አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Position 83: Legal Officer
Qualification: LLB degree in Law or related fields.
Experience: 4(four) years of relevant work
Location: Head Office.

Deadline: Nov 05, 2022
The compensation will be as per the Bank’s salary scale and Benefit package.
How to Apply:
Interested potential applicants who only fulfill the minimum requirements invited to apply online via email address of the bank tsedeybankhr@gmail.com their scanned application along with credential documents (educational qualification & work experience) and CV within 5 days from the date of this announcement.
Only short-listed applicants will be communicated
Applicants should apply only for one position
CV should not be more than 3 pages.
For all positions the location will be Addis Ababa and Hawassa.
For further information contact: 0582263541/058220165
For more
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://etcareers.com/job/27780/tsedey-bank-vacancy-2022-multiple-banking-vacancies/?utm_source=job-alert&utm_medium=email&utm_campaign=job-alert&alert_id=
👍4
የእውነተኛው ዳኛና የሁለቱ እውነተኞች ጐረቤቶች ታሪክ

Ale Hig አለ ህግ Law Societies


አንድ ሀብታምና አንድ ድኃ ሁለት ጎረቤቶች ነበሩ ። ከዕለታት አንድቀን ድኃው ትንሽ ገንዘብ አጠራቅሞ ለሀብታም ጐረቤቱ እባክህ ወንደሜ ትንሽ ገንዘብ አጠራቅሜአለሁና በእርዳታህ ጭምር ባጠራቀምኩት ገንዘብ ኩርማን መሬት እንድትሽጥልኝ እለምንህአለሁ አለው።

ሀብታሙ ጉረቤትም ደስ ደስ እያለው እሺ እኔም እሸጥልህአለሁ አለው ድኃውም ያለውን ገንዘብ ቆጥሮ ሰጠው። ሀብታሙ ሰውየም ኩርማን መሬት ሸጬልሃአለሁ ገንዘቡም ደርሶኛል ብሎ ኵርማን መሪቱን ለመሸጡ ፊርማው ሰጠው።

ድኃው ሰውየም እንግዲህ መሬት ከገዛሁ መሬቱን ቆፍሬ እልምቼ ያልፍልኛል ብሎ መሬቱን ይቆፍር ጀመር። መሬቱንም ሲቆፍር ካንድ ትልቅ ድንጋይ ሥር ወርቅ የሞላ እንስራ አገኘ መቸም የሰው ገንዘብ የማይፈልግ ሰው ይደነግጣል እንጂ ገንዘብ አገኘሁ ብሎ ደስ አይለውምና ስለዚህ ሰውየው ለጊዜው ደነግጠና ቆይቶ ይህ ገንዘብ መሬቱን የሸጠልኝ ጐረቤቴ ነው የሚሆን ብሎ ሒዶ ወንድሜ ይኸውና ከዚያ ከሸጥህልኝ ቦታ ወርቅ የሞላ እንስራ አግኝቼአለሁ ይኸውም ያንተ ሳይሆን አይቀርምና ውሰደው አለው ።

መሬት የሸጠለት መልካሙ ጐረቤትም እኔ ወርቅ ቢገኝበት ብርም ቢገኝበት እንግዲህ ወዲህ ደንብም አይሰጠኝ እኔም አልፈልግ ያንተ ነውና ዝም ብለህ ለራስህ ውስደው አለው። ወርቁን ያገኘው ሰውም እኔ ቀማኛ አይደለሁ እንዴት የሰው ገንዘብ ቀምቼ እወስዳለሁ አልቀበልም ያልኸኝ እንደሆነ ና በመንግሥት ወደ ዳኛ እንሒድ አለው። እሱም ዳኛ የሚፈርደውን እሰማለሁ እንጂ አለና አልቀበልህም ብሎት ተያይዘው ወደ ዳኛ ሔዱ። ከሳሹ ወርቅ ያገኘው ነውና በላይኛው መስመር እንደተጻፈ ነገሩን አስተካክሎ ለዳኛው አሰማው። ዳኛውም ተከሳሹን እንተስ ምን ትመልሳለህ አለው። ተከሳሹም መሬቴን ብሸጥለት ከሸጥህልኝ መሬት ወርቅ አግቼአለሁና ና ውሰድ ያንተ ነው ቢለኝ የዳኛውን ፍርድ እሰማለሁ እንጂ አይገባኝምና አልወስድም ብዬ ፍርድዎን ለመቀበል ወደርስዎ መምጣቴ እርግጥ ነው አለ።

ዳኛው ግን የሁለቱን ሐሳብ ከተረዳ በኋላ እኔ ላስታርቃችሁ አላቸው። እነሱም እሺ መንግሥትስ ለዚህ አይደለም የሾምዎ እኛም ዕርቅዎን እንሰማለን መንግሥት ይሙት አሉ። ከዚህ በኋላ ዳኛው ከሳሹን ወንድ ልጅ አለህን ቢለው አዎን አለኝ አለ። ተከሳሹንም እንተሳ ሴት ልጅ ኣለችህን ቢለው አዎን አለችኝ አለ። በሉ እንግዲህ ሁለቱን አጋቡዋቸውና ወርቁን ለነሱ ስጡዋቸው ብሎ አስታረቃቸውና ዕርቁን ተቀብለው ልጆቻቸውን አጋብተው ወርቁን እንደ እርቃቸው ለልጆቻቸው ሰጡዋቸው።በነዚህ በሦስቱ ሰዎችም እውነተኛነት የሰሙት ሁሉ ተደነቁ ይባላል።

ክቡራን ዳኞችና ጐረቤቶች ሆይ እነዚህ ሦስት ሰዎች የመዘምራን አለቃና የእግዚአብሔር ባርያ ዳዊት በ፲፭ ምዕ ከ፪ ቁጥር ጀምሮ እስከ መጨረሻው ባለው የተናገረውን ቃል እንዲፈጽሙ ነው እንደዚህ ያደረጉ። ስለዚህ ጉረቤቶች ሁነው እርስ በርሳቸው እንደነዚሁ ሳይፋቀሩ አገራችን ኢትትዮጵያን እንወዳትአለን ቢሉ ዳኞችዎ ሁነው እንደዚሁ ዳኛ ፍርዳቸውን ሳያስተካከሉ መንግሥታችንን እንረዳለን ቢሉ ኢሳይያስ “ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡን ከኔ በጣም የራቀነው ያለው” መድኃኒታችንም በወንጌሉ “አንተ ባልንጀራህን የማታውቅ ከሰማይ የሚኖር እግዚአብሔርን ግን አውቀዋለሁ የምትል ዋሾ ነህ” ያለው በነሱ ይፈጸማል።

ክቡራን የብርሃንና ሰላም አንባቢዎች ሆይ ይኸን ሁሉ ያሳሰበኝ የኢትዮጵያ ተወላጅ ሁሉ ስለአገሩና ስለመንግሥቱ ስለ ባልንጀራውም በፍቅር ሰንሰለት እንዲተሣሠር ብዬ ነውና ጉድለቴን አርማችሁ እንድታነቡልኝ እለምናችኋለሁ።
ተስፉ ደርሶ።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ምንጭ፤ ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ፥
ጥር 25፥ 1925 ዓ/ም እትም
የእውነተኛው-ዳኛና-የሁለቱ-እውነተኞች-ጐረቤቶች-ታሪክ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍17😁1
https://www.youtube.com/@Lawsocieties

#አለ_ህግ የእናንተን ድጋፍ የሚፈልግበት ጊዜ አሁን ነው።
የአለ ህግን ዩቲዩብ  ቻናል ሰብስክራብ (Subscribe) በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩን። 🙏👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/@Lawsocieties

#Ale_Hig #አለ_ህግ @Lawsocieties

Subscribe our youtube.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties

#አለ_ህግ የእናንተን ድጋፍ የሚፈልግበት ጊዜ አሁን ነው።
የአለ ህግን ዩቲዩብ  ቻናል ሰብስክራብ (Subscribe) በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩን። 🙏👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/@Lawsocieties

#Ale_Hig #አለ_ህግ @Lawsocieties

Subscribe our youtube.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/@Lawsocieties
👍2👏2
👏8
በፌዴራል ደረጃ ተመዝገበው በስራ ልይ የሚገኙ መመሪያዎችን በአንድ ማዕቀፍ ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ በአስተዳደር ሥነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝገበው፤ ቁጥር ተሰጥቷቸው ተፈጻሚ የሆኑ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላት መመሪያዎችን ለማግኘት ከዚህ በታች የሰፈረውን ሊንክ ይጫኑ፡፡ በቀጥታ ወደ መመሪያዎቹ ይወስዳችኋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ የተመዘገቡ መመሪያዎች 1007 የደረሱ ሲሆን መመሪያዎቹ የፌዴራል አስፈጻሚ ተቋማት ያወጧቸው ሲሆኑ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን መመሪያዎች ይጨምራል፡፡

መመሪያዎቹን በተቋማት መጠሪያ መሰረት በተዘጋጀ ማዕቀፍ መሰረት ወይም All Federal Directives የሚለውን ሁሉን መመሪያዎች በተራ ቁጥር ቅደም ተከተል የያዘውን ማዕቀፍ በመክፈት ፈልገው ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ህግን በማወቅ መብቱን የሚጠይቅ ግዴታውን፤ የሚወጣ ዜጋ እንሁን!

ይህንን ጠቃሚ መረጃ ለሌሎች በማጋራት (Share በማድረግ) ታግዙን ዘንድ በማክበር እንጠይቃለን

http://legal.eag.gov.et:8080/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
👍5🥰1
#Peace _agreement_of_TPLF
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Joint Statement between the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the Tigray Peoples’ Liberation Front (TPLF)

1. As per Article 3 of the Agreement for Lasting Peace and Permanent Cessation of Hostilities, the Representatives of the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the TPLF have agreed to announce to the people of Ethiopia and the rest of the world that after 10 days of intensive negotiations have concluded a peace agreement.
👇👇👇👇👇 to be continued
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Peace _agreement_of_TPLF

2. We have agreed to permanently silence the guns and end the two years of conflict in northern Ethiopia.

3. The conflict has brought a tragic degree of loss of lives and livelihoods and it is in the interest of the entire people of Ethiopia to leave this chapter of conflict behind and live in peace and harmony.

4. It is fundamental that we reaffirmed our commitment to safeguarding the sovereignty and territorial integrity of Ethiopia and to upholding the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia. Thus, Ethiopia has only one national defense force. We have also agreed on a detailed program of disarmament, demobilization, and reintegration for the TPLF combatants, taking into account the security situation on the ground.

5. We have agreed that the Government of Ethiopia will further enhance its collaboration with humanitarian agencies to continue expediting aid to all those in need of assistance.

6. We have agreed to implement transitional measures that include the restoration of Constitutional order in the Tigray region, a framework for the settlement of political differences, and a Transitional Justice Policy framework to ensure accountability, truth, reconciliation, and healing.

7. To start implementing these undertakings without delay, we have agreed to stop all forms of conflicts, and hostile propaganda. We will only make statements that support the expeditious implementation of the Agreement. We urge Ethiopians in the country and abroad, to support this Agreement, stop voices of division and hate, and mobilize their resources for economic recovery and rehabilitation of social bonds.

8. The Government of Ethiopia will continue the efforts to restore public services and rebuild the infrastructures of all communities affected by the conflict. Students must go to school, farmers, and pastoralists to their fields, and public servants to their offices. The Agreement requires the support of the public for its smooth implementation. This is a new and hopeful chapter in the history of the country.

9. We express our gratitude to all actors contributing to the success of this endeavor. In particular, the African Union Commission Chairperson, the African High-Level Panel led by His Excellency former President Olusegun Obasanjo, supported by His Excellency former President Uhuru Kenyatta, and Her Excellency Dr. Phumuzile Mlalmbo, former Deputy President of the Republic of South Africa. We thank the Chairperson of the African Union Commission, His Excellency Mr. Moussa Faki Mahamat, Commissioner Bankole Adeoye and his colleagues for their tireless work during these talks. We rely on their continued support as we implement the Agreement.

10. We thank His Excellency President Cyril Ramaphosa, the President of the Republic of South Africa, and Her Excellency Dr. Naledi Pandor, the Minister for the Department of International Relations and Cooperation of South Africa for the excellent facilities they put at the disposal of these talks and their words of encouragement to the parties towards these successful results. We are indebted for the hospitality accorded to us by the People and Government of the Republic of South Africa.

11. We are grateful to the people of Ethiopia for encouraging these talks and patiently waiting for the outcome. We are confident that they will embrace the results of these talks and ensure their timely implementation.

12. Finally, we are confident that friends of Ethiopia and members of the diplomatic community will lend their support in rebuilding infrastructures in affected communities and the economic recovery of the country. We call on all types of media outlets to support peace, reconciliation, unity, and prosperity in Ethiopia.
Jointly Delivered at Pretoria, the Republic of South Africa, on 2nd November 2022.
👍8🥰2😁2
👍2
።።።።።። ቀለብ የመስጠት ግዴታ ።።።።
የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር ኑሮውን ለመግፋት በርካታ ነገሮች የሚያስፈልጉት እንደመሆኑ ሁሉም እንደአቅሙ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሰማራት የራሱን እና የቤተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ገቢ ለማግኘት ጥረት ማድረጉ የተለመደ ነው፡፡ ሆኖም ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች መሥራት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚያስችል ገቢ ማመንጨት የማይችሉበት ሁኔታ መኖሩ የነባራዊው አለም እውነታ ነው፡፡ በዚህ መልኩ መስራትና የእራሳቸውን ገቢ በማንጨት ኑሯቸውን መግፋት የማይችሉ ሰዎች ፈታኝ ሁኔታ እንደሚገጥማቸው ታሳቢ በማድረግ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቀለብ የመስጠት ግዴታን እንደመፍትሄ አካቷል። በዚህ አጭር ጽሁፍ የቀለብን ምንነት፣ ቀለብ የማግኘት መብትን እና የመስጠት ግዴታን ከተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንፃር በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

።።።።።።።።።። የቀለብ ምንነት ።።።።።።

በዘልማድ ባለው የቃል አጠቃቀም “ቀለብ” የሚለው ቃል በአብዛኛው ከምግብ ጋር በተገናኘ ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ ሆኖም የቤተሰብ ህጉ ቀለብን የደነገገበት እሳቤ ከዚህ ሰፋ ያለ ነው፡፡ የቤተሰብ ህጉ ስለ ቀለብ ሲደነግግ የቀለብ ተቀባዩን ሁኔታና የአካባቢውን ልማድ መሰረት በማድረግ ለምግብ፣ ለመኖሪያ፣ ለልብስ፣ ለጤና መጠበቂያ እና እንደሁኔታው ለትምህርት የሚያስፈልገውን እንደሚያካትት ከአንቀፅ 197 ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ቀለብ የሚለው ቃል ምግብን ብቻ በመግለፅ የተወሰነ ሳይሆን እንደቀለብ ተቀባዩ ሁኔታ መሰረታዊ ፍላጎትን ያካተተ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ቀለብ የመስጠት ግዴታ በዋናነት የሚፈጸመው የቀለቡን ገንዘብ ለተቀባዩ በመስጠት ሲሆን መጠኑም ቀለብ ተቀባዩ ያለበትን ችግር እና የቀለብ ሰጪውን አቅም በማገናዘብ የሚወሰን ይሆናል፡፡

።።።።። ቀለብ የሚጠየቅበት ሁኔታ።።።።

ቀለብ አንድ ሰው ስለፈለገ ብቻ የሚጠይቀው አይደለም፡፡ ይልቁንም ቀለብ የመስጠት ግዴታ የሚኖረው ቀለብ ተቀባዩ ሰርቶ ለኑሮ አስፈላጊ የሆነ ገቢ ለማግኘት አቅም የሌለውና በችግር ላይ የወደቀ ሲሆን ብቻ እንደሆነ የተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 201 ደንግጓል፡፡

።።።። ቀለብ የመስጠት ግዴታ።።።።።።

ቀለብ የመስጠት ግዴታ በቀጥታ በወላጆችና በተወላጆች እንዲሁም በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ሲሆን በእህትና ወንድማማቾች መካከልም ቀለብ የመስጠት ግዴታ እንዳለ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 198 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ቀጥታ የጋብቻ ዝምድና የሚባለው ባል ከሚስቱ ወላጆችና ተወላጆች ወይም ሚስት ከባሏ ወላጆችና ተወላጆች ጋር ያላቸውን የጋብቻ ዝምድና ሲሆን ጋብቻው ከሞት ውጪ በሆነ ምክንያት ሲፈርስ ግን ይህ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ቀሪ ይሆናል፡፡ እነዚህ ዘመዶች ሁሉም በአንድ ጊዜ ለቀለብ ተቀባዩ ቀለብ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡ ይልቁንም ቀለብ የመስጠት ግዴታው በህጉ አንቀፅ 210 ሥር በተቀመጠው ቅድም ተከተል የሚፈፀም ነው፡፡ በዚህ መሰረት

1ኛ የቀለብ ተቀባዩ ባል ወይም ሚስት
2ኛ የቀለብ ተቀባዩ ተወላጆች እንደየደረጃቸው
3ኛ የቀለብ ተቀባዩ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደራጃቸው
4ኛ የቀለብ ተቀባዩ ወንድሞችና እህቶች
5ኛ የቀለብ ተቀባዩ የጋብቻ ተወላጆች እንደየደረጃቸው
6ኛ የቀለብ ተቀባዩ የጋብቻ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደረጃቸው

ባለው ቅደም ተከተል የሚፈፀም ይሆናል፡፡ በህጉ በተደነገገው ቅደም ተከተልም ቢሆን ቀለብ ሰጪዎች ቁጥራቸው ከአንድ በላይ ሊሆን የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ቀለብ ተቀባዩ አንዱን በመምረጥ ቀለብ ሊጠይቅ የሚችል ሲሆን የጋራ ቀለብ ሰጪዎችም መካከላቸው አንዱ ለቀለብ ተቀባዩ ቀለብ እንዲሰጥ የጋራ ስምምነት ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ ቀለብ ተቀባዩም ይህንን ስምምነት ከተቀበለ ከባድ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ከቀሪዎቹ ቀለብ ሰጪዎች መጠየቅ እንደማይችል በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 211 ተደንግጓል፡፡ በሌላ በኩል ከብዙ ቀለብ ሰጪዎች መካከል አንደኛው ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቀለብ ሲሰጡ የነበረ ከሆነ ሳይከፍሉ የቀሩት ድርሻቸውን እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

ከጉዲፈቻ ጋር በተያያዘ ጉዲፈቻ አድራጊ ቤተዘመዶች ቀለብ ለመስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ካልሆኑ በስተቀር ጉዲፈቻ የተደረገ ልጅ፣ የጉዲፈቻ ተደራጊው ልጅ ባል ወይም ሚስት እንዲሁም የቀጥታ መስመር ተወላጆች ከጉዲፈቻ ተደራጊውን ልጅ የስር ወይም የቀደምት ወላጆች ቤተዘመዶች ቀለብ መጠየቅ የማይችሉ ሲሆን በተመሳሳይ የቀደምት ቤተሰቦች ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ከዘመዶቻቸው ቀለብ ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ጉዲፈቻ የሰጡትን ልጅ ቀለብ ሊጠይቁ አይችሉም፡፡

ሌላው ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ስጦታ ተቀባይ ሲሆን ስጦታ ሰጪው ሰርቶ ለማግኘት አቅም ሲያጣና ፍጹም ድህነት ላይ ሲወድቅ ስጦታ ተቀባይ ቀለብ የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት የፍትሐብሔር ህግ ስለ ስጦታ በሚደነግግበት ክፍል በቁጥር 2458 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የስጦታ ውሉ ላይ እንኳን ቀለብ የመስጠት ግዴታ ስምምነት ባይኖርም ይህ ግዴታ ቀሪ ሊሆን አይችልም፡፡ ስጦታ ሰጪ ቀለብ የመቀበል መብቱን ከሌሎች ግዴታ ካለባቸው ሰዎች መውሰድ የሚችል ሲሆን ይህ በሆነ ጊዜ ቀለቡን የሰጠው ሰው የሰጠውን ቀለብ ከስጦታ ተቀባዩ ሊቀበል እንደሚችል የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2458(3) ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

።።።።። የቀለብ ገንዘብ ሊተላለፍና ሊያዝ የማይችል ስለመሆኑ ።።።።።።

በመርህ ደረጃ ለቀለብ የሚከፈል ገንዘብ ሊተላለፍ ወይም በምንም ሁኔታ ሊያዝ አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ ቀለብ ተቀባዩ ላለበት ችግር አሳቢ ለሚሆኑ ለእርዳታ ለተቋቋሙ ድርጅቶች እንዲሁም ለቀለብ ተቀባዩ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ላበደሩ ሰዎች የቀለብ ገንዘቡ ሊተላለፍ እንደሚችል የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 205 ያሳያል፡፡ ሌላው ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊገነዘበው የሚገባው የቀለብ ገንዘብ የማይጠራቀም መሆኑን ነው፡፡ በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 206 መሰረት ቀለብ ተቀባዩ ለኑሮ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ካላቀረበ በስተቀር ቀለቡን መቀበል ካለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሶስት ወራት ውስጥ ቀለቡን ያልተቀበለ ወይም ያልጠየቀ እንደሆነ የተጠራቀመውን ቀለብ መጠየቅ አይችልም፡፡

።።።። ቀለብ ተቀባይ መብቱን የሚያጣበት ሁኔታ።።።።።

በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 200 መሰረት ቀለብ ተቀባይ የሆነ ሰው በቀለብ ሰጪው ላይ ወይም በቀለብ ሰጪው ወደላይ እና ወደታች በሚቆጠሩ ወላጆች ወይም ተወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት ህይወት ወይም ንብረት ላይ የወንጀል ተግባር የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ እንደሆነ ቀለብ የማግኘት መብቱን የሚያጣ ይሆናል፡፡

።።።።። ቀለብ የመስጠት ግዴታን አለመወጣት የሚያስከትለው ተጠያቂነት።።።።።

ከላይ እንደተገለፀው ቀለብ የመስጠት ግዴት ከህግ የመነጨ ሲሆን ባለመብቱና ግዴታ ያለበት ወገን የቀለብ አሰጣጡን በተመለከተ በመስማማት ውል ሊፈጽሙ እንደሚችሉ በህጉ ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ከቀለብ አሰጣጥም ሆነ አቀባበል ጋር በተያያዘ በቤተሰብ ህጉ ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች በሚቃረን መልኩ ስምምነት ሊደረግ እንደማይችል በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 214 ላይ የተደነገገ እንደመሆኑ ይህን የሚቃረን ስምምነት ቢደረግም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
👍4
በሌላ በኩል በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀፅ 658 መሰረት ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው ያለ በቂ ምክንያት በህግ መሰረት ሊሰጥ የሚገባውን ቀለብ፡-

• ለባለመብቶቹ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ
• የፍቺ ውሳኔ እስከሚሰጥ ጊዜ ድረስ የፍቺ ጥያቄ ላቀረበ የትዳር ጓደኛ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ
• በህግ መሰረት ወይም በውል በገባው ግዴታ መሰረት ከጋብቻ ውጭ ላስረገዛት ሴት ወይም ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አብሮት ለኖረ ሰው ወይም ከጋብቻ ውጭ ለተወለደው ልጅ ሊያሟላ የሚገባውን የገንዘብ ግዴታ ያልተወጣ ከሆነ

የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን የግል አቤቱ ሲቀርብ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል፡፡

ማጠቃለያ

ቀለብ ሰርቶ ፍላጎቱን ለማሟላት የሚያስፈልገውን ገቢ ማግኘት የማይችል ሰው ከሥጋ ወይም ከቀጥታ የጋብቻ ዘመዶቹ መሰረታዊ ፍላጎቱ እንዲሟሉለት በህግ የተጣለ ግዴታ ሲሆን ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው ግዴታውን በአግባቡ የመወጣት የህግም የሞራልም ግዴታ እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍4
አከራካሪ_የወንጀል_ሕግ_ድንጋጌዎች_ማብራሪያ_.pdf
1.1 MB
በወንጀል ጉዳዮች የአተረጓጎም ልዩነት ያለባቸው ድንጋጌዎች ላይ ወጥነት ያለው ትርጉም ለማምጣት እንዲቻል የተዘጋጀ የሕግ ማብራሪያ

አዘጋጅ፡- ፍትሕ ሚኒስቴር
👍2