Dereje Habtewold official
161 subscribers
50 photos
9 videos
7 links
Download Telegram
በምሽት እቤቱ መግቢያ ላይ ጠብቀው ስልኩን ተረከቡትና "ቀጥል!" አሉት። ምንም ሳይመስለው ፈገግ እያለ ከደረት ኪሱ የተጠቀለለ ብር በማውጣት "ይህን ልጨምራችሁ"ብሎ ሰጣቸው።በሁኔታው ተገርመው አንድ ጥያቄ ጠየቁት:-የጅማ ሰው ነህ እንዴ?"
ደ'ሞ መጣሽ?
አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ሕዝቡንና ምዕራባውያንን ለማማለል በፍትህ፣ በምርጫ ቦርድና በሰብዓዊ መብት ተቋማት ላይ የሾሟቸው ሰዎች ዛሬ በቦታቸው የሉም። ቦታቸውም በካድሬዎች ተይዟል። ድሮም ሙከራቸው አሮጌን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ለማስቀመጥ ስለነበር፤ አልተሳካም። ዲሞክራሲ ወሬ አይደለማ።

ዶሮ ሲያደርጉ ዐይታ፣

ጡት ማስያዣ ገዝታ፣

አንዳ'ፍታ ዘነጠች- እቅድ ተከወነ፣

ዳሩ ምን ያረፋል?

ለጌጥ ያሰበችው ማሰሪያዋ ኾነ።
ግጥሞችን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ሥራዎችን በማሰናዳትና ለመድረክ በማብቃት የምትታወቀውን ልጅ አሰሯት አሉ።
ብልጽግና በዲሞክራሲያዊ ልምምድ ታጅቦ ሁለተኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።ትናንት ምሥራቅን፤ዛሬ ደግሞ ሰመረን አስሯል።

ነገ ደግሞ ማንን እንደሚያስሩ እናያለን።

የጨለማ ሥርዓት!
የመልካም ልደት ምኞታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ፦ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
የአድዋ ልጅ!

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል አደረሳችሁ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወንድም መንሱር! እስኪ ዛሬ እንኳ ትንሽ ልገስጽህ፦

በእስልምናም ኾነ  በክርስትና  አስተምህሮ ምጽዋት በዚህ መልክ እንዲሰጥ አይፈቀድም።ለታይታ የሚሰጡ ሁሉ፤ በምድር ላይ  ከሰዎች ውዳሴ ዋጋቸውን ስለሚቀበሉ በሰማይ ዋጋ አይኖራቸውምና። እንደ አርዳታ አስተባባሪ ከሰዎች አሰባስበህ የምትሰጠው ቢሆን ኖሮ ፤ አሰራርህን ግልጽ ለማድረግ  ሲባል እንዳደረግከው እንቆጥርልህ ነበር። አንተ ግን ከ20 ሺህ ብር የማይበልጥ ገንዘብ በሳምሶናይት ይዘህ እየመጸወትክ ነው የብዙ ሰዎችን ፊት በካሜራ ቀርጸህ ያሳየኸው።
ብሩ 20 ሺህ እንኳ ቢሞላ፤ በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት  150 ዶላር አካባቢ ነው።

ለዚህች ታህል ብር ብለህ ምን እምንዳደረግ እስኪ  ቪዲዮውን እንደገና  እያዬህ  ራስህን ጠይቀው?
በዒዱ አላህም፣ ሰውም የማይወደው ሥራ ነው የሠራኸው።