አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የስነ-ምግባርና የሙስና ወንጀል መከላከል ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 26/2015 በኢትዮጵያ የስነ-ምግባርና ሙስና ወንጀል መከላከል ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ ላይ በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በተዘጋጀው መድረክ ላይ እንደተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስጋት የሆነው የሙስና ወንጀልን ለመከላከል አስፈላጊው ሁሉ ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

ለዚህም ኮሚሽኑ ከሙስና የጸዳች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ላይ ፖሊሲ ተቀርፆ ወደ ስራ መግባት ያስፈልጋል ነው የተባለው።

ከፖሊሲው ዓላማዎች መካከል ሃላፊነትን መወጣት የሚያስችል አቅምን ማጠናከር እና ተቋማዊ ትብብርና ቅንጅትን ማረጋገጥ መሆኑ ተጠቅሷል።

በፖሊሲው የመንግስት ግዢ፣ መሬት አስተዳደር፣ ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶች፣ ፍቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር፣ የገቢ አሰባሰብ አስተዳደር፣ የጉሙሩክ አሰራር፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የፖሊስና የትራፊክ ፖሊስ አሰራር፣ የፍርድ ቤቶች አሰራር፣ የመንግስታዊ የልማት ድርጅቶች አሰራር እና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም /ማዕድን ልማት/ በአገራችን ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎች መሆናቸው በረቂቅ ፖሊሲው ተመላክቷል።

ፖሊሲው የተለያዩ መርሆዎችን በውስጡ የያዘ ሲሆን የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ስነ ምግባራዊ አሰራር፣ የአሰራር ነጻነት እና ሙያዊ ብቃትን ማሳደግ ተጠቃሽ ናቸው።

የፖሊሲው ስራ ላይ መዋል የጸረ ሙስና ትግሉን ለማሳለጥ እንደሚረዳም ተጠቁሟል።

በውይይት መድረኩ የሚዲያ ሃላፊዎች፣ የዲሞክራሲ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች፣ የጥበብ ሰዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
#በአለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ሼር በማድረግ ሰላምታውን አድርሱላቸው።
Debub Global Bank SC

1 - Administrative Assistant
2 - Attorney
3 - Branch Manager I
     Apply here
      👇👇👇
https://shegerjobs.com/job/debub-global-bank-s-c/

Deadline: December 09/2022

Share for your friends
We all have a role to play in stopping the spread of harmful misinformation online, which can result in people being left uninformed, unprotected & vulnerable during a crisis.
Before you share content online, verify facts by asking basic questions.
United nations
https://t.me/lawsocieties
From Awareness to Action! Make a promise to people around you today! I will not offend! I will not be silent when witnessing abuse! Inform the right authorities and help survivors!

If you are going through Sexual and Gender Based Violence call to the following hotline:
Call: 991 - to report to Addis Ababa Police on sexual assault and related cases.
Call: 6388 (Alegnta - Setaweet) - to receive in-depth counseling and referral services for gender-based violence.
Call: 7711 (Ethiopia Women Lawyers Association) - to receive free legal counseling service
Call : 8044 (Marie Stopes) - To get counseling service on reproductive health and family planning
Or head to one stop centers at Gandhi MCM, Menelik II, Tirunesh Beijing and Saint Paul Hospitals to report SGBV.
#linkupaddis
https://t.me/lawsocieties
የ2 ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የግድያ ወንጀል የፈጸመችው ግለሰብ በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣች።

በተደጋጋሚ ይሰድበኛል በሚል በባለቤቷ ላይ ቂም በመያዝ እንቅልፍ የተኛበትን አጋጣሚ በመጠቀም በመጥረቢያ ጭንቅላቱን ደጋማ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ አስራት እንድትቀጣ ፈርዶባታል።

ከበቡሽ አለሙ የተባለችው ግለሰብ የሁለት ልጆቿ አባት በሆነው ባለቤቷ ላይ የግድያ ወንጀሉን የፈፀመችው መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ/ም በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው 58 መዝናኛ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር አውሎ መዝገብ ካደራጀ እና በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
ከግብር/ታክስ ጋር በተያያዘ በወንጀል የሚያስጠይቁ ጥፋቶች

በግብር ወይም ታክስ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉን በመተላለፍ የሚፈፀሙ በመሆኑ ክሱ የሚመሰረተው የሚታየው እና ይግባኝ የሚቀርበው በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ነው፡፡

በወንጀል ከሚያስጠይቁ የጥፋት ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

1. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላይ የሚፈፀም ጥፋት፣
2. ህግን በመጣስ ግብር/ታክስ ባለመክፈል፣
3. የሀሰት ወይም አሳሳች መረጃ ማቅረብ፣
4. የግብር/ታክስ ሚኒስቴሩ ስራ ማሰናከል፣
5. ያለ ደረሰኝ ግብይት መፈፀም፣
6. በግብር/ታክስ ሚኒስቴሩ ሰራተኞች የሚፈፀሙ ጥፋቶች፣
- ሳይፈቀድ ግብር/ታክስ መሰብሰብ፣
- የተዘረዘሩትን እንዲፈፀሙ መርዳት ወይም ማበረታታት፣
7. በድርጅት የሚፈፀም ጥፋት፣
8. በተረካቢዎች የሚፈፀም ጥፋት፣
9. ለውጥን ያለማስታወቅ፣
10. የተጭበረበሩ ወይም ሕገ-ወጥ ደረሰኞችን ማዘጋጀት፣ ማተም፣ መሸጥ ወይም ማሰራጨት፣
11. ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ጠቅላላ ወንጀሎች፣
12. ሕገ-ወጥ የሆነ ተመላሽን ወይም ከተገቢው በላይ ማካካሻን መጠየቅ፣
13. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣
14. ከቴምብር ቀረጥ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣
15. ስልጣን ሳይኖር ታክስ መሰብሰብ፣
16. የታክስ ወንጀሎችን ማበረታታት ወይም መርዳት፣
17. ከሽያጭ መመዝገቢያ ጋር በተገኛኘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣
18. ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ የማድረግ ኃላፊነት ለተሰጠው ሰው ግብሩን ቀንሶ በማስቀረቱ ምክንያት ዕቃ ለማቅረብ ወይም አገልግሎት ለመስጠት እምቢተኛ ሆኖ መገኘት፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
የንግድ_ምዝገባ_ፈቃድ_እና_ድኅረ_ፈቃድ_ኢንስፔክሽን_መመሪያ_ቁጥር_935.pdf
946.7 KB
አዲስ መመሪያ

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፀደቀ አዲስ “የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 935/2015 “፡፡
የመከላከያ ማስፈቀጃ
በአጭር ስነ ስርዓት ታይቶ እንዲወሰን ክስ በሚቀርብበት ጊዜ ተከሳሹ ክሱን ለመከላከል እንዲፈቀድለት የሚያቀርበው አቤቱታ

በአጭር ሥነ ሥርዓት እንዲታይ በሚቀርብ ክስ አመራር ሥርዓት ተከሳሽ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በፍ/ቤቱ አግኝቶ የተጠየቀውን ገንዘብ ላለመክፈል በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው ፍ/ቤቱ ከአጭር ሥነ ሥርዓት ወደ መደበኛ የክርክር ሥነ ሥርዓት ውስጥ በመግባት ግራ ቀኙን በአግባቡ በማስረጃ ካከራከረ በኋላ ነው፡፡
የፈቃድ ጥያቄ ደረጃ ላይ የቼክ ባሕርይ ሳይሆን መታየት ያለበት ተከሳሽ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ያቀረበው ምክንያት ፈቃድ የሚያሰጥ መሆን አለመሆኑን ነው፡፡
የፍሬ ነገር ክርክር ከፈቃድ በኋላ የሚታይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43315 ያልታተመ፣  ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 284-286
........
https://t.me/lawsocieties
የፍርድ ቤቶች ስልጣን
የፍርድ ቤቶች አንድን ክርክር አይተዉ አከራክረዉ ለመወሰን ስልጣን አላቸዉ የሚባለዉ በህግ ተወስኖ ሲሰጣቸዉ ነዉ፡፡

የፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለይተዉ ከቀረቡ ህጎች መካከልም የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013፣ የተሻሻለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ቁጥር 361/1995፣ የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ስነ-ስርአት ሕግ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የፍርድ ቤቶች ስልጣንም ሲባል ከማህበራዊ ፍርድቤት ተነስቶ እስከ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ያሉትን ያካትታል፡፡

የአንድ ፍርድ ቤት ስልጣንም ሊወሰን የሚችለዉ፡-
1. በሚከራከሩበት ንብረት የዋጋ መጠን
2. በተከራካሪ ወገኖች ማንነት 
3. የሚከራከሩበት ንብረት የሚገኝበት ቦታ
4. ተከራካሪ ወገኖች የሚገኙበት ቦታ
5. በዉል ጉዳይ ከሆነ ዉሉ የተፈረመበት ቦታ፣ ሊፈጸምበት የታሰበዉ ቦታ በመሳሰሉት
6. በሚከራከሩበት ጉዳይ የግዝፈት መጠን እንዲሁም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ይወሰናል፡፡
የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ስልጣንን በተመለከተ
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ ስንመለከት አንቀጽ 4(16) ላይ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያይበት ስልጣኑ የተለየ ሲሆን በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዙሪያ አንቀጽ 5(ደ) ስር ተዘርዝረዉ ይገኛሉ፡፡
የተሻሻለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ቁጥር 361/1995 በሌላ መልኩ ደግሞ በአንቀጽ 41 ላይ የፍትሐብሔር እና ወንጀል ስልጣናቸዉን አስቀምጧል
ይህን ካልን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሉት ፍርድ ቤቶች  የመጀመሪያ ደረጃ እና  ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ናቸዉ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ለከተማዉ የተሰጠዉን የፍትሐብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች አጠቃሎ የሚያይ ሲሆን የይግባኝ ሰሚ  ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን በይግባኝ ያያል።  ነገር ግን በይግባኝ ፍርድ ቤቱ በተሰጠዉ ዉሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን በአገሪቱ ባሉ  ፍርድ ቤቶች የተሰጠን የመጨረሻ ዉሳኔ የማየት ስልጣን ለተሰጠዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ማቅረብ ይቻላል። በመጨረሻም ህገ መንግስታዊ ዉሳኔ ለሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፍትህ ስርዓቱን የመጨረሻ ዉሳኔ ይሰጣል።
ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስንመጣ  ከከተማ ፍርድ ቤቶች የሚለያቸዉ 3 እርከን ስላላቸዉ ነው። የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ናቸዉ። የፍርድ ስልጣናቸዉም በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ ተለይቶ ተቀምጥዋል። አንድ ተከራካሪ ወገንም የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን አቅርቦ ዳኝነት የጠየቀበት ጉዳይ ዉድቅ ቢደረግበት የይግባኝ ቅሬታዉን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ሲሆን የመጀመሪያው ዉሳኔ ከጸና ጉዳዩን ለሰበር ችሎት አቅርቦ የህግ ስህተት ካለ ከማሳረም ዉጪ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን አቅርቦ ለሁለተኛ ግዜ ይግባኝ ማቅረብ አይችልም። ይህም ማለት አንድ ጉዳይ ከአንድ ግዜ በላይ ይግባኝ ሊባልበት አይችልም። የከፍተኛ ፍርድ ቤትም በመጀመሪያ ፍቅደ ስልጣኑ ያየዉን ክርክር ይግባኝ ሊባልበት የሚችለዉ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሆናል።
ዉበአለም መስፍን የቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ
https://t.me/lawsocieties
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)

ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL (EHRCO)
የግማሽ ቀን አውደ ጥናት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በበጎ አድራጎት ማህበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ሐገር በቀል ድርጅት ሆኖ በ1984 ዓ.ም የተመሰረተና በምዝገባ ቁጥር 1146 ከ02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳግም ተመዝግቦ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የሰበዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ነው። ኢሰመጉ ለትርፍ ያልተቋቋመ ነፃና ገለልተኛ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሃይማኖት ተቋም፣ የብሄረሰብ ቡድን፣ ማህበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን የሰብዓዊ መብቶች ተሞጋች ተቋም ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
የምቹ የሥራ ሁኔታዎች እና ፍትህ የማግኘት ሂደት
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት (ኢሰመድህ) (ንዑስ አመልካች) ከአክሽን ኤድ ኢትዮጵያ (AAE) (ዋና አመልካች)፣ የህዝብ ጤና ኢትዮጵያ (HE)፣ የኢትዮጵያ ሴቶች እና ህጻናት ማህበራት ህብረት (UEWCA) እና አማኑኤል ልማት ድርጅት (EDA) (ንዑስ አመልካቾች) ጋር በመተባበር ከኖርዌይ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት ትብብር ኤጀንሲ (NORAD) በተገኘ ድጋፍ “በኢትዮጵያ ብዝዛን፣ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን፣ የግዳጅ ስራ እና ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መግታት” የተሰኘ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረትም በስሩ ከያዛቸው ድርጅቶች መሃከል የኢትዮጵያ ሱብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ሰራተኞች መብቶች ተሟጋች ጋር በመሆን ይህን ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት ኢሰመጉ በግለሰቦች የምቹ የሥራ ሁኔታዎች እና ፍትህ የማግኘት ሂደት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የግማሽ ቀን የምክክር አውደ ጥናት ለተለያዪ የመንግስት ተቋማት፣ ለቀጣሪ ድርጅቶችና ለሰራተኛና አሰሪ አገናኝ ድረጅቶች አዘጋጅቶ የተለያዩ የድርጅት ተወካዮች  በተገኙበት ዛሬ ህዳር 30/2015 በካሶፒያ ሆቴል ከ 2፡30 ሰዓት ጀመሮ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
https://t.me/lawsocieties
አካልን ነፃ ስለ ማዉጣት (Habeas Corpus)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሰዉ ልጆች ሰዉ በመሆናቸዉና በተፈጥሮ ያገኟቸዉ ሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ መብቶች አንዱ ህጋዊ ያልሆነ እስርን የመቃወም መብት (አካልን ነፃ ማዉጣት) አንዱ ነዉ፡፡ የሰዎች የነፃነት መብት የሚገደበዉ ሕጋዊ በሆነ ሥርዓት ብቻ ነዉ፡፡ ይህን ለመጠበቅ ሲባል የአያያዝ ሥርዓትም ሆነ እስር ላይ የሚቆይበት ሁኔታ በሕግ በግልጽ እንዲደነገግ ይደረጋል፡፡ የአያያዝ ሕጋዊነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል የያዘዉ ፖሊስ በ48 ስዓት ዉስጥ ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መደረጉ የነፃነት መብትን ማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ አካልን ነፃ ስለ ማዉጣት እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡

አካልን ነፃ ማዉጣት(Habeas Corpus) ምንነት

አካልን ነፃ ማዉጣት /Habeas Corpus/ ቃሉ የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም "that you have the body" ማለት ሲሆን ወደ አማረኛ ሲተረጎም አካል (ሰዉ) ይዘሃል የሚል ይሆናል፡፡ ሀብየስ ኮርፐስ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ተገድዶ እንዳይዘዋወር የተከለከለ ወይም የታሰረ ሰዉ ከዚህ ክልከላ ወይም እስራት እንዲለቀቅ የሚጠየቅበት ሥነ-ሥርዓት ነዉ፡፡ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ ሰዉ የታሰረዉ የወንጀል ድርጊት ፈጽመሀል በሚል ቢሆንም ሀብየስ ኮርፐስ የፍትሐብሔር ጉዳይ ነዉ፡፡ አካልን ነፃ ማዉጣት /Habeas Corpus/ ፅንሰ ሀሳብ በመጀመሪያ ተገልፆ የነበረዉ እ.ኤ.አ 1215 ለእንግሊዛዉያን ነዋሪዎች ልዩ ልዩ ነፃነቶችና መብቶችን ይዞ ብቅ ካለዉ ትልቅ ሰነድ /Magna Charta/ ማግና ካርታ ነዉ፡፡ መርሁም የንጉሶች ሳይሆን የህግ የበላይነት እንዲኖር ማድረግ ነዉ፡፡ ማንም ሰዉ ከሕግ ዉጪ በማንም ሊያዝ፣ ሊታሰር፣ ሊታገት እና እንቅስቃሴዉም ሊገደብ አይገባዉም የሚሉ ዓለም አቀፋዊ መርሆችን አቅፎ የያዘ ነዉ፡፡ ነፃነት ሊገደብ የሚችለው በህግ ሥርዓት (Due Process of law) ጠያቂና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ ሊሆን ይገባል በማለት የማግና ካርታ የዉስጥ ይዘት ያስረዳል፡፡

የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (International Convention on Civil and
Political Rights)

ሀገራችን ያፀደቀችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን በአንቀጽ 9(1) ማንኛዉም ሰዉ የግል ነፃነቱና ደህንነቱ እንዲረጋገጥለት መብት እንዳለው አመልክቷል፡፡ ማንኛዉም ሰዉ በህግ ከተደነገገዉ ምክንያትና ሥርዓት ዉጭ የግል ነፃነቱ አይነፈግም፡፡ በስምምነቱ አንቀጽ 9(4) መሰረትም ማንኛዉም በመታሰሩ ወይም በመያዙ ምክንያት ነፃነቱን የተነፈገ ሰዉ የእስራቱን ሕጋዊነት ወዲያዉኑ መርምሮ ያለአግባብ መታሰሩን ካረጋገጠ በነፃ እንዲለቀቅ እንዲያዝለት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አለዉ፡፡

የአካል ነፃነት አቤቱታ አቀራረብ እና አወሳሰን ሥነ-ሥርዓት

አካልን ነፃ ማዉጣት ከህግ አግባብ ዉጭ የታሰረ ሰዉ ከዚህ እስር እንዲፈታ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ የፍትሐብሔር ጉዳይ ነዉ፡፡ ነገሩ የሚታየዉ በፍትሐብሔር መዝገብ ቢሆንም በወንጀል ሰበብ የታሰረዉ ሰዉ ይጠቀምበታል፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 177 መሰረት በወንጀል ሕግ ወይም በዚህ ሕግ የተነገረዉን መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤት ሳይወስንበት ወይም ሳይፈርድበት ማናቸዉም ሌላ ትዕዛዝ ሳይሰጥ በማናቸዉም ሌላ ስልጣን ወይም በሌላ ሁኔታ ወይም በሌላ ሰዉ የተገደደ፣ እንዳይዘዋወር የተከለከለ፣ የተያዘ ወይም የታሰረዉ ሲኖር ይህ አድራጎት እንዲወገድለትና እራሱ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ሊያመለክት ይችላል፡፡ የመያዙ ወይም የመታሰሩ ትዕዛዝ የተሰጠዉ በሕግ ባለስልጣን ቢሆንም መያዙ ወይም መታሰሩ የተፈፀመበት ሁኔታ ሕግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ ከሆነ አቤቱታ ማቅረብ ተገቢ ነዉ፡፡ በተገዳጅ የሚቀርበዉ ማመልከቻ በመሀላ-ቃል የተደገፈ ሆኖ የተያዘዉን ወይም የተገደደዉን ሰዉ ስም፣ የአስገዳጁን ሰዉ ስም፣ ተገዶ የተያዘበትን ስፍራ፣ ይህንኑ የሚያረጋግጡ ሰዎች እንዳሉ የምስክሮችን ስምና አድራሻ ዘርዝሮ የሚገለጽ ሊሆን ይገባል፡፡ የተያዘዉ ሰዉ ራሱ መቅረብና የመሀላ-ቃሉን መስጠት የማይችል ከሆነ ሌላ ሰዉ ሊያቀርብለት የሚችል ሲሆን በዚህ ሁኔታ አቤቱታውን የሚያቀርበው ሰው በሚሰጠዉ መሀላ ላይ ዋናዉ ባለጉዳይ ለመቅረብ ወይም ማመልከቻ ለመፃፍ ያልቻለ መሆኑን ጨምሮ ሊገለፅ ይገባል፡፡

በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 15(2)(ቀ) መሰረት የሚቀርበዉን አቤቱታ የመቀበል ስልጣን ሙሉ በሙሉ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነዉ፡፡ በዚህ መሠረት ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ማመልከቻ ሲቀርብለት አስገዳጁ ወይም አሳሪዉ ተገዳጁን ወይም ታሳሪዉን ሰዉ ይዞ እንዲቀርብና ይህንንም ሰዉ የማይለቅበትን ምክንያት እንዲያስረዳ በመጥሪያዉ ላይ የመቅረቢያዉን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ እንዲሁም ለፍርድ ቤቱ በቀረበዉ ማመልከቻ ላይ ነገሩን በምስክርነት ለማስረዳት ይችላሉ ተብለዉ የተጠቀሱት ምስክሮች እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል (የፍ/ /ሥ/ሥ/ህ/ቁ 178)፡፡

በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 179 መሰረት ጉዳዩ በሚሰማበት ቀን በቀረበዉ ማመልከቻ ላይ የተገለፀዉን አቤቱታ እዉነተኛነት ፍርድ ቤቱ ይመረምራል፡፡ ስለማስረጃዉም ተገቢ መስሎ የታየዉን ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ አመልካቹ የተያዘዉ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዳዉ ወዲያዉኑ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ የዚህ ዓይነት ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት ከተሰጠ በኋላ ማናቸዉም ሌላ ትዕዛዝ እንዲኖር ሳያስፈልግ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ብቻ በቂ ሆኖ መፈፀም አለበት፡፡ በሌላ በኩል ማመልከቻዉ ላይ የተገለፀዉ የአቤቱታ ቃል በማናቸዉም ሁኔታ ለፍርድ ቤቱ የሚያጠራጥር መስሎ የታየዉ እንደሆነ አቤት ባዩ ዋስ ጠርቶ እንዲለቀቅ ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ ዋስትና የገንዘብ ማስያዝ ወይም የሰዉ ዋስ ሊሆን ይችላል፡፡ በዋስትናዉም የሚገባዉ ግዴታ እንዲለቀቅ ያደረገዉ ፍርድ ቤት በፈለገዉ ጊዜ እንዲቀርብ ወይም ማንኛዉንም ፍርድ ቤቱ የሚሰጠዉን ትዕዛዝ አክብሮ እንዲፈፅም የሚያስገድድ ይሆናል ፡፡

ማጠቃለያ

አካልን ነፃ ማውጣት (Habeas Corpus) የሰዎች ሰብአዊ ነፃነት በህገወጥ መንገድ እንዳይጣስ ለመከላከል አስፈላጊ የሆነ ሥርዓት ሲሆን በሀገራችንም የህግ ጥበቃ ያለው መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ ከህግ ውጪ የሆነ መያዝ ወይም መታሰር ሲያጋጥመው ይህን ህጋዊ መፍትሄ በመጠቀም መብቱን በማስከበር እና ህገወጥነትን በመካላከል የበኩሉን ሊወጣ ይገባል፡፡


በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties