አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#NewsAlert ‼️

#Ethiopia : ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ ከታወቀው አምስት ሰዎች ውስጥ አራቱ ቻይናዊያን ሲሆኑ አንዷ ኢትዮጵያዊ መሆኗ ታውቋል::
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
#NewsAlert ‼️

#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ ፀደቀ! ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ መፅደቁን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

"ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለወገን እና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ጥንቃቄአችንን ከበፊቱ በላይ እናጠናክር" ብለዋል ወይዘሮ አዳነች በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

ህብረተሰቡ ለራሱ ሲል በመንግስት እና በባለሞያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መመሪያዎች ችላ ሳይል እንዲተገብርና ለህግ አስከባሪው አካል እንዲታዘዝም አሳስበዋል።
#NewsAlert

የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ ተላለፈ !

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔው ሊተላለፍ የቻለው ባለፈው ነሃሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡

ውሳኔውን የሚከታተል የህገ መንግስት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈጸሙ በዛሬው ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ የቻለው፡፡

ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ 3 ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል። ውሳኔዎቹ ፦

1ኛ. የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡

2ኛ. የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማት እና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ብቻ የስራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

3ኛ. የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ አሳልፏል። (ኢቲቪ)

via tikvahethiopia
#NewsAlert

በሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገቡትን ‘Titan gel’ ፣ ‘Mara Moja’ እና ‘Relief’ የተሰኙ መድኃኒቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ።

ሕብረተሰቡ መድኃኒቶቹን ሲያገኟቸው ለባለስልጣኑና ለጸጥታ አካላት እንዲጠቆም ጥሪ አቅርቧል። በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመንገደኛ ሻንጣ እንዲሁም በሌሎች የመግቢያና መውጫ ኬላዎች አማካኝነት የተለያዩ መድኃኒቶችበሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በተገኘው መረጃ

👉Titan gel’ ፣
👉‘Mara Moja’ እና

👉‘Relief’ የተሰኙ መድኃኒቶች በባለሥልጣኑ ያልተመዘገቡ መሆናቸውን አመልክቷል።

መድኃኒቶቹ በሐኪም ብቻ በመታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ቢሆንም በድብቅና በሕገወጥ መንገድ ገበያ ላይ እየተሸጡ እንደሆነ አስታውቋል። ሕብረተሰቡ መድኃኒቶቹ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገቡ፣ጥራታቸው ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እንዲሁም በጤና ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ በመገንዘብ መድኃኒቶቹን እንዳይጠቀምባቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል።

ማንኛውም ግለሰብ ‘Titan gel’ ፣ ‘Mara Moja’ እና ‘Relief’ በሕጋዊ ተቋማትም ሆነ በሕገወጥ መንገድ ሲያገኛቸው በመስሪያቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482 እንዲሁም በአቅራቢያው ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪዎች ወይም ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ share ያድርጉ።
ኢትዮ መረጃ