አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ስለዚህ ዳኞች የጠፋው ሰው አጠፋፍ ‹መሞት የሚመስል› መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ ይጣልባቸዋል፡፡ መጥፋቱን ከተረዱት በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 157 መሰረት የመጥፋት ውሳኔ የመጨረሻ ወሬዎቹን የተሰማበትን ቀን በመጥቀስ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡ በሌላ በኩል ዳኞቹ ያገኙት ማስረጃ ወደሞት የሚያመዝን መስሎ ከታያቸው ‹የሞት ማስታወቂያ› ፍርድ ይሠጣሉ ሲል የፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 157(1) ደንግጓል፡፡ ዳኞች እንደነገሩ ሁኔታ የመጥፋት ውሳኔውን ወይም የመጥፋት ውሳኔ ማስታወቂያን ለአንድ አመት መቅጠር የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን የመጥፋት ውሳኔው ከተጠየቀ ከአንድ አመት በኋላ ወይም ሰውየው ከጠፋ አምስት አመት በኋላ የመጥፋት ውሳኔ መሰጠት አለበት፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
👍1