አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በም/አርሲ ዞን በሻሸመኔ የወረዳ አቃቤ ህግ በመሆን እያገለገለ ያለው ወንድማችን #በሪሶ_ካዱ_ጎዳና ( Bariisoo Kaduu Godaanaa)
ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከአገልግሎት ውጭ በመሆናቸው የኛ የወገኖቹ ድጋፍ አስፈልጎታል፡፡

ወንድማችን የሶስት ልጅ አባት ነው።😭 በሙያው ያለመታከት የአካባቢውን ማህበረሰብ እያገለገለ ያለ፣ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው መስጠትን የሚያውቅ፣ ቅን እና በሁሉም መስክ ያለውን አቅም ሳይሰስት እየሠጠ ያለ ወንድማችን ነው፡፡

ይሁን እንጂ ዛሬ እነዚህን ሁሉ የሚያደርግባቸው እግሮቹ በኩላሊት ህመም ምክንያት ተይዘዋል፡፡

ስለሆነም ወንድማችን ወደ ስራው እንዲመለስና ቆሞ እንድናየው ቋሚ የሆነ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ውጪ ሀገር ሄዶ መታከም አለብት ስለተባለ የሁላችንም ርብርብ አስፈልጓል።
👉👉ሼር ማድረግም ድጋፍ ነው።👈
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig


Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ማድረግም ድጋፍ ነው።
የኢትዮጵያ “ብሔራዊ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ” ፀድቆ ወደ ሥራ የገባ ስለመሆኑ የፍትህ ሚኒስትር ድኤታ አቶ አለምአንተ አግደዉ አስታወቁ

ዜጎች በሚያጋጥሟቸዉ የሕግ ጉዳዮች በኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፣ባህላዊና ሌሎች ምክንያቶች በተለይም የሕግ ድጋፍ ለማግኘት የገንዘብ አቅም ስለሌላቸዉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ስለሆኑ ብቻ ፍትህ የማግኘትና በህግ ፊት እኩል የመዳኘት መብታቸዉ እንዳይጓደል መንግስታት ነጻ የህግ ድጋፍ የማመቻቸት ግዴታ ያለባቸዉ ስለመሆኑ በተለያዩ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች እና በየአገራቱ ሕገ -መንግስታት ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስትም እነዚህ መብቶች እዉቅና የተሰጣቸዉ ናቸዉ፡፡ ሆኖም ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ባልተደራጀና በተበታተነ መንገድ እንዲሁም ግልጽ የሆነ ስትራቴጅክ አቅጣጫ ሳይቀመጥለት በተለያዩ አካላት ፣ በፍትህ ሚኒስቴርና በክልል ፍትሕ ቢሮዎች፣በተከላካይ እና የግል ጠበቆች፣በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ስር በሚገኙ የሕግ ትምህርት ቤቶች እና እንደ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባሉ ሲቪል ማህበራት አማካኝነት አገልግሎቱ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ሚኒስትር ድኤታዉ እንደገለጹት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(8) (ሀ) በተሰጠዉ ነጻ የሕግ ድጋፍ ስትራቴጂ የመቅረጽ፣አፈጻጸሙን የመከታተልና በመስኩ የተሰማሩ አካላትን የማስተባበር ተግባርና ኃላፊነትን መነሻ በማድረግ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ብሄራዊ ነጻ የሕግ ስትራቴጂን ቀርጾና ለሚኒስትሮች ም/ቤት አቅርቦ ስትራቴጂዉ ከታየ በኋላ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ በተሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት ከጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲዉል ተወስኗል፡፡

አቶ አለምአንተ አያይዘዉም የስትራቴጂዉ መጽደቅ በህገ-መንግስት ጥበቃ የተደረገላቸዉ ፍትህ የማግኘት መብት፣ በህግ ፊት እኩል የመዳኘት መብት፣ የሴቶችና ሕጻናት መብቶች፣የተያዙና የተከሰሱ ሰዎችን መብት በማስከበር ዜጎች በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ሌሎች ምክንያቶች ፍትህ እንይጓደልባቸዉ ለማድረግ የራሱ የሆነ ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ መሆኑን ፤ በኢትዮጵያ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ተደራሽ እና ጥራት ባለዉ አግባብ መስጠት እንዲቻል እንዲሁም አገልግሎቱን ለማስተባበር ፣ለማቀናጀትና ወጥ የአሰራር ስርዓት እንዲኖር ለማስቻል የሚረዳ ከመሆኑም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸዉ ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች የተጣለባትን ግዴታ በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዉ ስትራቴጂዉን የመተግበር ኃላፊነት ያለባቸዉ ሁሉም አካላት በስትራቴጂዉ በተቀመጠዉ አግባብና በትብብር መንፈስ እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig


Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ #Ale_Hig