የትራፊክ ቅጣት መክፈያ 👇👇👇👇
#6050
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የቅጣት ክፍያ ስርዓትን የሚያቀላጥፍ እና የሚያዘምን አዲስ አሰራርን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ዛሬ ይፋ አድርጓል።
የትራፊክ ህግ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ቅጣት ክፍያን ለመፈፀም በኢትዮ-ቴሎኮም የተዘጋጀው 6050 አጭር ቁጥር መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።
አዲስ ይፋ የተደረገው የትራፊክ ቅጣት ክፍያ ስርዓት በ6050 አጭር ቁጥር በመጠቀም ትራፊክ ፖሊሶች እና የኤጀንሲው የቁጥጥር ባለሙያዎች በወረቀት ይደረግ የነበረውን አሰራር እንደሚያስቀር ተገልጿል።
ቅጣቱን በሞባይል ስልክ ለተቀጪው በማድረስም መንጃ ፈቃዱ ሳይያዝበት ወይም ታርጋው ሳይፈታበት ጥፋቱን በፈፀመበት ቦታ ክፍያውን መፈፀም ያስችለዋል ተብሏል።
የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያን በቴሌብር አማካኝነት መክፈል የሚያስችለው ይህ አገልግሎት ወይም አሰራር ለዘመናት አድካሚ የነበረውን በወረቀት ላይ ያተኮረ የቅጣት ክፍያ አፈጻጸምን የሚያስቀር ነው ተብሎለታል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
#tikvahethiopia

👍2❤1🔥1
#Moot_Court
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት ላለፉት 4 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የምስለ-ችሎት (Moot Court) ውድድር ግንቦት 20/ 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ በተካሄደው የፍጻሜ ዝግጅት ፍፃሜውን አግኝቷል።
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙርያ ያተኮረው የዘንድሮው ውድድር ፦
➡️ በአዲስ አበባ፣
➡️ አዳማ፣
➡️ ሀዋሳ፣
➡️ ሆሳዕና፣
➡️ ሚዛን፣
➡️ ጋምቤላ፣
➡️ አሶሳ፣
➡️ ሰመራ፣
➡️ ሐረር፣
➡️ ድሬዳዋ፣
➡️ ጅግጅጋ እና ጎንደር ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን በ10 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 63 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 130 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በክልላዊ የቃል ክርክር ውድድሮች 1ኛ እና 2ኛ የወጡ 24 ተወዳዳሪ ቡድኖች የጽሑፍ ክርክራቸውን ለኢሰመኮ በመላክ የተወዳደሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 8 ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከግንቦት 15-20 ቀን 2014 ዓ.ም በሩብ ፍፃሜ እና ግማሽ ፍፃሜ ዙሮች ተወዳድረዋል።
ከነዚህም ውስጥ ከወላይታ ከተማ፣ ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪ ሳያት ደሳለኝ እና ተማሪ አስቻለው ማቴዎስ እንዲሁም፣ ከጎንደር ከተማ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒቲ ት/ቤት የመጡት ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ ግማሽ ፍፃሜ አሸናፊዎች በመሆን ለፍፃሜ ውድድር መቅረብ ችለዋል።
ዛሬ በተደረጉው ውድድር ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ #ከጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ኮሙኒቲ_ትምህት_ቤት የ2ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እና ፎቶዎች ከላይ ተያይዟል)
#EHRC
#tikvahethiopia @lawsocieties

👍21