አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ከህጋዊ ባልና ሚስት ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታቸው የግል እዳ ካለባቸው እዳው ከግል ንብረታቸው የሚከፈል ሲሆን የግል ንብረታቸው እዳውን ለመክፈል በቂ ካልሆነ ግን ከጋራ ንብረታቸው ላይ የሚከፈል ይሆናል፡፡
ልጆችን በተመለከተ አንድ ወንድ እና ሴት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት በሚኖሩ ወቅት የተረገዙ እና የተወለዱ ልጆች አባት ወንዱ ሴቷ ደግሞ እናት መሆናቸው የህግ ግምት ይወሰዳል፡፡ በእርግጥ ይህ የህግ ግምት በህክምና ወይም ሌላ አሳማኝ ማስረጃ በማቅረብ ቀሪ ሊሆን የሚችል ነው፡፡
3. ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት መኖር ግንኙነት ስለማቋረጥ
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ወንድ እና ሴት በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ግንኙነታቸው እንዲቋረጥ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት በህግ አግባብ ጋብቻ እንደፈጸሙ ሰዎች በሚለያዩበት ወቅት በፍርድ ቤት ቀርበው ፍቺ ማስወሰን ሳያስፈልጋቸው አብረው መኖር ማቆም እና ግንኙነታቸው ማቆም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ከሁለቱ አንዱ በሚሞቱ ጊዜ ይቋረጣል፡፡ ነገር ግን ግንኙነቱ የተቋረጠው በወንዱ እና/ወይም በሴቷ ፍላጎት ወይም በሁለቱ አለመጣጣም ሆነ በአንዳቸው ሞት ምክንያት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የመኖሩ ግንኙነቱ በሚቋረጥ ጊዜ ከጋራ ንብረት ላይ ድርሻቸው ለመካፈል ለፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ክፍፍል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
4. ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት የመኖር ግንኙነት ስለመኖሩ ለመስረዳት ስለሚቀርብ ማስረጃ
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ወንድ እና ሴት ከላይ በተገለጸው መሠረት ግንኙነታቸውን ማስረዳት አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ይህንን የሚያስረዱት “የግንኙነት ሁኔታ’’ እንዳለ በማስረዳት ነው፡፡ የግንኙነት ሁኔታ ማስረዳት ሲባል ወንድ እና ሴቷ ምንም እንኳን ጋብቻ ባይፈጽሙም ነገር ግን የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመዶቻቸው እና የሚኖሩበት ማህበረሰብ እንደተጋቡ ሰዎች ነው የሚኖሩት ብለው ሲገምቷቸው ነው፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ምክንያት እንደባልና ሚስት መኖር እንዳለ ማስረዳት የፈለገ ወገን የግንኙነት ሁኔታ መኖሩን በሰው ምስክር አሊያም ሌላ ሊያስረዳ ይቻላል የሚለው የሰነድ ማስረጃ ካለ ይህንን በማቅረብ ሊያስረዳ ይችላል፡፡ ማስረዳት የፈለገው ወገን በአሳማኝ ማስረጃ ይህንን ካረጋገጠ በወንዱ እና በሴቷ መካከል ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የመኖር ግንኙነት አለ ተብሎ የህግ ግምት ይወሰዳል፡፡ ይህንን የህግ ግምት ግን ማንኛውም አይነት አስተማማኝ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስ ወይም ግንኙነት እንደሌለ ማስረዳት ይቻላል፡፡
በሶስቱ የጋብቻ ሥርአት አይነቶች ከተፈጸመ ጋብቻ እና ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ከመኖር ግንኙነት ውጪ በወንድ እና ሴት መካከል ያሉ ግንኙነቶች በህግ በኩል ምንም አይነት ወጤት አይኖራቸውም፡፡

ታምሩ ያዕቆብ
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የጠበቆች ጉባዔ

የጠበቆች ጠቅላላ ጉባዔ የሚካሄድበት ቀን ጥር 15/2014 ነው፤
ቦታው ከሳዘንችስ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል (የቀድሞ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል)
ሰዓት፡ - ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ
በስብሰባው ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ነገር፦ የፌዴራል የጥብቅና ፈቃድ

በፌደራል ደረጃ የጥብቅና ፍቃድ ያላችሁ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ልክ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ጉባዔው የሚጀመር መሆኑን አውቃችሁ ቀደም ብላችሁ እንድትገኙ ሲል ፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር በጋራ መኖሪያና በንግድ ቤቶች ላይ ጥሎት የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ህትመት እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ
**
ዋዜማ ራዲ- የአዲስ አባ ከተማ አስዳደር በመሬት እና መሬት ነ አገልግሎት ላይ ጥሎት ከነበረው እገዳ መካከል፣ በኮንዶሚኒየም እና ንግድ ቤቶች ላይ የጣለውን የይዞታ ካርታ ህትመት እገዳን በማንሳት አገልግሎት እንዲጀመር አዘዘ።

የከተማ አስተዳድሩ ካቢኔ ካቢኔ ከነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አግዶት የቆየውን የመሬትና ይዞታ ነክ አገልግሎቶች በቅርቡ እንደሚያስጀምር ከጥቂት ሳምንታት በፊት መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት የከተማ አስተዳድሩ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀማል አልይ ፣ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በፃፉት ደብዳቤ የከንቲባ ፅህፈት ቤት የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ህትመት ላይ ጥሎት የነበረውን ዕግድ ማንሳቱን አስታውሰው ፣ ክፍላተ ከተሞቹ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ መመርያ መስጠታቸውን ዋዜማ ያገኘቸው ሰነድ ያሳያል፡፡

ሐላፊው የግብይት ስርዓቱና ልማት መስተጓጎል እንደሌለበት በመጥቀስ ለ 11 ክፍለ ከተሞች የተጻፈው ድብዳቤ የጋራ መኖሪያ ቤትና ንግድ ቤቶች ይዞታ ማረጋገጫ ህትመት የእዳ ማጣራት አገልግሎት እገዳ መነሳቱን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ቀሪ እግዶች በቅርቡ እንደሚነሱ የተገለጸ ሲሆን ከተማ አስተዳድሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ የህገወጥ የካርታ ድርጊቶች ተጋላጭነትን ያስቀራል የተባለለትን በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ አገልግሎት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

የቢሮ ሃላፊው በታህሳስ 2014ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በሰጡት መግለጫ ያላግባብ በየክፍላተ ከተሞች ተሠራጭተው የሚገኙ ካርታዎች ለሕገወጥ ወረራ ተጋላጭ እንዳይሆኑ 472 ሺሕ ካርታዎች ተለይተው መሰብሰባቸውንና ካርታዎቹ መምከናቸውን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
https://t.me/GudayAsfetsami
ጉዳይ አስፈፃሚ 🔷
(Guday Asfetsami)
https://t.me/GudayAsfetsami
ጉዳይ አስፈፃሚ 🔷
(Guday Asfetsami)
በዛሬው እለት በ15/05/2014 ዓ.ም በአዋጅ ጥቁር 1249/2013 አንቀፅ 57(1) መሠረት የተቋቋመው "የኢትዮጽያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር" ጠቅላላ ጉባኤ ወ/ሮ ስንዱ አለሙን ኘሬዘዳንት እንዲሁም አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸውን ምክትል ኘሬዘዳንት በማድረግ መርጧል።

የፍትህ ሚኒስቴር በህጉ በተደነገገው መሰረት ጉባዔውን በመጥራት የማህበሩ ፕሬዘዳንት እና ም/ል ፕሬዘዳፈንት እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት እንዲመረጡ በማድረግ ጉባዔውን ለማሳካት ያደረገው ጥረት በስኬት ተጠናቋል።
!
በተመሳሳይ ጠቅላላ ጉባኤው 7 /ሰባት/ የስራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል።
በዚህም መሠረት:-
1. ሂሩት መለሠ; 634
2. ፊሊጶስ አይናለም; 628,
3. ሊቁ ወርቁ; 522,
4. ዮሴፍ አዕምሮ;514,
5. ሆሳና ነጋሽ; 492,
6. ትደነቂያለሽ ተስፋ;424,
7. ሰለሞን እምሩ; 418,
የስራ አስፈጻሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ዝርዝር ዜናውን ይዘን እንቀርባለን።
ፍርድ ቤት እና ስነ_ስርዓቱ..❗️❗️🙏
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Legal Officer – 4 Positions at Berhan Insurance S. C

Company: Berhan Insurance S. C

Location: Ethiopia

State: Addis Ababa Jobs

Job type: Full-Time
Job Description

JOB REQUIREMENT

Educational Qualification: BA in Law, Law in Corporate Governance, LLM in Business Regulation and other related fields from a recognized University or College.

Experience: Minimum of 3 years of relevant work experience


Method of Application

Submit your CV, copies of relevant documents and Application as a single PD file to  hr@berhaninsurance.com
Use the title of the position as the subject of the email

Closing Date : 24 January. 2022
https://t.me/LawyerEthiopia
@LawyerEthiopia
የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ

በ97 ምርጫ ምክንያት ተጠሪነታቸው ለፌዴራል የተደረጉት የትራንስፖርት ቢሮዎች ለከተሞቹ ይመለሳሉ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የክልል መለያ በተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መራ፡፡
ምክር ቤቱ የተወያየበት ረቂቅ አዋጅ ከተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመርያና መመዝገቢያ አዋጅ ጋር በአባሪነት ተያይዞ ያለውን ሰንጠረዥ ይሽራል፡፡
በዚህ ረቂቅ አዋጅ የሚሻረው ሰንጠረዥ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶችና ምልክቶችን በዝርዝር የደነገገ ሲሆን፣ እንደ ተሸከርካሪዎቹ አገልግሎት የሚኖራቸውን ቀለምና መለያ አስቀምጧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰንጠረዡ እንደ አአ፣ ኦሮ፣ አማ፣ ደሕ እና ሌሎች አሥራ ሁለት የክልልና ከተማ አስተዳደሮችን የሚወክሉ ምህፃረ ቃሎችን ዘርዝሮ፣ ተሽከርካሪዎቹ እንደ ተመዘገቡበት ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ሰሌዳቸው እንዲሠፍር ያዛል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሁን ያዘጋጀው የመንገድ ትራንስፖርት አዋጅ፣ ይኼንን አሠራር በማስቀረት ወጥነት ያለው ብሔራዊ የተሽከርካሪ ሰሌዳ አሠራር ለመዘርጋት አልሟል፡፡ በሚኒስቴሩ የሕግ አማካሪ አቶ አበጀ ማሞ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ለተወካዮች ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ የክልል መለያ የያዙ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ተግባራዊ የሚሆኑት አዲስ ብሔራዊ ሰሌዳ ይፋ እስኪደረግ ብቻ ነው፡፡
እንደ አማካሪው ገለጻ፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የፈረመችው እ.ኤ.አ. የ1968 ‹‹የቬዬና የመንገድ ትራፊክ ኮንቬንሽን››፣ ፈራሚ አገሮች ብሔራዊ ደረጃን የያዘ መለያ በአገሮች ውስጥ ለሚገኙ ተሽከርካሪዎች እንዲሰጡ ያዛል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመርያና መመዝገቢያ አዋጅ ላይ የተቀመጠው አሠራር ክልሎች የየራሳቸውን መለያ የያዘ ሰሌዳ እንዲሰጡ እንጂ፣ ወጥነት ያለው አገር አቀፍ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ተግባራዊ እንዲደረግ አይፈቅድም፡፡ ‹‹ተሽከርካሪ ዓለም አቀፍ ቁስ ነው፣ አንድ መኪና ከዚህ ተነስቶ ኬንያም ሆነ ሱዳን ሲሄድ የአገሮቹ መንግሥት ግራ ሊጋቡ አይገባም፤›› ያሉት አቶ አበጀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ተግባራዊ የሚደረገው የሰሌዳ ዓይነት የሚገልጸው ተሽከርካሪነታቸውን ብቻ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስመዘገበችው የተሽከርካሪ ሰሌዳ መለያ ኢት (ETH) የሚል መሆኑን አቶ አበጀ አስረድተዋል፡፡ ይሁንና አሁን ባለው አሠራር መሠረት ይኼ መለያ ያለበት የተሸከርካሪ ሰሌዳ የሚያገኙት ንብረትነታቸው የፌዴራል መንግሥት የሆኑ፣ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎችን የሚያገናኝ የንግድ የመንገድ ማመላለሻ ሥራ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ይኼ ረቂቅ አዋጅ፣ የክልል መለያ በሰሌዳዎች ላይ እንዲኖር የሚያዘውን አባሪ እንዲሻር ቢያደርግም፣ በቀጣይ የሚኖረውን የሰሌዳ ዓይነት አይደነግግም፡፡ ‹‹ምን ዓይነት ሰሌዳ ይደረግ?›› የሚለው ከአዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚደረግ ጥናት እንደሚወሰን ያብራሩት የሕግ አማካሪው፣ ሰሌዳው ግን ‹‹የኢትዮጵያ ሰሌዳ›› እንደሚባል አስታውቀዋል፡፡
አቶ አበጀ አሁን ባለው የሰሌዳ አሠራር ምክንያት ተሸርካሪዎች ከክልል ወደ ክልል ሲንቀሳቀሱ ‹‹ሥጋት›› እና ‹‹ፍራቻ›› በውስጣቸው ሊፈጠር እንደማይገባ ገልጸው፣ አሁን ባለው የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ይኼንን ዓይነቱን ችግር መፍቻ አንዱ መፍትሔ ብሔራዊ ሰሌዳን መተግበር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ይሁንና የተሽከርካሪ ሰሌዳው ከየት እንደወጣ ወይም የት እንደተመዘገበ የሚገልጽ መለያ ሙሉ ለሙሉ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ የሕግ አማካሪው ጠቁመው፣ ነገር ግን ወደፊት በሚወጣው አዲስ አተገባበር ሰሌዳው የወጣበትን ቦታ የሚገልጸው መለያ የሚቀመጠው ‹‹በተቻለ መጠን›› የትራፊክ ፖሊሶችና የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች ብቻ እንዲያውቁት በሚያስችል መንገድ ነው ብለዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ በውስጡ ስለ ‹‹ሽግግር ጊዜ›› የሚያትት አንቀጽ እንዳለው ያስረዱት አቶ አበጀ፣ በዚህ መሠረት በሚኒስቴሩ የሚከናወነው ጥናት ተጠናቆ አዲስ አሠራር እስኪተገበር ድረስ ነባሩ አሠራር ተግባራዊነቱ እንዲቀጥል ያዛል ብለዋል፡፡ አዲሱ አሠራር መተግበር ሲጀምር ክልሎች በአዲሱ አሠራር መሠረት የተሽከርካሪ ሰሌዳዎችን መስጠት እንደሚቀጥሉ ተነግሯል፡፡
የመንገድ ትራንፖርት ረቂቅ ከዚህም ተጨማሪ ለውጦችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፣ አንደኛው ጉዳይ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ትራንስፖርት ቢሮዎችን የሚመለከት ነው፡፡ የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኢሕአዴግ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ በአዲስ አበባ ከተሸነፈ በኋላ፣ አዲሱ ፓርላማ ከመግባቱ በፊት ያወጣቸው ሕጎች እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ አበጀ፣ ከእነዚህ ሕጎች መካከል የትራንፖርት አዋጅ አንዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በጊዜው የወጣው አዋጅ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የትራንፖርት ቢሮ ተጠሪነታቸው ለፌዴራል መንግሥት ሆኖ፣ ራሳቸውን የቻሉ ቢሮዎች ሳይሆን ቅርንጫፍ እንዲሆኑ የሚያዝ ነበር፡፡
አሁን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ይኼንን ሕግ ሽሮ የከተማ አስተዳሮቹ ትራንስፖርት ቢሮዎች ራሳቸውን ችለው የከተማ አስተዳደሩ አንድ መዋቅር እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ ትራንፖርት ቢሮ አሁንም የፌዴራሉ ቅርንጫፍ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ግን ሕጉ ሳይሻሻልም የራሱን ትራንስፖርት ቢሮ ከፍቶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የሚኒስቴሩ የሕግ አማካሪ አስረድተዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ሲፀድቅ ለአዲስ አበባ ትራንፖርት ቢሮ ሕጋዊ መሠረት ይሰጠዋል ተብሏል፡፡
ተቋርጦ የቆየው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን ከሰኞ ጥር 23/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀምር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
አገልግሎቱ ከሰኞ ጥር 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን አገልግሎቱ ተገልጋዮች በትዕግስት ስለጠበቁት ምስጋና አቅርቧል፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት እና የተቋሙን ድረ-ገጽ www.dars.gov.et በመጠቀም ተቋሙ ባዘጋጀው የonline አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም በመሙላትና ሲስተሙ የሚሰጠውን የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በመያዝ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን ተናግሯል፡፡
ShegerFM
https://t.me/GudayAsfetsami
ጉዳይ አስፈፃሚ 🔷
(Guday Asfetsami)
https://t.me/GudayAsfetsami
ጉዳይ አስፈፃሚ 🔷
(Guday Asfetsami)
በአዲሱ የንግድ ሕግ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ጥበቃ ምን ይመስላል?
በንግድ ማኅበራት አስተዳደር ውስጥ ከሚጠቀሱት ጉዳዮች አንዱ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት ጥበቃ ነዉ፡፡ ሕግ በተለይም የንግድ ሕግ የባለአክሲዮኖችን መብትና ግዴታ ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንደሆነ ሁሉ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብትንም የሚጠብቅ መሆን አለበት፡፡ ሀገራት ለአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት ማስጠበቂያ ደንቦችን በንግድ ሕጎቻቸዉ ያካትታሉ፡፡ በሀገራችን አዲሱ የንግድ ሕግ ከተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ጥበቃ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች ምንነት እና በንግድ ማህበራት እንቅስቃሴ ውስጥ ለእነዚህ ባለአክሲዮች የሚጠበቁ መብቶች ተዳሰዋል፡፡

1. የአነስተኛ ባለአክስዮኖች ምንነት
በንግድ ማኅበራት አስተዳደር ዉስጥ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች የሚለዉ ሐረግ አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም የለዉም፡፡ አንድ ባለአክሲዮን ብቻዉን አነስተኛ ባለአክሲዮን ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻዉን የንግድ ማኅበር ከግማሽ በላይ አክሲዮኖች የያዘ አንድ ባለ አክሲዮን ደግሞ ከፍተኛ (አብላጫ) ባለአክሰዮን ይሆናል፡፡ በተቃራኒዉ ደግሞ ከግማሽ በታች ያላቸዉ ብዙኃን ባለአክሲዮኖች በድምፅ ከተበለጡ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የሀገራችን የንግድ ህግ ሲታይ በተለያዩ ክፍሎች ዉስጥ አነስተኛ ባለ አክሲዮኖች የሚለዉን ሀሳብ እንደ አዉዱ በተለያየ መንገድ ይፈታዋል፡፡ በአብዛኛዎቹ ክፍሎች ዉስጥ ከጠቅላላ ካፒታል አሥር በመቶ (10%) ያላቸዉን እንደ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ሲወስድ በአንዳንድ ክፍሎች ቢያንስ ሃያ በመቶ (20%) ያላቸዉን እንደ አነስተኛ ባለአክሲዮን በመዉሰድ ለመብት ማስጠበቂያ ድንጋጌዎች መፈጸም እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል፡፡ በሌሎች ድንጋጌዎች የአክስዮን መጠን ሳይጠይቅ ማንኛዉም ባለአክስዮን እንደ አነስተኛ ባለአክሲዮን የሚበቅባቸዉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ አነስተኛ ባለአክሲዮን ማለት በማኅበሩ ያላቸዉ የአክሲዮን ድርሻ ከግምሽ በታች የሆነ ወይም ዝቅተኛ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ማለት ነዉ፡፡

2. አነስተኛ ድርሻ ላላቸው ባለአክሲዮኖች የሚደረግ የሕግ ጥበቃ እና የጥበቃው መነሻ
እንደ ሀገራችን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሰዎች ለኢንቨስትመንት የሚሆን ተቀማጭ ገንዘብ ስለማይኖራቸው ዜጎች ያላቸውን ውስን ሀብት አስተባብሮ ወደ ሥራ ማስገባት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ እንዲሳካ ደግሞ ዜጎች የቆጠቡትን ትንሽ ገንዘብ በንግድ ማኅበር ውስጥ ካስገቡ በኋላ ለምዝበራ እንዳይዳረጉ የሚከላከል ስርዓት መኖር አለበት።

የቀድሞዉ የንግድ ሕጋችን በማኅበራት ውስጥ አነስተኛ ድርሻ ይዘው የሚገቡትን ባለሀብቶች ከዘረፋ፣ ካልተገባ ጫና ወይም በደል ለመታደግ ያለሙ ድንጋጌዎች በበቂ ሁኔታ አላካተተም። አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 364 ይህን ሁኔታ ለመለወጥ እና አነስተኛ ድርሻ ያላቸውን የኩባንያ አባላት ከምዝበራ እና ኢፍትሃዊ አሰራር ለመጠበቅ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን አካቷል። በዚህ ረገድ ሕጉ ያደረጋቸው ለውጦች በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው። እነዚህም፡-
1. ግልጽነትን ማስፈን፡- አንድ ኩባንያ ከኩባንያው ጋር ዝምድና ካላቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር ስለሚያደርጋቸው ውሎች አነስተኛ ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች የተሟላ መረጃ እንዲያገኙ እና የጥቅም ግጭትን ለማስወገድ የሚረዱ በርካታ ድንጋጌዎች በህጉ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን አንቀጽ 323፣ 324፣ 325፣ 406፣ 392፣ 393፣ 396፣ 503 እና 504ን መጥቀስ ይቻላል።

2. ተጠያቂነትን ማስፈን፡- የንግድ ማኅበር ሥራ አመራር በተለይ የዳይሬክተሮችን ኃላፊነት በማያሻማ መልክ የሚያስቀምጡ እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍኑ አሰራሮችን ለመዘርጋት ያለሙ በርካታ ድንጋጌዎች በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ተካተዋል። በዚህ ረገድ አዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 308፣ 326፣ 327፣ 329፣ 339፣ 366(1)(2)፣ 367(2) 400 እና 406 ተጠቃሽ ናቸው።


3. በሥራ አመራር ውስጥ የማኅበርተኞችን ተሳትፎ ማጎልበት፡- አዲሱ የንግድ ሕግ ማኅበርተኞች በንግድ ድርጅታቸው አመራር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚደነግጉ በርካታ ድንጋጌዎችን ተካተዋል፡፡ በዚህ ረገድ አዲሱ ሕግ አንቀጽ 312(3)፣ 316፣ 354፣ 362፣ 405፣ 406፣ 453፣ 520 እና 529ን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። እያንዳንዱ የአክሲዮን ማኅበር ድረ-ገጽ እንዲኖረው እና በድረ-ገጹም ላይ የማኅበርተኞችን ንቁ ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚረዱ መረጃዎች እንዲሰጥ የሚደነግጉት አንቀጽ 492-494 ይህን ያሳያሉ።

3. የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ማስጠበቂያ መንገዶች
የንግድ ሕጉ ያስቀመጣቸዉ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ማስጠበቂያ ድንጋጌዎች በሁለት ዓይነት ሊታዩ የሚችሉ ሲሆኑ አነዚህም ጉዳትን ተከላካይ /Preventive/ እና የማስተካከያ /restorative/ ናቸዉ፡፡ ጉዳት ተከላካይ ድንጋጌዎች አነስተኛ ባለአክስዮኖች ላይ የመጨቆን ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ውሳኔዎችን ከመወሰናቸዉ በፊት አነስተኛ ባለአክስዮኖች እንዲሰማሙ በመደንገግ ዉሳኔዉን ከመፈፀም እንዲያግዱት ያስችላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የማስተካካያ ድንጋጌዎች ጉዳት ከደረሰ በኋላ የማስተካከያ መንገዶችን ይደነግጋሉ፡፡ ለምሰሌ በፍርድ ቤት ከሶ ካሳ የማስከፈል መብት ከእነዚህ የሚመደብ ነዉ፡፡ ከጉዳት በኋላ በፍርድ ቤትም ይሆን በአስተዳደራዊ መንገድ ማስተካከል ከባድ ስለሚሆን ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከማስተካከል የተሻለ ይሆናል፡፡

ማንኛዉም የድምፅ የበላይነትን በመጠቀም ከፍተኛ ባለአክስዮኖች አነስተኛ ባለአክስዮኖችን አግልለዉ የማኅበሩን ሀብት ለግላቸዉ የሚጠቀሙበት አሰራር በአነስተኞች ላይ በደል ማድረስ ነዉ፡፡ አነሰተኛ ባለአክስዮኖች በኩባንያዉ ጉዳዮች ላይ እንዳይሳተፉ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የሚያገል አሰራር የባለአክስዮኖችን መብት የሚጥስ ነዉ፡፡ ለአነሰተኛ ባለአክስዮኖች የመብት ጥሰቶች ህጎች የተለያዩ ዓይነት መፍትሔዎች የሚሰጡ ሲሆኑ አንዳንዶቹ በቀጥታ የመክሰስ (የማስተካከያ እርምጃ የመዉሰድ) መብት ሲሰጡ ሌሎች ደግሞ በተዘዋዋሪ ይከለክላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕግ በአብዛኛዉ ለእንደነዚህ ያሉ የመብት ጥሰቶች የሚሰጠዉ ከአሁን በፊት ያለዉ ተዘዋዋሪ ነበር፡፡ በአዲሱ የንግድ ሕግ ግን በቀጥታ የመክሰስ (የማስተካከያ እርምጃ የመዉሰድ) መብትን ሰጥቶ እናገኘዋለን፡፡ በአብዛኛዉ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ በጉባዔዉ የመብት ጥሰት ያስከተሉ ዉሰኔዎችን ዉድቅ ማስደረግ ወይም በዳይሬክተሮች ቦርድ አማካኝነት ጉዳት በማኅበሩ ላይ ደርሶም ከሆነ እንዲከሰሱ በጠቅላላ ጉባዔዉ አሰወስኖ መክሰስ ነዉ፡፡

4. የጉባዔ አካሄድ እና የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት
በጠቅላላ ጉባዔ አካሄድ ድንጋጌዎች ዉስጥ የአነስተኛ ባለአክስዮኖችን መብት የሚያስጠብቁት አሰራሮች በብዙ ሕጎች ሰፍረዉ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ በደብዳቤ በድምፅ የመስጠት መብት፣ ጉባዔ በሚደረግበት ጊዜ አክስዮንን በማኅበሩ የማስቀመጥ ግዴታ አለመኖር፣ የድምር ድምፅ /Commulative Voting/ አሰራር እና አንድ አክስዮን አንድ ድምፅ የሚለዉ አሰራር በንግድ ህጋችን በቁጥር 383 (2) ስር ተመልክቷል፡፡ ይህ ንዑስ ቁጥር እያንዳንዱ አክስዮን አንድ ድምፅን ይሰጣል ይላል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ዓላማ የተወሰኑ አክስዮኖች እጥፍ ድምፅ የሚያስገኙ፣ የሌሎች ደግሞ አንድ፣ የከፊሎቹ ግማሽ ወዘተ… በሚል ዓይነት ልዩነት እንዳይፈጠር ለመከላከል ነዉ፡፡ ስለዚህ በአንዳንድ አባላት
የተለየ ድምፅ የሚያስገኝ ልዩ አክስዮን ሊኖራቸዉ አይችልም፡፡ በቦርድ አባላት ምርጫ ወቅት የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ማስጠበቂያ አሰራር የድምር ድምፅ አሰራር ነዉ፡፡ ይህ ግን በሕጋችን በግልፅ የተቀመጠ ደንብ አይደለም፡፡ ነባሩ ንግድ ሕግ ቀጥር 352 ስለተመጣጣኝ ዉክልና የሚናገር ሲሆን በግልፅ የድምር ድምፅ አሰራር ግን አይደነግግም፡፡

ሌላዉ ከጠቅላላ ጉባዔዉ ዉሳኔ ጋር በተዘዋዋሪ የሚያያዘዉ እና የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር የሚችል ጉዳይ አዳዲስ አክስዮኖች ሲወጡ እያንዳንዱ አባል ባለዉ ድርሻ መጠን የመግዛት መብት ነዉ፡፡ ይህ በቁጥር 345 (4) እና በቁጥር 470(1) ላይ የተቀመጠ መርህ ነዉ፡፡ የዚህ መርህ ዓላማ በማኅበሩ ዉስጥ ያለዉን የይዞታ ስብጥር ማስጠበቅ ሲሆን ጠቃሚነቱ በማኅበሩ ዉስጥ ያለዉ የኃይል ሚዛን እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡

5. አነስተኛ ባለአክስዮኖች ከኦዲትና ቁጥጥር አንፃር ያላቸዉ መብቶች
ከኦዲት ሥራ ጋር የተያያዘ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብቶች በአዲሱ የንግድ ሕግ ዉስጥ ተካተዋል፡፡ እነዚህም በቁጥር 343(2) እና በቁጥር 355 ላይ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ናቸዉ፡፡ "ከማኅበሩ ዋና ገንዘብ ዉስጥ ቢያንስ 20% ያለዉ ባለአክስዮን (ባለአክስዮኖች) ራሳቸዉ የመረጡትን የውጭ ኦዲተር መሾም ይችላሉ" በማለት የአነስተኛ ባለአክስዮኖች የራሳቸዉን ኦዲተር የመሾም መብት እንዳላቸዉ ይናገራል፡፡ ይህን መብት አነስተኛ ባለአክስዮኖች ከተጠቀሙበት በማኅበሩ ዉስጥ ቢያንስ ሁለት ኦዲተሮች (በጠቅላላ ጉባዔዉ የሚሾምና በአነስተኛ ባለአክስዮኖች የሚሾም) ይኖራሉ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ኦዲተሮች ለዳይሬክተሮች ወይም ለአብላጫ ባለአክስዮኖች በመወገን ሊፈጠሩ የሚችሉትን አደጋ ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቁጥር 355 ላይ ነፃ ኦዲተር እንዲሾም ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም አግባብ ያለዉ ሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ማመልከቻ ስለማቅረብ ይናገራል፡፡ የማኅበሩ ሥራ አመራር አነስተኛ የአክስዮን ድርሻ ያላቸዉን ማኅበርተኞች ወይም ማኅበሩን በሚጎዳ አኳኋን መከናወንና አለመከናወኑን መርምረዉ ሪፖርት የሚያቀርቡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ኤክስፐርቶች መሾም አለበት፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ከማኅበሩ ካፒታል አስር በመቶ (10%) ያለዉ (ያላቸዉ) ባለአክስዮኖች ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴሩ አቤቱታ ማቅረብና ማኅበሩ ኦዲት እንዲረግ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ከኦዲት ስራ ጋር የተያያዙ የአነስተኛ ባለአክስዮኖች መብት ቀላል አይደሉም፡፡ በማኅበሩ አስተዳዳሪዎች ወይም በከፍተኛ ባለ አክስዮኖች የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰት ለመግታት እና መብታቸውን ለማስከበር አጅግ ጠቃሚ ናቸዉ፡፡

6. አክስዮን ሸጦ የመውጣት የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 292 መሰረት የማህበሩን ዋና ገንዘብ ዘጠና በመቶ የሚወክለ አክስዮኖች በአንድ ጊዜ በማህበርተኛ የተያዙ እንደሆነ አነስተኛ ባለአክስዮኖች ማህበርተኛው አክስዮኖቻቸውን እንዲገዛቸው የመጠየቅ መብት አላቸው። ጥያቄ አቅራቢው ባአአክስዮን አክስዮኖቹ ስለሚገዙበት ሁኔታ በተለይም የአክስዮኖቹን ዋጋ የንግድ ሕግ ስለወሰነበት መንገድ መረጃ ከጥያቄው ጋር ማቅረብ አለበት። ጥያቄ የቀረበለት ማህበርተኛ የቀረበለትን ዋጋ ያልተቀበለ እንደሆነ ማህበሩ በተመዘገበበት ቦታ ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የአክስዮኖቹን ዋጋ የሚወስን ባለሞያ መሾም አለበት። አክስኖቹን ለመሸጥ ጥያቄ ያቀረበው ባለአክሲዮን የአክሲዮኖቹን ዋጋ ለመወሰን የወጣውን ወጪ መሸፈን አለበት። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አክስዮን እንዲገዛ ጥያቄ የቀረበለት ማህበርተኛ የሰጠው ዋጋ ተማኙ ባለሞያ ከወሰነው ያነሰ እንደሆነ ወጪውን በከፊል ወይም በሙሉ እንዲሸፍን ፍርድ ቤቱ ሊያዘው ይችላል፡፡

በአጠቃላይ የአነስተኛ ባለአክሲዮኖች መብት መጠበቅ የማኅበሩን ህልውና መጠበቅ ነዉ፡፡ ይህም የማኅበሩን መልካም አስተዳደር የተሳካና የንግድ አላማውን ዉጤታማ ያደርገዋል፡፡ በዚህ የተነሳ አነስተኛ ባለአክስዮኖች ከሌሎች ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ባለአክስዮኖች፣ ከዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ከጠቅላላ ጉባዔዉ እና በአዲተሮች አማካኝነት ከሚሰነዘሩ ያልተገቡ ጫናዎችና የመብት ጥሰቶች መጠበቂያ መንገዶች በአዲሱ የንግድ ሕግ ተደንግገዉ ይገኛሉ፡፡
ፍትህ ሚኒስቴር
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties