#ተገጣጣሚ_ቤቶች
ከተማ አስተዳደሩ በስምንት ቢሊዮን ብር ሊያስገነባቸው የነበሩ ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ በፍርድ ቤት ታገደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስምንት ቢሊዮን ብር በጀት ያስጀመረውና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ወርቁ ሠፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሊያከናውነው የነበረው የአምስት ሺሕ ተገጣጣሚ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ሕንፃዎች ግንባታ፣ በፍርድ ቤት ዕግድ እንዲቆም መደረጉ ተገለጸ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በ21.8 ሔክታር መሬት ላይ የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር ጥር 4 ቀን 2014 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ቢያስቀምጥም፣ መሬቱ የባለቤትነት ጥያቄ ተነስቶበት ፍርድ ቤት ዕግድ በማውጣቱ ግንባታው እንዲቆም መደረጉን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና የቤቶቹን ግንባታ የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቀዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥንፉ ሙጬ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ግንባታው ይፋ ከተደረ በኋላ ኮርፖሬሽኑ 291 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተገጣጣሚ ሕንፃ አካላት ኮንክሪትና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ወደ ቦታው አስገብቷል፡፡ በግንባታ ቦታው ላይ አሥር ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አፈር ጠረጋና ምንጣሮ ሥራ መካሄዱንም አስረድተዋል፡፡
ይሁንና የመሬቱ ባለቤትነት ይገባኛል ያለ ግለሰብ ጥያቄ በማንሳቱ፣ ኮርፖሬሽኑ ሥራ በጀመረ በቀናት ውስጥ ዕግድ ወጥቶበታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ እግዱ ቢወጣም የግንባታ ሥራውን እንደቀጠለ ያስረዱት አቶ ጥንፉ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ዕግድ ከመጣ በኋላ ግን መሬቱ ላይ ያለው ሥራ እንዲቆም መደረጉን ተናግረዋል፡፡......... ይቀጥላል....
#አለ_ህግ
#አለ_Share....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties