አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
It is urgent
Please contact us today.
Anyone from;

Bahir Dar
Dire Dawa
Adama
Awassa

Research data collection and coordinating the focus group discussion.
Contact us: @LawsocietiesBot
lawsocieties@gmail.com
This is Good opportunity for you❗️
Who knows what comes with....
Notice❗️
It is only for 5 days❗️
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et

3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot

4) በ9444 SMS)፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)
@tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እናያለን ❗️❗️❗️❗️
Hagbes Private Limited Company ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
👩 position:Legal Advocate
https://jobs.amazonethiopia.com/job/legal-advocate-2/
📚 ትምህርት ዓይነትእናደረጃ፡-
LLB Degree in Law
🇪🇹 የስራ ቦታ: አዲስ አበባ
🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ.ም
Legality of Levying Income Tax on Illegal Amounts Received by a Taxpayer ---- Personal Reflection

By:- Natae Ebba Kitila

The central focus this piece wants to press on is the legality of the collection of income tax on illegally driven amounts. In doing so, the writer will try to unpack some important elements from the Income-tax proclamation No 979/2016.

Enjoy reading!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2024-legality-of-levying-income-tax-on-illegal-amounts-received-by-a-taxpayer-personal-reflection
የኢትዮጵያ የህግ ምንጮች እና ተዋረድ

መግቢያ

ህጎች የተለያዩ መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡፡ በዚህ መሰረት “የሲቪል ሎው (civil law)” እና “የኮመን ሎው (common law)”፣ “ፐብሊክ ሎው (public law)” እና “የግል ህግ (private law)”፣ “የወንጀል ህግ” እና “የፍትሀብሄር ህግ”፣ “የስነ ስርዓት ህግ (procedural law)” እና “መሰረታዊ ህግ (substantive law) እና የመሳሰሉትን መስፈርቶች በመጠቀም ህጎችን ማከፋፈል ይቻላል፡፡ የሀገራት ህጎች በሁለት ዋና ዋና የህግ ስርዓቶች ማለትም የኮመን ሎው እና የሲቪል ሎው በሚል ይታወቃሉ፡፡ የሲቨል ሎው የህግ ስርዓት ተከታይ አገራት ፍትሀብሄርን የሚመለከት ዐብይ ህግ በአንድ ጥራዝ (codified) ታውጀው እና የወንጀል የሚመለከት ዐብይ ህግ በአንድ ጥራዝ (code) ታውጀው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በአገራችን አጠራር የፍትሀብሄር ህግ እና የወንጀል ህግ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ስለሆነም ይህን ስርዓት የሚከተሉ ሀገሮች ዋና የህግ ምንጭ በህግ አውጪ አካል ታውጀው የሚጠረዙ ህጎች ናቸው ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል የኮመን ሎው ስርዓትን የሚከተሉ ሀገሮች ዋና የህግ ምንጫቸው በህግ አውጪ አካል የሚወጡ ህጎች ሳይሆኑ በፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ጉዳይ ቀደም ብለው የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች (precedent) ናቸው፡፡ እንዲሁም ያልተፃፉ ህጎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

በሀገራችንም የተለያዩ የህግ ምንጮች ያሉ ሲሆን የህጎች ተዋረድ ወይም የህግ የበላይነት ደረጃ (hierarchy of laws) በህግ ስርዓት ውስጥ ጉልህ ቦታ ካላቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ በዚህ የንቃተ ህገ ፅሁፍ የኢትዮጵያ የህግ ምንጮችን እና የህጎቹን ተዋረድ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

1. የኢትዮጵያ ህግ ምንጮች (sources of Ethiopian laws)
በአገራችን ህጎች በፌደራል እና በክልል ደረጃ ወጥተው ስራ ላይ ይውላሉ፡፡ እነዚህም ህጎች በፌደራል እና በክልሎች የተለያዩ ምንጮች አሏቸው፡፡

1.1. የፌደራል የህግ ምንጮች
i. ህገ መንግስት (constitution)
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9 ህገ መንግስት የሀገሪቱ የበላይ ሕግ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ማንኛውም ህግ ለምሳሌ አዋጅ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህ ማለት ህገ መንግስት የማንኛውም ህጎች መነሻ እና ምንጭ እንዲሁም ህጋዊነታቸውን (validation) የሚያገኙበት መሰረት ነው፡፡
ii. አለም አቀፍ ስምምነቶች (international treaties)
ሀገራት አለም አቀፍ ስምምነት ሲፈርሙ ስምምነቱን እንደ አንድ አለም አቀፍ ህግ እንተቀበሉ ማስረጃ ነው፡፡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 (4) እንደሚደነግገው ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ስራ ላይ ለመዋል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ እና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትመው መውጣት አለባቸው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱ ህግ አካል ሆነው ተግባራዊ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
iii. ኮዶች (codes)
በሀገራችን በ1960ዎቹ አምስት ኮዶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ እነዚህም የፍትሀ ብሄር ህግ፣ የንግድ ህግ፣ የባህር ህግ በ1960፣ የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ በ1961 እና የፍትሀ ብሄር ስነ ስርዓት ህግ በ1965 ናቸው፡፡ እነዚህም ህጎች በነጋሪት ጋዜጣ በአዋጅ መልክ ታውጀው ስራ ላይ ውለዋል፡፡ ከዚህም በኃላ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ፣ የወንጀል ህግ እና አዲሱ የንግድ ህግ በኮድ መልክ ስራ ላይ የዋሉ የአገራችን የህግ ምንጮች ናቸው፡፡
iv. አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ (proclamations, regulations & directives)
አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ደንቦች በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና መመሪያዎች ደግሞ በፌደራል ሚኒስትሮች መስሪያ ቤቶች ወይም በሚስትሮች ምክር ቤት መመሪያ እንዲያወጡ በደንብ ውክልና በተሰጣቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ይወጣሉ፡፡ በተጨማሪም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማወጅ ስልጣን በህገ መንግስቱ ተሰጥቶታል፡፡ እነዚህም የህግ ክፍሎች ወይም አይነቶች የአገራችን የህግ ምንጭ በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆኑ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ይህም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በሚነስትሮች ምክር ቤት ከታወጁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡
v. አስገዳጅ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች (precedent)
ይህ የህግ ምንጭ አይነት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አስገዳጅ ወይም ህግ የሚሆንበት ስርዓት ነው፡፡ በአገራችን ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ እንደ ህግ እንደሚያገለግሉ እና አስገዳጅ እንደሆነ የሚገልፀው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10/2 ስር እንደተደነገገው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ ባለ የፌደራል እና የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል ይላል፡፡ ይህ ማለት እነዚህ ውሳኔዎች የህግ ምንጭ ሆነው ስራ ላይ ይውላሉ ማለት ነው፡፡
vi. ልማዳዊ ህጎች (customary laws)
ልማዳዊ ህጎች በኢትዮጵያ ህጎች ውስጥ በተለያየ ጊዜ እንደምንጭ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ የፍትሀ ብሄር ህጉን ያረቀቁት ፕሮፌሰር ሬኒ ዳቪድ በረቂቁ ውስጥ የኦርቶዶክስን ልማዳዊ ህግ ‘ፍትሀ ነገስትን‘ እንደምንጭ እንደተጠቀሙበት ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 34/5 ስር እንደተደነገገው የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሀይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጎች መሰረት መዳኘት እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በመሆኑም ባህላዊ ወይም ልማዳዊ ህጎች እንደ አንድ የህግ ምንጭ ያገለግላሉ ማለት ነው፡፡

1.2. የክልል ህግ ምንጮች
i. የክልል ህገ መንግስት(state constitutions)
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 52/2 ስር እንደተደነገገው ክልሎች የራሳቸው ህጎች ማውጣት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ክልሎች የራሳቸው ህገ መንግስት ከፌደራል ህገ መንግስት ጋር በሚጣጣም መልኩ አውጥተዋል እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡ የክልል ህገ መንግስት በክልሎቹ ውስጥ የበላይ ህግ ነው፡፡
ii. የክልል አዋጆች (state proclamations)
የፌደራል ህገ መንግስት ክልሎች ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ የክልሎቹን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሰረት ለምሳሌ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና የደ/ብ/ብ/ህ ክልል የራሳቸው የቤተሰብ ህግ አውጀዋል፡፡
iii. የክልል ደንቦች እና መመሪያዎች (state regulations & directives)
የፌደራል ህገ መንግስት የክልል አስፈፃሚ ምክር ቤቶች በክልል ወሰን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ እንዲሁም ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣት እንደሚችሉ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡
2. የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws)
የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws) የህጎች የበላይነት ደረጃን ወይም የትኛው ህግ ከየትኛው ህግ የበላይ ህግ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ በአገራችን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ ድርጊት እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ይደነግጋል፡፡ ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ህገ መንግስቱ ነው ማለት ነው፡፡

የፌደራል ህገ መንግስት በፌደራልም ይሁን በክልል ደረጃ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ በመቀጠል የአገሪቱ የበላይ የህግ አውጪ አካል ማለትም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ህጎች ማለትም አዋጆች ይከተላሉ፡፡ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የህግ ተዋረድ በተመለከተ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም በህገ መንግስቱ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገረቱ ህግ አካል ይሆናሉ ስለሚል ከአዋጅ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ የሚል ሀሳብ አለ፡፡ በህግ ተዋረድ በመቀጠል የሚመጡት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጡት ደንቦች እና በሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚወጡት መመሪያዎች በቅደም ተከተል ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ተዋረድ (hierarchy) ላይ ባሉ ህጎች መካከል መቃረን ሲኖር ተፈፃሚ የሚሆነው በጊዜ ዘግይቶ የወጣው ህግ (latest prevails) ነው፡፡ ይህ ማለት ዘግይቶ የወጣው ቀድሞ ከወጣው ይልቅ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ልዩ ህግ (special law) ከጠቅላላ ህግ ይልቅ ቅድሚያ ተቀባይነት (special law prevails over general law) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
ተቋርጦ የነበረው የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በወረዳዎች መስጠት ጀምሯል
.
አገልግሎቱን ለማግኘትም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከሚኖሩበት ወረዳ መታወቂያውን ለማግኘት ወደሚያመሩበት ወረዳ የመሸኛ ማሰረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡
.
በአዲስ አበባ ከተማ ተቋርጦ የሰነበተው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያን የመስጠት አገልግሎት ከወረዳ ወረዳ በሚደረግ የመሸኛ አሰጣጥ ብቻ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኤጀንሲው ሰምቷል፡፡
.
በአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገና እና መረጃ ኤጀንሲ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ መላክ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በያዝነው ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ ምትክ እና እድሳት አገልግሎት በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ፡፡
.
ከዚሁ በተጨማሪ ተቋርጦ የሰነበተውና ከወረዳ ወረዳ በመሸኛ አማካኝነት ሲሰጥ የነበረው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በዛሬው እለት መጀመሩን ነግረውናል፡፡
.
ይሁን እንጂ ከክልል ከተሞች የሚመጡ መሸኛዎችን በመቀበል የሚሰጠው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ገና እንዳልተጀመረ የነገሩን አቶ መላክ አገልግሎቱን ከሳምንት በኋላ ለማስጀመር እየተሰራበት መሆኑን ነግረውናል፡፡
.
የውልሰው ገዝሙ
EthioFM
Forwarded from Yim.... Mi
if you have any information about 14th amhara national justice professionals trading and legal research institute exam result please inform us