አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት ስህተትን ስለማረም
ባለሥልጣኑ በታክስ ሕግ መሠረት ለታክስ ከፋዩ የሰጠው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ በታክስ ሕግ ወይም በጉዳዩ ኩነቶች ላይ ትርጉም ጥያቄ የማያስነሳ የጹሑፍ፣የሂሳብ ስሌት ወይም ሌላ ማንኛውንም ስህተት የያዘ በሚሆንበት ጊዜ ባለሥልጣኑ ስህተቱን ለማረም ሲባል የታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ወይም ሌላውን ሰነድ የታክስ ስሌት ማስታወቂያው ወይም ሰነዱ ለታክስ ከፋዩ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5/አምስት/ ዓመታት ውስጥ ማሻሻል ይቻላል፡፡
በዚህ መሠረት የሚታረም የታክስ ስህተት የሚባለው:-
• የመደመር፣ የመቀነስ፣ የማባዛትና የማካፈል ስህተት፣
• በስሌት ማጠቃለያ ላይ ከመንደርደሪያ ሀሳብ መለየት ወይም መቃረን፣
• ከአንድ የሒሳብ ቁጥር ከፊት ወይም ከኋላ የቁጥር መጨመር ወይም መቀነስ ወይም የሒሳብ ቁጥር ቦታ መቀያየር (transposition)፣
• የገቢ ወይም የወጪ ኮድ አመዘጋገብ ስህተት፣
• የቃል ወይም የሐረግ በአዎንታ ወይም አሉታ መቀያየር፣
• የሒሳብ ቁጥር ወይም ሀሳብ መተው ወይም መዘለል (omission)፣
• ከግብር ነጻ የሆነ ገቢን ግብር በሚከፈል ገቢ ውስጥ መጨመር፣
• በአንድ ታክስ ከፋይ ሒሳብ ውስጥ የሌላ ታክስ ከፋይ ሒሳብ መጨመር ወይም ማቀያየር፣
• የታክስ መጣኔን ወይም የትርፍ ህዳግን መሳሳት፣
• በታክስ ቅሬታ አጣሪ የሥራ ክፍል፣ በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ወይም በመደበኛ ፍ/ቤት እንዲስተካከል የተወሰነን ጉዳይ አለማስተካከል፣
• በዚህ መሠረት ስህተት ሊታረም የሚለው በታክስ ውሳኔ መጠን ላይ በመጨመር ወይም በመቀነስ ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን ብቻ ሆኖ ለውጥ የማያመጣ በመሆኑ የማይታረም ስህተት ሲኖር ለታክስ ከፋዩ በጽሑፍ ይገለጻል፡፡
በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት ቀጥሎ በተመለከተው መንገድ የሚታረም ይሆናል፡፡
🔹የግምት የታክስ ውሳኔ ላይ ስህተት አለበት የሚል ታክስ ከፋይ የግምት ታክስ ስሌት ማስታወቂያ በተሰጠው ከ5 ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የታክስ ስሌቱን ላከናወነው ወይም ውሳኔውን ለሰጠው የሥራ ሂደት ጥያቄውን በጽሑፍ በማቅረብ ስህተቱ እንዲታረምለት ሊጠይቅ ይችላል፡፡
🔹የግምት ታክስ ስሌቱን የሠራው ሥራ ሂደት የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ከተሰጠ በኋላ በታክስ ስሌትና አወሳሰን ሂደት የተፈጸመ ግልጽና የማያከራክር ስህተት የፈፀመውን ባለሙያ ወይም የሌላ ባለሙያ አስተያየት ጭምር በማያያዝ ስህተቱ እንዲታረም የውሳኔ ሀሳብ ለቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ያቀርባል፡፡
🔹የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ስህተቱ እንዲታረም ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በአግባቡ መመርመር ያለበት ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበለትን ባለሙያና የሥራ ሂደት አስተባባሪን ጠርቶ ማነጋገርና ማወያየት ይችላል፡፡
🔹ታክስ ከፋዩ ጥያቄ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥያቄው ላይ ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡
🔹የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሊታረም የሚል ስህተት አለመኖሩን በመግለጽ ውሳኔ የሰጠ እንደሆነ ታክስ ከፋዩ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ካለው ውሳኔው በደረሰው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዋና መ/ቤቱ የሚመለከተው ዳይሬክቶሬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ዳይሬክቶሬቱም በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ለሀገር ውስጥ ታክስ ከፋይ ወይም ለሕግ ማስከበር ም/ዋና ዳይሬክተር (ሚኒስትር ዴኤታ) ያስተላልፋል፡፡
🔹በቀረበው ቅሬታ ላይ የሀገር ውስጥ ታክስ ወይም የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ለጥያቄው በቀረበ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል፡፡
🔹 በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ታክስ ከፋይ ውሳኔው በደረሰው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዋና ዳይሬክተሩ በጽ/ቤቱ በኩል ሊያቀርብ ይችላል፡፡
🔹ጥያቄው በቀረበ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት በኩል ለታክስ ከፋዩ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
🔹ስህተቱ እንዲታረም ከተወሰነ፡- የታረመው ውሳኔ የመጀመሪያ ውሳኔ በሰጠው የሥራ ክፍል በኩል የተስተካከለ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ይሰጣል፡፡
🔹ለታክስ ከፋዩ ተስተካክሎ የሚሰጠው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ቀደም ሲል የተሰጠው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የተሻረ መሆኑን የሚገልጽና ስህተቱ በታረመበት ጊዜ ያለውን ቀንና ቁጥር የያዘ መሆን አለበት፡፡
🔹ስህተትን ለማረም የሚወስደው ጊዜ በታክስ ውሳኔ ላይ በመደበኛ መንገድ ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜን ከመቆጠር የሚያስቀር አይሆንም፡፡
🔹ከላይ በተዘረዘሩት መሠረት የሚቀርብ ስህተት የማረም ጥያቄ ጉዳዩ በቅሬታ ወይም በይግባኝ ወይም በፍ/ቤት ደረጃ ደርሶ የታየ ቢሆንም የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

via #taxandbusinesslawblog
https://t.me/lawsocieties