አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ፍሰት ማነቆ የሆኑ 80 ህጎች ማሻሻሏን አስታወቀች


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳለው ለንግድ እና ኢንቨስትመንት አመቺ ያልሆኑ ህጎች መሻሻላቸውን አስታውቋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-says-revises-investment-laws
Forwarded from የፍቅር ሰው
በየትኛውም ህግ ነው ተማሪዎች apparentship ወተው የተግባር ልምምድ ሳያደርግ የሚመረቁት
ከምንም በላይ የወራቤ ተማሪዎች ፍትህን ይፈልጋል።
በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎቹ በመንከራተት ላይ ይገኛሉ
እንደሚታወቀው ይህ ወክት ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና የሚዘጋጅበት ጊዜ ነው። በተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ከንባብ ሙድ እየወጡ ይገኛሉ።

ውድ የአለ ቤተሰቦች ለሚመለከተው አካል በማስተላለፍ እንድትተባበሩ እንጠይቃለን።
ስለሚታደርጉት ትብብር ከልብ እናመሰግናለን።
አባቱን ገድሏል የተባለው ተከሳሽ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወላጅ አባቱን ገድሏል በተባለው አቶ መሐሩ ዮሐንስ በተባለ ተከሳሽ ላይ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ፍርድ አስተላልፏል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ነው።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው ግለሰቡ ድርጊቱን ከመፈጸሙ በፊት "የሰበሰብከውን ንብረት አትበላም" እያለ ሲዝት እንደነበርና ምሽት ላይ ሟች ተኝቶ ባለበት በዘነዘና ጭንቅላቱን በመቀጥቀጥ ግድያውን መፈጸሙን ገልጿል።

አቃቤ ህግም በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ተከሳሽ ክሱን እንዲከላከል ቢታዘዝም መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በጽሑፍና በቃል ማስረጃ የለኝም ብሎ በማረጋገጡ ሚያዝያ 3 ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሹ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡

@tikvahethmagazine
Ethiopia is the third most expensive country to live in based on cost of living .

The high cost of living is a major concern for many individuals and families around the world. It is an issue that affects people of all income levels and can significantly impact their quality of life. Several factors contribute to the high cost of living in a country, including economic policies, inflation, and the cost of essential goods and services.

One of the primary reasons for the high cost of living in a country is the state of its economy. Countries with a strong economy tend to have a higher cost of living due to the high demand for goods and services. This is because when people have more money to spend, they are willing to pay more for the things they need and want.

Inflation is another factor that contributes to the high cost of living. Inflation occurs when the general price level of goods and services increases over time. This means that people have to spend more money to buy the same goods and services they could buy for less in the past. Inflation can be caused by various factors, such as increases in the money supply, changes in government policies, or external factors like global supply chain disruptions.

Based on the analysis Ethiopia reason of higher cost of living is not due to strong economy which creates strong demand rather due to high inflation which rocken the economy badly.

Rank Country Cost of living index Local purchasing power
1. Senegal 46.4 21.7
2. Ivory Coast 42.7 7.8
3. Ethiopia 42.3 11.6
4. Mauritius 42.2 30.8
5. Zimbabwe 40.8 18.7
6. South Africa 37.8 83.9
7. Namibia 35.8 51.3
8. Botswana 34.4 63.6
9. Cameroon 33.6 18.4
10. Kenya 32.4 32.8

EII.
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተዘጋጀ የፍትሐብሔር ክስ ለማቅረብ የሚከፈል የዳኝነት ክፍያ መጠንን ለማስላት የሚያስችል ሲስተም፡፡

👉  https://www.fsc.gov.et/Court-Services/Registry-Services/Court-Forms-and-Fees
አለአግባብ መበልጸግ በኢትዮጵያ ህግ
=============================⤵️
ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ይህ የህግ ክፍል የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጪ ያለ ሃላፊነት ህጎች የማይገዙትን የሰው ግንኝኑነት ክፍተት ለመሙላት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ህግ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ይህ የህግ ክፍል የሰዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከመግዛት አኳያ ሰፊ ድርሻ ያለው ነው፡፡
ያለአግባብ መልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡
አጠቃላይ መርሆዎች
የዚህ ህግ ዋንኛ አላማ ሰዎች በገንዘባቸው፣ በንብረታቸው እና በጉልበታቸው ላይ ሚኖራቸውን ህጋዊ መብት መጠበቅ ነው፡፡ ስለሆነም የፍታብሔር ህጋችን በቁጥር 2162 ስር ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እና ባለሀብቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ጥቅም ባገኘበት ልክ ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ ይህ ድንጋጌ በስሩ የያዛቸው ነጥቦችን ስንመለከት ያለአግባብ የመበልጸግ ህግ ማንኛውም ሰው (ማለትም የተፈጥሮ ወይም የህግ ሰውነት ያለው ሰው) ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን እንደመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ በዚህ ህግ ተጠያቂ የሚሆን ሰው የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም ሊያገኝ ይገባል፡፡ ይህም ማለት ጥቅሙ በንብት ላይ የተቋቋመ (right in rem) ወይም ከሌላ ሰው የሚጠየቅ መብት (right in personam) ወይም የነበረ እዳ የመሰረዝ፣ ግዴታ የመቅረት አይነት ወይም የኪሳራ መቅረት አይነት ጥቅም ሊሆን የሚችል ሲሆን ይህ ጥቅም ያለአግባብ የመበልፀግ የህግ ክፍል ስር ሊያስቀጣ የሚችለው ጥቅሙ የህሊና እርካታ ሊያስገኝ የሚችል ብቻ ሳይሆን በገንዘብ ሊለካ የሚችል ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ የተገኘው የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም በሌላ ሰው የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ስራ ምክንያት የተገኘ መሆን ያለበት ሲሆን ጥቅሙን ያገኘው ሰው ጥቅሙን ላገኘበት ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆንም በዚህ የህግ ክፍል ተጠያቂ የሚያደርግ ክስ የቀረበበት ሰው ጥቅሙን ላገኘበት ማንኛውም ህጋዊ ምክንያት ያቀረበ እንደሆነ ካሳ መክፈል ግዴታ አይኖርበትም፡፡ ሌላው በህጉ የተቀመጠው ቅድመሁኔታ በተከሳሽ ድርጊት ምክንያት ከሳሽ የሚታወቅ ኪሳራ ወይም ድህነት ሊደርስበት ሚገባ ሲሆን የከሳሽ ጥቅም ማጣት (ኪሳራ) እና የተከሳሽ ጥቅም ማግኘት ምክንያት አንድ መሆን አለበት፡፡ ይህም ማለት በደረሰው ኪሳራ እና በተገኘው ጥቅም መካከል የውጤት እና የምክንያት ግንኝነት መኖር አለበት፡፡
ከላይ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ ሃላፊነትን የሚወስድ ሰው በምን ያህል መጠን ከሳሽን የመካስ ግዴታ አለበት የሚለውን በተመለከተ የተገኘው ጥቅም እና የደረሰው ኪሳራ እኩል በሚሆንበት ግዜ ምንም አይነት ችግር ሊገጥም አይችልም ምክንያቱም ተከሳሽ አለአግባብ የበለፀገበት መጠን እና ከሳሽ ላይ የደረሰው ጉዳት እኩል ስለሆነ በዚሁ ልክ ካሳ እንዲከፍ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ ሁኔታዎች ያለአግባብ የተገኘው ብልፅግና ከደረሰው ጉዳት ሊያንስ ወይም ሊበልጥ ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በሚያጋጥምበት ግዜ ምንም እንኳን የደረሰው ጉዳት ከተገኘው ብልፅግና የሚያንስ ቢሆንም ህጉ በግልፅ ተከሳሽ መክፈል ያለበት ኪሳራ ያለአግባብ ባገኘው ብልፅግና መጠን መሆን እንደሚገባው ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይ ያለአግባብ የተገኘው ብልፅግና ከደረሰው ጉዳት የሚያንስ ከሆነ ወይም ጉዳቱ ከብፅግናው የሚበልጥ በሚሆንበት ግዜ የተከሳሽ ተጠያቂነት መጠን በተገኘው ብልፅግና ልክ ብቻ በመሆኑ ካሳ እንዲከፍል የሚገደደውም በዚሁ መጠን ብቻ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ ያአለአግባብ መበልፀግ በመሰረታዊነት ሶስት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን አንድን ሰው በዚህ የህግ ክፍል በመክሰስ ካሳ ለማስከፈል እነዚህ ሶስት ሁኔታዎች በድምር መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ተከሳሽ በገንዘብ ሊለካ የሚችል ጥቅም ያገኘ መሆኑ ሁለተኛው ይህ ጥቅም የተገኘው በከሳሽ ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መሆኑ እንዲሁም ሶስተኛው የተገኘበት መንገድ አለአግባብ ወይም ምንም አይነት ህጋዊ መንገድ/ምክንያት የማይቀርብበት መንገድ መሆኑ ናቸው፡፡
ያለአግባብ የመበልፅ ክሶችን ይበልጥ ለመረዳት ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 34406 የሰጠውን ውሳኔ መመልከት ይቻልል፡፡ በዚህ መዝገብ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት ሰዎች ባለቤት እና አባት የሆኑት ግለሰብ መኖሪያ ቤታቸውን ያከራዩት ሰው ለተከሳሽ ቤቱን አስረክቦ ይጠፋል፡፡ የቤቱ ህጋዊ ዋራሽ ከሳሾች ቤቱን ለተረከቡት ግለሰብ ቤቱን ለቀው እንዲያስረክቧቸው ቢጠይቋቸውም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው አለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲያስረክቡ እና ንብረቱን በያዙበት ወቅት ያለክራይ በመኖር ያገኙትን ያለአግባብ ብልፅግና እንዲከፍሉ ክስ አቅርበዋል፡፡ ተከሳሽም በሰጡት መልስ ቤቱን ያለአግባብ ይዛለች ከተባለ እንኳን ይህን ካወቁ 10 ዓመት በላይ ስለሆነ በይርጋ ይታገዳል፣ የደረሰባቸው የጥቅም ጉዳት ከውል ውጪ እንደመሆኑ የኪራይ ማስከፈል ጥያቄአቸው ሁለት አመት ካለፈው በይርጋ ይታገዳል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ከመረመሩ በኋላ ተከሳሽ ያለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲመልሱ እና ከንብረቱ ያለአግባብ የተጠቀሙትን መጠን ካሳ እንዲከፍሉ ወስነው ተከሳሽም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሰበር ሰሚ ችሎቱ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ የሰበር ሰሚ ችሎቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት ግለሰቦች ይዞታችን በሃይል ተወስዷል ወይም በይዞታችን ላይ ሁከት ተፈጥሯል በማለት ያቀረቡት ክስ የለም ክሣቸው በኪራይ የተረከቡትን ቤት ተከሳሽ መብት ሣይኖራቸው ገብተው አልወጣም ብለዋልና አለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲለቁ የቀረበ ክስ ስለሆነ 10 ዓመት ቢያልፈው እንኳን በይርጋ አይታገድም፡፡ በጨማሪም ተከሳሽ የቀረበው የካሣ ጥያቄም ቢሆን በይርጋ ቀሪ ይሆናል በሚል ያቀረቡት ክርክር በተመለከተ ማንኛውም በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም በሌላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ኪሣራ መክፈል እንዳለበት በፍ/ህ/ቁ. 2162 ሥር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ በቤቱ አላግባብ በበለፀጉበት መጠን ኪሣራ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸው ህጉን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የካሣ ጥያቄ ሊቀርብ የሚገባበት የጊዜ ገደብ በተመለከተ ክርክር ቀርቧል፡፡ ያለአግባብ ስለመበልፀግ የሚናገረው ምእራፍ የካሣ ጥያቄ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ አይናገርም፡፡ ነገር ግን አላግባብ ስለመበልፀግና ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት የሚናገሩት ድንጋጌዎች በአንድ አንቀጽ ውስጥ ተካትተው መገኘታቸው እንዲሁም ያለአግባብ መበልፀግም ከውል ውጪ የሚደርስ ሃላፊነት በመሆኑ ከውል ውጭ የሚደርስ ሃላፊነት ሥር የተመለከተው የይርጋ ዘመን በተመሣሣይ
አላግባብ መበልፀግ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት ከውል ውጭ ሃላፊነትን በተመለከተ ተበዳዩ ክስ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2 አመት ድረስ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 2143/1/ ሥር ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ ላሉት ሁለት አመታት አላግባብ በቤቱ በተገለገሉበት መጠን እንዲከፈሉ የተጠየቁት ካሣ በይጋ የሚታገድ አይሆንም:: ሆኖም ከዛ በፊት ያሉት ግዜያት የተጠቀሙት ክፍያ ግን በይርጋ ቀሪ የሚሆኑ ናቸው በማለት ወስኗል፡፡
ሌላው መታየት ያለ ጉዳይ አንድ ሰው ያለአግባብ በልፅጓል ተብሎ ክስ በሚቀርብበት ወቅት ይህ አለመሆኑን ስለሚያሳይበት መንገድ ነው፡፡ የፍታብሔር ህጋችን በቁጥር 2163 ያለአግባብ መበልፀግ ስለሚቀርበት ሁኔታዎች የሚደነግግ ሲሆን በዚህም መሰረት ያለአግባብ በልፅገሃል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ንብረቱን መልስ በሚባልበት ግዜ ላለመበልፀጉ ማስረጃ ያቀረበ እንደሆነ ማሰረጃ ባቀረበበት ልክ ኪሳራ እንዲከፍል አይጠበቅበትም፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን ከሳሽ ተከሳሽ በእርሱ ኪሳራ መበልፀጉን ማስረዳት ቢችልም ተከሳሽ ክሱ በቀረበበት ወቅት የተገኘው ብልፅግና ከእርሱ ጋር እንደሌለ (ወይም ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑን) ማስረዳት ከቻለ ካሳ መክፈል ላይኖርበት ይችላል፡፡ ሆኖም ተከሳሹ በክፉ ልቦና ተነሳስቶ ወይም መመለስ እንዳለበት እያወቀ ንብረቱን ወይም ዕቃውን ሌላ ሰው አስተላልፎ ከሆነ ምንም እንኳን የተገኘው ብልፅግና እርሱ ጋር የሌለ ቢሆንም ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2163(2) ስር ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ተከሳሽ ያለአግባብ የበለፀገበትን ሀብት ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈው ያለ ዋጋ እንደሆነ ከሳሽ ይህን ሶስተኛ ወገን ያለ ዋጋ የወሰደውን ንብረት እንዲመልስለት ሊጠይቀው ይችላል፡፡
መክፈል የማይገባውን ክፍያ ስለመክፈል
ማንኛውም ሰው ሊከፍል የማይገባውን ነገር የከፈለ እንደሆነ ያለአግባብ የከፈለው ክፍያ እንዲመለስለት መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም ማለት ማንም ሰው በስዕተት ሊከፍል የማይገባውን ክፍያ የፈፀመ እንደሆነ ይህ የከፈለው ገንዘብ እንዲመለስልት ካሳ መጠየቅ የሚችል ሲሆን ክፍያውን የተቀበለው ሰው በእምነት ማጉደል ሀሳብ ተነሳስቶ የተቀበለ እንደሆነ ክፍያውን የፈፀመው ሰው ክፍያው ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ የከፈለው ነገር የሰጠውን ፍሬ ወይም ህጋዊ ወለድ ጨምሮ መጠየቅ እንደሚችል ህጉ ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ሰውየው የከፈለው መክፈል የማይጠበቅበትን ክፍያ ቢሆንም እንኳን በሚከተሉት ሁኔታዎች የከፈለው ክፍያ እንዲመለስለት መጠየቅ አይችልም፡-
• ክፍያውን የፈፀመው ዕዳ እንደሌለበት እያወቀ ወይም ይህን ሁኔታ በግልፅ እየተረዳ በፍቃደኝነት ከሆነ፤
• ግለሰቡ የሚከፈለውን ነገር ያለዋጋ የመስጠት የህግ ችሎታ ያለው ሆኖ ክፍያውን የፈፀመው በይርጋ የታገደውን ዕዳውን ወይም የሕሊና ግዴታውን እና የበጎ አድራጎት መንፈሱን ተከትሎ እንደሆነ፤
ክፍያውን ከፈፀመለት ሰው የከፈለው እንዲመለስለት መጠየቅ እንደማይችል የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2165 እና 2166 ስር ያስቀምጣል፡፡
በሌላ በኩል ያለአግባብ የተከፈለውን ክፍያ የተቀበለ ሰው የተከፈለውን ነገር ከመመለስ የሚድንበት መንገድ ህጉ በቁጥር 2168 ስር ያስቀመጠ ሲሆን በዚህም መሰረት የማይገባውን ገንዘብ የተቀበለ ሰው በሌላ ሰው ላይ ያለው ገንዘቡ የተከፈለው መስሎት በቅን ልቦና የብድሩን ሰነድ አበላሽቶ ወይም ዋሶቹን ከዕዳው ነፃ አድርጎ ወይም ከእውነተኛ ባለዕዳ ሊቀበል የሚገባውን ገንዘብ በይርጋ አሳልፎ እንደሆነ፤ ያለአግባብ የተቀበለውን ገንዘብ የመመለስ ግዴታ ማይኖርበት ሲሆን እንዲህ ባለው ሁኔታ ክፍያውን ያለአግባብ የከፈለው ግለሰብ ክፍያው እንዲመለስለት ለመጠየቅ የሚችለው ከዋናው ባለዕዳ ብቻ ነው፡፡
በሌላ ሰው ንብረት ላይ የወጣ ወጪን ስለማስመለስ
ይህ የህግ ክፍል የሌላ ሰው ንብረት ያየዘ ሰው ንብረቱ በሚመልስበት ግዜ ንብረቱን ለመጠበቅ ያወጣውን ወጪ እንዲመለስለት ስለሚጠይቅበት አግባብ ወይም ንብረቱ በግለሰቡ ቁጥጥር በነበረበት ወቅት ያስገኘውን ጥቅም የራሱ ስለሚያደርግበት መንገድ የሚደነግግ የህግ ክፍል ነው፡፡ ዋናው ያለአግባብ መበልፀግ ህግ አላማ ማንኛውም ሰው መክፈል የማይገባውን ክፍያ እንዳይከፍል ወይም ማውጣት የሌለበትን ወጪ እንዳያወጣ ይህን ካደረገም ተገቢው ካሳ ተከፍሎት ፍትሀዊነት እንዲሰፍን ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው የራሱ ባልሆነ ንብረት ላይ በቀና ልቦና ያወጣው ወጪ ሳይቀናነስ ንብረቱን ለባለቤቱ መልስ መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2168 ስር አንድ ሰው ለተወሰነ ግዜ በእጁ የቆየውን ዕቃ እንዲመለስ የተገደደ እንደሆነ የሕግ ወይም የውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከሌለ በቀር ይህ ሰው የተባለውን ዕቃ ከመለዋወጥ የተነሳ ያሉት መብቶችና ግዴታዎች በዚህ የህግ ክፍል እንደሚገዛ ያደነግጋል፡፡
በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው በእጁ የነበረውን የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ በሚገደድበት ወቅት ዕቃው እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ለማድረግ ያወጣውን ወጪ እንዲመለስለት ለመጠየቅ እንደሚችል በቁጥር 2168 ስር ተቀምጧል፡፡ ሆኖም ይህ ወጪ የወጣው ዕቃውን እንዲመልስ በተገደደው ሰው ወይም እርሱ ሃላፊነትን በሚወስድለት ሰው ጥፋት ምክንያት ከሆነ ወጪው እንዲመለስለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው በውል ህግ መሰረት በተቃራኒው ካልተዋዋሉ ወይም ወጪው አላስፈላጊ ካልሆነ ወይም ወጪው ዕቃውን እንዲመልስ በተገደደው ሰው ጥፋት ምክንያት የተፈፀመ እስካልሆነ ድረስ የሌላን ሰው ንብረት እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ለማድረግ ያወጣው ወጪ እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ህጉ ያስቀምጣል፡፡
ነገርግን ይህ የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ የተገደደ ሰው በውል በሌላ መልኩ ካልተዋዋሉ በስተቀር በማንኛውም መልኩ ለዕቃው አጠባበቅ ያወጣው ወጪ ወይም በንብረቱ ይዞታ ምክንያት የከፈለው ግብር እንዲመለስለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡ ይህ መርህ መሰረት ያደረገው ህጉ የሌላ ሰው ንብረትን የያዘ ሰው ንብረቱን በእጁ በሚያስገባበት ወቅት ምንም አይነት መብት የሌለው መሆኑን የሚያውቅ ካልሆነ በስተቀር ንብረቱ ከሚያፈራው ፍሬ እንዲጠቀም መብት የሚሰጥ በመሆኑ ይህ ግለሰብ ፍሬ ያፈራለትን ንብረት ለመጠበቅ ያወጣው ወጪ ይመለሰልኝ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ስለሆነም በእጁ ያለው ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው የተቀበለው ዕቃ ያፈራውን ፍሬ የማስቀረት ህጋዊ መብት ያለው ሲሆን ዕቃውን በይዞታው ስር ባደረገበት ወቅት በዕቃው ላይ ምንም ዓይነት የውልም ሆነ የህግ መብት እንደሌለው እያወቀ ድርጊቱን ከፈፀመ ግን ይህን የንብረቱን ፍሬ ለራሱ የማስቀረት መብቱ ቀርቶ ለትክክለኛው የንብረቱ ባለቤት ዕቃው በእሱ ይዞታ ስር በነበረበት ወቅት ያፈራው ፍሬ ግምት ልክ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
ሌላው የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ ከተገደደ ሰው መብት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ይህ ግለሰብ ንብረቱ በእጁ በነበረበት ወቅት በቅን ልቦና በመነሳሳት ወጪ አውጥቶ የዕቃውን ዋጋ ከፍ በሚያደርግበት ግዜ ስለሚኖረው ህጋዊ መብት ነው፡፡ የፍታብሔር ህጉም በቁጥር 2171 ስር በሌላ ሰው ዕቃ ላይ የተደረገ ወጪ የዕቃውን ግምት ከፍ አድርጎት ከሆነ ዕቃውን እንዲመልስ የተገደደው ሰው ለዚሁ ጉዳይ ያወጣው ወጪ የዕቃውን ዋጋ ከፍ ባደረገው መጠን ብቻ ሊመለስለት እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡
በዚህም መሰረት ይህ ንብረቱን እንዲመልስ የተገደደ ሰው የዕቃውን ዋጋ ከፍ ለማድረግ ያወጣው ወጪ እንዲመለስለት የሚከተሉትን ነገሮች ማስረዳት ይጠበቅበታል፡-
• በዕቃው ላይ ወጪ ያወጣ መሆኑን፤
• የዕቃውን ዋጋ መጨመሩን እና የዕቃው ዋጋ የጨመረው እሱ ባወጣው ወጪ ምክንያት መሆኑን፤
• የዕቃው ዋጋ መጨመር ንብረቱ እንዲመለስ በተጠየቀመት ግዜ የሚታይ መሆኑን፡፡
ነገር ግን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟሉ ማለት ሰውየው በዕቃው ላይ ያወጣው ወጪ በእርግጠኝነት ይመለስለታል ማለት አይደለም፡ ከነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ የቅን ልቦና መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳን ወጪውን በማውጣት ሂደት ቅን ልቦና አለ የሚለው ግምት የሚወሰድበት ቢሆንም ይህ ግን ተቃራኒ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ነው፡፡ የፍታብሔር ህጉም በቁጥር 2172 ስር ወጪው በተፈፀመበት ግዜ ዕቃውን እንዲመልስ የተገደደው ሰው ዕቃውን የመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበር ወይም የማወቅ ግዴታ ያለበት መሆኑን ማስረዳት ከተቻለ የወጪው ኪሳራ እንዳይከፈል ወይም የንብረቱ ባለቤት ኪሳራውን የመክፈያ እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ግዜ እንዲሰጠው ዳኞች ለመወሰን እንደሚችሉ አስቀምጧል፡፡

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
የታክስ አይነቶች

ቀጥታ ታክስ

የደመወዝ ገቢ ግብር
የኪራይ ገቢ ግብር
የንግድ ሥራ ገቢ ግብር
የሌሎች ገቢዎች ግብር

ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች

የተጨማሪ እሴት ታክስ ( Value Added Tax )
ኤክሳይዝ ታክስ ( Excise Tax )
ተርን ኦቨር ታክስ ( Turnover Tax )
የቴምብር ቀረጥ ( Stamp Duty )
የጉምሩክ ቀረጥ ( Customs Duty )
ሱር ታክስ ( Surtax )

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ
በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን
እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!
scd17.pdf
1 MB
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አውጥቷል።

መመሪያው ተፈጻሚ የሚሆነው ከሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ይህንን መመሪያ ከ https://www.pocketlaw.abyssinialaw.com/ ማግኘት ይችላሉ። በነጋሪ መተግበሪያም በቅርቡ እናካትታለን።
ንፋስ አመጣሽ ትርፍ

1. “ንፋስ አመጣሽ ትርፍ” ያለልፋት (ያለጥረት፣ ያለተጨማሪ ወጪ ወዘተ) የሚገኝ ያልተጠበቀ ወይም ሌላ ተደጋግሞ የማይገኝ ትርፍ ነው፡፡
2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ ከተመለከቱት የንግድ ስራዎች በሚገኝ ንፋስ አመጣሽ ትርፍ ላይ በመመሪያው በተመለከተው የማስከፈያ መጣኔ (ልክ) ግብር ይከፈልበታል፡፡
3. ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ፡
ሀ. ነፋስ አመጣሽ ትርፍ ነው ሊባል የሚችለውን የገቢ መጠን፣
ለ. ግብሩ የሚመለከታቸውን የንግድ ስራዎች አይነት፣
ሐ. ግብሩን ለማስከፈል የወጣው መመሪያ ስራ ላይ የሚውልበትን ቀን፣
መ. የግብር አወሳሰኑን ዘዴና ለግብሩ አወሳሰን መሰረት የሚሆኑ ታሳቢዎችን ይወሰናል፡፡
4. ለተለያዩ የንግድ ስራዎች የሚወሰነው የነፋስ አመጣሽ ትርፍ መጠንና የግብር ማስከፈያ መጣኔውም የተለያየ እንዲሆን ሚኒስትሩ ሊወሰን ይችላል፡፡
ቅድመ ታክስ ክፍያ /Withholding/

አብዛኛውን ጊዜ እንደ አንድ የታክስ አይነት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ሆኖም ዊዝሆልዲንግ ታክስ ማለት አንድ ግብር ከፋይ ሊያገኝ የሚችለውን ገቢ መሠረት በማድረግ የግብር ሰብሳቢው ተቋም ከገቢ ማስታወቂያ ጊዜ አስቀድሞ ግብር የሚሰበስብበት ሥርአት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ዊዝሆልዲንግ ወይንም ከክፍያ ላይ የሚሰበሰብ ቅድመ ታክስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ዊዝሆልዲንግ በግዢና ሽያጭ ወይም የአገልግሎት ክፍያ በሚፈፀምበት ወቅትም ተሰልቶ ተከፋይ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ ዊዝሆልዲንግ ገቢ በማግኘት የታክስ ግዴታቸውን ሳይወጡ የሚሰወሩትን በቀላሉ አነስተኛውን ምጣኔ እንዲከፍሉ ለማድረግ ስለሚያሰችል ለግብር አሰባሰቡ የመቆጣጠሪያ ዘዴ (Controlling mechanism) ነው፡፡

ቅድመ ታክስ በሁለት መልኩ ይከናወናል፡¬

1. ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ እቃዎች በሚከፈል የመድህን አረቦን (Insurance Premium) እና የመጓጓዣ ወጪ (Fright) ላይ ታስቦ አስመጪው 3 በመቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይህ ክፍያ ግብር ከፋዩ ለዓመቱ መክፈል ከሚኖርበት ግብር ይታሰብለታል፡፡ በዊዝሆልዲንግ የከፈለው በልጦ ከተገኘ ትርፉ ክፍያ በተረጋገጠ በዘጠና ቀናት ውስጥ ለግብር ከፋዩ ተመላሽ ይደረግለታል፡፡ በዘጠና ቀናት ውስጥ ካልተመለሰለት ባለፈው ሩብ ዓመት በንግድ ባንኮች ስራ ላይ በዋለው በከፍተኛው የማበደሪያ ልክ ላይ 15% ተጨምሮበት ወለድ ይከፈለዋል፡፡
2. በአንድ ጊዜ ግዥ ወይም በአንድ የእቃ አቅርቦት ከብር 10,000 በላይ ለሆነ ክፍያ ወይም በተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ጊዜ ግዥ ወይም በአንድ አገልግሎት ውል ከብር 3,000 በላይ ከሚፈፀም ክፍያ ላይ 2% ዊዝሆልድ ይደረጋል፡፡ ይህ ተቀናሽ ተደርጎ የሚያዘው በዊዝሆልዲንግ ኤጀንቶች ነው፡፡ ዊዝሆልድ የተደረገው መጠን ግብር ከፋዩ በዓመት ከሚከፍለው የበለጠ እንደሆነ በቁጥር አንድ በተገለፀው መልኩ ይፈፀማል፡፡ ከሚከፈላቸው ክፍያ ላይ 2 በመቶ ዊዝሆልድ የሚደረግባቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ለሚችሉ ሲሆን ማቅረብ የማይችሉ ከሆነ ግን 30 በመቶ ዊዝሆልድ ይደረግባቸዋል፡፡
https://t.me/lawsocieties
961-2023 Directive.pdf
194.9 KB
A Directive to Provide for the Repeal of Tax and Duty Exemption for Vehicles
Rendering Taxi Transport Services No. 961/2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM