አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የማከማቸት ሕግ (the law of accumulation)

ታዋቂው የስኬትና የመልካም ስብእና አስተማሪ ብራያን ትሬሲ ስለ አንድ የማይለወጥ ሕግ ይነግረናል፡፡ ይህንን ሕግ፣ የማከማቸት ሕግ (the law of accumulation) በማለት ይጠራዋል፡፡ ሕጉ እንደዚህ ይላል፡-

“ማንኛውም የምናደርገው ነገር ሁሉ ወይ ወደ ክሬዲት ወይም ደግሞ ወደ ዴቢት በመግባት ይቆጠራል“።

ከዚህ ውጪ ምንም ስሌት የለም፡፡ ከራስ በራስ ጋር ባለን ግንኙነት እሳቤም ሆነ አንዳንድ ልማዶች አንጻር ስንመለከተው የምናደርገው ነገር ሁሉ ወይ እንድናከማች ወይም እንድናባክን ያደርገናል፡፡

ዛሬ በግዢ፣ በሽያጭ፣ በመስጠት፣ በመቀበልና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ከገንዘብ ጋር የነበራችሁ ንክኪ አስቡት ይህ ሂደት ወይ ክሬዲት ተጨምሮላችኋል ወይም ዴቢት ሆኖ ተቀናሽ አድርጋችኋል፡፡

ከሰዎች ጋር ባለንም ግንኙነት ስሌቱ ይኸው ነው፡፡ የምደርጋቸው ነገሮች፣ ከማድረግ የምንከለከላቸው ነገሮች፣ የምንናገራቸው ነገሮች . . . በሙሉ ወይ ጨምረውልናል ወይም ቀንሰውብናል፡፡

ሁኔታዎችን በዚህ መልኩ ማየት ስንጀምር ለምናደርጋቸውም ሆነ ለማናደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እንድንንቀሳቀስ ያግዘናል፡፡

ካደረግን ወይም ካላደረግን፣ ከተናገርን ወይም ዝም ካልን በኋላ ስለወጤቱ ከማሰብና ከመጨነቅ ቀድ ሞውኑ ይህ ነገር የሚታሰብልኝ ወደ ክሬዲት ነው ወይስ ወደ ዴቢት ብለን እናሰብ፡፡
via #Dreyob በዶ/ር እዮብ
#Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo
https://t.me/Ethiopialegalinfo