አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን

ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባቀረጥና ታክስ የሚታሰበው የተሸከርካሪዉን ሲሲ መሰረት በማድረግ  CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡ ተሽከርካሪው ያገለገለ ከሆነ ከተመረተበት አንድ ዓመት ጊዜ ጀምሮ ከFOB ዋጋዉ ላይ በየዓመቱ 10% በመቀነስ በጠቅላላዉ እስከ 3 አመት ወይም 30% ድረስ የእርጅና ቅናሽ ካለዉ በማስላት የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ በማባዛት ቀረጥና ታክሱን ማወቅ ይቻላል፡፡

የተሽከርካሪው የፈረስ ጉልበት ማለትም ሲሲው 1300 ከሆነ 125%ሲሆን 1301ሲሲ እስከ 2500 ሲሲ ደግሞ ከ176.24% እስከ 244.55% ባሉትየጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ ይሰላል፡፡ለሰው ማጓጓዣ የሚያገለግሉ ሌሎች ተሸከርካሪዎች ሲሆን ደግሞ በሌላ ስፍራ ያልተጠቀሰ ከሆነ የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ 125.00075% ሲሆን ሹፌሩን ጨምሮ አስር ወይም ከዛ በላይ ሰዎችን ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሸከርካሪዎች ከ15 ተጓዦች ያነሰ መቀመጫ ያላቸው ተሸከርካሪዎች 58.25% እንዲሁም 15 እና ከዚያ በላይ ሰው የሚይዝ መቀመጫ ያላቸው የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔው 29.50% ነው፡፡

የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ የተሸከርካሪ ቀረጥና ታክስ ለመወሰን አምስት የሰሌት ደረጃዎችን(ማለትም የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ) እንከተላለን፡፡ የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ በምሳሌ እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ሲገባ:-

በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35% =24,500 ይሆናል፡፡

ቀጥሎ ኤክሳይስ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) 30%=28,350 ይሆናል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350) 15% = 18,427.5 ብር ይሆናል፡፡

በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350 +18,427.5)10%= 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡

በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70,000 X 3%= 2,100 ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት

24,500 + 28,350 + 18,427.5 + 14,127.75 + 2,100= 87,505.25 ብር ይሆናል፡፡                                                          #ጉምሩክ ኮሚሽን
👍3
#ጉምሩክ

" ሰርኩለሩ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " - አስመጪዎች

በርካታ የመኪና አስመጪዎች ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አስመጪዎቹ በጋራ ፈርመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባላኩት ደብዳቤ ፤ " መንግስት በሀምሌ 22/2016 ዓ.ም በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ያስተላለፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ በፊት የነበሩ ውስብስብ የንግድ መዛባቶችን እና ብሮክራሲዎችን እንደሚያስቀር እንተማመናል " ብለዋል።

ነገር ግን የኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ነሐሴ 03/2016 እና ነሐሴ 10/2016 ያወጣቸው ሰርኩላሮች ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

" ይህም ሰርኩላር ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ እና ከጉምሩክ ትራንዚት እና መጋዘን አስተዳደር የሚጣረስ በመሆኑ ነው " ብለዋል።

አስመጪዎቹ " የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FXD/01/2024 ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን ከ22/11/2016 በፊት የተመዘገቡ እና ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች ላይ በደብዳቤ ቁጥር 4/0/04/17 ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ስርኩለት የተላከ ሲሆን ነገር ግን ሰርኩለር በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " ነው ብለዋል።

ጉዳዩን ሲያብራሩም ፦

" በጉምሩክ ደንቡ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የቀረጥ ማስከፈያ የሚወሰነው ዲ/ዬን. በተመዘገበበት እለት ያለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ተመን በመጠቀም ነው።

ይህ ማለት በዮኒሞዳል አሰራር ሕጋዊ ዶክሜንት አሟልተን ዲ/ዬን ሞልተን ክፍያ ፈፅመን ሰነዱን የተሟላ መሆኑን ለጉምሩክ ኦፊሰር ተረጋግጦ ትራንዚት ተፈቅዶልናል፡፡

ትራንዚት ካስፈቀድን በኋላ ደግሞ ሕጉ በሚፈቅደው በአንድ ወር የትራንዚት ጊዜ ገደብ ውስጥ ኘሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን ወደ አገር ውስጥ አስገብተናል የጉምሩክ ሪስክ የሚጣለው ደግሞ እቃዎቹ አገር ውስጥ / መድረሻው ጣቢያ / ሲደርሱ መሆኑን ከግምት ያላስገባ ውሳኔ ነው።

እቃዎቹ ተጓጉዘው በድሬዳዋ መስመር /ደወሌ/ ለሚገቡ በድሬዳዋ ድልድይ ተሰብሮ ከ3 ሳምንት በላይ መቆማቸው ግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ነው " ብለዋል።


" የጉምሩክ ኮሚሽን ከላይ የተገለጸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስቸኳይ የውሳኔ ማሻሻያ እንዲደረግልን እና በአዋጁ መሰረት እንድንስተናገድ " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ፤ " ጉምሩክ  ኮሚሽን አዋጅን በሴኩላር በማሻር የማይሆን ስራ እየሰራ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀረቡ አስመጪዎች አሁንም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሴኩርላር ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም።

አሁንም ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል።

ጉዳዩ  በገበያና ስራው ላይ ሚያመጣውን ከፍተኛ ተፅእኖ በመረዳት እውቀትን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በውይይት መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Customs #Ethiopia

@tikvahethiopia
👍163🔥1