አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
.......👇👇👇👇👇👇👇
በፍትህ ስርዓቱ ስላጋጠመው አደጋ የመፍትሄ አቅጣጫ እና
ለዳኞች እና አቃቤ ህጎች ፍልሰት  ምክንያቶቹ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች‼️

👆👆👆👆👆👆👆👆👆

እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
🔘 Live on Telegram 👈👈

#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆

የእለቱ እንግዳችን
👇👇👇👇👇👇👇👇
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ.......

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig

Watch "Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
201235.pdf
833.1 KB
በሁከት ይወገድልኝ ክርክር የማይስተናገዱ ጉዳዮች
Abrham Y
ውል እንዲፈርስ ሰ/መ/ቁ 201235
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ላይ ለይዞታው መነሻ የሆነ ሽያጭ ወይም ሌላ ውል እንዲፈርስ የተጠየቀ ዳኝነት በሌለበት ሁኔታ ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፍርድ ሊሰጥ አይገባም።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊቀርብ የሚችለው በይዞታው በእውን በሚያዘው ሰው ሰላማዊ የይዞታ አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል። በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ የሚሰጠው ዳኝነትም የተነሳው ህውከት እንዲወገድ እንዲሁም ስለደረሰ ጉዳት ኪሳራ እንዲከፈል ሊሆን ይችላል። በተለይ ተከሳሽ አድራጎቱን የሚፈቅድ መብት እንዳለው በፍጥነትና በማይታበል ዓይነት ካላስረዳ በቀር ሁከቱ እንዲወገድ እንደሚታዘዝ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3) ሥር ተመልክቷል። በአንፃሩም ሁከቱን ፈጠረ ከተባለው ሰው ጋር የተደረገ በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካለ ግንኙነቱ የሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ ተለይቶ ራሱን ችሎ ዳኝነት ሊሰጥበት ይገባል።
ፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3)፤ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2)
አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አዲስ የስራ ማስታወቂያ በ0 አመት እና በልምድ በተለያዩ የስራ መደቦች
35 Positions
Deadline: Nov 25, 2022
ስለ ህግ ጉዳይ መረጃ እና ማብራሪያዎች ከፈለጉ
ይህንን የዩቱብ ቻናል ሰብስክራብ አድርጉ እንዲደረግ ለሌሎች አጋሩ።
please, Subscribe‼️🙏
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆
"Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
📌New Vacancy Abyssinia bank S.c .
Position 3: Administrative Assistant

Position 4: Foreclosure Officer
Position 5: Surveillance Officer
Position 6: Senior Attorney

📌For More Detail
https://lucyjob.com/job/abyssinia-bank-s-c-6-positions/
#ተከሳሽ_በሌለበት_የወንጀል_ክስን_ማየት
በመርህ ደረጃ ክስ መሠማት ያለበት ተከሳሽ ባለበት ነው፡፡ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱ ደርሶትና ተረድቶት የመሰማት ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንሥግሥት አንቀጽ 2ዐ ደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ግን የወንጀል ክስ ሁሉ ተከሳሽ ፍርድ ቤት ካልቀረበ ታይቶ አይወሰንም ማለት አይደለም፡፡

በሕግ ተለይተው በተመለከቱ ወንጀሎች ላይ ተከሳሽ በሌለበትም ክሱን መርምሮ መወሰን ይቻላል፡፡ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ አራተኛ መድሐፍ አንቀጽ 2 ልዩ ሥነ ሥርዓት በሚለው በምዕራፍ አንድ ቁጥር 160/2/ ሥር ነገሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሽ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት የሚሰጥለት እንደራሴ ካልቀረበ እንዲያዝ ትዕዛዝ ፍ/ቤት እንደሚሰጥ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት መፈፀም ካልተቻለ ተከሳሹ በሌለበት ነገሩን ለመስማት ፍ/ቤቱ እንደሚያስብበት የዚሁ ቁ. 160/3/ ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ መርህ ሁለት ነጥቦችን እናያለን፡፡ ተከሳሽ ሲቀር የመጀመሪያው የፍ/ቤቱ ተግባር እንዲያዝ ማዘዝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሌለበት ጉዳዩን ለማየት ማሰብ ናቸው፡፡

አንድን የወንጀል ክስ ተከሳሽ በሌለበት መስማትና መወሰን የሚቻለው በቁ. 161/2/ መሠረት ከ12 ዓመት በማያንስ ጽኑ እሥራት የሚያሳስር ወንጀል የሠራ ወይም በቀድሞ ወ/መ/ሕግ ቁ. 354-365 በአዲሱ የወንጀል ሕግ ቁ. 343 እስከ 354 ድረስ ያሉ ወንጀሎች ፈጽሞ ጽኑ እሥራት ወይም ከ5ዐዐዐ ብር በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን እና እንዲሁም በውጭ ሀገር ጥገኛ ሆኖ ጥገኛ ያደረገው ሀገር አሳልፎ ያልሰጠው እንደሆነ ነው ቁ. (161/3/) ተከሳሹ በቁ. 160/2/ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት ካልተሰጠና ወንጀሉ በቁ. 161/2/ እና /3/ የተመለከተው ከሆነ ክሱ በሌለበት እንዲሰማ ይታዘዛል፡፡ በቁ. 162 መሠረት ፍ/ቤት በጋዜጣ ማስታወቂያ ተከሳሽ እንዲጠራ የሚያዘው ነገሩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ባይቀርብ በሌለበት ጉዳይ እንዲታይ በታዘዘው መሠረት ቀጥሎ እንደሚታይ ለማስታወቅ ነው፡፡ ከጋዜጣ በተሻለ በሌላ መንገድ መጥሪያው ለተከሳሽ ሊደርስ ይችላል ከተባለም አማራጩ ለፍ/ቤት የተተወ ነው፡፡

በተግባር የሚታየው አሠራር የተለየ ሊመስል ይችላል በቁ. 161 የተመለከቱት ሁኔታዎች በተሟሉበትም ቢሆን ፍ/ቤት የተከሳሽን ጉዳይ በሌለበት ለማየት የሚወሰነው በጋዜጣ ማስታወቂያ ጥሪ ካደረገ በኋላ ነው ምናልባትም ይህ አሠራር የተከሳሹን መብት በተሻለ መንገድ ይጠብቅለታል ከሚል የመነጨ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤቱ ተከሳሹ የቀረው ያለበቂ ምክንያት መሆኑን ካረጋገጠ በጋዜጣ ጥሪ የሚያደርግበት አግባብ የለም፡፡

በዚህ ሁኔታ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ የተፈረደበት ሰው ፍርዱ ውድቅ እንዲደረግለት ፍርዱን ባወቀ በ3ዐ ቀን ውስጥ ለፈረደው ፍ/ቤት ማመልከት ይችላል (ቁ. 164,197,198) ማመልከቻውም ተቀባይነት የሚያገኘው ተከሳሹ ፍ/ቤት ያልቀረበው መጥሪያው ስላልደረሰው ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የቀረ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ምንድነው የሚለውን የመወሰን ኃላፊነት የፍርድ ቤቱ ነው፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት አግኝቶ ፍ/ቤቱ በሌለበት የሰጠውን ውሣኔ ውድቅ ካደረገው ጉዳዩ/ ክሱ እንደገና በሌላ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት እንዲታይ ይታዘዛል ቁ. 202፡፡

በሌለበት የተፈረደበት ፍርድ እንዲነሳለት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ ይግባኝ ማለት የሚችለው በቅጣቱ ላይ ብቻ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
201235.pdf
833.1 KB
በሁከት ይወገድልኝ ክርክር የማይስተናገዱ ጉዳዮች

ውል እንዲፈርስ ሰ/መ/ቁ 201235
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ላይ ለይዞታው መነሻ የሆነ ሽያጭ ወይም ሌላ ውል እንዲፈርስ የተጠየቀ ዳኝነት በሌለበት ሁኔታ ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፍርድ ሊሰጥ አይገባም።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊቀርብ የሚችለው በይዞታው በእውን በሚያዘው ሰው ሰላማዊ የይዞታ አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል። በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ የሚሰጠው ዳኝነትም የተነሳው ህውከት እንዲወገድ እንዲሁም ስለደረሰ ጉዳት ኪሳራ እንዲከፈል ሊሆን ይችላል። በተለይ ተከሳሽ አድራጎቱን የሚፈቅድ መብት እንዳለው በፍጥነትና በማይታበል ዓይነት ካላስረዳ በቀር ሁከቱ እንዲወገድ እንደሚታዘዝ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3) ሥር ተመልክቷል። በአንፃሩም ሁከቱን ፈጠረ ከተባለው ሰው ጋር የተደረገ በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካለ ግንኙነቱ የሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ ተለይቶ ራሱን ችሎ ዳኝነት ሊሰጥበት ይገባል።
ፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3)፤ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2)
By Abrham Yohannes

https://t.me/lawsocieties
የአስተዳደር_ተቋም_ረቂቅ_መመሪያ_ለፍትሕ_ሚኒስቴር_ለአስተያየት_የሚላክበት_እና_የፀደቀ_መመሪያ_የሚመዘገብበት.pdf
283.4 KB
የአስተዳደር ተቋም ረቂቅ መመሪያ ለፍትሕ ሚኒስቴር ለአስተያየት የሚላክበት እና የፀደቀ መመሪያ የሚመዘገብበት የአሠራር ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 911.2014
የሥነምግባር ደንብ መርሆዎች Principles of Ethical Service

1. ቅንነት (Integrity)

2. ታማኝነት (Loyalty)

3. ግልፅነት (Transparency)

4. ሚስጢር ጠባቂነት (Confidentiality)

5. ሀቀኝነት (Honesty)

6. ተጠያቂነት (Accountability)

7. የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም (Serving the public interest)

8. ሥልጣንን በአግባቡ መጠቀም (Exercising legitimate authority)

9. አለማዳላት (Impartiality)

10. ሕግ ማክበር (Respecting the law)

11. ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት (Responsiveness)

12. አርአያ መሆን (Exercising leadership)

https://www.youtube.com/@Lawsocieties
We need you on YouTube. Subscribe now.🙏🙏🙏‼️
https://t.me/lawsocieties
ዳኛ እና አቃቤ ህግ ለአንድ አገር አይን እና ጀሮ ናቸው።
Anonymous Poll
73%
ሀ. እውነት
14%
ለ. ሀሰት
13%
ሐ. ሀ እና ለ
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት እንዲያድግ እና እንደስሙ ፍትህ ሰጪ ተቋም መሆን ካለበት፣
ህግና ደንቦች ይከበሩ
1. ዳኞች ይከበሩ
2. አቃቤ ህጎች ይከበሩ
3. የህግ መምህራን ይከበሩ
4. ጠበቆች ይከበሩ
5. የህግ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ክትትል እና ድጋፍ ያግኙ
6. ጠበቆች፣ ዳኞች፣ አቃቤ ህጎች ያስተምሩ ዘንድ ይፈቀድ።
7. የህግ አስፈጻሚው ጣልቃ ገብነት ይቁም
10. የህግ የበላይነት ይረጋገጥ.....
ጨምሩበት......
#Ale_Hig #አለ_ህግ #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
"ብዙ ሰዎች የሂደቱ አካል መሆን አይፈልጉም። የውጤቱ አካል መሆን ይፈልጋሉ። ነገር ግን ሂደቱ የውጤቱ አካል መሆን የሚገባው ማን እንደሆነ የሚወሰንበት ነው።"
አሌክስ ሞርተን - አስተሳሰብ
በአንድነት ለፍትህ ስርዓቱ እንቁም‼️
ጥቅሙ የጋራ ነው።
https://t.me/lawsocieties
በተናጠል መሄድ አያዋጣም‼️
*በአንድነት ለፍትህ ስርዓቱ እንቁም‼️
ጥቅሙ የጋራ ነው።*

https://t.me/lawsocieties
ከቅድመ ምርመራ ነጻ የመሆን መብት

ማንኛውም ፕሬስ እና ሚዲያ ከቅድሚያ ምርመራ ነጻ የመሆን መብት እና የህዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድል ሊኖረው ይገባል፡፡ ነገር ግን እንደ ነገሩ ሁኔታ የፌደራል ወይም የክልል ዓቃቤ ሕግ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ከሥርጭት በኋላ በማስቀጣት ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና የማይቀር ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በየጊዜው የሚወጣ ሕገ ወጥ ህትመት ወይም የብሮድካስት አገልግሎት ሊሰራጭ መሆኑን ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖረው የህትመት ውጤቱ ወይም የብሮድካስት አገልግሎቱ እንዳይሰራጭ ለፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲያዝ ማመልከት ይቻላል፡፡

ይህ ክልከላ ህጋዊ ወይም አሳማኝ ሊሆን የሚችለው ስርጭቱ ግልጽና የማይቀር ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖር ብቻ እን ደሆነ እና ከዚህ ውጪ የሚደረግ ክልከላ ህገወጥ የሆነና ከህገመንግስቱ አንቀጽ 29 (3) ላይ ከተቀመጠው ከቅድመ ምርመራ ነጻ የመሆን መብት ጋር የሚጋጭ ነው።

👉(የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 29(3) እና የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1238/2013፤ አንቀጽ 85)

Right to be free from Censorship

All press and media should have the right to be free from censorship and have access to information that is in the public interest. However, as the case may be, when the federal or state prosecutor has sufficient reason to believe that an illegal publication or broadcast service is about to be disseminated that will cause irreparable, clear and severe unavoidable damage to national security after publication, it may apply to Federal High Court to get a grant of an order to impound the periodical or an injunction order forbidding transmission of a broadcasting service.

This prohibition can only be legal or plausible when there is sufficient reason to believe that the dissemination will cause clear and imminent grave danger, and any prohibition other than this is illegal and contrary to the right to be free from censorship as set forth in Article 29 (3) of the Constitution.
👉FDRE Constitution Article 29(3) & Media Proclamation No. 1238/2021 Article 85
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ -
ኢሰመጉ
https://t.me/lawsocieties
ስለ ቅድመ ሙስና ባህሪያቶች ሶሺዮሎጂስቶች እንዲህ ይላሉ:
1- ሆቴል ወይም ሬስቶራንት ውስጥ ሆነህ ቤት ውስጥ ከምታደርገው በላይ ስኳር ወተት፣ ሻይ . . . ውስጥ የምታደርግ ከሆነ
2- በቤት ውስጥ ከምታደርገው በላይ ሶፍት፣ ሳሙና ሬስቶራንቱ ውስጥ የምትጠቀም ከሆነ
3- ሰርግ ላይ እቤት ከምትበላው በላይ ምግብ የምትበላ ከሆነ ወይም ሌላ ሰው ሂሳብ ስለሚከፍል ብቻ በጣም የምትጠቀም ከሆነ (የህዝብ ገንዘብ ለመብላት እድሉ ቢኖሩህ እንደምትበላ ይህ ምስክር ነው።)
4- ብዙውን ጊዜ ባለተራዎችን ከፊትህ የተሰለፉትን ከዘለልክ. . . (ስልጣን ላይ ለመውጣት በሌሎች ትከሻ ላይ የመውጣት እድልን ትጠቀማለህ ማለት ነው)
5-የትራፍሪክ መመሪያውችን ከጣስክና ለትራፍሪክ መብራቱ ምንም ግምት ከሌለህ
(ንጹሃን ቢወድቁ እንኳን ለበደላቸው ምንም ቦታ የለህም ማለት ነው)
ስለዚህ ሙስናን መታገል ከራስ ይጀምራልና ታማኝ ሁን። ታማኝነት በአንተና በራስህ መካከል የምታደርገው እንጂ በሰዎች ዘንድ የምታደርገው ብቻ አይደለም።
ከ facebook መንደር
https://t.me/lawsocieties
ለእጩ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ መደብ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በ2013 እና 2014 የትምህርት ዘመን ከከፍተኛ የትምሀርት ተቋማት በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቁ ተወዳዳሪዎችን በመጋበዝ በእጩ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ መደብ የቅድመ ስራ ስልጠና በመስጠት አወዳድሮ ለመቅጠር መስከረም 06 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት በተወዳዳሪነት የተመዘገባችሁ እና በማስታወቂያው የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች (ለፈተና የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ከሚፈተኑበት አዳራሽ አድራሻ ጋር ከዚህ ማስታወቂያ ስር ተያይዟል) የመጀመሪያ ዙር የፅሁፍ ፈተና ኅዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የፍትሕ ሚኒስቴር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የመሚሰጥ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በሰአቱ ቦታው እንድትገኙ እያሳውቅን ወደ ፈተና አዳራሹ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ፣ ማጣቀሻም ሆነ ሕግጋትን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡