"ጉዳዩ ለውሳኔ ለሚቀጥለው ዓመት ተቀጥሮ አድሯል" - አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ
በሕጻን ሄቨን ጉዳይ አማራየ ክልል ፍትሕ ቢሮ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቱ ተከትሎ ምን ተደረገ? ጉዳዩስ ምን ላይ ነው? የሚለውን የሚዳስስ ነው።
አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ያስቀመጠው የፍርድ ሂደት፦
ድርጊቱ የተፈጸመው ከፍተኛ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ግጭት (ጦርነት) በነበረበት ወቅት መሆኑን፤ ወንጀለኛው በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላም መለቀቁንና የተጎጅ ቤተሰብን፣ የሕግ አካላትን ሳይቀር ተጽዕኖ ለማድረስ መሞከሩን ያስረዳል።
ተጠርጣሪው ዳግም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ምርመራው ተደርጎ በምርመራው እና ባሉት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች መነሻነት በተደራራቢ ወንጀል ሁለት ክስ ማቅረብ ተችሏል፡፡
ክሶቹም የግፍ ግድያ የወንጀል ሕጉ 539 እና በመድፈር መግደልን 620 (3) ያጣቀሰ ነበር። ይህም የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ድረስ የሚያስቀጣ ነው ብሏል፡፡
በክርክር ሂደት ተከሳሽ ክዶ ጠበቃ አቁሞ የተከራከረ መሆኑንና ይህም ሕጋዊ አሠራር መሆኑን አንስቷል።
* የክልሉ ፍትህ ቢሮ በማብራሪያው በክርክሩ የታዩ የሙያ ሥነ ምግባር ጉዳዮች ወይም ወንጀል ከተፈጸመ ተጠያቂነት ይኖራል ቢልም በሂደቱ ላይ ምርመራ ስለመጀመሩ ግን አልገለጸም።
የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ [የሥር ፍርድ ቤት] የቀረበው ማስረጃ የግፍ ግድያን ሳይኾን (539) በመደፈር መሞቷን የሚያረጋግጥ መኾኑን በማረጋገጥ ተጠርጣሪው በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ሊቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን አንስቷል፡፡
ፍርደኛው አሁንም ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ የጠቀሰው ማብራሪያው በአሁኑ ወቅት ፍርደኛው የፍርደኛ ይግባኝ አቅርቦ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛል ብሏል። ይሄም ሕጋዊ እና የተለመደ አሠራር ነው ሲል ነው ያስረዳው፡፡
ጉዳዩም ለውሳኔ ለሚቀጥለው ዓመት መቀጠሩን እና አሁንም ፍትሕ ቢሮው ጉዳዩን በአግባቡ እየተከታተለው እንደሚገኝ ጠቁሟል።
"ምናልባት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ #በአሉታዊ ቢኾን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በዐቃቢ ሕግ በኩል የሚቀርብ እንደኾነም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡" ሲል ነው ቢሮው በማብራሪያው የገለጸው።
@tikvahethmagazine