አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#በጋራ አብሮ የመስራት ውል (joint Venture Agreement)
በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 234 መሰረት የአሽሙር ማህበር ማለት “ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚያቋቁሙት በሦስተኛ ወገኖች የማይታወቅ የሕግ ሰውነት የሌለው የንግድ ማኅበር ነው፡፡” በማለት ይገልጸዋል፡፡
በዚህ አንቀጽ መሰረት ይህ አይነት ማህበር ስለሌሎች የንግድ ማህበሮች የተደነገጉት የማስመዝገብ ስርዓቶች በዚህ ማህበር ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆኑ ይገልጻል፡፡
በመሆኑም ተገልጋዮች በጋራ አብሮ የመስራት ውል(የአሽሙር ውል) ለመዋዋል ወደ መስሪያ ቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
. የተዋዋይ ወገኖች ወገኖች የተናጠል ወይም የየግላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
. ተዋዋይ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረጃ ጽሁፍ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፣
. በውል ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጸና ማስረጃ የሚያስፈልገው የባለቤትነት ወይም የመብት ማጣቀሻ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጣ ማስረጃ፣
. የተዋዋይ ወገኖች የታደሰ መታወቂያ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተገልጋዮች የተባሉትን ዝርዝር ነገሮች አሟልተው ሲቀርቡ ለዚህ አገልግሎት የሚወስደው ጊዜ 25 ደቂቃ ነው፡፡
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ( share ) በማድረግ ብልሹ አሰራር እና ሙስናን ይከላከሉ፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig via @Lawsocieties
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት