የውጭ አገር ሰዎች /ኩባንያ #የንግድ_ምልክት የተቃዉሞ አቤቱታ ሰ/መ/ቁ 193292
የሀገራችን የንግድ ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ሆነ ሌሎች የሀገሪቱ አዕምሯዊ ንብረት ህጎች ከአለማቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣሙ ሆነው የተቀረፁ በመሆኑ፤ ሀገሪቱ ለውጪ ሀገር ሰዎች ዜጎቿ ያላቸውን መብትና ግዴታ በተመሳሳይ በማወቅ የንግድ ምልክት ምዝገባና ተያያዥ ተግባራትን ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ስታካሂድ የኖረች መሆኑም የተረጋገጠ በመሆኑ የውጭ አገር ሰው /ኩባንያ/ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ምልክት በተመለከተ መቃወሚያው ማቅረብ ይችል።
የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reciprocity) በሀገራት መካከል ግልፅ የሆነ ስምምነት ባይኖርም እንኳ አንድ ሀገር ለሀገሩ ዜጎች የሚያከብረውን መብት እና የሚጥለውን ግዴታ ለሌሎች ሀገሮች ዜጎችም በተመሳሳይ እንደሚያደርግ የሚያስገነዝብ ነው። በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 3 ሥር የተመለከተው የእንካ ለእንካ መርህ ሊተረጎም የሚገባውም ሌላው ሀገር ለዜጎቹ የሚያደርገውን የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ ለኢትዮጵያዊያን የማያደርግ ከሆነ የዚያ ሀገር ዜጎችም ሆነ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የንግድ ምልክታቸው እንዲመዘገብና ጥበቃ እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ እንዲሁም የተያያዥ መብቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም ተብሎ ነው።
https://chilot.me/2022/09/03/objection-to-trademark-registration-by-foreign-companies-c-f-n-193292/
የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reciprocity) በሀገራት መካከል ግልፅ የሆነ ስምምነት ባይኖርም እንኳ የውጭ አገር ሰው /ኩባንያ/ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ምልክት በተመለከተ መቃወሚያው ማቅረብ ይችላል።
ከችሎቱ ሐተታ በከፊል
የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reciprocity) በዘርፉ የሚታወቅ ሲሆን መርሁ የሚይዘው ትርጉም “አንተ ባደረክግልኝ መጠን እኔም አደርግልሃለሁ” እንዲሁም “እኔ ባደረኩልህ መጠን አንተም ታደርጋለህ” የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡ ይህን መርህ ተጠቅመው ሃገራት ጥቅማቸውን ያስከብራሉ የሌሎችንም ጥቅም በዚያው መጠን ያከብራሉ፡፡ ይህ የእንካ ለእንካ መርህ የ”ናሽናል ትሪትመንት” (National Treatment) አካል ሲሆን የ”ናሽናል ትሪትመንት” መሰረተ ሃሳብ የአለማቀፍ ልማዳዊ ህግን መሰረት የሚያደርግ ሆኖ በሃገራቱ መካከል ግልፅ የሆነ ስምምነት ባይኖር እንኳ አንድ ሀገር ለሀገሩ ዜጎች የሚያከብረውን መብት እና የሚጥለውን ግዴታ ለሌሎች ሀገሮች ዜጎችም በተመሳሳይ እንደሚያደርግ የሚያስገነዝብ ነው።
ከአእምሯዊ ንብረት መብት እና በልዩ ሁኔታም ከንግድ ምልክት ጋር በተያያዘም የ WTO እና TRIPS ስምምነት፤ እንዲሁም የበርን ኮንቬንሽን (Berne Convention)፣ የፓሪስ ኮንቬንሽን (Paris Convention)፣ እና የማድሪድ ፕሮቶኮል (Madrid Protocol) የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህና መሰል የአለም አቀፍ ስምምነቶች የሚመሩበት መሰረታዊ መርህ ብሄራዊ ስምምነት ሲሆን ለአንድ ሀገር ዜጎች የሚጠበቀው መብት ወይም የሚጣለው ግዴታ በሌሎች ሀገሮች ዜጎችም ያለ አድሎ በእኩልነት ተፈጻሚነት እንዲኖረው የሚገባውን ግዴታ የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ለአብነት በ TRIPS አለምአቀፍ ስምምነት አንቀጽ 3 ስር ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ሀገራት ለውጭ ሀገር ዜጎች ጨምሮ የአእምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ የሚያደርጉ ሲሆን የሚሰጠው ጥበቃ አይነትና ተፈጻሚነት ግን የአለም አቀፍ ስምምነቶች አባል በሆኑት እና የሁለትዬሽ እና አህጉራዊ ስምምነቶችን ባጸደቁ ሀገራት የተሻለ ሆኖ ይታያል፡፡ አንዳንድ ሀገራት ደግሞ አብዛኞችን አለም አቀፍ ስምምነቶች ሳያጸድቁ ነገር ግን የአእምሯዊ ንብረት መብቶችን የተመለከቱ አለማቀፋዊ መርሆችና አሰራሮችን በሀገራቸው ህጎች ደንግገው ይገኛሉ፡፡ በዚህ መልኩ ለመብቱ ጥበቃ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል ኢትዬጵያ አንዷ ስትሆን አዋጅ ቁጥር 501/98 እና ሌሎቹ የአእምሯዊ ንብረት አዋጅና ደንቦች ይህን የሚያሳዩ ናቸው፡፡
By #Abrham_Yohanes

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የመድን ህግ -ቅሪት ሰ/መ/ቁጥር 204256
በመኪና ላይ ለደረሰ ጉዳት ለማስጠገኛ ወጪ ክፍያ የሚቀበል የመኪና ባለቤት ከጥገና የሚቀሩ ቅሪቶችን በዓይነት ወይም ግምታቸውን በገንዘብ ለመድን ሰጪው ድርጅት ሊመልስ ይገባል፡፡
የጉዳት ካሳ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት የመድን ድርጅት ከጉዳት የተረፉ ቅሪቶች በዓይነት እንዲሰጠው ወይም በዋጋቸው ልክ ከሚከፍለው ላይ እንዲቀነስለት ለመጠየቅ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማቅረብ ሳይኖርበት በመከላከያ መልሱ ላይ ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል፡፡
#Abrham_Yohanes