አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#አንድ ሰው #ሁለት #ሚስቶችን #ያገባ እንደሆነ እና #ጋብቻው በሞት ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት #የፈረሰ እንደሆነ እና ከሁለቱ ሚስቶች አንደኛዋ ንብረቶቹን በማፍራት ሂደት የተለየ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ያረጋገጠች እንደሆነ ከተፈራው ንብረት ግማሽ ድርሻ የሚገባት ሲሆን፣ የሌላኛዋ ተጋቢ ከባል ጋር ግማሹን ትካፈላለች።

በእርግጥ ሟች ሁለት ሚስቶች ኖረውት የሞተ እንደሆነ ሁለቱ ሚስቶች የንብረቱን ድርሻ ግማሹን ለሁለት ሊካፈሉ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅሊይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁጥር 24625 ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁጥር 45548 ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመው) አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ያሉት እንደሆነ ንብረቶቹን በማፍራት ረገድ ከሚስቶቹ አንደኛዋ ሚስት ከሌላኛዋ የተሻለ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ባደረገችው አስተዋጽኦ ልክ ልትካፈል ትችላለች የሚል ሃሳብ መነሻ በማድረግ ባል ንብረቱን በሚያፈራበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በትዳር የነበረች ሚስት ንብረቱን በማፍራት ረገድ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳደረገች ግምት ተወስዶ ከንብረቱ ግማሹን ድርሻ የማግኘት መብት እንዳላት እና በአንፃሩ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያላደረገች ሚስት ከባል ድርሻ ግማሹን የማግኘት መብት ብቻ ያላት ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በሰ/መ/ቁጥር 50489 (ቅጽ 11 እንደታተመው) ጨምሮ በሌልች በርካታ መዛግብት ላይም ይህንኑ የሚያጠናክር ውሳኔ ሰጥቷል። የሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
via:- @Habesha Legal Advocates
በፌስቡክ FB
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም
https://t.me/lawsocieties

YouTube
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
በመርህ ደረጃ ከሥራ ዉል መቋረጥ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች የይርጋ ጊዜ ዉሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ 6 ወር ሲሆን የስራ ዉሉ መቋረጡ በግልጽ ባለመገለጹ ወይም ባለመታወቁ ወይም አሻሚ በመሆኑ ሳይታወቅ በቆየበት ሁኔታ ክስ ለማቅረብ መወሰን በማይቻልበት ሁኔታ ግን የስራ ዉሉ መቋረጡን አዉቆ ክስ መመስረት ይችል ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር 6 ወር ይሆናል፡፡
ሰ/መ/ቁጥር 231470 ሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም
👉Constitution
👉 Proclamation
👉Regulations
👉 Directives
👉 Decree and administrative order (circular)

☑️Supreme court decisions
የኢትዮጵያ የህግ ምንጮች እና ተዋረድ
https://t.me/lawsocieties
ህጎች የተለያዩ መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡፡

በዚህ መሰረት “የሲቪል ሎው (civil law)” እና “የኮመን ሎው (common law)”፣ “ፐብሊክ ሎው (public law)” እና “የግል ህግ (private law)”፣ “የወንጀል ህግ” እና “የፍትሀብሄር ህግ”፣ “የስነ ስርዓት ህግ (procedural law)” እና “መሰረታዊ ህግ (substantive law) እና የመሳሰሉትን መስፈርቶች በመጠቀም ህጎችን ማከፋፈል ይቻላል፡፡ የሀገራት ህጎች በሁለት ዋና ዋና የህግ ስርዓቶች ማለትም የኮመን ሎው እና የሲቪል ሎው በሚል ይታወቃሉ፡፡ የሲቨል ሎው የህግ ስርዓት ተከታይ አገራት ፍትሀብሄርን የሚመለከት ዐብይ ህግ በአንድ ጥራዝ (codified) ታውጀው እና የወንጀል የሚመለከት ዐብይ ህግ በአንድ ጥራዝ (code) ታውጀው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በአገራችን አጠራር የፍትሀብሄር ህግ እና የወንጀል ህግ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ስለሆነም ይህን ስርዓት የሚከተሉ ሀገሮች ዋና የህግ ምንጭ በህግ አውጪ አካል ታውጀው የሚጠረዙ ህጎች ናቸው ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል የኮመን ሎው ስርዓትን የሚከተሉ ሀገሮች ዋና የህግ ምንጫቸው በህግ አውጪ አካል የሚወጡ ህጎች ሳይሆኑ በፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ጉዳይ ቀደም ብለው የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች (precedent) ናቸው፡፡ እንዲሁም ያልተፃፉ ህጎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

በሀገራችንም የተለያዩ የህግ ምንጮች ያሉ ሲሆን የህጎች ተዋረድ ወይም የህግ የበላይነት ደረጃ (hierarchy of laws) በህግ ስርዓት ውስጥ ጉልህ ቦታ ካላቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ በዚህ የንቃተ ህገ ፅሁፍ የኢትዮጵያ የህግ ምንጮችን እና የህጎቹን ተዋረድ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

1. የኢትዮጵያ ህግ ምንጮች (sources of Ethiopian laws)
በአገራችን ህጎች በፌደራል እና በክልል ደረጃ ወጥተው ስራ ላይ ይውላሉ፡፡ እነዚህም ህጎች በፌደራል እና በክልሎች የተለያዩ ምንጮች አሏቸው፡፡

1.1. የፌደራል የህግ ምንጮች 
i. ህገ መንግስት (constitution)
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9 ህገ መንግስት የሀገሪቱ የበላይ ሕግ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ማንኛውም ህግ ለምሳሌ አዋጅ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህ ማለት ህገ መንግስት የማንኛውም ህጎች መነሻ እና ምንጭ እንዲሁም ህጋዊነታቸውን (validation) የሚያገኙበት መሰረት ነው፡፡
ii. አለም አቀፍ ስምምነቶች (international treaties)
ሀገራት አለም አቀፍ ስምምነት ሲፈርሙ ስምምነቱን እንደ አንድ አለም አቀፍ ህግ እንተቀበሉ ማስረጃ ነው፡፡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 (4) እንደሚደነግገው ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ስራ ላይ ለመዋል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ እና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትመው መውጣት አለባቸው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱ ህግ አካል ሆነው ተግባራዊ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
iii. ኮዶች (codes)
በሀገራችን በ1960ዎቹ አምስት ኮዶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ እነዚህም የፍትሀ ብሄር ህግ፣ የንግድ ህግ፣ የባህር ህግ በ1960፣ የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ በ1961 እና የፍትሀ ብሄር ስነ ስርዓት ህግ በ1965 ናቸው፡፡ እነዚህም ህጎች በነጋሪት ጋዜጣ በአዋጅ መልክ ታውጀው ስራ ላይ ውለዋል፡፡ ከዚህም በኃላ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ፣ የወንጀል ህግ እና አዲሱ የንግድ ህግ በኮድ መልክ ስራ ላይ የዋሉ የአገራችን የህግ ምንጮች ናቸው፡፡
iv. አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ (proclamations, regulations & directives) 
አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ደንቦች በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና መመሪያዎች ደግሞ በፌደራል ሚኒስትሮች መስሪያ ቤቶች ወይም በሚስትሮች ምክር ቤት መመሪያ እንዲያወጡ በደንብ ውክልና በተሰጣቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ይወጣሉ፡፡ በተጨማሪም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማወጅ ስልጣን በህገ መንግስቱ ተሰጥቶታል፡፡ እነዚህም የህግ ክፍሎች ወይም አይነቶች የአገራችን የህግ ምንጭ በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆኑ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ይህም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በሚነስትሮች ምክር ቤት ከታወጁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡
v. አስገዳጅ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች (precedent)
ይህ የህግ ምንጭ አይነት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አስገዳጅ ወይም ህግ የሚሆንበት ስርዓት ነው፡፡ በአገራችን  ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ እንደ ህግ እንደሚያገለግሉ እና አስገዳጅ እንደሆነ የሚገልፀው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10/2 ስር እንደተደነገገው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ ባለ የፌደራል እና የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል ይላል፡፡ ይህ ማለት እነዚህ ውሳኔዎች የህግ ምንጭ ሆነው ስራ ላይ ይውላሉ ማለት ነው፡፡
vi. ልማዳዊ ህጎች (customary laws)
ልማዳዊ ህጎች በኢትዮጵያ ህጎች ውስጥ በተለያየ ጊዜ እንደምንጭ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ የፍትሀ ብሄር ህጉን ያረቀቁት ፕሮፌሰር ሬኒ ዳቪድ በረቂቁ ውስጥ የኦርቶዶክስን ልማዳዊ ህግ ‘ፍትሀ ነገስትን‘ እንደምንጭ እንደተጠቀሙበት ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 34/5 ስር እንደተደነገገው የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሀይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጎች መሰረት መዳኘት እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በመሆኑም ባህላዊ ወይም ልማዳዊ ህጎች እንደ አንድ የህግ ምንጭ ያገለግላሉ ማለት ነው፡፡

1.2. የክልል ህግ ምንጮች
i. የክልል ህገ መንግስት(state constitutions)
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 52/2 ስር እንደተደነገገው ክልሎች የራሳቸው ህጎች ማውጣት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ክልሎች የራሳቸው ህገ መንግስት ከፌደራል ህገ መንግስት ጋር በሚጣጣም መልኩ አውጥተዋል እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡ የክልል ህገ መንግስት በክልሎቹ ውስጥ የበላይ ህግ ነው፡፡
ii. የክልል አዋጆች (state proclamations)
የፌደራል ህገ መንግስት ክልሎች ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ የክልሎቹን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሰረት ለምሳሌ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና የደ/ብ/ብ/ህ ክልል የራሳቸው የቤተሰብ ህግ አውጀዋል፡፡
iii. የክልል ደንቦች እና መመሪያዎች (state regulations & directives)
የፌደራል ህገ መንግስት የክልል አስፈፃሚ ምክር ቤቶች በክልል ወሰን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ እንዲሁም ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣት እንደሚችሉ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡
2. የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws)
የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws) የህጎች የበላይነት ደረጃን ወይም የትኛው ህግ ከየትኛው ህግ የበላይ ህግ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ በአገራችን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ ድርጊት እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ይደነግጋል፡፡ ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ህገ መንግስቱ ነው ማለት ነው፡፡

የፌደራል ህገ መንግስት በፌደራልም ይሁን በክልል ደረጃ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ በመቀጠል የአገሪቱ የበላይ የህግ አውጪ አካል ማለትም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ህጎች ማለትም አዋጆች ይከተላሉ፡፡ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የህግ ተዋረድ በተመለከተ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም በህገ መንግስቱ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገረቱ ህግ አካል ይሆናሉ ስለሚል ከአዋጅ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ የሚል ሀሳብ አለ፡፡ በህግ ተዋረድ በመቀጠል የሚመጡት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጡት ደንቦች እና በሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚወጡት መመሪያዎች በቅደም ተከተል ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ተዋረድ (hierarchy) ላይ ባሉ ህጎች መካከል መቃረን ሲኖር ተፈፃሚ የሚሆነው በጊዜ ዘግይቶ የወጣው ህግ (latest prevails) ነው፡፡ ይህ ማለት ዘግይቶ የወጣው ቀድሞ ከወጣው ይልቅ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ልዩ ህግ (special law) ከጠቅላላ ህግ ይልቅ ቅድሚያ ተቀባይነት (special law prevails over general law) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

በፌስቡክ FB
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም
https://t.me/lawsocieties

YouTube
https://www.youtube.com/@Lawsocieties

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሰራተኛ
ሰ/መ/ቁጥር 212420 ጥር 27 ቀን 2014 ዓ/ም
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው።
ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።
የካሳው መጠን የሙከራ ጊዜ ማለትም 60 ቀናት በስራ ላይ ቢቆይ ኖሮ ሊያገኝ ይችል የነበረው ማለትም የሁለት ወር ደመወዝ ነው።

Habesha Legal Advocates LLP

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ማስረጃ ለመመዘን ሥልጣን የተሠጠው ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲቀበል የተከራካሪዎችን እኩል የመደመጥ መብት ካላከበረ፣ የማስረዳት ሸክም (burden of production) የማን ነው የሚለውን ካልለየ፣ የማስረጃ ተቀባይነትና ተገቢነት ላይ መከተል የሚገባውን ሥርዓት ካልተከተለ፣ በምዘና ጊዜ የሁሉንም ተከራካሪዎች ማስረጃ አብሮ ካልመዘነ፣ ከማስረዳት ደረጃ (standard of proof) አንጻር በሚጠይቀው ደረጃ ልክ መረጋገጡን ካላሳየ እና
በመሠረታዊ ሕግ ሆነ በሥነ-ሥርዓት ሕግ ያሉትን የማስረጃ ሕጎችና መርሆች ካላከበረ ጉዳዩ የማስረጃ ምዘና ሳይሆን የሕግ አተረጓጎም ስህተትና ፍርድ ቤት ያለበትን ኃላፊነት አለመወጣት ስለሚሆን የሰበር ሰሚ ችሎቱ የሚመለከተው ነው።
ሰ/መ/ቁ. 217634 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም።

ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል።

ሰ/መ/ቁጥር 215444
ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ግብር/ታክስ

ያልተከፋፈለ ትርፍ

• በአንድ የግብር ዓመት ግብር ከተከፈለ በኋላ ለአባላቱ ያልተከፋፈለ እና መልሶ ኢንቨስት ያልተደረገ የተጣራ የድርጅት ትርፍ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡

በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት ወደ ወጭ የሚላክ ትርፍ

• በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የንግድ ስራ የሚያከናውን በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው በቋሚነት ከሚሰራ ድርጅት በሚላክለት ትርፍ ላይ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
231571.pdf
822 KB
ፍርድ ቤት የንብረት አስተዳዳሪ ስለሚሾምበት አግባብ
ሰ/መ/ቁ 231571 ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 166(1)(ሀ) ስር እንደተደነገገው ፍርድ ቤቱ የሚመችና ትክክለኛ መሆኑን የገመተ እንደሆነ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ወይም ከሰጠ በኃላ ማናቸውንም ንብረትና ሀብት ተቀብሎ የሚጠብቅ ሰው መርጦ መሾም ይችላል፡፡ እንዲህ አይነቱን ማመልካቻ ፍርድ ቤቱ የሚቀበለው ከሆነ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚገባው አመልካቹ የጠየቀውን አቤቱታ፣ ተሿሚው ሊሰበስብ ወይም ሊያገኝ የሚችለውን፤ አስተዳዳሪውን ለመሾም ሚደረገውን ወጪ በማመዛዘንና በተለይም ምርመራ እንዲደረግበት ሌላም ተጨማሪ ነገር ቢኖር አብሮ እንዲጣራ በማድረግ ስለመሆኑ ከድንጋጌው ንዑስ ቁጥር 2 መገንዘብ ይቻላል።
ከተጠቀሰው ድንጋጌ መረዳት እንደሚቻለው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን ለመስጠትና ላለመስጠት ፍቅድ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዚህ መልኩ በህጉ የተሰጠውን ፈቅድ ስልጣን ተጠቅሞ ሲወስን ከግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸውን ጉዳዩች ሁለ ተመልክቶና አረጋግጦ ሊወስን እንደሚገባ በህጉ ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም አንደኛው ተከራካሪ ንብረትና ሀብት ተቀብሎ የሚጠብቅ ሰው ተመርጦ እንዲሾም ስለጠየቀ ብቻ የነገሩ ሁኔታ ሳይመዘን ንብረት አስተዳዳሪ እንዲሾም ማለት እንደማይቻል ሁሉ የነገሩ ሁኔታ ታይቶ የሚመችና ትክክለኛ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የገመተ እንደሆነ ንብረትና ሀብት ተቀብሎ የሚያስተዳድር ሰው ሊሾም አይገባም የሚባልበት የህግ ምክንያትም የለም፡፡
Abrham Yohanes Law Corner
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
1287_2015_የኤክሳይዝ_ታክስ_አዋጅ_ማሻሻያ_.pdf
7.6 MB
#ETHIOPIA

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቋል።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ይህ አዋጅ የታክሱን መሰረት በማስፋት እና የታክሱን አስተዳደር ስርዓት በመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታን ማስገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ የአዋጁ ማሻሻያ ተደርጓል ሲል አስታውሷል።

የአዋጁ ማሻሻያ ታሰቢ ያደረገው ፦

- #ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣

- ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣

- የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት መሆኑ ተመላክቷል።

ምክር ቤቱ በአስተዳደር ምክንያት የተደረጉ ማስተካከያዎችን እና የማሻሻያውን ዋና ዋና ምክንያቶችን ከመረመረ በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1287/2015 እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡

በመሆኑም ገቢዎች ሚኒስቴር የአዋጁ ማሻሻያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል እንዲደረግ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ሁሉ እንዲያውቁት መመሪያ ሰጥቷል።

(የአዋጁ ማሻሻያ ከላይ በ #PDF ተያይዟል)

#የገቢዎች_ሚኒስቴር
#tikvahethiopia
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce)

ጋብቻ የቤተሰብ መሰረት በመሆኑ በህግ እውቅና የተሰጠው እና ከምስረታው ጀምሮ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ በዚህም የሚፈርስበት ሁኔታ ጭምር በቤተሰብ ህጉ በግልፅ ተመላክቷል፡፡ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ እንደተደነገገው ጋብቻ የሚፈርሰው ከተጋቢዎች አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ፣ ጋብቻ ለመፈፅም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በህግ መሰረት ጋብቻ እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ በቤተሰብ ህጉ ፍቺ የሚፈፀምባቸውን ሁኔታዎች እና በፍርድ ቤት ሳይወሰን ተለያይቶ መኖር በህጉ የሚስተናገድበትን ሁኔታ እንመለከታለን፡፡

ፍቺ የሚፈፀምበት ሁኔታ

ጋብቻ በፍቺ እንዲፈርስ ሊወሰን የሚችለው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት ሲወስኑና ይህንኑ ለፍርድ ቤት አቅርበው ውሳኔያቸው ተቀባይነት ሲያገኝ እና ከተጋቢዎቹ አንዱ ወይም ሁለቱም ተጋቢዎች በአንድነት ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነው፡፡ ጋብቻ በስምምነት ሲፈርስ ፍርድ ቤት የፍቺ ስምምነቱን የሚያፀድቀው የባልና ሚስቱ ትክክለኛ ፍላጎት መሆኑን እንዲሁም ስምምነቱ ከህግና ሞራል ጋር የማይቃረን መሆኑን ሲያምን ነው (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ (አንቀጽ 80 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2)፡፡
https://t.me/lawsocieties
ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce)
ፍርድ ቤቱ የፍቺን ስምምነት ያፀደቀው እንደሆነ ስለፍቺው ውጤት ያደረጉትንም ስምምነት አብሮ ሊያፀድቀው የሚችል ሲሆን ባልና ሚስቱ ስለፍቺ ውጤት ያደረጉት ስምምነት የልጆቻቸውን ደህንነትና ጥቅም በበቂ ሁኔታ የማያስጠብቅ ወይም የአንደኛውን ተጋቢ ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ካገኘው ፍርድ ቤት የፍቺውን ስምምነት ብቻ በማፅደቅ የፍቺውን ውጤት በተመለከተ ጉድለቶቹ እንዲስተከካሉ ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ይሰጣል (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 80/3)። በመሆኑም ጋብቻ በፍቺ የሚፈርሰው ፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ መሆኑን መረዳት ይቻላል::

ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce) ምንነት

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ1999 ዓ.ም በሰበር መዝገብ ቁጥር 20938 ሰጥቶት በነበረው ውሳኔ መሰረት ሳይፋቱ ፍቺ ማለት በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሳይሰጥበት ባልና ሚስት ለበርካታ ዓመታት ተለያይተው በመኖር፣ የየራሳቸውን ሕይወት እየኖሩ (አግብተው ወይም ሳያገቡ) ከቆዩ፣ ምንም እንኳን ቀደም ብሎ የተፈጸመ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም ሁለቱም በየፊናቸው የየራሳቸውን ሕይወት መጀመራቸው ከተረጋገጠ ጋብቻቸው እንደፈረሰ የሚቆጠርበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው፡፡

ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce) በኢትዮጵያ ህግ የሚታይበት ሁኔታ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው ውሳኔ በሥር ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅ በመሆኑ ምክንያት ችሎቱ የሰጠው የህግ ትርጉም ሥራ ላይ ሲውል የቆየ ቢሆንም በርካታ ሴቶች ሀብት ንብረታቸውን እንዳሳጣቸው ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡ ይኸውም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79 ሕግ የመተርጎም ሥልጣን ለፍርድ ቤት፣ በአንቀጽ 55 ደግሞ ሕግ የማውጣት ሥልጣንን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠ ቢሆንም ሰበር ሰሚ ችሎት ግን ከሕጉ ዓላማ ውጪ የሆነ አስገዳጅ ትርጉም መስጠቱ ሕገ መንግሥቱን እንደሚቃረን በመጥቀስ ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ቀርቧል፡፡

ሰበር ሰሚ ችሎት በውሳኔው ጋብቻ ሊፈርስ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በተመለከተ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75 እና 82 የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በማለፍ አራተኛ ምክንያት ማስቀመጡም ተገቢ አለመሆኑ፣ የጋብቻን ፍቺ የመወሰንና የጋብቻው በፍቺ መፍረስ የሚያስከትለውን ውጤት የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤት ብቻ ሆኖ የተደነገገበት የራሱ ዓላማ ያለው መሆኑን፣ ጋብቻ በፍቺ ሲፈርስ የተጋቢዎችን የንብረት ክፍፍልና የሕፃናትን የአስተዳደግ ሁኔታ አገናዝቦ ውሳኔ መስጠት ያለበት ፍርድ ቤት መሆኑ እንዲሁም ተጋቢዎች ተለያይተው በመኖራቸውና የየራሳቸውን ሌላ ሕይወት በመጀመራቸው ‹‹ጋብቻቸው ፈርሷል›› የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ተጋቢዎች በቸልተኝነት ጋብቻቸውን ከፍርድ ቤት ዕውቅና ውጪ በፍቺ መልክ እንዲያቋርጡ መንገድ የሚከፍትና ሕገ-ወጥነትን የሚያበረታታ መሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስቻሉ ምክንያቶች ናቸው፡፡

በመሆኑም የሰበር ሰሚ ችሎቱ አስገዳጅ ውሳኔ ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ከተመለከተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር፣ በአንቀጽ 51 ከተመለከተው የፌዴራል መንግሥት ሥልጣንና ተግባር ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ ሆኖ ስላገኘው የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ጉባዔው በሙሉ ድምፅ በመወሰን በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 84(1) እና በአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀጽ 3(1) ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤትም የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በመቀበልና ይሁንታ በመስጠት አስገዳጁን የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰርዞ ጋብቻ ሊፈርስባቸው ከሚችሉ ሦስት በህግ ከተመለከቱ ምክያቶች ውጪ ዝም ብሎ መለያየትና መቆየት ጋብቻን ሊያፈርስ እንደማይችል በፌደሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም የመዝገብ ቁጥር 49/10 ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 11/1 እና 56 መሰረት በህገ-መንግስት ትርጉም ላይ ምክር ቤቱ የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ አጠቃላይ ውጤት የሚኖረው ሲሆን ወደፊት በሚወሰኑ ተመሳሳይ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ የአስገዳጅነት ባህርይ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ምክር ቤቱ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ውሳኔውን የማክበርና የመፈፀም ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

በአጠቃለይ የጋብቻ መፍረስ በልጆች እና በንብረት አስተዳደር ላይ ውጤት ያለው በመሆኑ በህጉ የተቀመጡትን የጋብቻ መፍረስ ምክንያቶች ብቻ መከተል ግዴታ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ከሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም መረዳት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በጋብቻ ውስጥ ያሉ ሰዎች መለያየት ከፈለጉ በህጉ መሰረት ፍቺ መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties