አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ልዩነታችን ውበታችን ነው። ብናውቅም ባናውቅም የተለያየ እምነት እና ባህል ላከበረው ሀብት ነው።
እንኳን አደረሳችሁ። መልካም ጥምቀት።
#አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
በጃንሜዳ በከተራና በጥምቀት በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ
👉 ከተለያዩ ግለሰቦች የተሰረቁ 20 ሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፣

**
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ፖሊስ ስርቆትና ሌሎች ደረቅ ወንጀሎች ቢፈፀሙ እንኳ ፈጣን ምላሽ እና አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በጃንሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚቋቋም መግለፁ ይታወሳል።
ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥር 10 በጃንሜዳ በተከበረው የከተራ በዓል ዕለት የስርቆት ወንጀት የፈፀሙ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ 3 ሞባይል ስልክ በኤግዚቢትነት ተይዟል።
በተሳሳይ ጥር 11 በበዓሉ ዕለት ፀበል ለመረጨት የነበረውን ግፊያ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በቁጥር በርከት ያለውን ሰልክ መስረቃቸውን የጠቀሰው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አንደኛው 9 ስልኮችን በኪሱ፣ አንደኛው ደግሞ 8 ሞባይል ስልኮችን በሆዱ ደብቀው የተገኙ ናቸው ተብሏል።
ሞባይ ስልክ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያው ቀርበው በማመልከታቸው ከተያዙት ስልኮች መካከል የተወሰኑት ባለቤቶቻቸው የተገኙ ሲሆን ሌሎቹን አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርቦ መጠየቅና ማረጋገጥ እንደሚቻል ተገልጿል።
በአጠቃላይ 13 ተጠርጣሪዎች እና 20 ሞባይል ስልክ የተያዘ ሲሆን በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ህብረተሰቡ እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር ቆመው እያሳዩት ላለው ተባባሪነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።
https://t.me/lawsocieties
የብሔር ማንነቴን በአባት ለመወስን የሚያስገድድ የሕግ አንቀጽ የሚያሳየን ካለ! #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ወራሽነቱን በፍርድ ቤት አሳውጆ የቤት ስመ ንብረት ካዞረ ሰው ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ የሽያጭ ውል በመፈፀም ቤት የገዛ ግለሰብ የቅን ልቦና ገዥ በመሆኑ በሌሎች ወራሾች ውሉ እንዲፈርስ የሚጠየቅበት አግባብ የለም።
የፌ/ጠ/ፍ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተያያዘ የቅን ልቦና ገዥነትን አስመልክቶ የሰጠው የህግ ትርጉም- ያልታተመ*

https://t.me/lawsocieties
222680.pdf
869 KB
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ላይ የሚገኘው parol evidence rule በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ በሚታመንበት ጊዜ ተፈጻሚነት የለውም።
ውሉ ይዘት ለምሳሌ የገንዘቡ መጠን፡ በውሉ ላይ ያለው ቀን ወዘተ በሌላ ውጫዊ ማስረጃ ሊስተባበል ይችላል።
በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ የውሉ ይዘት ፊርማን ጨምሮ በአከራከረ ጊዜ በምን አይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል? የሚለው ጥያቄ በተመለከተ የሰበር ችሎት የሚከተለውን የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የቤት ሽያጭ ውል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት መደረግ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገበት አንዱ አላማ ውሉ በጽሁፍ በሰፈረው አግባብ በእርግጥ የተደረገ ስለመሆኑ እና ይዘቱም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡በመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡
https://t.me/lawsocieties
መንግስት ስለጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ የህግ ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

ሙስና ብሄራዊ የደህንነት ስጋት ነው ያለው መንግስት ሙስናን ለመዋጋትም ሰባት አባላት ያሉት ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስር መጀመሩ ይታወሳል፡፡https://am.al-ain.com/article/who-do-lawyers-say-about-anti-corruption-campaign

https://t.me/lawsocieties
የደላላነት ስራን ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፍቃድ ሳይኖር የደላላነት ስራ ሰርቻለሁ ብሎ ክፍያ ለማስከፈል የሚቀርብ ክስ የህግ ጥበቃ በሌለው መብት ላይ ተመስርቶ የሚደረግ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም።ቅፅ 25 ሰ/መ/ቁ204199
ልዩነታችን በምን ነው?
ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ስብእና....!
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Ethiopia
https://t.me/lawsocieties