አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ላይ ስላለው ተፈጻሚነት የሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም
በአሠሪና ሠራተኛ ህግ አፈጻጸም አስቸጋሪ ሆነው ከቆዩት ጉዳዮች አንዱ አዋጁ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ላይ ያለውን ተፈጻሚነት ይመለከራል። በእርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ አዋጁ ግልጽ ነው።
ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች አዋጁ ተፈጻሚ እንዳይሆን ካልተደረገ በቀር የአዋጁ ተፈጻሚነት ጥያቄ ውስጥ አይገባም
ሆኖም ትልቁ ችግር የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን ሳይሆን እነዚህ ድርጅቶች ከዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች ወይም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከሚያደርጉት ስምምነት የመነጨ ያለ መከሰስ መብት ስለሚኖራቸው የስራ ክርክር ጉዳይ ሳይታይ ክሱ ወዲያው ውድቅ ይደረጋል።
በ ሰ/መ/ቁ 98541 ቅጽ 17 (አመልካች አቶ አለማየሁ ኦላና እና ተጠሪ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (UNDP) ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም.) ተጠሪ በዋናው ክርክር ሳይከራከር መዝገቡ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እያለ ያለ መከሰስ መብቱ በምክንያትነት ተጠቅሶ አመልካች በፍርድ ያገኙትን መብት ተነጥቀዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም በተወሰነ መልኩ ይህንን ኢ-ፍትሐዊ የመብት መጣስ የሚያስቀር ይመስላል።
ምክር ቤቱ በውሳኔው ላይ ለሁለት መሰረታዊ ነጥቦች እልባት ሰጥቷል። ይኸውም

1. ያለ መከሰስ መብት ተፈጻሚነቱ ከዲፕሎማቲክ መብትና ድርጊት ጋር በተያያዘ እንጂ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ አይደለም።

2. ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገቡት ውል መሰረት ያለ መከሰስ መብት ሲያገኙ በውሉ የተመለከተው የአለመግባባት መፍቻ መንገድ ተግባራዊ መሆን ካልቻለ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን አይቶ የመዳኘት ስልጣን አላቸው። @Lawsocieties
የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ለቤኒሻንጉል ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ አካላት ባለሙያዎች ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን ሥልጠና ዛሬ አጠናቀቀ

(ሰኔ 03 ፣ 2014 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ለቤኒሻንጉል ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ አካላት ባለሙያዎች (ለዳኞች፣ ለዓቃቤያነ ህግ እና ለፖሊስ ኮሚሽነሮች) ለስድስት ተከታታይ ቀናት በአሶሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ አጠናቀቀ።

ሥልጠናው ሶስት የተለያዩ ርዕሶችን፡ የፀረ ሽብርተኝነት ህግ' ፣ 'የክስ አመሰራረትና ክርክር ክህሎት' እና 'የቅጣት አወሳሰን መመሪያን' ያካተተ ሲሆን ርዕሶቹ በክልሉ ፍትሕ አካላት አመራሮች የተመረጡ እና ከዚህ በፊት በክልሉ ሲያጋጥሙ የነበረ ክፍተትን ለማሟላት የታሰበ መሆኑም ተገልጿል።

በሥልጠናው የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው የመዝግያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰዒድ ባባከ የለውጡን ቀጣይነት እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ለማሳደግ እንዲሁም በክልሉ የህብረተሰቡን የፍትሕ ጥያቄ ለመመለስ የተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠናው ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሰዒድ አክለውም ሁሉንም አስቸጋሪ ጉዳዮችን ለመዳሰስ አስቸጋሪ ቢሆንም የክልሉ ፍትሕ አካላት አመራሮች እና ባለሙያዎች ወጪ ቆጣቢ፣ ፈጣንና ፍትሐዊ የሆነ በተለይም በተሰጡት የስልጠና ርዕሶች ላይ አትኩረው በጥብቅ ስራዎችን በማከናወን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ዘገባው:- የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Urgent❗️❗️
paid internship vacancy
Location; Adama
Number; 2
#ተመዝገቡ
Address: Oda ( Warka) Team Business center, 2nd floor
office no. 95

Phone number: 0910100328 / 0974600876

The deadline is on Monday 07/10/2014 ዓ.ም

Transparency International Ethiopia

Head office for General info...
ስልክ +251118279746
@Transparency_Ethiopia_Bot

ethiopiatransparency@gmail.com

@TransparencyEthiopia

https://t.me/TransparencyEthiopia
ዶክተር ለማ
ኢንጂነር ለማ
ህግ....... አቶ
ከዛሬ ጀምሮ በህግ የተመረቀ ሰው የክብር ስሙ *በህግ* ለምን ይባልም
*በህግ ለማ* ከስማችሁ መጀመሪያ ላይ እያስገባችሁ ሞክሩት።
ከተስማማችሁ like and share.
አምስት አመት ተምሮ አቶ ⁉️
ይህ ስም እንዲፀድቅ የሚፈልግ ብቻ share‼️
ጥቆማችሁን #comment ላይ አድርሱን
ማን ይሁን
።።።።።።።። #አለ_ህግ #Ale_Hig ።።።።።።
@Lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

በፌስቡክ Facebook
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም Telegram
https://t.me/lawsocieties

ሊክድን LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

በ ቲክቶክ Tiktok
tiktok.com/@lawsocieties

ትዊተር Twitter
https://twitter.com/Lawsocieties?t=VFQWzXMBnNQnXyZu7z52bQ&s=09

በዩቲዩብ YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw

Email address
lawsocieties@gmail.com

Telegram Bot
@LawsocietiesBot
👍👍👍👍👍👍👍👍❗️❗️❗️❗️❗️❗️


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።🙏
ዳኛ
አቃቤ ህግ
ህግ ባለሙያ
ጠበቃ
ነገረ ፈጅ
..............
......ሌሎችን የህግ ምሩቃን ማን ብዬ ልጥራቸው
መጠሪያ ግን ይህን ያህል አገብጋቢ ጉዳይ ነው
via #Lawsocieties
Federal Justice and Law Institute begins training of Gambella National Regional State Judiciary

Federal Justice and Law Institute has started capacity building training for judges, prosecutors and police at various levels under the Gambella National Regional State in Gambella town.

The training was opened by the head of the Gambella Regional Justice Bureau, Akwai Abuti, who conveyed a message of welcome to the participants.

He said the main purpose of the training is to build the capacity of the judiciary, adding that participants should attend the training properly and contribute their share to the success of the judiciary.

The training will be delivered by Gambella National Regional State Supreme Court Judge Dol Ukuri, Regional Prosecutor W / Yesus Gelan and Regional Supreme Court Judge Chang Teng.

"
Rural and Urban Land Administration Law,
the Anti-Corruption Law and the Penal Code
" will be given for six consecutive days, including today.

This training is in line with the Federal Justice and Law Institute's plan to provide capacity building training to state and city administration judicial professionals who do not have their own training center in the 2014 fiscal year.

>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

The report is from the Directorate of Communication Affairs!