አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን

ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባቀረጥና ታክስ የሚታሰበው የተሸከርካሪዉን ሲሲ መሰረት በማድረግ  CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡ ተሽከርካሪው ያገለገለ ከሆነ ከተመረተበት አንድ ዓመት ጊዜ ጀምሮ ከFOB ዋጋዉ ላይ በየዓመቱ 10% በመቀነስ በጠቅላላዉ እስከ 3 አመት ወይም 30% ድረስ የእርጅና ቅናሽ ካለዉ በማስላት የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ በማባዛት ቀረጥና ታክሱን ማወቅ ይቻላል፡፡

የተሽከርካሪው የፈረስ ጉልበት ማለትም ሲሲው 1300 ከሆነ 125%ሲሆን 1301ሲሲ እስከ 2500 ሲሲ ደግሞ ከ176.24% እስከ 244.55% ባሉትየጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ ይሰላል፡፡ለሰው ማጓጓዣ የሚያገለግሉ ሌሎች ተሸከርካሪዎች ሲሆን ደግሞ በሌላ ስፍራ ያልተጠቀሰ ከሆነ የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ 125.00075% ሲሆን ሹፌሩን ጨምሮ አስር ወይም ከዛ በላይ ሰዎችን ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሸከርካሪዎች ከ15 ተጓዦች ያነሰ መቀመጫ ያላቸው ተሸከርካሪዎች 58.25% እንዲሁም 15 እና ከዚያ በላይ ሰው የሚይዝ መቀመጫ ያላቸው የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔው 29.50% ነው፡፡

የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ የተሸከርካሪ ቀረጥና ታክስ ለመወሰን አምስት የሰሌት ደረጃዎችን(ማለትም የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ) እንከተላለን፡፡ የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ በምሳሌ እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ሲገባ:-

በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35% =24,500 ይሆናል፡፡

ቀጥሎ ኤክሳይስ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) 30%=28,350 ይሆናል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350) 15% = 18,427.5 ብር ይሆናል፡፡

በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350 +18,427.5)10%= 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡

በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70,000 X 3%= 2,100 ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት

24,500 + 28,350 + 18,427.5 + 14,127.75 + 2,100= 87,505.25 ብር ይሆናል፡፡                                                          #ጉምሩክ ኮሚሽን
መንግሥት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሥራ ግብር ቅናሽ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ኢሠማኮ መንግሥት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሥራ ግብር ቅናሽ እንዲያደርግ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤትና ለገንዘብ ሚንስቴር ጥያቄ ማቅረቡን ሪፖርተር አስነብቧል። ጥያቄው ለመንግሥት የቀረበው ሠራተኞች ያለባቸውን ከባድ የኑሮ ውድነት ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ የገለጡት የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ፣ ከሠራተኛ ደመወዝ ላይ የሥራ ግብር ምጣኔ መቀነስ በሌሎች አገራት የተለመደ አሠራር መሆኑን ጠቅሰዋል። ግብር የተጣለበት ዝቅተኛው ወርሃዊ የሠራተኛ ደመወዝ 600 ብር መሆኑ ቀርቶ ከፍ ባለ ደመወዝ ላይ እንዲሆን እና ከ10 ሺህ 900 ብር ወርሃዊ ደመወዝ ላይ የሚጣለው 35 በመቶ የግብር ምጣኔም እንዲቀንስ ኢሠመኮ ጠይቋል።
#Black future consultance SC#

▪️🚩Required No - 35
▪️1 - Health officer
▪️2 - Law Expert 👈👈👈👈👈
▪️3 - Nurse
▪️4 - Sales Expert
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3UERkzK

▪️Deadline: September 30/2022
በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት የተከሰሰው ኬንያዊ ጠበቃ ሞቶ ተገኘ

በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በምስክሮች ጣልቃ ገብነት ክስ ቀርቦበት የነበረው ኬንያዊው ጠበቃ ፖል ጊቼሩ ሞቶ ተገኘ።

ፖሊስ እንዳስታወቀው ጠበቃው ፖል ጊቼሩ ሰኞ ምሽት በመዲናዋ ናይሮቢ በሚገኘው ቤቱ ሞቶ መገኘቱን አረጋግጧል።

ጠበቃው በአውሮፓውያኑ 2007 ምርጫ ማግስት ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለምስክሮች ጉቦ በመስጠት ነው ክስ የቀረበበት።

ምስክሮቹ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአይሲሲ ተከሰው በነበረበት ወቅት ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች እንደነበሩም ተገልጿል።

በዚህ ሁከት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።ጠበቃው የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል።

ጠበቃው የአይሲሲ የእስር ማዘዣ ካወጣበት ከአምስት ዓመት በኋላም በአውሮፓውያኑ 2020 ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል።

አቃብያነ ህግ እንደሚሉት ጠበቃው ፈጸመው በተባለው ተግባር ምክንያት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፍርድ ቤቱ የቀረቡባባቸውን ክሶች ውሃ እንዳይቋጥር አድርጎታል ብለዋል።

https://t.me/lawsocieties

Via BBC Amharic
Vacancy Announcement.png
77 KB
የሥራ ማስታወቂያ
ድርጅት፡- ብላክ ፊውቸር አ.ማ
የሥራ መደብ፡- የሕግ ባለሙያ
ተፈላጊ የሥራ ልምድ፡- ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት
ብዛት፡- በድምሩ 10
የሥራ ቦታ፡- አዲስ አበባ
የምዝገባ ጊዜ፡- እስከ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም
የጤና ባለሙያ ነኝ
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አለኝ
ነገር ግን ሰርተፊኬቱን ከኔ እውቅና እና ፍቃድ ውጪ አንድ ድርጅት የኔን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፍኬት ተጠቅሞ ፍቃድ አውጥቶበት እየሰራበት መሆኑን ደረስኩበት
ድርጅቱ ምን ሲሰራበት እንደነበር አላወቅኩም
ከማንም ጋርም ውል የለኝም
ምን ማድረግ እችላለው?

እኔ የድርጅቱ ሰራተኛ ሳልሆን, ምንም አይነት ውል ሳልዋዋል ሰራተኛቸው እንደሆንኩ አድርጎ ነው እየተተቀመበት ያለው

ድርጅቱ በወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎስ ከነበር የኔ ተጠያቂነት ምን ድረስ ነው?
አቶ_አህመድ_አብዱራህማን_ከ_ኢልይስ_ዲተርጀንት_ኢንዱስትሪ_ኩባንያ_የሰ_መ_ቁ_193292.pdf
805.2 KB
ሰበር ችሎቱ የውጭ ሃገር ሰዎች (ኩባንያ) የንግድ ምልክት ጥበቃ ላይ የህግ ትርጉም ሰጠ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎ በአመልካች አቶ አህመድ አብዱራህማን እና በተጠሪ ኢልይስ ዲተርጀንት ኢንዱስትሪ ኩባንያ መካከል በሰ/መ/ቁ/ 193292 የንግድ ምልክትን አስመልቶ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Vacancy Announcement.png
491.2 KB
Job openings at Selale University

Position 1: Lecturer of Laws
Number: 2


Position 2: Assistant Professor of Laws or Human Rights, or above
Number: 2

Deadline: September 25, 2015 E.C
ሐሰተኛ የሕክምና ምስክር ወረቀት መስጠት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሐሰተኛ የሕክምና ምስክር ወረቀት መስጠት በወንጀል የሚያስቀጣ ድርጊት ነው ፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሐኪም ፡ የጥርስ ሐኪም ፡ የመድሀኒት ቅመማ ባለሙያ/ፋርማሲስት/ ፡ የእንስሳት ሐኪም ፡ አዋላጅ ወይም በሕክምና ሙያው ምስክር ወረቀት ለመስጠት ፍቃድ ያለው ማንኛውም ሰው የምስክር ወረቀቱ ስራ ላይ እንደሚውል እያወቀ ፡ ለተቀባዩ ሰው የማይገባ ጥቅም ለማስገኘት ወይም የሌላውን ሰው ሕጋዊ ጥቅም የሚጎዳ ሐሰተኛ የሕክምና ምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ የሰጠ እንደሆነ በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል ፡፡

ወንጀሉ በተደጋጋዊ ጊዜ የተፈፀመ ከሆነ ደግሞ ፡ የሐኪሙ የሙያ ፍቃድ ሊሻር ይችላል ፡፡ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 387 እና 123 (ሐ)
ሐሰተኛ የሕክምና ምስክር ወረቀት መስጠቱ የተከናወነው በስጦታ ፤ በስጦታ ተስፋ ወይም በሌላ ጥቅም እንደሆነ ፤ ቅጣቱ ከአስር አመት የማይበልጥ ፅኑ እስራትና ከ 50 (ሀምሳ) ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል ፡፡ በተጨማሪም ሐሰተኛውን የሕክምና ምስክር ወረቀት ያዘጋጀው የመንግስት ሠራተኛ ሆኖ ወንጀሉን የፈፀመው በዚሁ ስልጣኑ እንደሆነ የወንጀል ቅጣቱ እስከ አስራ ኣምስት አመት ሊደርስ ይችላል ፡፡ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 387 (3)

ማንም ሰው በሀሰት የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት መሆኑን እያወቀ ሌላውን ሰው ለማታለል የተገለገለበት ከሆነ ደግሞ ፤ በቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ማለት ነው ፡፡
የወንጀል ሕግ አንቀፅ 387 (4)
በሳሙኤል ግርማ
https://t.me/lawsocieties
የሰብዓዊ_መብቶች_ዓለም_አቀፍ_ቃል_ኪዳኖች_በአማርኛ፣_2001_ዓ_ም.pdf
621.5 KB
International Covenant on Civil and Political Rights (የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች) በ2001 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (በቀድሞ አጠራር የአትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን) በአማርኛ የተዘጋጀ
Legal Advisor
Reach Ethiopia
Addis Ababa Educational Requirements: Qualification Licensed and proven experience as a Legal Advisor in business environment; Demonstrated ability to create legal response with defensive or proactive strategies; High degree of professional ethics and integrity; Sound judgement and ability to analyze situations and information; LLM from accredited Law school; Minimum of 5 years of practical experience in providing consultancy services in the legal area for business...

Required Experience:
Not Provided https://www.greatethiopiajobs.com/jobs/job-detail/job-Legal-Advisor-job-at-Reach-Ethiopia-64134?utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic
ልጓም ያጣው የመኪና እና የቤት ንግድ

ንግድ በተለያዩ የኢኮኖሚ ተዋናዮች መካከል የሚደረግ በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ልውውጥ ነው። ንግድ እንደየአገሩ ነባራዊ ሁኔታ በሚወጡ ሕጎች የሚተዳደር ሲሆን፣ መንግሥታትም የአገራቸውን የንግድ ስርዓት በሚያወጧቸው ሕጎች መሠረት ይቆጣጠራሉ።

በኢትዮጵያም ንግድ የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው ሲሆን፣ ዓለም ዐቀፋዊ መልክ ባለው አሁናዊ የንግድ ስርዓትና ገበያ ውስጥ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱ መስማት የተለመደ ሆኗል። ከሰሞኑም የመኪና እና መኖሪያ ቤት ዋጋ ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ብዙዎችን በማነጋገር ላይ ይገኛል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3RqBtSl
_____________________
"ዳኛ የ8 ሰዓት ሰራተኛ ሳይሆን የ24 ሰዓት ሰራተኛ ነው። ዳኝነትን በመንግስት የስራ ሰዓት ብቻ መስራት አይቻልም።
ዳኛ ቢሮ ባለጉዳይን በማስተናገድ፣ ቤት ደግሞ የምርመራ ስራን በመስራት የሚደክም ነው። በዳኝነት ስራ ምክንያት ለረጅም ጊዜ በመቀመጥና በማቀርቀር በርካታ ዳኞች የጤና እክል እየደረሰባቸው ነው። ህብረተሰቡ የዳኞችን ድካም ሊረዳው ይገባል።"
``~~``
©ወ/ሮ እትመት አሰፋ
{የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ}
በፋና ቴሌቪዠን
https://t.me/lawsocieties
Share👍👍👍👍👆👆👆👆