Dagmawi Babi
6.43K subscribers
14.8K photos
1.96K videos
231 files
2.06K links
Believer of Christ | Creative Developer.

Files Channel: https://t.me/+OZ9Ul_rSBAQ0MjNk

Community: @DagmawiBabiChat
Download Telegram
Dagmawi Babi
The lyrics is just so beautiful ❤️ Alehu by Bereket Tesfaye • https://t.me/c/1156511084/458 #Songs #Alehu #BereketTesfaye @Dagmawi_Babi
እነ ሚካኤል እነ ገብርኤል
እነ ሱራፌል እነ ኪሩቤል
በክንፎቻቸው ተከልለውት
ፊቱ የሚቆሙለት አምላክ የሚሉት

በገራፊወች ፊት ቆመልኝ እሱ ግን ስለኔ
ፍቅር ግድ ቢለው ሊያወጣኝ ከሀጥያት ከኩነኔ

ዙፋን የነበረው ከሰማይ ዳዊትን የረዳ
ተንከራተተልኝ እየሱስ ከናዝሬት ይሁዳ

ፍቅሩ ፈሰሰ ከሰማያት ደጅ
እግዚአብሄር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ
ኑሮዬን ኑር አለኝ የኔን ልብስ ለበሰ
ቆሻሻ ህይወቴን በደሙ ቀደሰ

አለሁ ሞቴ ተሽሯል
አለሁ ምህረቱ ገኗል
አለሁ ህመሜን ወስዷል
አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ

#Lyrics #Alehu #BereketTesfaye
@Dagmawi_Babi