አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የዳይሬክቶች ቦርድ አባላት የወንጀል ተጠያቂነት
የንግድ ማኅበር ዳይሬክተሮች የተሰጣቸዉን ኃላፊነት በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩ ወይም የማኅበሩን ጥቅም በሚፃረር እና በሚጎዳ ሁኔታ ቢሰሩ ከሚኖርባቸዉ ፍትሐብሔራዊ ኃላፊነት በተጨማሪ የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል፡፡ ሥራዉን እንዲመራ በሕግ ወይም በዉል ግዴታ የተቀበለ ሰዉ (የንግድ ማኅበር አስተዳዳሪ) በተሰጠዉ ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል ወይም የተጣለበትን ግዴታ ባለመፈጸም በሚጠብቀዉ (በሚያስተዳድረዉ) የንብረት ጥቅም ላይ ወይም በድርጅት አገልግሎት ላይ አስቦ ጉዳት ካደረሰ እንደነገሩ ክብደት በቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ በኢፊዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 702 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ አስተዳዳሪዉ ጥፋቱን የፈፀመዉ በቸልተኝነት የተፈፀመ ከሆነ በመቀጮ ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡ አስተዳዳሪዉ ጥፋቱን የፈፀመዉ የንብረት ጥቅም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት አስቦ ከሆነ ደግሞ ቅጣቱ ከአንድ ዓመት ያላነሰ ቀላል እስራት ሆኖ ከብር ከብር ሰላሳ ሺህ የማይበልጥ መቀጮ በተጨማሪ ይወሰንበታል፡፡ እንደሁኔታዉ የቅጣቱ መጠን ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል በወንጀል ሕግ በዝርዝር ተገልጧል፡፡ ጥፋቱ ከወንጀል ሕጉ በተጨማሪ ከነገሩ ጋር አግባብነት ባላቸዉ ሌሎች አዋጆችም ሊታይ ይችላል፡፡

በማኅበሩ ውስጥ የማታለል ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ የተወሰኑ ባለአክሲዮኖችን መብት የሚጎዳ ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ ሕገወጥ የሆነ ወይም የማታለል ድርጊት ያለበት አሠራር በማኅበሩ ውስጥ ያለ እንደሆነ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወይም ሌላ ሥልጣን ያለው አካል ምርመራ ሊያደርግና የአስተዳደር ወይም የወንጀል ክስ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግም በሕግ ወይም በውል ሥራ እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ኃላፊነቱን ሳይወጣ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ከተረጋገጠ እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ 50,000 ብር በሚደርስ መቀጫ ሊቀጣ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ አዲሱ የንግድ ሕግ ውስጥ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በእጅጉ የገዘፈና ኃላፊነቱም የግል ሀብትና ንብረት ድረስ የሚመጣ፣ ለእስራት የሚዳርግ ስለሆነ ኃላፊነቱን የሚወስዱ ሰዎች ዝርዝር ጉዳዩን አውቀው ወደ ሥራው እንዲገቡ እናስገነዝባለን፡፡
👍2
የፌዴራል_የፍትህ_እና_ሕግ_ኢንስቲትዩት_የቅድመ_ሥራ_ሠልጣኞች_የኪስ_ገንዘብ_አከፋፈል_እና_የጥቅማጥቅም.pdf
195 KB
የፌዴራል የፍትህ እና ሕግ ኢንስቲትዩት የቅድመ-ሥራ ሠልጣኞች የኪስ ገንዘብ አከፋፈል እና የጥቅማጥቅም አሰጣጥ መመሪያ
👍3
ከባንክ በሳምንት ከ5 ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ተነሳ!

ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

“የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃ
👍3
ጋብቻ በሚፈርስበት ወቅት የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ሥነ-ሥርዓት ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ

በ፡ ሙሉቀን ሰይድ

በዚህ አጭር ጽሁፍ የጋራ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ አከራካሪ ከሆኑ ጉዳዩች መካከል የትኞቹ ንብረቶች የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት ይባላሉ፤ ተጋቢዎቹስ ምን ያህል ምጣኔ ድርሻ በንብረቶቹ ላይ ይኖራቸዋል፤ የጋር ንብረት ክፍፍል ጥያቄስ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባዋል የሚሉ ነጥቦችን የፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ እና ከተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔ አንጻር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2018-procedures-of-partition-of-common-property-after-divorce
ስለ ኑዛዜ ከውርስ ሕግና ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ
በ፦ ሙሉቀን ሰይድ ሀሰን

የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ ኑዛዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም ባይኖርም አንድ ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር የሚያስቀምጡ የሕግ ድንጋጌዎችን ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 857 እስከ 908 ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡

በዚህ ጽሁፍ ኑዛዜ በምን አግባብ ቢደረግ በሕግ ዘንድ ውጤት ይኖረዋል፤ በውርስ ሕጋችን ላይ የተቀመጡት የኑዛዜ አደራረግ ስርዓቶች አስገዳጅነታቸው እስከምን ድርስ እንደሆነና ኑዛዜ በፍርድ ቤት ቢጸድቅ ሊያስገኝ የሚችለው ውጤትና ባለመጽደቁ የሚያመጣው ተጽእኖ ምን እንደሆነ ከውርስ ሕግ እና አስገጋጅ ከሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔዎች አንጻር በአጭሩ ዳሰሳ ለማድርግ ተሞክሯል፡፡
መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2003-wills-presented-with-succession-laws-and-cassation-decisions
ስለጉዳዩ በዝርዝር የሚጠየቁትን ትተን የሚከተሉትን አሰልቺ ጥያቄዎች ለመመለስ መዘጋጀት አለብዎት፦

ክሱ ለምን እዚህኛው ፍርድ ቤት ሆነ? ለምን የዳኝነት ይከፈላል? ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት እንደጠበቃ ገንዘብ ይቀባለል? አይቀንስም? ይህንን ክፍያ በኋላ ፍርድ ቤቱ ይመልስልኛል? ስንት ዳኞችና ናቸው ጉዳዩን የሚያዩት? በስንት ጊዜ ውሳኔ ይሰጣሉ? ውሳኔ የሚሰጥበት ቁርጥ ያለ ጊዜ ልትነግረን ትችላለህ? ከዳኞችም ሱፍ ለምን አይለብሱም? ለምን ዳኛው ቢሮ ውስጥ ጠራህ/አስተናገደህ? ፍርድ ቤቶች ሽንት ቤት የላቸውም? ፍርድ ቤቱ የቀጠረን ሰዓት ለምን አያከብርም? ለምርመራ ምን ማለት ነው? አሁንም ቀጠሮ? ቃል ክርክር ምን ማለት ነው? አዲስ ማስረጃ ማስገባት አይቻለም? ለምን ዳኛው ጋር ሔደን በዝርዝር ጉዳዩን እንዲረዳ አናደርገውም? ጉዳዩን የሚያየው አንድ ዳኛ ብቻ ነው? ለምን ሌሎች ዳኞች አላዩትም? ችሎት ጸሐፊ ምንድነው? ሬጂስትራርስ? አቤቱታ ምንድነው? የአቤቱታ ቀን ለምን ሁሉ ጊዜ አይሆንም? ጠበቆች ለምን ፕሮቶኮል አይጠብቁም? ጠበቆችም እንደባለጉዳይ ነው ሚታዩት? ጠበቃዬ እስከሆንክ ለምን ይህንንም ጉዳይ አታማክረኝም? ከተከራካሪ ወገን ጠበቃ ጋር ለምን ትነጋገራለህ? ጉዳዩን ለምን በዝርዝር ለፍርድ ቤቱ አልተናገርክም? ሌላኛው ጠበቃ ሁለቴ ተናግሮ አንተ አንድ ጊዜ ብቻ ለምን ተናገርክ? ስልክህን ለምን አታነሳም? በፈለኩህ ጊዜ ላገኝህ አልቻልኩም፥ ምን ይሻላል? ………. ወዘተ

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2019-four-types-of-clients-group-one
👍2
ሆልዲንግ ካምፓኒ በአዲሱ የንግድ ህግ

መግቢያ

እስከቅርብ ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የሀገራችን የንግድ ህግ (ኮድ) አዋጅ ቁጥር 166/1952 ስድስት መጽሐፍት የነበሩት ሲሆን ስለነጋዴዎችና ስለንግድ መደብሮች፣ ስለ ንግድ ማህበሮች፣ ስለማጓጓዝ ስራና ስለ ኢንሹራንስ፣ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችና የባንክ ስራዎች፣ የኪሳራና መጠበቂያ ስምምነት እና መሻጋገሪያ ህግን ያካተተ ነበር፡፡ አዲሱ የንግድ ህግ/ኮድ በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 ሆኖ ሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ስራ ላይ ውሏል፡፡ ይህ የንግድ ህግ በይዘቱ በሶስት መጽሐፍት የተከፋፈለ ሲሆን እነዚህም መጽሐፍ አንድ ስለነጋዴዎች፣ የንግድ ስራዎችና ስለ ንግድ መደብሮች፣ መጽሐፍ ሁለት ስለ ንግድ ማህበራት፣ እና መጽሐፍ ሶስት ስለቅድመ ጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር፣ መልሶ የማደራጀት እና የመክሰር ህግ ናቸው፡፡

በኩባንያዎች መካከል የሚፈጠረው ዝምድና አንዱ ኩባንያ በሌላው ኩባንያ ከፍያለ የአክሲዮን ድርሻ በሚኖረው ጊዜ ወይም አንድ ባለሀብት በተለያዩ ኩባንያዎች ትልልቅ የአክሲዮን ድርሻ በሚኖረው ጊዜ የሚፈጠር ነው፡፡ ይህም የኩባንያዎች ቡድን የሚፈጥር እና ግንኙነቱም የእናት እና የተቀጥላ ኩባንያ ወይም የእህት ኩባንያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ይህን መሰል ግንኙነት በተለይም ከፍያለ የአክሲዮን ድርሻ የሚይዝ ሆልዲንግ ኩባንያ በተመለከተ በዚህ ፅሁፍ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡

ትርጓሜዎች

በንግድ ህጉ የተሰጡ ትርጓሜዎች መሰረት የንግድ ማህበራት ቡድን ማለት የእናት ኩባንያ እና ተቃራኒ ድንጋጌ እስከሌለ ድረስ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የተመዘገቡ የሁሉም ተቀጥላዎች ማህበራት ስብስብ ነው፡፡ ሆልዲንግ ካምፓኒ ማለት ደግሞ በቀጥታ ራሱ ምርትና አገልግሎት ባያቀርብም በዚህ ተግባር በተሰማሩ ሌሎች የንግድ ማህበራት ውስጥ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ ድርሻ የሚይዝ ኩባንያ ማለት እንደሆነ በንግድ ህጉ አንቀፅ 9 ተመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል እናት ኩባንያ ማለት በቀጥታም ሆነ በሌላ ኩባንያ አማካኝነት በተዘዋዋሪ ሌላ ኩባንያን በቁጥጥር ስር ያደረገ ኩባንያ እንደሆነ በህጉ አንቀፅ 550 ደንግጓል፡፡ ተቀጥላ የንግድ ማህበር ማለት ደግሞ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በሌላ ኩባንያ አማካኝነት በእናት ኩባንያ ቁጥጥር ስር የወደቀ ኩባንያ ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የተያዘ ኩባንያ ማለት ኩባንያው እና ከእናት ኩባንያው ሌላ ተቀጥላ ኩባንያ ወይም በእናት ኩባንያው ስም ከሚሰሩ ሰዎች ወይም በእናት ኩባንያው ተቀጥላዎች ስም ከሚሰሩ ሰዎች በስተቀር ሌላ የውጭ ባለአክሲዮኖች የሌሉበት ኩባንያ ማለት እንደሆነ በአንቀፅ 551 ላይ ተገልፆል፡፡

በህጉ አንቀፅ 552 መሰረት ቁጥጥር አለ የሚባለው እናት ኩባንያው ብቻውን ወይም ከሌሎች ባለአክሲዮኖች ጋር በመሆን የተቀጥላ ኩባንያውን የፋይናንስ እና የአሰራር ፖሊሲዎችን የመንደፍ እና የመምራት ስልጣን ሲኖረው ወይም ከግማሽ በላይ የሆነውን ድምፅ የመስጠት መብት ካለው ነው፡፡ ቁጥጥር የሚኖረው ወይም ሆልዲንግ ኩባንያ ግንኙነት አለ የሚባለው በሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አክሲዮን ማህበር ኩባንያዎች በተመለከተ መሆኑ ሌላው ልብ የሚባል ጉደይ ነው፡፡

የሆልዲን ኩባንያ ጥቅሞች

የንግድ ማህበራት ቡድን በመፍጠር ወይም የእናት እና ተቀጥላ የንግድ ማህበር ግንኙነት በመመስረት የአደረጃጀት እና የአስተዳደር ውጤታማነትን ለማምጣት እና ስጋት (risk) ለመቀነስ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ከዚህ አንፃር የንግድ እንቅስቃሴው በጣም ሰፊና በርካታ የማይገናኙ ዘርፎች ያሉት ሲሆን አደረጃጀቶችን በመፍጠር ሊደራጅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ስኳር ፋብሪካ የአገዳ ማምረት እርሻ ስራውን በአንድ ንግድ ማህበር፣ የፋብሪካ ምርት ሂደቱን በሌላ ኩባንያ፣ የሽያጭ ስርጭት ስራውን በሌላ ኩባንያ አድርጎ አደረጃጀቶችን በንግደ ማህበራት በመፍጠር ውጤታማነቱን በየሙያውና በየዘርፉ ከፋፍሎ ሊሰራ ይችላል፡፡ ከአስተዳደርም አንፃር እነዚህን ሁሉ ሰፊ የንግድ ተግባራት በአንድ ንግድ ማህበር ለመስራት በመሞከር የአስተዳደር ችግር ውስጥ ከመግባት ስራዎቹን በዘርፍ ከፋፍሎ አስተዳደሩን በማቃለል ውጤታማነቱን ለማሳደግ ሊመርጥ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከግዙፍ ድርጅቶች አንፃር በርካታ የንግድ ዘርፍ ስራዎችን በአንድ ላይ ሲከወን በአንዱ ዘርፍ የሚኖር ኪሳራ ወደ ሌላው ዘርፍ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅእኖ ለመገደብ ንግድ ስራዎቹን በዘርፍ ከፍሎ ማደራጀቱ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

በሌላ በኩል አንድ ባለሀብት በተለያዩ የማይገናኙ የንግድ ዘርፎች ለምሳሌ በተሸከርካሪ መገጣጠም፣ በሆቴል፣ በሰሊጥ እርሻ ወዘተ ቢሳተፍ እነዚህን ተግባራት በተለያዩ የንግድ ማህበራት እያደራጀ እህት ኩባንያዎች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ይህም ማለት የድርጅቶቹ ባለቤቶች ወይም ባለአክሲዮኖች ተመሳሳይ ሲሆኑ ድርጅቶቹ እህትማማች ይባላሉ፡፡ እዚህ ላይ የሚታየው የእህት አቻ ኩባንያ ግንኙነት እንጂ የእናት እና ተቀጥላ ንግድ ኩባንያ ግንኙነት አይታይም፡፡ ሆኖም እነዚህን እህት ኩባንያዎች አስተዳደር (የሚያስተዳድር) ወይም ደግሞ ካፒታላቸውን (አክሲዮናቸውን) በትልቅ ደረጃ (ድርሻ) የሚይዝ እናት ኩባንያ በመመስረት ሊያደራጅ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ልብ የሚባለው የእናት እና ተቀጥላ ኩባንያ ወይም የሆልዲንግ ኩባንያ አለ የሚባለው እናት የሚሆነው ግለሰብ ሳይሆን ድርጅት ወይም ኩባንያ መሆኑ እና ይህ ድርጅት የሌላ ድርጅት አክሲዮን ባለቤት ሲሆን እና ይህም የድርሻ መጠን በተቀጥላው ኩባንያ ውስጥ ውሳኔ ለመስጠት (አመራርና ዳይሬክተሮች ለመሾም ወይም የፋይናንስ ውሳኔዎች ለመስጠት) የሚያስችለው ደረጃ ያለው ሲሆን ነው፡፡

በዚህ መልኩ የሚኖር የንግድ ማህበራት መቧደን ወይም የሚደራጁ የእናት እና የተቀጥላ ኩባንያ ግንኙነት ወይም የንግድ ማህበር ግንኙነት በቀድሞው የንግድ ህግ ግልፅና ፈቃጅ ድንጋጌዎች አልነበሩትም፡፡ ሆኖም እንዲህ ያሉ አደረጃጀቶች ከሚኖራቸው የአደረጃጀት እና የአስተዳደር ውጤታማነትን ለማምጣት እና የንግድ ማህበራትን ስጋት (risk) ለመቀነስ ከሚኖረው ጠቀሜታ አንፃር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከፍትሀዊ የንግድ ውድድር፣ የህዝብን ወይም የሸማቾችን ጥቅም ለመጠበቅ፣ የሌሎች ባለአክሲዮኖችን መብት ለማስጠበቅ፣ የተቀጥላ ንግድ ማህበራቱን ህልውና ለመጠበቅ እና በሌሎች መሰል አላማዎች አዲሱ የተሻሻለው የንግድ ህጋችን ስርአትን አበጅቶ ፈቃጅ ሆኖ ተደንግጓል፡፡

የማህበራቱ ግንኙነት የሚመራበት ስርአት

ይህን የመሰለ የንግድ ማህብራት ዝምድና እና ግንኙነት ባለበት ሁኔት ሊወሰዱ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ማየት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የአንድ የንግድ ማህበር እና ከማህበሩ ጋር ቅርበት ባላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች መካከል የንግድ ውል ስምምነት የጥቅም ግጭትን ለማስቀረት በቅድሚያ በዳይሬክተሮች ቦርድ መፈቀድ ያለበት መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀፅ 306 ተመልክቶ እናገኛለን፡፡ ይህም እናት ወይም ተቀጥላ የሆነ የንግድ ማህበር እንዲሁም እርስ በእርስ አክሲዮን የተገዛዙ ማህበራት መካከል የሚኖር ስምምነትን ይመለከታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በህጉ አንቀፅ 307 መሰረት አንድ ኩባንያ በጠቅላላ ጉባኤው ተፈቅዶ ካልሆነ በስተቀር ለሆልዲንግ ኩባንያ ብድር ዋስትና ለመስጠት አይፈቀድለትም፡፡
👍3
ተቀጥላ ኩባንያ በእናት ኩባንያ ውስጥ ምንም አክሲዮን መያዝ አይችልም፡፡ በሌሎች ሁኔታዎችም ቢሆን አንድ የንግድ ማህበር በሌላ የንግድ ማህበር ውስጥ ከ5% ወይም በላይ አክሲዮን ድርሻ ካለው ለንግድ ሚኒስቴር የማሳወቅ ግዴታ እና ድርሻውን ከ5% በታች እስኪሆን ድረስ የመቀነስ ግዴታ እንዳለበት አንቀፅ 555 ይደነግጋል፡፡ በንግድ ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤትም የንግድ መዝገብ አክሲዮኖቹ በማን እንደተያዙ የሚያሳይ መረጃ መያዝ ግዴታ እንዳለበት አንቀፅ 313 ያመለክታል፡፡

በህጉ አንቀፅ 556 እና 557 ላይ እንደተገለፀው እናት ኩባንያ ለተቀጥላ ኩባንያ በጠቅላላ ጉባኤ ወቅት አመራር ወይም ትእዛዝ ለመስጠት የሚችልና መረጀዎችን ለማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ የተቀጥላ ንግድ ማህበር ሂሳብ መግለጫ በሆልዲንግ የንግድ ማህበር አመታዊ ጉባኤ ወቅት እንዲቀርብ መደረግ እንዳለበት ህጉ ይጠብቃል፣ ይህም አንቀፅ 431 ስር ተገልፆል፡፡ የአንድ የንግድ ማህበር ሂሳብ በኦዲተር ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ወይም በንግድ ሚኒስቴር አጣሪዎች ቁጥጥር በሚደረግበት ጊዜ የተቀጥላ ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ማድረግ ካስፈለገ ኦዲት ለማድረግ እንደሚቻል ህጉ የሚፈቅድ መሆኑን አንቀፅ 353 እና 355 ያሳያሉ፡፡

ከእዚህ ላይ ልብ ሊበል የሚገባው ሌላው ነጥብ እናት ኩባንያ በተቀጥላው ኩባንያ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ወይም ለተቀጥላው ኩባንያ ህልውና ወይም ለሌሎች ተወዳዳሪዎች እና ለመንግስት ከግብር ስወራ አንፃር የሚኖርበት ተጠያቂነት ነው፡፡ እናት ኩባንያው የመቆጣጠር መብቱን በመጠቀም በተቀጥላው እና በራሱ መካከል የሚኖር የንግድ ግንኙነትን ለራሱ ባልተገባ በሚጠቅም መልኩ እንዲሆን ወይም ተቀጥላው ድርጅት ምርቱን ከፍ ባለ ወይም ዝቅ ባለ ዋጋ እንዲሸጥ ወይም ጥሬ እቃዎችን እናት ኩባንያውን ያላግባብ ከሚጠቅም ድርጅት ከፍ ባለ ወይም ዝቅ ባለ ዋጋ እንዲገዛ የሚያደርግ እርምጃ ቢወስድ ሊኖርበት የሚችለው ተጠያቂነት ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ እናት ኩባንያዎች ከዚህ አንፃር የንግድ ስነ ምግባር፣ የውድድር ህጎች እና ሌሎች የፍትሀብሔር ሀላፊነቶች አንፃር ያሉበትን ግዴታዎች ታሳቢ በማድረግ በጥንቀቄ ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ አዲሱ የንግድ ህግ ከቀድሞው በተለየ መልኩ የሆልዲንግ ኩባንያ አደረጃጀትን እውቅና የሚሰጥ ነው፡፡ በሆልዲግ ኩባንያ አደረጃጀት መሰረት አንድ እናት ኩባንያ የውሳኔ ሰጪነት ሚና ያለው የአክሰዮን ድርሻ በተቀጥላ ኩባንያ ወይም ኩባንያዎች ውስጥ ሲይዝ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ይህም አደረጃጀት ለውጤታማነት፣ ቅልጥፍና እና ስጋትን በተሻለ ለማስተዳደር ጥቅም ይሰጣል፡፡ የንግድ እንቅስቃሴዎቻችንም ዘመናዊ እንዲሆኑ እና በተግባር ያሉ የተለያዩ የንግድ አማራጮችን፣ የስራ ፈጠራን ለማካተት ያስችላል፡፡ እንዲህ ያሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችም በእናት ኩባንያዎች በጥንቃቄ ህግን ተከትለው ሊተገበሩ እና ጥቅም ላይ ሊውሉ ይገባል፡፡

ምንጭ፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር
Lecturer or above
#dilla_university
#legal_services
#human_rights
#lecturer
Dilla
MA or above in Human Rights, Law and Child Rights with BA in Law, Civics and Ethical Education, having second degree CGPA of 3.50 with first degree CGPA of 3.00 & above for male applicants, for female applicants having second degree CGPA of 3.35 with first degree CGPA of 2.75 & above, applicants with disabilities and from pastorals regions having second degree CGPA of 3.15 with first degree CGPA of 2.50 & above and for applicants with affirmative actions(never been on probation) having second degree CGPA of 3.10 with first degree CGPA of 2.50 & above. Having thesis grade result Very Good(B+) & above
Quanitity Required: 1
Minimum Years Of Experience: #0_years
Deadline: January 15, 2022
How To Apply: In person at Dilla University Main Campus, to the Human Resource Administration Directorate, office no. 26 or in Addis Ababa at the Liaison Office, located in front of Bole Rwanda Embassy. For additional information, contact Tel. 0463311564 / 0463314220
NB: Applicants should bring their credential; original & copies of non-returnable application letter, CV, educational transcripts, renewed ID & other supporting documents. Qualified and selected applicants are required to bring release paper from their current employers.
#hahujobs
DARA Requirements - Page 9
👍2
👍1
Legal Officer

Berhan Insurance S.C

Addis Ababa

Full–time

Berhan Insurance S.C is established and licensed to provide general insurance services (property, liability, and pecuniary insurances) to the customers at twenty-four branches with a plan to expand further in Addis Ababa and regional towns.
The company would like to invite potential candidates who fulfill the job requirement for the following post.
Position Title: Legal Officer Educational Qualification:
• BA in Law, Law in Corporate Governance, LLM in Business regulation and other related fields from a recognized University or College Experience:
• Minimum of 3 years of relevant work experience
No. Required: 04
Terms of Employment: Permanent

Place of Work: Addis Ababa

Salary: Based on the company scale
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍4
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት “ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትህ፤ ግጭቶች ሲከሰቱ ወይም ከግጭት በኋላ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሲምፖዚየም ላይ ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡
• ፍ/ቤት ወቅታዊ የመሆን ባህሪይ የለውም፤ ወቅታዊ መሆንም አይጠበቅበትም፡፡ ሆኖም ዛሬ ውይይት እንዲደረግበት ያሰብናቸው ርዕሶች ከፍ/ቤቶች ሚና እና ከፍትህ አኳያ ውይይት ሊደረግባቸው ይገባል ባልናቸው አሁናዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ነው፡፡
• የዛሬ ውይይታችን ትኩረት በተለይም በሃገራችን የተከሰቱ ግጭቶችን ማን ፈጸማቸው? እንዴት ተፈጸሙ? በሚለው ላይ አይሆንም፤ ምክንያቱም ይህ አይነቱ ጉዳይ በፍ/ቤት ደረጃ ልዩ በሆነ እና በጥብቅ የስነ-ስርዓት እና የማስረጃ አቀራረብ ስርዓት የሚመራ ሂደት በመሆኑ ነው፡፡
• ባለፉት ሶስት አመታት በፍ/ቤቶቻችን ሕጎችን በማሻሻል፣ መመሪያ እና ደንቦችን በማውጣት፣ የአሰራር ስርዓትን በመለወጥ፣ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ተቋማዊ ስርዓት በመገንባት ላይ ነን፡፡
• በተለይም የፍ/ቤቱን ነጻነት እና የዳኞች ሙያዊ ነጻነት እንዲረጋገጥ የተወሰዱት አዎንታዊ እርምጃዎች ዳኞች በሰጡዋቸው ውሳኔዎች የተገለጡ ናቸው፡፡
• ፍ/ቤቱ በUSAID ከሚደገፍ ፕሮጀክት ጋር በትብብር ባሰራው የህዝብ አስተያየት መለኪያ “Public Perception Survey” በፍርድ ቤቶች ላይ የሕዝብ አመኔታ እየጨመረ እንደመጣ ግኝቶቹ አመላክተዋል፡፡ ሆኖም የተጀመሩት የለውጥ ስራዎች ስር እየሰደዱ እና ፍሬ እያፈሩ እንዲሄዱ ቀጣይ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡
• በተለያየ የሃራችን ክፍሎች የተፈጠሩ ግጭቶች በፌዴራልም ሆነ በክልል ፍ/ቤቶች ላይ ተጨማሪ ጫና ማሳደራቸው አልቀረም፡፡
• ከተከሰቱ ግጭቶች ጋር በተገናኘ በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት አግኝተዋል፡፡ በእያንዳንዱ ፋይል የተከሳሾች ቁጥር በአማካይ ከ 50 – 200 ይደርሳል፡፡ ጉዳዩቹ ደግሞ እጅግ ውስብስብ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የክስ አቀራረቡ ጥራት የለውም፣ ምስክሮች በተባለው ጊዜ አይቀርቡም፡፡ ጥይት እየተተኮሰ ዳኞች ችሎት ያካሄዱበት ሁኔታም ተከስቶ ነበረ፡፡
• የሽግግር ፍትህ እና እርቅ በተለያዩ ሃገሮች የተሞከሩ እና ተግባራዊ የሆነ አማራጭ የፍትህ ማዕቀፎች ናቸው፡፡ ሆኖም እንዲህ ያለው አማራጭ ከእያንዳንዱ ሃገር እውነታ ጋር የሚዛመድ መሆን ይገባዋል፡፡
• የግጭቱ ይዘት፣ ማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ ባህላዊ እና ስነ-ልቦናዊ እውነታዎች ከግምት መግባት ይገባቸዋል፡፡
• እንደሚታወቀው በአንድ ሃገር በተለይም ግጭቶች ከተከሰቱ በኋላ የሚተገበረው የሽግግር ፍትህ ዋና ዋና የወንጀል ተዋናዮችን በእየፍ/ቤት ተጠያቂ ከማድረግ ባለፈ ሰፋ ያሉ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ሌሎች ተቋማዊ ለውጦችን በማድረግ ሁለንተናዊ የቂም በቀል ማብረጃ እና አዳሽ ዘዴዎችን ለመፈለግ ነው፡፡ ስለዚህ የሽግግር ፍትህ ከመደበኛ ፍትህ ጎን ለጎን የሚከናወን ይሆናል ማለት ነው፡፡
• በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው ኮሚሽን በከፍተኛ ጉጉት እና ተስፋ እየተጠበቀ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በሚጠበቀው ደረጃ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ሚናቸውን በቅን ልቦና፣ በብስለት፣ በትዕግስት እና በአርቆ አሳቢነት መወጣት ሲችሉ ነው፡፡
• እንደእኔ አስተያየት ይችን ታሪካዊ አጋጣሚ ለመጠቀም ዝግጁ መሆን ይገባናል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ /የፌ/ጠ/ፈ/ቤት ፕሬዝደንት/