አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Investment Flows to Africa Reached a Record $83 billion in 2021

Foreign direct investment (FDI) to African countries hit a record $83 billion in 2021, according to UNCTAD’s World Investment Report 2022 published on 9 June.
#EthiopianBusinessDaily
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
👍2
በአንድ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ!

ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር ሆቴል በሚባል አካባቢ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በክፍል ውስጥ ርንቺት ተኩሶ ከት/ቤት ውስጥ አምልጦ የሄደ አንድ ተማሪን አራት የፖሊስ አባላት ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል ፈጽመውበታል፡፡

ህገ- ወጥ ድርጊቱ በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ድል በር 2ኛ ደረጃ በሚባል ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ነው በሚል ፕሮግራም ላይ በክፍል ውስጥ በተደረገ ዝግጅት አንድ ተማሪ ርችት እንደተኮሰ እና በት/ት ቤት ውስጥ ርችት መተኮሱ ሌሎች ተማሪዎችን እንደረበሻቸው ለፖሊስ መረጃ ይደርሰዋል፡፡

በእለቱ ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለው ተማሪ ከት/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንደወጣ የተነገራቸው 4 የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ክትትል በማድረግ ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር የሚባል ሆቴል አካባቢ ተማሪውን ይዘውት ተገቢ ያልሆነ ድብደባ ፈፅመውበታል፡፡

የአ/አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ፖሊስ መረጃው ካደርሰው በኋላ ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ ይገኛል፡፡

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ የዜጎችን ህጋዊ መብት በሚፃረሩ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በማንኛውም ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ህ/ሰቡ በያገባኛል ስሜት የሚሰጠውን መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ኢትዮመረጃ
👍5😢1
የአማራ ክልልአቃቤ ህግ ማህበር ጠቅላይ ሚኒስትሩለህዝብ እንደራሴዎች 2ኛ ደረጃ ሌባ ዐቃቤ ህግ ነው ብለው የተናገሩትን ብያኔያዊ መግለጫ ማስተካከያ የማይሰጡበት ከሆነ ተገቢ ያልሆነውን ብያኔ ተከትሎ የሚመጣውን የአስፈፃሚ አካላት ጫና ማህበሩ እንደሚታገል ተገለፀ!
-----
@የአማራ ክልል ዓቃብያነ ሕግ ማሕበር
👍23👎3
የነዳጅ_ውጤቶች_የሥርጭት፣_የርክክብና_የሽያጭ_አፈፃፀም_መመሪያ_904_2014.pdf
324.5 KB
⛽️ የነዳጅ ውጤቶች የሥርጭት፣ የርክክብና የሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ቁ. 904/2014

የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁ. 1263/2014 አንቀጽ 19(4) መሠረት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡ ይህ መመሪያ ከወደብ እስከ ነዳኝ ማደያዎች ድረስ ባለው የሥርጭት፣ የርክክብና የሽያጭ ሂደት ላይ ተሳታፊ በሆኑና የቁጥጥር ሚና ባላቸው አካላት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
👍5
መልካም የእረፍት ቀን ለሁሉም የአለ_ህግ ቤተሰቦች🙏

stay updated about all legal issues🔴

Share, invite and add...❗️👇👇👇

https://t.me/lawsocieties
#Ruwanda!

#የሩዋንዳው ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ ከዚህ በፊት ብዙ መስኪዶችን አዘግተው ነበር አሁን ደግሞ ከ6000 በላይ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተሰማ።
#ፕሬዝዳንቱ ቸርች ለመክፈት ማንኛውም የቤተክርስቲያኑ መሪ የስነመለኮት ዲግሪ ሊኖረው ይገባል ያሉ ሲሆን
#እኔ ከዚህ በኋላ ቤተክርስቲያን የንግድ ተቋም ሲሆን ቆሜ አላይም ብለዋል።

#ሩዋንዳን በምታክል ትንሽ ሀገር ላይ በቂ ሆስፒታልና
ት/ቤቶች ሳይኖሩ ሀሰተኛ ቤተክርስትያናትና ፓስተሮች በዝተዋል ያሉት ፖል ካጋሜ ይህንን የሚቆጣጠርም አዲስ ሕግ እንዲወጣ አድርገዋል ተብሏል።
@ ምንጭ: 35 News GH

https://t.me/lawsocieties
👍16👏1
የ 37 ዩኒቨርሲቲ የ Exit Exam የፈተና ጣቢያቸው እና የተፈታኞች ስም ዝርዝር
የሁሉም የህግ ተቄማት የ Exit Exam ምዝገባ እና የፈተና ጣቢያ ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ በዚህ ሊንክ ስምዎን መኖሩን ያረጋግጡ https://t.me/AleHig
2014 law exit exam center and registration number
👍2
37 ዩኒቨርሲቲ የ Exit Exam የፈተና ጣቢያቸው እና የተፈታኞች ስም ዝርዝር፣
የሁሉም የህግ ተቋማት የ Exit Exam ምዝገባ እና የፈተና ጣቢያ ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ፣


ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ በተመዘገቡበት ዩኒቨርሲቲ በመግባት ስምዎን መኖሩን ያረጋግጡ።
2014 law exit exam center and registration number


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31167

አልፋ ዩኒቨርስቲ https://t.me/AleHig/31170

አምቦ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31172

አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31175

አርሲ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31177

አሶሳ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31179

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31181

ቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31183

ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ https://t.me/AleHig/31185

ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31187

ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31189

ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31191

ዲላ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31193

ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31195

ኢትዮጲስ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31197

ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31199

ጎንደር ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31200

ሀራማያ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31202

ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31204

ጅማ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31206

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31389

ማዳወላቡ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31208

መቱ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31210

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31212

MoE Tigray ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31214

ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31216

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31218

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31221

ሰመራ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31224

ሴንትሜሪ ዩኒቨርስቲ https://t.me/AleHig/31226

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31230

ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31232

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ https://t.me/AleHig/31234

ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31236

ወለጋ ዩኒቨርስቲ https://t.me/AleHig/31238

ወሎ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31240

አፍሪካ ቤዛ ዩኒቨርስቲ
https://t.me/AleHig/31245


https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👍14🔥5👏2😁1
Names of books that brought to Exam hall

2021/2022 ACADEMIC YEAR


PART I: PRIVATE LAWS

THIS IS A CLOSED BOOK EXAM EXCEPT PERTINENT ETHIOPIAN LAWS.

Part Ii: public Laws

Laws that can be brought to the exam room are
The UN Charter,
The Vienna Convention on the Law of Treaties,
The FDRE Constitution,
The Criminal Code,
The Income Tax Proclamation,
The VAT Proclamation,
The Environmental Pollution Control Proclamation, And
The EIA Proclamation.

Part III: Procedural Laws

A closed book exam for all materials except clean copies of
the Civil Procedure Code,
the Criminal Procedure Code
the Criminal Code,
the Federal Courts Establishment Proclamation, and
Corruption Crime Proclamations (substantive and procedural)
Which cannot be lent to nor borrowed from other students.

Part IV: Miscellaneous Law Courses

It is a closed book examination.

Via @Lawsocieties Ale_Hig አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
👍155
አንድ የመንግሥት ሠራተኛን በኃላፊ በተፃፈ ደብዳቤ ብቻ ከሥራ ማሰናበት ሕገ መንግሥታዊ ነውን?

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 37(1) መሰረት ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት ያለው ስለመሆኑ ተደንግጓል። በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 42 ስር ለሠራተኞች የተደነገጉ በርካታ መብቶች አሉ። በተለይም ከዚህ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ አርዕስት መረዳት አንደሚቻለው ሠራተኞች በሕገ መንግሥቱ የተጠበቀላቸው የሥራ ዋስትና መብት ያላቸው መሆኑን መረዳት ይቻላል። በሕገ መንግሥቱ ለሠራተኞች የተጠበቀው የሥራ ዋስትና መብት ከሚከበርበት መንገድ ውስጥ አንዱ ሠራተኞች በሕግ አግባብ ከተቀመጠው ሂደት እና አሠራር ውጪ ከሥራቸው መባረር የሌለባቸው መሆኑ ነው። ሠራተኞች በሥራ ቦታ ለሚያጠፉት ጥፋት በሕግ አግባብ በተቀመጠው የዲስፕሊን ሂደት የመዳኘት መብት አላቸው። ይህ መብት ከላይ በተጠቀሰው የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) መሰረት የሚተገበር ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በተለይም የመንግሥት ሠራተኞች በዲስፕሊን ጥፋት ከሥራ የሚሰናበቱት ጉዳያቸውን ለማየት እና ፍርድ ወይም ውሳኔ ለመስጠት በሕግ ስልጣን ባለው አካል ብቻ ነው። በሕግ በግልፅ ከተደነገገው አግባብ ውጪ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ተገቢውን ክርክር ሳያደርግ፤ ያለውን ማስረጃ በማቅረብ እራሱን ሳይከላከል አንዲሁም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ላለው አካል ይግባኝ አቅርቦ ሳይከራካር ከሥራ ሊሰናበት አይችልም።.......ይቀጥላል 👇👇👇👇👇
👍9👎1🔥1
የቀጠለ.......👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አንድ ሠራተኛ ጥፋት ሲያጠፋ ተገቢው ክስ ቀርቦበት በቀረበበት ክስ ላይ ሠራተኛው መልስ ሰጥቶ የመከራከር፣ ማስረጃ የማቅረብ እና የመከላከል መብቱ ሊከበርለት ይገባል።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 9(1) መሰረት ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሠራር፣ አንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ሆኖ ሲገኝ ተፈፃሚነት አንዳይኖረው በሕገ መንግሥት ትርጉም ስርዓት ውድቅ ይደረጋል።
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 84 እና 9(1) ጣምራ ንባብ መሰረት ማንቸውንም ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ስልጣን አለው። በሚያደርገው ማጣራትም ማናቸውንም ሕግ፣ ልማዳዊ አሠራር፣ የባለስልጣን ወይም የመንግሥት አካል ውሳኔ የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ሆኖ ከተገኘ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው የውሳኔ ሃሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል። ምክር ቤቱም የጉባዔውን የውሳኔ ሃሳብ ተቀብሎ ካፀደቀው ውሳኔው የመጨረሻ ይሆናል።
በዚሁ መሰረት ቀጥለን የምናየው ጉዳይ አስፈፃሚ የመንግሥት አካል የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ የክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የአንድን መምህር የዲስፕሊን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ ኢ-ሕገ መንግሥታዊነትን ነው።
አመልካች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ትምህርት ቤት መምህር ናቸው። እኝህ በአዲስ አበባ ከተማ በመምህርነት የሚያገለግሉ አመልካች በትምህርት ቤቱ ያሉ መምህራንን በማስተባበር የሥራ ማቆም አድማ አንዲደረግ አድርገዋል እንዲሁም የመማር ማስተማሩን ሥራ አስተጓጉለዋል በሚል በክ/ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ ደብዳቤ ከሥራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። አመልካች ይህን የክ/ከተማውን ፅ/ቤት ውሳኔ ለማሻር የይግባኝ ቅሬታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አልተቀበላቸውም። ቀጥሎም አመልካች አቤቱታቸውን ለሌሎች የተለያዩ የመንግሥት አካላት ቢያቀርቡም የሚቀበላቸው እና መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም።
በመጨረሻም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ለማጣራት ስልጣን ለተሰጠው የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በአስተዳደር አካሉ ውሳኔ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም አንዲሰጣቸው አመልክተዋል።
ጉባዔውም ጉዳዩን ለማጣራት ያመች ዘንድ አመልካች በወቅቱ ለአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር የይግባኝ ማመልካቻ ማቅረብ አለማቅረባቸውን እና አንድ ጉዳይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ሳይታይ በሥራ ኃላፊ ደብዳቤ ብቻ የተሰናበተ ከሆነ ለሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እና መዝገብ ማስከፍት ይችላል ወይ የሚለውን አጣርቷል። ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ በወቅቱ የነበረው ሬጅስትራር የለቀቀ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ምላሽ መስጠት የማይቻል መሆኑን ጠቅሷል። በሌላ በኩል አንድ ጉዳይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ሳይታይ በሥራ ኃላፊ በተፃፈ ደብዳቤ ከሥራ ቢሰናበት በዚሁ ደብዳቤ መነሻነት የይግባኝ መዝገብ መክፈት የሚቻል መሆኑን በመግለፅ መልስ ሰጥቷል።
አመልካች የስንብት ደብዳቤ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የይግባኝ ማመልከቻ ለአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት አቅርበው የነበረ መሆኑን ለጉባዔው ካቀረቡት ማስረጃ መረዳት ይቻላል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጉዳይ ተቀብሎ ማስተናገድ ሲገባው “አንቀበልም’’ ማለቱ አመልካች በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) የተረጋገጠላቸውን ፍትህ የማግኘት መብታቸው መጣሱን ያረጋግጣል።
የአመልካች ዓይነት የይግባኝ አቤቱታን የመቀበል፣ የመመርመር እና ፍርድ ወይም ውሳኔ የመስጠት ሕጋዊ ግዴታ የተጣለው በአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ላይ ነው። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ በሕግ በተሰጠው የዳኝነት ስልጣን መሰረት የአመልካችን አቤቱታ በመቀበል ተገቢውን ማጣራት እና ክርክር በማድረግ ውሳኔ ወይም ፍርድ መስጠት ነበረበት። የአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ይህን ኃላፊነቱን ባለመወጣት እና የአመልካችን አቤቱታ ተቀብለው ባለማስተናገዳቸው አመልካች ማግኘት የነበረባቸውን ፍትህ ሊያገኙ አልቻሉም።
ጉባዔው ጉዳዩን ካጣራ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጉዳይ ተቀብሎ ማስተናገድ ሲገባው አንቀበልም ማለቱ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) ስር የተደነገገውን ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብቱን የሚጥስ ነው በማለት፣ አመልካች በፅ/ቤቱ ኃላፊ ደብዳቤ ብቻ የተላለፈባቸው የሥራ ስንብት ውሳኔ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት የሕገ መንግሥት ትርጉም እንደሚያስፈልገው የውሳኔ ሃሳቡን አሳልፏል።
ስለሆነም አመልካች ጉዳያቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት አላቸው በማለት ጉባዔው የውሳኔ ሃሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተላልፏል። ምክር ቤቱም የአጣሪ ጉባዔውን የውሳኔ ሃሳብ በመቀበል በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቷል።
በያደታ ግዛው
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍11