Dereje Habtewold official
160 subscribers
50 photos
9 videos
7 links
Download Telegram
ስድስት የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ከታይላንድ ባንኮክ የተነሳ አውሮፕላን፤በደቡብ ኮሪያ- ሙዋን አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፍ ሲል በተከሰተ አደጋ እስካሁን 177 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። የተቀሩት ሦስት ሰዎችም እጅግ አስጊ ኹኔታ ላይ ናቸው። ከእንዲህ ያለ የከፋ አደጋ ይሰውረን።
ምን ሊያደርጉ ነው?
መከላከያ እና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ ኃይሎች በከባድ መሳሪያዎች ታግዘው የመሬት መንቀጥቅጡ ወደሚነሳበት ቦታ ማምራታቸውን፤ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጃል ሰኚ ገለጹ እያሉ ነው የመንግስት ሚዲያዎች።

መሬት መንቀጥቀጡን ትጥቅ ሊያስፈቱት ነው?
መላው ዓለም ርችት ሲያበራላት ያደረችው ዕድለኛ ማናት? ካላችሁ....
በዛሬዋ ሌሊት ወደዚህ ምድር የመጣችው የኔዋ ፍቅር ናት።

መልካም ልደት የኔ ፍቅር።
እግዚአብሔር ምህረቱን ያውርድልን።በሀገር ቤት ያላችሁ ወገኖች
አይዟችሁ ! በጸሎት ከእናንተ ጋር ነን።እርሱ ቸር ነው፤የምህረት ፊቱን ይመልሳል።
አማኞች ብትሆኑም የመሬት መንቀጥቀጥን ለምን ከጌታ ቁጣ ጋር ታያይዙታላችሁ? በማለት በቅንነት ጥያቄ ያቀረባችሁ አንዳንድ ወዳጆቻችንን ዐይቻለሁ።

በአጭሩ ምላሽ ለመስጠት ያህል ያን የሚለን፤ የምንመራበት (የምናምነው) መጽሐፍ ነው።
እነሆ በጥቂቱ፦

“ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።”
መዝ 18፤7
“ ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፥ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች።”
ኢሳ 13፤13

'ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል።
፤ ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።” ኢሳ 29፤ 5-6
አሳዛኝ ዜና፦
ሀገራችን ካሏት ጥቂት ስመ ጥር ኢኮኖሚስቶች መካከል አንዱ የኾነው ግልጹና ጨዋታ አዋቂው ዶ/ር በፈቃዱ ደግፌ ማረፉን ሰማሁ።
ዶ/ር በፈቃዱ በ1997ቱ ታሪካዊ ምርጫ ቅንጅትን ወክሎ በአዲስ አበባ ተወዳድሮ ያሸነፈ ቢሆንም፤ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ለሁለት ዓመታት ከቅንጅት መሪዎች፣ ከሰብ ዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ከእኛ ከጋዜጠኞች ጋር ለሁለት ዓመታት ታስሯል።(አንተ ያልኩት ከነበረን ቅርበት አኳያ መሆኑ ይጤን)

በሰላም እረፍ ቤፍ! ለቤተሰቡ በሙሉ መጽናናት ይሁን።
"ነጭ ቀብተህ ብልጭ ድርግም አምፖሎችን ስለደረደርክባቸው ብቻ የማያምሩ ነገሮች አሉ።" ፍጹም ጎሳዬ
በምሽት እቤቱ መግቢያ ላይ ጠብቀው ስልኩን ተረከቡትና "ቀጥል!" አሉት። ምንም ሳይመስለው ፈገግ እያለ ከደረት ኪሱ የተጠቀለለ ብር በማውጣት "ይህን ልጨምራችሁ"ብሎ ሰጣቸው።በሁኔታው ተገርመው አንድ ጥያቄ ጠየቁት:-የጅማ ሰው ነህ እንዴ?"
ደ'ሞ መጣሽ?
አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ሕዝቡንና ምዕራባውያንን ለማማለል በፍትህ፣ በምርጫ ቦርድና በሰብዓዊ መብት ተቋማት ላይ የሾሟቸው ሰዎች ዛሬ በቦታቸው የሉም። ቦታቸውም በካድሬዎች ተይዟል። ድሮም ሙከራቸው አሮጌን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ለማስቀመጥ ስለነበር፤ አልተሳካም። ዲሞክራሲ ወሬ አይደለማ።

ዶሮ ሲያደርጉ ዐይታ፣

ጡት ማስያዣ ገዝታ፣

አንዳ'ፍታ ዘነጠች- እቅድ ተከወነ፣

ዳሩ ምን ያረፋል?

ለጌጥ ያሰበችው ማሰሪያዋ ኾነ።
ግጥሞችን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ሥራዎችን በማሰናዳትና ለመድረክ በማብቃት የምትታወቀውን ልጅ አሰሯት አሉ።
ብልጽግና በዲሞክራሲያዊ ልምምድ ታጅቦ ሁለተኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።ትናንት ምሥራቅን፤ዛሬ ደግሞ ሰመረን አስሯል።

ነገ ደግሞ ማንን እንደሚያስሩ እናያለን።

የጨለማ ሥርዓት!
የመልካም ልደት ምኞታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ፦ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
የአድዋ ልጅ!

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል አደረሳችሁ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወንድም መንሱር! እስኪ ዛሬ እንኳ ትንሽ ልገስጽህ፦

በእስልምናም ኾነ  በክርስትና  አስተምህሮ ምጽዋት በዚህ መልክ እንዲሰጥ አይፈቀድም።ለታይታ የሚሰጡ ሁሉ፤ በምድር ላይ  ከሰዎች ውዳሴ ዋጋቸውን ስለሚቀበሉ በሰማይ ዋጋ አይኖራቸውምና። እንደ አርዳታ አስተባባሪ ከሰዎች አሰባስበህ የምትሰጠው ቢሆን ኖሮ ፤ አሰራርህን ግልጽ ለማድረግ  ሲባል እንዳደረግከው እንቆጥርልህ ነበር። አንተ ግን ከ20 ሺህ ብር የማይበልጥ ገንዘብ በሳምሶናይት ይዘህ እየመጸወትክ ነው የብዙ ሰዎችን ፊት በካሜራ ቀርጸህ ያሳየኸው።
ብሩ 20 ሺህ እንኳ ቢሞላ፤ በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት  150 ዶላር አካባቢ ነው።

ለዚህች ታህል ብር ብለህ ምን እምንዳደረግ እስኪ  ቪዲዮውን እንደገና  እያዬህ  ራስህን ጠይቀው?
በዒዱ አላህም፣ ሰውም የማይወደው ሥራ ነው የሠራኸው።