መጋቢት 16፣ 2013
ከ62 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሻሽሎ እንደ አዲስ የተዘጋጀው የንግድ ህግ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡
ንግድና ከንግድ ጋር የተያዙ ህጎች ከዚህ ቀደም በተለያዩ አዋጆች ተበታትነው የተደነገጉ ነበሩ የተባለ ሲሆን አሁን ህጎቹ በአንድ ተሰባስበው በአዲሱ ሕግ በመድብል መልክ ተዘጋጅቷል፡፡
ህጉን ለማፅደቅ የሚያስችለውን የውሳኔ ሐሳብ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት አባተ እንዳሉ አዲሱ የንግድ ህግ ከአለም የንግድ ህጎችን አሰራሮች ጋር እንዲጣጣም ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ባለችው ጥረትና እንቅፋት የነበሩ ድንጋጌዎች ከህጉ እንዲፋቁ መደረጉም ተነግሯል፡፡
የቀደመው የንግድ ህግ በ1952 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለንግድ እንቅስቃሴው መቀላጠፍና ለአፈፃፀም አመቺ እንዲሆን ያስችላሉ የተባሉ ጥናቶች ላለፉት 34 አመታት ሲካሄድ የቆየ መሆኑንም ወ/ሮ መሰረት አስታውሰዋል፡፡
ህጋዊ ሰውነት ያላቸው የአስተዳደር አካላትን የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የህብረት ስራ ማህበራት በሽርክና የንግድ ማህበራት ውስጥ ባለድርሻ ሆነው ቢሳተፉ እንደ ነጋዴ ተቆጥረው ህጉ በእነዚህም ላይ የሚሰራ እንዲሆን መደንገጉንም ተናግረዋል፡፡
የተበታተነና ውስብስብ ችግር ነበረበት የተባሉ የንግድ ህጎችን በአንድ መመደብ የያዘው አዲሱና ዛሬ የታቀደው የንግድ ህግ ኢትዮጵያን ለንግድ ህግ ምቹ እንድትሆን ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ጥሎበታል፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባው ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የደረሱትን የስምምነት ሰነድም አፅድቋል፡፡
የፌዴራል የጥብቅና አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን ደግሞ በዝርዝር እንዲታይ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
#Ethiopia #ShegerWerewoch #ንግድ_ህግ #ሕዝብ_እንደራሴዎ_ችምክር_ቤት
ከሸገር ወሬዎች፣
#Join
#share #ALE
#ሼር #አለ
#law #Societies
@lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/