተካሰሱ ባሉበት ስለ መርገጥ ፣ ስለ በቀል፣ስለ ፍርድ እና ስለ መፈራረጅ ሳይሆን ሀገር ስለማዳን ከኾነ፤ ሁላችንም እልኻችንን ውጠን አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ አቅጣጫ መተለም ግድ ይለናል።

አሁንኮ አንዱ ነው ከአዲስ አበባ ደውሎ የሚከተለውን የሚነግረኝ:-
"የብልጽግና አክቲቪስቶች "እስኪ ዛሬ ይፀለይላችሁ" ተብለው ተጠርተው ነበር።ጸሎቱ ሲጀመር ሁላችንም ባልጠበቅነው ሁኔታ ራሳቸውን ስተው እየጮሁ ወደ መድረኩ ወጡ። በሁኔታው ግራ የተጋባው የፕሮግራሙ መሪ በኃይለ ቃል መገሰጽ ጀመረ።ይህኔ ጩኸታቸውና ጫጫታቸው ይበልጥ ጨመረ። የፕሮግራም መሪም ይበልጥ ድምፁን ጨምሮ በቁጣ;-"እንዲህ እያስጨነቅክ የምታስጮኻቸው አንተ ማነህ?"ሲላቸው ሁሉም በአንድ ላይ ምን ብለው ቢመልሱ ጥሩ ነው:-" ጃዋር!"

እጅ ከፍንጅ የተያዘው ህጻናት አጋች፤ያገታትን ልጅ ተሸክሞ ከተማውን እንዲዞር ተደረገ።
በላይ አርማጭሆ ወረዳ በፎቶው የሚታየው ግለሰብ ከሌሎች 3 ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የ8 ዓመት ህጻን ያግትና ለማስለቀቂያ ቤተሰቦቿን 250 ሺህ ብር ይጠይቃል።
በመጨረሻም የህጻኑዋ ወላጆች ተደራድረው 100 ሺህ ብር ይዘው ወደ አጋቹ በመሄድ ብሩን ያስረክባሉ።
አጋቹ ከታጋች ቤተሰብ የተሰጠውን ብር እየቆጠረ እያለ የላይ በአርማጭሆ ታጣቂዎች ከእነ ብሩና ከልጅቱ ጋር እጅ ከፍንጅ በመያዝ ወደ ትክል ድንጋይ ከተማ ይወስዱታል።
ከዚያም ያገታትን የ8 አመት ህፃን ተሸክሞ "እኔን ያየ ይቀጣ" እያለ ከተማዋን እንዲዞር ተደርጓል።
ሕዝቡም ከኋላ ኋላው እየተከተለ "ሌባ፡ ሌባ፡ ሌባ" እያለ የሚገባውን ማህበራዊ ቅጣት ቀጥቶታል።
ከዚያም በኋላ ጋቹም ከግብረ አበሮቹ ጋር ወደ እስር ቤት ተወስዶ፡ ክስ እንዲመሠረትበት ተደርጓል።

ስድስት የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ከታይላንድ ባንኮክ የተነሳ አውሮፕላን፤በደቡብ ኮሪያ- ሙዋን አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፍ ሲል በተከሰተ አደጋ እስካሁን 177 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። የተቀሩት ሦስት ሰዎችም እጅግ አስጊ ኹኔታ ላይ ናቸው። ከእንዲህ ያለ የከፋ አደጋ ይሰውረን።
ምን ሊያደርጉ ነው?
መከላከያ እና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ ኃይሎች በከባድ መሳሪያዎች ታግዘው የመሬት መንቀጥቅጡ ወደሚነሳበት ቦታ ማምራታቸውን፤ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጃል ሰኚ ገለጹ እያሉ ነው የመንግስት ሚዲያዎች።
መሬት መንቀጥቀጡን ትጥቅ ሊያስፈቱት ነው?

እግዚአብሔር ምህረቱን ያውርድልን።በሀገር ቤት ያላችሁ ወገኖች
አይዟችሁ ! በጸሎት ከእናንተ ጋር ነን።እርሱ ቸር ነው፤የምህረት ፊቱን ይመልሳል።

አማኞች ብትሆኑም የመሬት መንቀጥቀጥን ለምን ከጌታ ቁጣ ጋር ታያይዙታላችሁ? በማለት በቅንነት ጥያቄ ያቀረባችሁ አንዳንድ ወዳጆቻችንን ዐይቻለሁ።
በአጭሩ ምላሽ ለመስጠት ያህል ያን የሚለን፤ የምንመራበት (የምናምነው) መጽሐፍ ነው።
እነሆ በጥቂቱ፦
“ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።”
መዝ 18፤7
“ ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፥ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች።”
ኢሳ 13፤13
'ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል።
፤ ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።” ኢሳ 29፤ 5-6

አሳዛኝ ዜና፦
ሀገራችን ካሏት ጥቂት ስመ ጥር ኢኮኖሚስቶች መካከል አንዱ የኾነው ግልጹና ጨዋታ አዋቂው ዶ/ር በፈቃዱ ደግፌ ማረፉን ሰማሁ።
ዶ/ር በፈቃዱ በ1997ቱ ታሪካዊ ምርጫ ቅንጅትን ወክሎ በአዲስ አበባ ተወዳድሮ ያሸነፈ ቢሆንም፤ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ለሁለት ዓመታት ከቅንጅት መሪዎች፣ ከሰብ ዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ከእኛ ከጋዜጠኞች ጋር ለሁለት ዓመታት ታስሯል።(አንተ ያልኩት ከነበረን ቅርበት አኳያ መሆኑ ይጤን)
በሰላም እረፍ ቤፍ! ለቤተሰቡ በሙሉ መጽናናት ይሁን።