አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ገና ዛሬ አይደል እንዴ አውራሪስ ምን እንደሚመስል ያየሁት!🙈
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ፎቶ መላክ የሚጠበቅባቸው update.pdf
1.6 MB
ፎቶ ግራፍ መረጃ ላላሟላችሁ ጠበቆች
**
የኢ
.ፌ.ጠ.ማ  የአባልነት ማረጋገጫ  ደረጃውን የጠበቀ መታወቂያ  ለማሰራት  በዝግጅት  ላይ መሆኑን እና በምዝገባ ወቅት መረጃ  ያላሟላችሁ  እንድታሟሉ  ከአሁን በፊት አሳውቀናል።

በመሆኑም  እስካሁን ድረስ ፎቶ ግራፍ  ያልሰጣችሁ  ጠበቆች ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ ስለሆነ ለመጨረሻ ጊዜ  እስከ ሐሙስ መጋቢት 08 ቀን 2015  ዓ.ም ድረስ  ከማህበሩ መ/ቤት  አራዳ ምድብ የፌዴራል ፍርድ ቤት በሚገኘው የፍትህ አካለት ህንፃ 9ኛ ፎቅ  በአካል በመምጣት እና በስልክ ቁጥር 0913- 661578/ 0912432335  በመጠቀም በቴሌግራም የተሟላ መረጃ (ፎቶ፣ መሉ ስም በአማረኛና እንግሊዘኛ፣ ጥብቅና ቁጥር፣ TIN No)  እንድትልኩ እናሳውቃለን ለመጨረሻ ጊዜ።

ሁሉም የማህበሩ አባል  መረጃውን የሰማ፤ ላልሰማ በማጋራት  ኃላፊነታችሁን እንድትወጡና ትብብር እንድታደርጉ አደራ ማለት እንወዳለን።
መጋቢት 06 ቀን 2015  ዓ.ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ስልጣን ባለው አካል ፊት መረጋገጥና መመዝገብ ስላለባቸው ውሎች
ሰዎች በማኅበራዊ ህይወት ውስጥ ሲኖሩ በግብይ መልክ ያላቸውን ይሰጣሉ የሌላቸውን ይቀበላሉ፡፡ በዚህም የተለያዩ ህጋዊ ልውውጦችን ያካሂዳሉ፡፡ በመሆኑም ሂደቱ አስተማማኝ እንዲሆን፣ በሀብትና ንብረቶቻቸው ላይ ያሏቸው መብቶች ዋስትና እንዲያገኙ የልውውጡን ሥርዓት የሚገዛ ሕግ ያስፈልጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ውል አንዱ ነው፡፡ ውሎች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1731 መሠረት በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው፡፡ ይህም ለሕግና ለሞራል እስካልተቃረነ ድረስ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን ያሳየናል፡፡ ከነዚህ ውሎች መካከል ሕግ ባለ ጊዜ እና ተዋዋይ ወገኖች ሲፍቀዱ በጽሁፍ እና ሥልጣን ባለው አካል ፊት መደረግ ያለባቸውና መመዝገብ ያለባቸው ውሎች ብዙ ናቸው፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት አሥፈላጊነትና ጠቀሜታ፣ መረጋገጥና መመዝገብ ስለሚገባቸው ሰነዶች፣ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውሎችን አረጋግጦ ስለ መመዝገብ የሚሉትን እንመለከታለን፡፡

የውሎች ምዝገባ ሥርዓት አሥፈላጊነትና ጠቀሜታ
የውሎች ምዝገባ አስፈላገነት ከማየታችን በፊት ስለ ውል (ሰነድ) ትርጉም ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ "ሰነድ መመዝገብ" ማለት አንድን ሰነድ ለዚሁ በተዘጋጀ መዝገብ መለያ ቁጥር በመስጠት መመዝገብና ማስቀመጥ ወይም በሕግ መሠረት በሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋም ዘንድ እንዲቀመጥ የተባለ ሰነድን ተቀብሎ መመዝገብና ማስቀመጥ ነው በማለት የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ (2) ንዑስ አንቀጽ (3) ደንግጎት እናገኘዋለን፡፡

ውሎች በጽሁፍ የሚደረጉት አንድም አንዳንድ በባህሪያቸው ለየት ያሉ የውል ዓይነቶች የግድ በጽሁፍ መደረግ አለባቸው የሚሉ አዛዥ ደንቦች በሚኖሩበት ጊዜ አለያም ተዋዋዮቹ ራሳቸው ውላቸውን በጽሁፍ ለማድረግ በሚስማሙበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንድ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው ሁሉም ዓይነት የጽሁፍ ሰነዶች የሚጋሩት የውል ባህርይ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2005 የተመለከተውና የጽሁፍ ሰነዶች በላያቸው ላይ ስለ ሰፈረው ፍሬ ነገር በተዋዋዮቹ መሀከል ሙሉ እምነት የሚጣልባቸው በቂ ማስረጃዎች ናቸው ይላል፡፡ የዚህ ደንብ ዝርዝር የአፈጻጸም ሥርዓቶችና ልዩ ሁኔታዎች በዚሁ ሕግ ከቁጥር 2006 እስከ 2019 በተመለከቱት ደንቦች ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፊት (በባለሥልጣን ፊት) የተደረገ (authentic deed) በግል ከተደረጉ ጽሁፎች (non-authentic deeds or private acts) በይዘት፤ በቅርጽ፤ ይልቁንም ተአማኒነቱና ህጋዊነቱ የበለጠ አስተማማኝ ነው፡፡ መንግስት በአንድ በኩል በእርሱና በዜጎቹ መካከል ያለውን ግንኙነት በሌላ በኩል ደግሞ ዜጎች የግለሰቦችን እርስ በእርሳቸው የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች የህግ አግባብ የተከተለና ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲመሩ፣ ለእነዚህ ግኑኝነቶች ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና መስጠት ካለው ሀላፊነት አንፃር የሚመነጭ በተለይም ለፍትህ ሥርዓቱ አስተዳደር እና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል፡፡

የውሎች ምዝገባ ሥርዓት ወንጀል ከመከላከልና የማጭበርበር ተግበራትን በመከላከል ረገድም አይነተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የውሎች ምዝገባ የሚካሄዱት የንግድም ሆነ ሌሎች ተግባራትን (transactions) ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲካሄድ የተዋዋይ ወገኖች ማንነት በማረጋገጥ ተዋዋዮች በሚዋዋሉት ተግባር የተሟላ ግንዘቤ እንዲኖራቸውና ውጤቱን አውቀውና ፈቅደው እንዲገቡ በማስቻል፣ ሲፈርሙ እርግጠኛ ሁነው እንዲፈርሙ በማድረግ አመኔታ ያለው የንግድና ሌላም ህጋዊ ተግባራት እንዲካሄዱ ያግዛል፡፡ ስለዚህ የውሎች ሥልጣን ባለው አካል በመመዝገብ ሂደት ማጭበርበር (forgery)፣ የማይመለከተው በማሳሳት (misrepresentation)፣ ማስገደድን ለማስወገድ እና ግድፈቶችን (omission) ለመከላከል ውጤታማ እገዛ አለው፡፡ ስለዚህ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት በሚከተሉት ሁኔታዎች የንብረት ማጭበርበርን የመመዝገብ ሥልጣን ባለው አካል ፊት በመገኘትና በመፈፀም ዜጋው ያልሆኑ ተግባራትን እንዳይፈጽም ይከላከላል፡፡ በዚህም እጅግ ወሳኝ የሆኑ ቀጣይ ዋስትናዎችንም በንብረት ማስተላለፉ ሂደት ያካሄዳል፡፡

1. በአካል መቅረብን (personal appearance) ህጎችና አሰራሮች ተዋዋይ ወገኖች ንብረትን ሲያስተላልፉ በአዋዋዩ ፊት ቀርበው ፈቃዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
አረጋጋጩ ፊት ያልቀረበና ያልተፈረመ ፊርማ ተቀባይነት የለውም፡፡ በስሚስሚ (Hearsay) ማረጋገጥ የለበትም፡፡ ቀደም ሲል አንደኛው ወገን ፈርሟል በሚልም የሚደረግ ማዋዋል አይኖርም፡፡ በዚህም የአረጋጋጩ ሁሉም ተግባራት ወይም አገልግሎት ሰነዶችን የሚፈርሙ ሁሉም ወገኖች በአካል በመቅረባቸው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

2. ማንነትን መለየት (identification) ፈራሚው በአረጋጋጩ ፊት በአካል ከቀረበ በኋላ አረጋጋጩ የፈራሚው ግለሰብን ማንነት በጥንቃቄ ያጣራል፡፡ የፈራሚው ማንነት ማረጋገጥ ፈራሚው አስመሳይ አለመሆኑንና ታማኝ ባልሆነ ሰነድ እንዳያጭበረብር ዋስትና ነው፡፡

3. መሰረታዊ ግንዛቤ መፍጠርና የኃይል አለመኖር ማረጋገጥ (basic awareness and absence of duress):: የፈራሚዎችን ማንነት በማረጋገጥ ሂደት አረጋጋጩ ፈራሚዎች ስለ ጉዳዩ ተጠንቅቀውና ዕውቅና ኖሯቸው ያለምንም ማስገደድ ወይም ፍርሃት እየፈረሙ ለመሆናቸው ይታዘባል፣ የረጋግጣል፣ ጥርጣሬ እያለውና ተዋዋዮች አውቀውና በነፃ ፍቃዳቸው የገቡበት ተግባር መሆኑን በጥንቃቄ ያረጋግጣሉ፡፡

4. ሰነዶችን መመዘገብ (paper trail) አረጋጋጮች በህግ ወስደው ከመልካም ልምድ (best practice) መሰረት እያንዳንዱ የሚያረጋግጡት ሰነድ መመዝገብ ወይም ሪከረድ ማድረግ ይጠበቀባቸዋል፡፡ ይህም ሰነድ የህግ መዝገብ ስለሚሆን የማጭበርበር ተግባር ወይም የማጭበርበር ወንጀል በሚኖር ጊዜ ለዓቃቢ ህግ አይነተኛ ማስረጃ ይሆናል፡፡

5. የተሟላ ሰነዶች መቅረብ (complete documents) አረጋጋጮች ሰነዶች የተሟሉ መሆናቸውና በባዶ ሰነዶች (blanck cheque) እንዳያረጋግጡ ሁሉንም ሰነዶችና ገጾችን መመርመር ማጣራት ይኖርባቸዋል፡፡

የንግድ እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ዘመን ጀምሮ የማጭበርበር ወንጀልም አብሮ የነበረ ነውና ይህን ለመቀነስ ወይም ለመከላከል፡-
• የተፃፉ ውሎችን በመመስረት እንዲረጋገጡ ማድረግ፣
• ወሳኝ የሆኑ ውሎችና ተግባራት በተዋዋይ ወገኖች ወይም ፈራሚዎች በዕውቀትና በነፃ ፈቃድ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት ጊዜ የፈቀደው ሂደት መሆኑን መገንዘብ፣
• ቋሚና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን (Real-estate) መመዝገብ ግልጽ የሆነ ህዝብ ሪከርድ (መዝገብ) ስለሆነ መንግስትና ተዋዋይ ወገኖች የሚተማመኑበት ሰነድ ነው፡
ስለዚህ በተዋወይ ወገኖች የሚደረጉ ውሎች፣ ስምምነቶችና ማረጋገጫዎች ለአጭበርባሪዎች የተጋለጡና ተገልጋዩን ለከፍተኛ ችግር ሊዳርጉ የሚችሉ ስለሆነ ማንኛውም ግለሰብ የሚፈልገውን ሰነድ በህግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና የተመዘገበ ሰነድ ከሆነ ዋስትና ያለው መሆኑን አረጋጋጩም የሚቀርቡለትን ሰነዶች አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ትክክለኛነታቸውን ማመሳከሪያዎችን በመጠቀም፣ በማረጋገጥና በመመዝገብ እምነት የሚጣልበት ሰነድ እንዲሆንና አጭበርባሪዎችን መከላከል የስፈልጋል፡፡
በአጠቃላይ የውሎች ምዝገባ ስርዓት አስፈላጊነቱና ጠቀሜታው በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፡-
 መንግስትና ዜጎች/ግለሰቦች/የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና ለመስጠት፣
 ለፍትህ ሥርዓቱ እገዛ ማድረግ፣
 በተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤቶች ሊፈጠር የሚችል የሙግት መጨናነቅን መቀነስ፣
 ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማቀላጠፍ፣
 የእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ኑሮ በሕግ እንዲመራ ማድረግ ናቸው።

መመዝገብ ስለሚገባቸው ሰነዶች

መመዝገብ የሚገባቸው ሰነዶች በዋናነት የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 9 ላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ በአስገዳጅ ሁኔታ መመዝገብ እንዳለበቸው በንዑስ ቁጥር (1) ላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች እና በዚህ አዋጅ መሰረት ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ በስተቀር ህጋዊ ውጤት አይኖራቸውም በማለት
የተደነገጉት፡-

ሀ. አግባብ ባለው ህግ መሰረት መረጋገጥና መመዝገብ ያለባቸው ሰነዶች፣
ለምሳሌ፡- የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚመለከቱ ውሎች በጽሁፍ በሚገባ አኳኋን ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ፊት መሆን አለባቸው፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1723፡፡ ስለኑዛዜ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 891 እና ስለ ንግድ ቤት ኪራይ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 10(1) መሰረት የተመለከቱ ሰነዶችና ውሎች እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ለ. የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም መሻሪያ ሰነዶች፣
ሐ. የንግድና ሌሎች ማኅበራት መመስረቻ ጽሁፎች፣ መተዳደሪያ ደንቦች እና ማሻሻያዎቻቸው፣
መ. ባለጉዳዮች እንዲረጋገጡላቸውና እንዲመዘገቡላቸው የሚያቀርቧቸው ሌሎች ሰነዶች ናቸው፡፡

የሽያጭ ውል፣ የመያዣ ውል፣ የስጦታ ውል፣ የብድር ውል፣ የሥራ ቅጥር ውል፣ የእንደራሴነት ውል፣ የውርስ መብት ድርሻ መልቀቅ ውል፣ ከጋብቻ በፊት ንብረት የማስመዝገብ ውል፣ ቃለ መሀላና ማረጋገጫ (Declaration) የመሳሰሉት የተለያዩ የስምምነት ውሎች ሁሉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ይመዘገባሉ፡፡

ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት

ውል ለመመዝገብ ሥልጣን በኢትዮጵያ በአዋጅ ቁጥር 922/2008 መሰረት በሌላ ህግ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቋማት እንደተጠበቀ ሆኖ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት የሚከተሉት ናቸው፡-
1. የፌደራሉ ሰነድ የማረጋገጥና የመመዝገብ ሥራ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች)፣
2. በክልል መስተዳድሮች ሰነድ የማረጋገጥና የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት (የክልል ፍትህ ቢሮዎች) ፣
3. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የውጭ ሀገር ኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች የተረጋገጡ ሰነዶች፤ በተቀባዩ ሀገር ሕግ እንዲረጋገጡ የሚፈለጉና እና ወደ ውጭ የሚላኩ ሰነዶችን ያረጋግጣል፣
4. በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ ሰነዶችን ያረጋግጣሉ፣
5. የመከላከያ ሰራዊት የክፍል ሹሞች በግዳጅ ላይ የሚገኙ የሰራዊቱ አባላት የሚያቀርቡላቸውን ሰነዶች ያረጋግጣሉ፣
6. የፌደራል ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ከታራሚዎች ወይም ከቀጠሮ እስረኞች የሚያቀርቡላቸውን ሰነዶች ያረጋግጣሉ፣
7. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የክፍል ሹሞች በግዳጅ ላይ ከሚገኙ የፌደራል የፖሊስ አባላት የሚያቀርቡላቸውን ሰነዶች ያረጋግጣሉ፡፡

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውሎችን አረጋግጦ ስለ መመዝገብ ጠቅላላ ሁኔታ
ውል በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚደረግ በህግ ተቀባይነት ያለው ስምምነት ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች ሕጉ ተዋዋይ ወገኖች የተለየ ሂደት እንዲከተሉ ያስገድዳል፡፡ ከእነዚህ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ የውሉ ፎርም በጽሁፍ እንዲሆንና ውሉ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት ማስመዝገብን ያካትታል፡

በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1725 በግልጽ እንደተደነገገው የተለየ ፎርም /በፅሁፍ መሆን ያባቸው/ ሲል የሚያስቀምጣቸው የውል ዓይነቶች አሉ እነዚህም፡-
1. የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚመለከቱ ውሎች፣
2. ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች፣
3. ለብዙ ዘመን የሚቆዩ ውሎች ማለትም የዋስትና፣ የኢንሹራንስ እና ሌሎች በህግ በፅሁፍ መሆን አለባቸው የተባሉ ሌሎች ውሎች ናቸው፡፡

እነዚህን በተመለከተ ለሚደረጉ ውሎች ህጋዊነት በህጉ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ግድ ይላል፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን አስመልክቶ የተቀመጠን ቅድመ ሁኔታ በተመለከተ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1723(1) ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ተዋዋይ ወገኖች ይህን ሳይፈጽሙ ቢገኙ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2877 በተጠቀሰው መሰረት ውሉ ፈራሽ ይሆናል፡፡ ለውሉ ህጋዊነት ማግኘት የውሉ ማረጋገጥና መመዝገብ ሌላው አስገዳጅና አስፈላጊው መከናወን ያለበት ተግባር ነው፡፡
በአጠቃላይ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በማስመልከት የሚፈጸሙ ውሎች ከሌሎች ውሎች ለየት ባለ ሁኔታ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርበው እንዲረጋገጡ ማድረግ በአብዛኞቹ የሕግ ሥርዓቶች የሚፈጸም አካሄድ ነው፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ሕግ ሥልጣን ባለው አካል ፊት እንዲመዘገቡ ያላቸውና እንዲሁም ተዋዋይ ወገኖች በራሳቸው ፈቃድ እንዲመዘገቡላቸው የሚፈልጓቸውን ውሎች ከሌሎች አስረጅ ሰነዶች ጋር በማድረግ ውሎችን ለመመዝገብ ሥልጣን ወደ ተሰጠው አካል ቀርበው የሚያደርጉት ውል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ከመሰጠቱ በፊት ኦዲት የሚያስፈልጋቸው አገልግሎቶች

የሚሸጠው ወይም የሚተላለፈው የንግድ ሥራ ሀብት ከሃምሳ በመቶ ያነሰ ከሆነ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ከመሰጠቱ በፊት አገልግሎት ኦዲት ሥራ መከናወን አለበት፡፡
በከፍተኛ እና በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የሚስተናገድ ታክሰ ከፋይ በግብር ዘመኑ መካከለኛ እና ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነ በሚከተሉት አገልግሎቶች ላይ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ከመሰጠቱ በፊት አገልግሎት ኦዲት መደረግ አለበት፤
 ከሃምሳ በመቶ በላይ የንግድ ሥራ ሀብት ለመሸጥ ወይም ለማስተላለፍ፣
 ድርጅትን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመዝጋት፣
 የንግድ ዘርፍ ለመቀየር ወይም ለመቀነስ ከሆነ፡፡

በተጨማሪም በከፍተኛ እና በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የሚስተናገድ ታክስ ከፋይ በግብር ዘመኑ በከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነ በሚከተሉት አገልግሎቶች ላይ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ከመሰጠቱ በፊት አጠቃላይ ኦዲት መደረግ አለበት፣
 ከሃምሳ በመቶ በላይ የንግድ ሥራ ሀብት ለመሸጥ ወይም ለማስተላለፍ፣
 ድርጅትን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመዝጋት፣
 የንግድ ዘርፍ መቀየር ወይም መቀነስ ከሆነ፣
 ድርጅቶች በአንድ ላይ ለመደራጀት ወይም ለመዋሀድ በውህደት የሚፈጠረው ድርጅት የተዋሀደውን ድርጅት የታክስ ዕዳን ለመክፈል ግዴታ ገብቶ የሚዋሃዱ ስለመሆኑ የሚያስረዳ ሰነድ ከቀረበ፣
 የንግድ መደብሩን ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ፣ በስጦታ ወይም በውርስ ለማስተላለፍ፣
በየትኛውም የስጋት ደረጃ ላይ የሚገኝ የአነስተኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ታክስ ከፋይ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ሲጠይቅ ከሀምሳ በመቶ በላይ የሆነውን የንግድ ሥራ ሀብቱን ወይም የንግድ መደብሩን ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ፣ በስጦታ ወይም በውርስ ለማስተላለፍ ወይም የንግድ ሥራውን ለማቋረጥ ካልሆነ በስተቀር በአገልግሎት ኦዲት ብቻ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
የአነስተኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ታክስ ከፋይ ከሀምሳ በመቶ በላይ የሆነውን የንግድ ሥራ ሀብቱን ወይም የንግድ መደብሩን ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ፣ በስጦታ ወይም በውርስ ለማስተላለፍ ወይም የንግድ ሥራውን ለማቋረጥ የክሊራንስ የምስክር ወረቀት ጥያቄ በሚያቀርብበት ጊዜ አጠቃላይ ኦዲት ተከናውኖ ዕዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀቱ ይሰጠዋል፡፡
Urgent 👈 Vacancy 🔜         
               
1. ጀማሪ /Junior Accountant  
2. ጀማሪ/ junior law graduate
         
Place: 👉Addis Ababa

👉required Skills
Microsoft word
Microsoft Excel
English language
Communication

          👉 How to Apply 👈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
lawsocieties@gmail.com


Deadline March 22/2023
Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
Call for Volunteers
በበጎ ፈቃድ ማገልገል ለምትፈልጉ የህግ ተመራቂዎች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
lawsocieties@gmail.com

Place: Addis Ababa
በፍርድ ክልከላ የተደረገበት ሰው ክልከላው እንዲደረግ ያደረጉት ምክንያቶች በቀሩ ጊዜ እና የተከለከለው ሰው ንብረቱን ለመምራት እና ለማስተዳደር የሚችል የሆነ እንደሆነ በተደረገው ክልከላ ምክንያት ሌላ አድስ ክስ ማቅረብ የማይችል ቢሆንም የተደረገው ክልከላ እንዲነሳለት ማመልከት ይችላል።
ቅፅ 24 መ/ቁ 167560
በኢፌዴሪ_የወንጀል_ሕግ_አንቀጽ_543_ንዑስ_ቁጥሮች_መካከል_ያለው_የልዩነት_ወሰን.pdf
596.8 KB
በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 ንዑስ ቁጥሮች መካከል ያለው የልዩነት ወሰን እና በሥራ ላይ የሚታዩ ተግባራዊ ችግሮች
ጸሐፊ፡- ታፈሰች ወልዴ
Share Premium .pdf
301 KB
የገቢ ግብር ደንብ (ማሻሻያ ) ደንብ ቁጥር  520/2014
ይቅርታ በኢትዮጵያ ህግ

በወንጀል ህግ ውስጥ ይቅርታ ማለት የቅጣት ፍርድ በሙሉ ወይም በከፊል ቀሪ እንዲሆን ወይም የቅጣት ፍርዱ አፈፃፀምና አይነት ቀለል ተደርጎ እንዲፈፀም ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይቅርታ መብት ሳይሆን እድል ሲሆን በሀገራችን ይቅርታ የሚገዛው በይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም ስነስርአት አዋጅ ቁጥር 840/2006 ነው፡፡
የይቅርታ አላማ የህዝብ፣ የመንግስትና የታራሚዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል መንግስት የወንጀል ጥፋተኞች በጥፋታቸው የተፀፀቱና የታረሙ መሆኑን በማረጋገጥ ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅለው አምራች እና ህግ አክባሪ ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ በአጠቃላይም የወንጀል ህግ አላማ የሆት የጠቅላላውን ሰላም፣ ደህንነት፣ ስርአት፣ መብትና ጥቅም ያስጠብቃል፡፡

ይህ የይቅርታ አዋጅ የተፈፃሚነት ወሰኑ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ የመጨረሻ የወንጀል ቅጣቶች ላይ እንዲሁም በማናቸውም የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ውሳኔ ላይ ነው፡፡

ይህም ማለት የክልል ፍርድ ቤቶች በህገመንግስታችን በውክልና የተሰጣቸው የፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር በሚወድቁ ጉዳዮችን ላይ የሚሰጡዋቸውን የመጨረሻ ውሳኔዎች ይጨምራል፡፡ የይቅርታ አይነቶችን ስንመለከት ይቅርታ ለተጣለው ቅጣት በሙሉ ወይም ከፊል ሊሰጥ የሚችል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በቅድመ ሁኔታ የተመሰረተ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ ይቅርታ ናቸው፡፡ በቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ ይቅርታ ማለት ቅጣቱ ቀሪ ተደርጎ የሚቆየው ተቀጪው ተወስነው የተገለፁለትን ቅድመ ሁኔታዎች (በአብዛኛው የመልካም ጠባይ አመራር) እንዲያከብር ሲጠበቅበት ነው፡፡

ይቅርታ ለማግኘት በቅድሚያ የተጣለበት የፍርድ ቅጣት የመጨረሻ መሆን ያለበት መሆኑ ሲሆን ይህም ማለት በይግባኝ እየታየ ከሆነ ይህው እልባት ማግኘቱ ወይ ይግባኝ ያልተባለ ወይም የማይባል ከሆነ የይግባኝ ጊዜው ያለፈ መሆኑ ናቸው፡፡ አንድ የይቅርታ ጥያቄ የቅጣት ውሳኔው የመጨረሻ እንደሆ መቅረብ የሚችል ሲሆን ጥያቄው ታይቶ በተለያየ ምክንያት ውድቅ ከተደረገ ደግሞ ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ሊቀርብ ይችላል፡፡

ይቅርታው በከፊል ከተሰጠ ደግሞ ለቀሪው ቅጣት ከአንድ አመት በኋላ በድጋሚ ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ይህ ጊዜ ሳይጠበቅ የይቅርታ ጥያቄ እንዲታይ ካስፈለገ የይቅርታ ቦርዱ በ¾ኛ ድምፅ በማናቸውም ጊዜ እንዲታይ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

በአዋጁ መሰረት ይቅርታ የሚሰጠው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚዳንት ብቻ ነው፡፡ ለእርሳቸው ጥያቄዎችን አደራጅቶ እና ከአስተያየት ጋር ለውሳኔ የሚያቀርብላቸው በአዋጁ የተደራጀው የይቅርታ ቦርድ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የይቅርታ ቦርድ 11 አባላት ያሉት ሲሆን የፍትሕ ሚኒስትሩ ሰብሳቢ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ ምክትል ሰብሳቢ ሲሆኑ አባላቱ ደግሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና አብዛኛውን ህብረተሰብ ክፍል ከሚወክሉ አደረጃጀቶች በፍትሕ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚዳንት የሚሰየሙ ሁለት አባላት ናቸው፡፡ ይህ ቦርድ የይቅርታ ጥያቄዎችን መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚዳንት የሚያቀርብ ነው፡፡

የቦርድ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ የሚሟላ ሲሆን፣ ውሳኔ በተገኙ አባላት አብላጫ ድምፅ ያልፋል፣ ድምፅ እኩል በኩል በተከፈለ ጊዜ ሰብሳቢው ያለበት ውሳኔ ያልፋል፣ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ደንብ ስነስርአት የሚያወጣ ሲሆን፣ በወር አንድ ጊዜና እንደአስፈላጊነቱ ይሰበሰባል፣ በየስድስት ወሩ ሪፖርት ለክብርት ፕሬዚዳንት ያቀርባል፡፡

የይቅርታ ቦርዱ ደግሞ በፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ የተደራጀ የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ስራው የሚታገዝ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ የይቅርታ ማመልከቻዎችን ይቀበላል፣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ለቦርድ ውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ የቦርድ መዛግብት ይይዛል፣ ውሳኔዎች ይይዛል፣ ይቅርታዎችን በመዝገብ ያሰፍራል፣ አግባብነት ባለው ህግ መሰረት ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፣ ስታትስቲክስ ያዘጋጃል፣ ውሳኔዎችን ያሳውቃል፣ የይቅርታ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይቅርታ ውሳኔ ዋጋ ማጣትና የቅጣት ፍርድ አፈፃፀም መቀጠል በሚመለከት የቦርድ ውሳኔ ለሚመለከታቸው አካላት ያስተላልፋል፡፡

የይቅርታ ጥያቄ በአንድ የፍርድ ተቀጪ በራሱ፣ በወኪሉ፣ በጠበቃው በኩል ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በባለቤቱ ወይም በቅርብ ዘመዱ ደግሞ እርሱ የፈረመበትን ጥያቄ ሊያቀርቡለት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል እንደ አስፈላጊነቱ የፍትሕ ሚኒስቴር ወይም ማረሚያ ቤቱ ለታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ለቦርዱ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ በስሙ የቀረበለት የይቅርታ ጥያቄ ለታራሚው በቅድሚያ መድረስ ያለበት ሲሆን፣ እርሱም በ15 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ በፅሁፍ ካልተቃወመ እንደተስማማ ይቆጠራል፡፡

አለመስማማቱን ለመግለፅ ከአቅም በላይ ችግር ከገጠመው ይህ ችግር እንደተወገደ በ15 የስራ ቀን ውስጥ ተቃውሞ ካለው ማስታወቅ አለበት፡፡

የይቅርታ ጥያቄ የሚከተሉትን የያዘ መሆን አለበት፡-
– የአመልካች ሙሉ ስም፣ የእናት ሙሉ ስም፣ እድሜ፣ ፆታ፣ ዜግነት፣ ብሔር፣ የበፊት ስራ፣ አድራሻ፣ ከመታሰሩ ቀድሞ ያለ አምስት አመት የመኖሪያ አድራሻ፣ የተከሰሰበት ወንጀል፣ ጥፋተኛ የሆነበት ወንጀል፣ የተወሰነበት ቅጣት፣ የፈረደው ፍርድ ቤት፣ የፍርድ መዝገብ ቁጥሩ፣ የፍርዱ አፈፃፀም ደረጃ፣
– ቀድሞ ተፈርዶበት ከሆነ የወንጀሉ አይነት፣ የተወሰነው ቅጣት፣ የፍርዱ አፈፃፀም ደረጃ፣ የፈረደው ፍርድ ቤት፣
– ያለበት ማረሚያ ቤት ስም፣ የይቅርታ ጥያቄው ምክንያት፣ የስነምግባር አስተያየት ከማረሚያ ቤቱ፣ ከቅጣት ፍርዱ በፊት ስላለው ስነምግባር ሊመሰክሩ የሚችሉ የስጋ የጋብቻ ወይም የጥቅም ግንኙነት የሌላቸው 3 ምስክሮች ሙሉ ስምና አድራሻ፣
– የወኪሉ ውክልና ወይም የዝምድና ማስረጃ፣
– የማረሚያ ቤት አስተያየት ከምክንያት ጋር፣
– መቀጮ ወይም ካሳ እንዲከፍል ተወስኖበት ከሆነ ስለመክፈሉ፣ ካልከፈለ ምክንያቱ፣
– ቀደም ሲል ይቅርታ ተደርጎለት ከነበረ ወይም ጥያቄ ቀርቦ ውድቅ ተደርጎበት ከነበረ ውሳኔው የተሰጠበት ቀንና ዓመተ ምህረት፣
– ለጥያቄው ደጋፊ ማስረጃውን፣ ሰነዶች ካሉ፣ በእጁ የሌሉ ደጋፊ ሰነዶች ካሉ የሚገኙበት ቦታ የሚያለክት ሊሆን ይገባል፡፡

በዚህ መሰረት ጥያቄ የቀረበለት የይቅርታ ቦርድ ምስክር ሊሰማ ይችላል፣ የዓቃቤ ህግ እና የፍርድ ቤት መዝገብ ሊመለከት ይችላል፡፡ የይቅርታ ጥያቄዎችን ከመንግስትና ህዝብ ጥቅም አንፃር ይመዝናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ ባወጣው የይቅርታ አሰራር ስነስረአት መመሪያ መሰረት የሚከተሉት ጉዳዮች ከግምት እንደሚገቡ ይጠበቃል፡-
• የአመልካቹ አደገኛነት፣
• የወንጀሉ ክብደት፣
• የማረሚያ ቤት ቆይታ ጊዜ፣
• ከቀድሞ መስሪያ ቤት፣ ከመኖሪያ አካባቢ ማህበረሰብ፣ ከቤተሰብ፣ ከሐኪም፣ ከሌሎች የተሰበሰቡ መረጃዎች፣
• ለወደፊት በሰላም ለመኖር የሚያሳየውን ባህሪ፣
• ጥፋተኝነቱን አምኖ በመቀበል የተፀፀተ መሆኑ፣
• ከተጎጂ/ቤተሰብ ጋር ለመታረቅና ለመካስ ያደረገው ጥረት፣ የተወሰነበትን ካሳ ለመክፈል ያለውን አቅምና ፍላጎት፣ (ማህበራዊ ፍርድ ቤት ድህነት ማስረጃ)
• ተጎጂ/ቤተሰብ ለማግኘት ከተቻለ በጥያቄው ላይ ያላቸው አስተያየት፣
• የማረሚያ ቤት ፀባይና ስነምግባር፣
• የአመልካች የቤተሰብ፣ የጤንነት (ለመታረም አስቸጋሪ ያደረገ በቦርድ የተረጋገጠ)፣ እድሜ ሁኔታ፣
• የህዝብና መንግስት ጥቅም ልዩ ሁኔታ፣
• እድሜ ልክ ፍርደኛ ከሆነ 12 አመት እስር መጨረሱን፣ ሌሎች ፍርደኞች 1/3ኛ እስር መጨረሳቸውን፣ የግዴታ ስራ ካለበት ይህን መጨረሱን፣ ናቸው፡፡

ቦርዱ የሙስና፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሽብር፣ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሀሰተኛ ገንዘብ መስራት ማዛወር፣ አደገኛ እፅ፣ ሴቶችና ህፃናት መድፈር ወይም መጥለፍ፣ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ወንጀል የፈፀሙ ፍርደኞችን ጉዳይ በጥንቃቄ በልዩ ሁኔታ ካልሆነ እደሌሎች ወንጀሎች አያይም፡፡

በዚህ መልክ ታይቶ የሚፈቀድ የይቅርታ ውሳኔ ውጤትን ስንመለከት ውሳኔው በግልፅ በከፊል መሆኑ ካልተመለከተ በቀር ይቅርታው የፍርድ ቅጣቶችን በሙሉ ያስቀራል፡፡ ሆኖም ይቅርታ ከወንጀል ፍርዱ የሚመነጩ የፍትሐብሔር ሀላፊነቶችን አያስቀርም፡፡ በተጨማሪም በፍትሐብሔር የጠፋውን እንደነበር ለመመለስ እና በተበዳይ ላይ ለደረሰ ጉዳት የሚከፈል ካሳና ኪሳራ አያስቀርም፡፡ ሆኖም በተለይ ካልተገለፀ በቀር ለመንግስት ሊከፈል የሚገባ ወይም ያልተከፈለ ኪሳራ ቀሪ ይሆናል፡፡ ይቅርታው ከመሰጠቱ ቀድሞ የተፈፀሙ ቅጣቶች ደግሞ የፀኑ ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ በተሰጠበት ወንጀል በአጥፊው ላይ የተያዘው የወንጀል ሪከርድ በወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተመዝግቦ ይኖራል፡፡
ይቅርታ የተሰጠው በሀሰተኛ ወይም በተጭበረበረ ማስረጃ ተመስርቶ ከሆነ ይቅርታው ዋጋ አይኖረውም፡፡

በቅድመ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ይቅርታ ቅድመ ሁኔታው ከተጣሰ ዋጋ ያጣል፡፡ በዚህም መሰረት አጥፊው ቀሪ ቅጣቱን እንዲፈፅም ለማድረግ እንዲቻል ቦርዱ ይቅርታው እንዲሰረዝ ክብርት ፕሬዚዳንት ትእዛዝ እንዲሰጡ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ ይህ ተቀባይነት እንዳገኘ ትእዛዙ ለአጥፊው እንዲደርሰው ይደረግና ቅሬታ ካለው ትእዛዙ በደረሰው በአስራ አምስት ቀን ለቦርዱ ማቅረብ አለበት፡፡ ቅሬታው ተቀባይነት ካጣ የይቅርታ ምስክር ወረቀቱን እንዲመልስ ይደረጋል፣ በዚህም መሰረት የመያዣ ትእዛዝ እንዲሰጥ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥያቄ ቀርቦ ቀሪ ቅጣቱን እንዲፈፅም ይደረጋል፡፡

በአጠቃላይ የይቅርታ አላማ ከላይ እንደተመለከትነው አጥፊዎች ከጥፋታቸው ታርመውና ተፀፅተው ህግ አክባሪና መልካም ዜጋ ሆነው መኖር እዲችሉ ለማድረግ የሚሰጥ እድል ነው፡፡ የወንጀል ቅጣታቸው የመጨረሻ የሆነ፣ አንድ ሶስተኛ እስራታቸውን የጨረሱ፣ በማረሚያ ቤት በመልካም ባህሪ የቆዩ፣ ከጥፋታቸው የተፀፀቱና በቀጣይም ህግን አክብረው ለመኖር የሚችሉ ሰዎች የሚያገኙት ሁለተኛ እድል ሲሆን ይቅርታ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ብሎም ከወንጀል የተጠበቀ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ይቅርታ የሚሰጣቸው ሰዎችም ይህን ተገንዘበው ህብረተሰቡን በመካስ በህግ አክባሪነትና በመልካም ስነ ምግባር መመራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ሠ/መ/ቁጥር 211841 ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ/ም
በአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ ዉል መሠረዝ (Unilateral cancellation of contract) ተግባራዊ ሊሆን የሚችለዉ በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 1786 እስከ 1889 ከተደነገጉት አራት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ተሟልቶ ሲገኝ ነዉ፡፡እነዚህም ቅድመ ሁኔታዎች፡-(1) የዉል ማፍረሻ የሚሆኑ የዉል ቃሎች በዉሉ ተገልጸዉ ሲገኙና ይሄዉ ሁኔታ ተፈጽሞ ሲገኝ ፤(2) ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ በዉሉ ከተመለከተ፣በማስጠንቀቂያዉ ላይ በተሰጠዉ ጊዜ ወይም በፍርድ ቤት በተሰጠ የችሮታ ጊዜ ዉስጥ ተዋዋዩ ግዴታዉን ካልተወጣ ፤(3) ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን የገባበትን ግዴታ ለመፈጸም የማይቻለዉ ሆኖ ከተገኘና በዚህ ምክንያት የዉሉ መሰረታዊ ስምምነት ከተነካ ፤ እንዲሁም (4) ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን የዉል ግዴታዉን የማይፈጽም ስለመሆኑ ግልጽ በሆነ መንገድ ሲያሳዉቅ የሚሉ ናቸዉ፡፡ሕጉ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በመስፈርትነት ያስቀመጠዉ በተቻለ መጠን በሕግ አግባብ የተደረጉ ዉሎች እንዲፈጸሙ ጥበቃ ለማድረግና በተናጠል የሚደረገዉ የዉል መሰረዝ የመፍትሄ አማራጭ በልዩ ሁኔታ በተወሰኑ ሁኔታዎች ብቻ ተፈጻሚ እንዲሆን በመፈለግ ነዉ፡፡ ስለሆነም አንደኛዉ ተዋዋይ ወገን ሌላዉ ወገን ግዴታዉን ባለመወጣቱ ዉሉን በተናጠል ሰርዣለሁ በማለት በተከራከረ ጊዜ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ቢያንስ አንዱ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ታክስን/ግብርን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ታክስዎን/ግብርዎን በወቅቱ ሲከፍሉ ከብዙ እንግልት ከመዳንዎ በተጨማሪ አላስፈላጊ ቅጣት ከመቀጣት ይድናሉ፡፡ ግብርን በወቅቱ ከከፈሉ ደግሞ ለሀገርዎ እና ለእርስዎ የሚጠቅመውን በወቅቱ እና በአስፈላጊው ወቅት እንዳደረጉ ይቆጠራል፡፡

ታክስዎን በተለያየ ምክንያት ሳይከፍሉ ካዘገዩ ከሚደርስብዎት ውጣ ውረድ በተጨማሪ ቅጣቶችንም ለማስተናገድ ይገደዳሉ፡፡ ከነኚህ ቅጣቶች ውስጥ ለእርስዎ ለግንዛቤ ይረዳዎት ዘንድ የሚከተሉት ተቀንጭበው ቀርበዋል፡፡

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦
1. ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና
2. ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡
I. የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
II. መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
III. ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
222680.pdf
869 KB
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ላይ የሚገኘው parol evidence rule በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ በሚታመንበት ጊዜ ተፈጻሚነት የለውም። የውሉ ይዘት ለምሳሌ የገንዘቡ መጠን፡ በውሉ ላይ ያለው ቀን ወዘተ በሌላ ውጫዊ ማስረጃ ሊስተባበል ይችላል።
በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ የውሉ ይዘት ፊርማን ጨምሮ በአከራከረ ጊዜ በምን አይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል? የሚለው ጥያቄ በተመለከተ የሰበር ችሎት የሚከተለውን የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የቤት ሽያጭ ውል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት መደረግ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገበት አንዱ አላማ ውሉ በጽሁፍ በሰፈረው አግባብ በእርግጥ የተደረገ ስለመሆኑ እና ይዘቱም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡በመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡