አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
እና መግባባት ማከናወን ያለባቸው ሲሆን አንዱ የሚያከናውነው ተግባር ሌላኛውን ተጋቢ ሊጎዳ ስለሚችል እያንዳንዱ እንቅስቃሳቸው በጋራ ስምምነት እና መግባባት ላይ ያተመሰረተ መሆን ይገባዋል ፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
JOB DESCRIPTION

Awash Insurance Vacancy

Head, Legal & Advisory Services

Job Overview

Salary Offer As per Company Scale

Experience Level Senior

Total Years Experience 7

Date Posted December 26, 2021

Deadline Date January 1, 2022

Key Responsibilities

In collaboration with pertinent managers, provide leadership and ensure efficient & effective management of legal and advisory services;

Coordinates the provision of legal advisory services;

Monitors the management of defense and intervention cases as well as recovery cases;

Supervises the observance of service delivery standards in the provision of legal services;

Provides guidance for the efficient and cost effective resolution of defense and intervention cases as well as recovery cases;

Monitors the change in the laws and practices that impact the insurance business and advise same to the Company;

Verifies pleadings and petitions to be submitted to court;

Supports Company units on drafting agreements, policies and procedures;

Represents the Company on negotiations and submit settlement proposals to the Company;

Reviews progress of outstanding litigations and submit regular report to the Management;

Designs legal compliance checklist and monitors its implementation;

Coordinates tailored interventions on coaching, mentoring and trainings for the staff members in the unit.

Job Requirement

Educational Qualification: LL. M or LL. B Degree in law

Experience Requirement: Nine years experience for LL.M or Thirteen years experience for LL.B

Additional Requirement:Fluency in English, Amharic and Afan Oromo.

Age:Below 45 years

Place of work: Addis Ababa

Salary & Benefits:Negotiable salary with attractive benefits package

How To Apply

Interested applicants should send a non-returnable CV and copies of relevant credentials together with their hand written application within seven days of appearance of this announcement in the Newspaper to:

Human Capital Management

Awash Insurance Company S.C.

P.O. Box 12637, Addis Ababa

Only short – listed applicants will be contacted.

Hand delivered applications will not be acceptable.
በቀጣዮቹ 4 ዓመታት 70 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ መታወቂያን ይይዛሉ ተባለ🔷
December 27, 2021
“የብሔራዊ መታወቂያ ዓላማ የቀበሌ መታወቂያን መተካት አይደለም”- ዮዳሄ ዘሚካኤል፤ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ
ከ 10 ዓመት በፊት የተወጠነው የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት አሁን በሙከራ ትግበራ ላይ ይገኛል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዋና ሥራ እንደሚገባ በተገለጸው በዚህ ፕሮጀክት በቀጣይ አራት ዓመታት ከ 70 ሚሊዮን የሚልቁ ኢትዮጵያውያ ብሔራዊ መታወቂያ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ ብሔራዊ መታወቂያ ሲባል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ዜጋም ሆነ ነዋሪ የትኛውንም አገልግሎት ሲያገኝ እራሱን የሚለይበት እና የሚያስተዋውቅበት መንገድ እንደሆነ የገለጹት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል መታወቂያውን በ2018 ዓ.ም ህፃናትን ሳይጨምር 95 ከመቶ ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ብሔራዊ መታወቂያ ማንኛውም ዜጋ ወይም ነዋሪ ሊኖረው የሚገባው መታወቂያ እንደሆነ ያነሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብሔራዊ መታወቂያ በካርድ ከሚሰጠው ይለያል ብለዋል፤ እኔነትን የሚያረጋግጥ የመረጃ ስርዓት እንደሆነ በመጠቆም፡፡
ራስን ለማረጋገጥ የሚያስፈልግ ማንኛውንም የመረጃ ስርዓት “ብሔራዊ መታወቂያ” ብሎ ጠቅለል አድርጎ መጥራት እንደሚቻልም አንስተዋል የፕሮጀክቱ ኃላፊ፡፡

ብሔራዊ መታወቂያ በዋናነት ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር የመስራት ጉዳይ እንደሆነ ያነሱት አቶ ዮዳሄ፤ ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር በሚሰራበት ጊዜ፤ አንዳንዶቹ አገልግሎት ሰጭዎች መታወቂያ ማተም ሊፈልጉ እና አንዳንዶች ደግሞ በ“ዲጂታል ብቻ ይበቃናል” ሊሉ እንደሚችሉም አስታውሰዋል፡፡
እንደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ የመታወቂያ ካርድ የሚያትሙ አገልግሎት ሰጭዎች ላይ የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር እንደሚቀመጥም ነው የተገለጸው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተማሪዎች መስጠት የጀመረውን መታወቂያ እንደ አብነት ያነሱት ዋና ስራ አስኪጁ የብሔራዊ መታወቁያ ዓላማ የቀበሌ ወይም የነዋሪ መታወቂያን መተካት እንዳልሆነ አነስተዋል፡፡ ከዛ ይልቅ ብሔራዊ መታወቂያ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ማናቸውንም አገልግሎት ሰጭዎችን ማስተሳሰር ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

አለፈለገ ሰላም
ለአብነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪነት መታወቂያ ሲሰጥ፤ ይህንን መታወቂያ ከሌሎቹ ጋር ማስተሳሰር የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ስራ እንደሆነም ተነስቷል፡፡
“አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል ስልት ባዮሜትሪክ የሚባል ዳታ፤ የእጅ እና የዐይን አሻራ፣ የፊት ፎቶ ከተያዝ በኋላ ብሔራዊ መታወቂያ ካዘጋጀው ልዩ ቁጥር ጋር እንደሚያያዝ ነው የገለጹት አቶ ዮዳሄ፡፡
ይህ ልዩ ቁጥር ከአሻራ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ የትኛውም አገልግሎት ሰጭ ጋር በመሄድ አገልግሎት ማግኘት ቢያስፈልግ፤ አገልግሎት ሰጭው የራሱን አገልግሎት ልዩ ቁጥር ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ያተሳስራል ተብሏል፡፡
አገልግሎት ሰጭው ከአንድ ዘርፍ ወደ ሌላ ዘርፍ ፤ከአንድ ሱቅ ወደሌላ ሱቅ፤ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ቢሄድም የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር እንደማይቀየርና በዛ ቁጥር መሰረት እንደሚተሳሰር ተገልጿል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል ከአራት ዓመታት በኋላ በ2018 ዓ.ም 70 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ዲጂታል መታወቂያ እንዲይዝ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርን በአካል በሚሰጥ እና መታወቂያ ላይ ያለውን መረጃ በመውሰድ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በያዝነው ዓመት “አነስ አነስ ያሉ የሙከራ ትግበራዎችን” ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር እንደሚሰራም ነው፤ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዋና ትግበራ ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡
ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር ፕሮጀክት በመቅረጽ እንደሚሰራ ያነሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ፤ ባንክ እንደምሳሌ ቢወሰድ ባንኩ አንድ የተለየ አገልግሎት ለማግኘት ደንበኛው ወደ ባንኩ ቢሄድ ቅድሚያ “የብሔራዊ መታወቂያ አሻራህን ሰጥተህ ነው ይህንን አገልግሎት የምንሰጥህ እንዲል “የማስቻል ስራ ይሰራል ነው የተባለው፡፡ በዚህም መሰረት 10 ዲጂት ቁጥር ያለው የብሄራዊ መታወቂያ ቁጥር ከሌሎች ሴክተሮችም ጋር እየተሳሰረ እንደሚሄድ ተገልጿል፡፡
ብሔራዊ መታወቂያ የግድ በኪስ ተይዞ የሚኬድ እንዳልሆነ የገለጹት ዋና ስራ አስኪጁ፤ ምናልባት የዛሬ አምስት ወይም 1 0 ዓመት ሁሉም መታወቂያዎች በብሔራዊ መታወቂያ ይቀየሩ ቢባል ካርዱን የማተም ሥራው አንድ በመቶ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
የሥራው 99 በመቶ ዳታውን መሰብሰብ እና ከዛ ከሲስተሞች ጋር ተናቦ ማረጋገጫ የመስጠት ሲሆን ካርድ መስጠት ግን እስካሁን በሕግ ደረጃ እንደሌለ ተገልጿል፡፡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ነዋሪነት ወይም አድራሻ የማረጋገጥ ስራ አይሰራም ብለዋል፡፡ አዲስ አቅጣጫ ካልመጣ በስተቀር አሁን ያሉት መታወቂያዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉና በነሱ ላይ የብሔራዊ መታወቂያ ልዩ ቁጥር እንደሚቀመጥ አስቀምጠዋል ስራ አስኪያጁ፡፡

https://t.me/GudayAsfetsami
በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ስለአክሲዮን ማህበር የተካከተቱ መሰረታዊ ነጥቦች

መግቢያ
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ መሆኑ ይታወቃል። ሻል ያለ ደረጃ ላይ የሚገኙት ጥቂቶችም ቢሆኑ ትርጉም ያለው ተቀማጭ ገንዘብ የላቸውም ሊባል ይችላል። በመሆኑም አገራችን ሥራ ላይ ሊውል (ኢንቨስት ሊደርግ) የሚችል ካፒታል ከፍተኛ እጥረት አለባት። በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ በሚገኝ አገር ውስጥ እድገት ለማምጣት ዜጎች በተናጠል ያላቸውን እጅግ ውስን ሀብት አስተባብሮ ወደ ሥራ ማስገባት የግድ ይላል። ይህ እንዲሳካ ደግሞ ዜጎች የቆጠቡትን ትንሽ ገንዘብ በንግድ ማኅበር ውስጥ ካስገቡ በኋላ ለምዝበራ እና ጭቆና እንዳይዳረጉ የሚከላከል ሕግ መኖር አለበት።

የ1952ቱ ንግድ ህግ በኩባንያዎች ውስጥ አነስተኛ ድርሻ ይዘው የሚገቡትን ባለሃብቶች ከዘረፋ፣ ካልተገባ ጭቆና ወይም በደል ለመታደግ ያለሙ ድንጋጌዎች በበቂ ሁኔታ አላካተተም። በዚህም የተነሳ ኢኮኖሚው ያፈራውን አነስተኛ ካፒታል አሟጦ በተደራጀ መልክ ሥራ ላይ ማዋል አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። አልፎ ተርፎም ይህ ክፍተት አገሮች ለንግድ ምን ያህል አመቺ እንደሆኑ በሚለካው በዓለም ባንክ የሚደረግ ምዘና ኢትዮጵያ በየዓመቱ በጣም ዝቅተኛ ውጤት እንድታገኝ አድርጓል። በዚህም የተነሳ አገራችን የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ በምታደርገው ጥረት ላይ ዕንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።በመሆኑም አዲሱ የንግድ ህግ ከቀድሞው የንግድ ህግ በተሸለ ሁኔታ የማህበር አባላትን መብት በሚያስጠብቅ ሁኔታ የህግ ድንጋጌዎችን አካቶ በስራ ላይ ውሏል፡፡
የአክሲዮን ማህበር በቀድሞው እና በአዲሱ የንግድ ህግ ከተካተቱ የንግድ ማህበራት አይነቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ማህበሩ የመጠሪያ ስም ኖሮት ከስሙ መጨረሻ ላይ “የአክሲዮን ማህበር” የሚል ሀረግ በመጨመር በንግድ መዝገብ እንደተመዘገቡ የሕግ ሰውነት እንደሚያገኝ በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀፅ 174፣175፤246 ተመልክቷል፡፡በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ፅሁፍ በአዲሱ የንግዱ ህግ ስለአክሲዮን ማህበር የተካተቱ አንዳንድ ነጥቦችን በወፍ በረር ለማየት ይሞከራል፡፡

የአክሲዮን ማህበር ትርጉም
የአክሲዮን ማህበር ማለት ዋና ገንዘቡ ወይም ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዮን የተከፋፈለና ኃላፊነቱ በማህበሩ ሀብት ብቻ የተወሰነ ማህበር ሲሆን የአባላት ቁጥር ከአምስት ባለአክሲዮኖች በታች መሆን የሌለበት የንግድ ማህበር አይነት ነው፡፡ የባለአክሲዮኖች ኃላፊነት ለማህበሩ ቃል የገቡትን መዋጮ በመክፈል የተወሰነ ሆኖ በሌላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር፣ የማህበሩ ዋና ገንዘብ ወይም ካፒታል ከሃምሳ ሺህ የኢትዮጵያ ብር ያነሰ ሊሆን እንደማይችል እና እያንዳንደ አክሲዮን ላይ የሚጻፈው ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች ሊሆን እንደማይችል በንግድ ህጉ አንቀፅ 245/1/ እና 2 ስር ሰፍሯል፡፡

የአክሲዮን ማህበር አባላት ሃላፊነት የተወሰነ ነው ማለት ማህበሩ ከሦስተኛ ወገኖች ማለትም ከአበዳሪዎች፣ከደንበኞቹ እና ከሠራተኞቹ ወ.ዘ.ተ ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ጉዳት ቢደርስ የማህበሩ አባላት (ባለአክሲዮኖች) ሃላፊነት እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውን ይመለከታል፡፡ ይኸውም የማህበሩ አባላት ሃላፊነት ለማህበሩ ካፒታል ባዋጡት ወይም በሚያዋጡት መጠን ብቻ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ከንግድ ህጉ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡:: ይህም ማለት አባላቱ ማህበሩ ሲመሠረት ወይም ከተመሰረተ በኋላ ለሽያጭ ከቀረበው የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ በገዙት የአክሲዮን መጠን ብቻ ተጠያቂ የሚሆኑ ሲሆን አባሉ የሚጠበቅበትን መዋጮ ያልከፈለ እንደሆነ አክሲዮን ማህበሩ በእዳ ሲያዝ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡ የአክሲዮን ማህበሩ ሃብት ጉዳቱን ለመካስ በቂ ሆኖ ባይገኝ ወደ ባለአክሲዮኖቹ ንብረት መሄድ አይቻልም ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የአባላቱ የግል እዳ ከኩባንያው ሃብት አይከፈልም፡፡

• የአክሲዮን ማህበር ጥቅም/ አስፈላጊነት
የአክሲዮን ማህበራት በሃገራችን መበራከት ሀገራዊ እና ግለሰባዊ ፋይዳ አለው፡፡ ሀገራዊ ፋይዳውን ስናይ አክሲዮን ማህበር ትልልቅና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቁ የንግድ ዘርፎች(ለምሳሌ ባንክ፣መድን ድርጅት፣በግብርና ዘርፍ፣በቤቶች ግንባታ ወዘተ ) ላይ ለመሰማራት የሚረዳ የማህበር አይነት በመሆኑ የእነዚህ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች በሃገራችን መፈጠር ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል፡፡ በሌላ በኩል የግለሰቦችን ስራ ፈጣሪነት ያበረታታል፡፡ ይህ ሲባል ግለሰቦች የሀገርን ኢኮኖሚ እድገት ሊያፋጥን የሚችል የንግድ ሃሳብ አመንጭተው ካፒታል ከህዝቡ በመሰብሰብ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ሙያዊ ብቃታቸውን ተጠቅመው የሚሰሩ ስራ ፈጣሪዎች ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያበረታታ ሲሆን ለማህበሩ መፈጠር የደም ስር የሆነውን ካፒታል ያዋጡ ሰዎች ደግሞ ወደ ፊት ማህበሩ የሚያስገኘውን ትርፍ የድርሻቸውን በመውሰድ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ያስችላል፡፡በአጠቃላይ አክሲዮን ማህበር ባለሀብቱን (capitalist) ከስራ ፈጣሪ (entrepreneur) ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ፡፡

• የአክሲዮን ማህበራት አቋቋም
የአክሲዮን ማህበራት በሁለት አይነት መንገድ ሊቋቋሙ ይችላሉ፡፡ እነዚህም፡-
1. ለህዝብ ክፍት የሆነ የአክስዮን ማህበር ፡- በአደራጅ አማካኝነት የሚቋቋም ሲሆን አደራጁ ለሕዝብ ክፍት የሆነ ማህበር ምስረታን ያነሳሳል፤ መግለጫ አዘጋጅቶ ሰዎች ማህበሩን እንዲቀላቀሉ ይጋብዛል ወይም በአጠቃላይ የማህበሩን ምስረታ ዓላማ አድርጎ ይህንኑ ለማስፈጸም በመንቀሳቀስ ማህበሩ የማይመሰረት ከሆነ ባለመመስረቱ ምክንያት ለሚመጣ ጉዳት ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ የአክሲዮን ማህበራት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የተፈጥሮ ሰዎች ወይም ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው ሰዎች ሊደራጁ የሚችል ሆኖ የአክሲዮን ማህበር አባላት ቁጥር ከአምስት ባለአክሲዮኖች በታች መሆን የለበትም፡፡

አደራጆቹ ለህዝብ አክሲዮን በመሸጥ አክሲዮን ማህበራት ሲያቋቁሙ ሊከተሏቸው ወይም መፈፀም ያለባቸውን ድርጊቶች እና ሊያሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች በንግድ ህጉ አንቀጽ 249፣ 250 እና 251 ስር ተመልክቷል፡፡በአጠቃላይ በዚህ አይነት መንገድ የሚቋቋም አክሲዮን የንግድ ሀሳቡ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቅ ከሆነ ገንዘቡን ትንሽ ሠዎችን በማሣመን መሰብሰብ ስለሚያስቸግር ለሕዝብ አክሲዮን በመሸጥ አክሲዮን ማህበሩን ማቋቋም ይችላሉ፡፡

2. በመሥራቾች መካከል የሚደረግ መቋቋም
ይኸኛው የአክስዮን ማህበር አይነት ምስረታ የሚደረገው የተወሰኑ ሰዎች ለሕዝብ ጥሪ ሳያደርጉ የአክሲዮን ማህበር ምስረታን የተመለከቱ የንግድ ህግ ድንጋጌዎችን በማሟላት በመካከላቸው የአክሲዮን ማህበር የሚያቋቁሙበት ነው።በተመሳሳይ በሌላ ህግ የተለየ ቁጥር ካልተወሰነ በስተቀር የአክሲዮን ማህበር መሥራቾች ቢያንስ አምስት መሆን እንዳለባቸው በንግድ ህጉ አንቀፅ 252 ስር ተደንግጓል፡፡

• የማህበሩ አመሰራረት
ለአክሲዮን ማህበር ምስረታ ከሚያስፈልጉ ጠቅላላ ሁኔታዎች ውስጥ የማህበሩ ዋና ገንዘብ በሙሉ ለማዋጣት መፈረም ፤እና ለጥሬ ገንዘብ በተሠጡ አክሲዮኖች ላይ ከተፃፈው ዋጋ ውስጥ ቢያንስ አንድ አራተኛው በመመስረት ላይ ባለው ማህበር ስም በተከፈተ ዝግ የባንክ ሒሳብ መቀመጥ ያለበት መሆኑ ይገኙበታል፡፡የተቀመጠውን ገንዘብ ማህበሩ በንግድ መዝገብ ሳይመዘገብ ከተቀመጠበት ሒሳብ ማውጣት አይቻልም፡፡
በሌላ በኩል የአክሲዮን ሽያጭ ገንዘብ ባንክ መቀመጥ ከጀመረበት ቀን አንስቶ በንግድ ህጉ አንቀጽ 259 መሠረት በሚቀርበው የማህበሩ መግለጫ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማህበሩን ማስመዝገብ ካልተቻለ በማህበሩ አባልነት መቀጠል የማይፈልጉ ፈራሚዎች ገንዘባቸው ከባንክ ወለድ ጋር እንዲመለስላቸው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ገንዘቡ እንዲመለስ ጥያቄ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ አደራጆች በንግድ ማህበር መዝጋቢው አካል መዋጮው እንዲመለስ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ መዝጋቢው አካልም ለጥያቄ አቅራቢው ፈራሚ መዋጮው እንዲመለስለት የሚመለከተውን ባንክ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የማህበሩ ምስረታ በቀሪዎቹ ፈራሚዎች ሊቀጥል ይችላሉ።

• የማህበሩ በንግድ መዝገብ መመዝገብ
የአክሲዮን ማህበሩ የተቋቋመው በምንም ዓይነት ቢሆንም በንግድ መዝገብ መግባት ያለበት ሲሆን ማህበሩ የሕግ ሰውነት የሚያገኘው በምዝገባ ይሆናል። ከምዝገባው ማመልከቻ ጋር በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ማህበሩ ለሕዝብ ክፍት የሆነ እንደሆነ የማህበሩ መግለጫ፣ የዓይነት መዋጮዎች እና የምስረታ ኦዲት ሪፖርቶች እንዲሁም የፈራሚዎች ጉባዔ ቃለጉባዔ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡ የአክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖችን መዝገብ በወረቀት ወይም ለረጅም ዘመን በሚቆይ የኤላክትሮኒክ ዘዴ መያዝ ይችላል።

አክሲዮኖች የሚወጡበት ዘዴ በማህበሩ የመመስረቻ ፅሁፍ ወይም ማሻሻያው ሊወሰን የሚችል ሆኖ በወረቀት ወይም በግዑዝ አልባ ማለትም ይህንን ስራ እንዲሰራ በህግ ሥልጣን በተሰጠው ተቋም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ተፈጥሮ በኤለክትሮኒክ የአክሲዮን ሂሳብ የሚያዝ አክሲዮን ሊሆን ይችላል፡፡መዝገቡ የባለአክሲዮኖችን ስም፣ አድራሻ፣ዜግነት፣ የአክሲዮኖችን ብዛትና መለያ ቁጥር፣ የተከፈለውን ገንዘብ መጠንና ባለአክሲዮኖቹ የተመዘገቡበትን ቀን መያዝ አለበት።

የአክሲዮኖች አይነት
አክሲዮኖች በሚገዙበት ሁኔታ ላይ መሰረት በማድረግ በጥሬ ገንዘብ የሚገዙ አክሲዮኖች እና በአይነት መዋጮ የሚደረጉ ተብለው ሊከፈሉ እንደሚችሉ ከንግድ ህጉ አንቀፅ 281 እና 282 መገንዘብ ይቻላል፡፡
በጥሬ ገንዘብ የሚገዙ አክሲዮኖች በተፈረሙ ጊዜ እጅግ ቢያንስ ከተጻፈባቸው ዋጋ አንድ አራተኛ ወይም በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ከፍ ያለ መጠን ተወስኖ ከሆነ ይኸው ዋጋ በሙሉ መከፈል አለበት።በመመስረቻ ጽሁፍ ያነሰ ጊዜ ካልተወሰነ በስተቀር፤ ያልተከፈለው የአክሲዮኖች ዋጋ ማህበሩ በንግድ መዝገብ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ እስከ አምስት ዓመት መከፈል አለበት፡፡

በዓይነት መዋጮ የተደረገ እንደሆነ የአይነት ማዋጮ የከፈለ ፈራሚ የባለሙያ ግምት ሪፖርት ማቅረብ አለበት።የግምት ሪፖርቱ መዋጮ የተደረጉትን ንብረቶች፣ የእያንዳንዱን የዋጋ ግምት እና የአገማመቱን ዘዴ በዝርዝር መገለፅ ያለበት ሆኖ ሪፖርቱም ከመመስረቻ ጽሁፍ ጋር መያያዝ ይኖርበታል።

በሌላ በኩል ከሚያስገኙት ጥቅም አንፃር የአክሲዮን ማህበራትን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን እነዚህም ልዩ መብት የሚያስገኙ አክሲዮኖች እና ትርፍ ብቻ የሚያስገኙ አክሲዮኖች ናቸው፡፡ ልዩ መብት የሚያስገኙ አክሲዮኖች የሚሰጡት ልዩ ጥቅም ወደ ፊት የሚወጡትን አክሲዮኖች በቅድሚያ የመግዛትን፣ ከትርፍ በቅድሚያ የመከፈልን ወይም የማህበሩ ንብረት በሚጣራበት ጊዜ መዋጮ ሲመለስ ወይም ተራፊ ሀብት ሲከፋፈል በቅድሚያ ክፍያ የማግኘትንና የመሳሰሉትን ሊያካትት ይችላል። ትርፍ ብቻ የሚያስገኙ አክስዮኖች ደግሞ ማህበሩ ዋናው ገንዘቡን ሳይቀንስ ካገኘው ትርፍ ወይም ካስቀመጠው መጠባበቂያ ገንዘብ ለባለአክሲዮኖች በአክሲዮኖቻቸው ላይ የተጻፈውን ዋጋ የሚመለስበት ነው፡፡

በተጨማሪም በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 267 እንደተገለጸዉ በሚወጡበት መንገድ ላይ መሰረት በማድረግ በባለአክሲዮን ስም የሚወጡ የአክስዮን አይነቶች በባለአክሲዮን ስም የሚመዘገቡ ሲሆን ላምጪው የሚል አክሲዮኖች ሌላኞቹ የአክሲዮን አይነቶች ናቸው፡፡ ተቃራኒ ስምምነት ቢኖርም እንኳን አዲሱ የንግድ ሕግ ከመውጣቱ በፊት ላምጪው የሚል አክሲዮኖች በሚገኙባቸው ማህበሮች ለአምጪው በሚል የወጡ አክሲዮኖች ባለቤት የሆነ ማንኛውም ሰው አክሲዮኖቹ በስም በሚመዘገብ እንዲለወጡለት ማህበሩ ዘንድ በመቅረብ ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሦስት ዓመት ውስጥ ማመልከት አለበት።

• የማህበሩ ስራ አመራር
የአክሲዮን ማህበራት የስራ አመራር የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ተቆጣጣሪ ቦርድ ይኖራቸዋል፡፡የአክሲዮን ማህበር በባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ቢያንስ ሦስት ቢበዛ አስራ ሦስት ዳይሬክተሮች እንደሚኖሩት እና ከዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት መካከል ከሦስት ሁለት እጅ (2/3ኛ) በማህበሩ የዕለት ተዕለት ሥራ አመራር ውስጥ የሥራ አስፈጻሚነት (ኤክስኪዩቲቭ) ሚና የሌላቸው መሆን እንዳለባቸው በንግድ ህጉ አንቀፅ 296 ስር ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪ የማኅበር አባል ያልሆነ ሰዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ሊመረጥ ይችላል፡፡ እንዲሁም የዳይሬክተሮች ቦርድ በሕግ፣ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎች የሚሰጥ ሀላፊነት እና ሥልጣን ይኖረዋል።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በንግድ ህጉ ዝርዝር ሀላፊነቶች እና ስልጣን ተካቶ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ለሚደርሰው ጉዳት ለማህበሩ በአንድነትና በተናጠል ተጠያቂ እንደሚሆኑ በንግድ ህጉ አንቀፅ 325 እና ተከታዮቹ ተመልክቷል።

በሌላ በከል የአክሲዮን ማህበራት ተቆጣጣሪ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ የሚሾሙ ቁጥራቸው ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ አባላት ሊኖሩቱ የሚችል ሲሆን ጠቅላላ ጉባዔው የተቆጣጣሪ ቦርድ አባላትን በማንኛውም ጊዜ ሊሽራቸው ይችላል፡፡

የተቆጣጣሪ ቦርድ አባል ሆነው መመረጥ የሚችሉት ባለአክሲዮኖች ብቻ ሲሆኑ የተቆጣጣሪ ቦርዱ ተጠሪነት ለባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ይሆናል።የተቆጣጣሪ ቦርድ አባላት ስልጣን ፣ ተግባር እና ሀላፈነቶች በንግድ ህጉ አንቀፅ 332 እና ተከታዮቹ ተዘርዝሮ የሚገኝ ሲሆን ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች መረጃዎችን የማስቀረብ እና የመመርመር አንዱ ተግባር ነው ፡፡

ስለማህበሩ መፍረስ እና ማህበሩ የሚፈርስባቸው ምክንያቶች
የአክሲዮን ማህበር በሚከተሉት ምክንያቶች ሊፈርስ ይችላል፡--
የባለአክሲዮኖች ቁጥር በሕግ ከተፈቀደው ዝቅ ሲልና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሌላ አባል መተካት ባለመቻሉ ምክንያት ጥቅም አለኝ በሚል ሰው በቀረበ ማመልከቻ መሠረት የንግድ ማህበራትን የሚመዘግበው አካል ማህበሩ እንዲፈርስ ሲወስን፤የአስተዲደር አካላት የሌሉት በመሆኑ ምክንያት ጥቅም አለኝ በሚል ሰው ጠያቂነት የንግድ ማህበራትን የሚመዘግበው አካል ማህበሩ እንደፈርስ ሲወስን እና ማህበሩ የዋና ገንዘቡን ሦስት አራተኛ በኪሣራ ሲያጣ ናቸው።እንዲሁም በንግድ ህጉ እንቀፅ 181 የተዘረዘሩ የአጠቃላይ የንግድ ማህበራት መፍረስ ምክንያቶች ለአክሲዮን ማህበር መፍረስ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
በንግድ ሕጉ መሠረት ማህበሩ እንዲፈርስ በማህበሩ የተወሰነ እንደሆነ የመፍረሱ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሃያ አንድ ቀናት ውስጥ ማህበሩ እንዲፈርስ ስለመወሰኑ ሰፊ ስርጭት ባለው ጋዜጣና በማህበሩ ድረ ገጽ በይፋ መገለጽ ያለበት ሲሆን ማስታወቂያውም “በመጣራት ላይ ያለ” የሚል ሀረግ ተጨምሮበት የማህበሩን ስም፣ የዋና ገንዘቡን መጠን፣ የፈረሰበትን ምክንያት፣ የሂሳብ አጣሪውን ስምና አድራሻ እንዲሁም የሥልጣን ወሰን መያዝ አለበት። እንዲሁም ማህበሩ እንዲፈርስ የተሰጠው ውሳኔ እና በውሳኔው መሠረት ሒሳብ
አጣሪ መሾሙን የሚያመለክቱ ሰነድች በማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጥ እንዲሁም በንግድ መዝገብ መመዝገብ አለባቸው፡፡

የንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
Legal Advisor

Reach Ethiopia
Addis Ababa


Terms of Reference for Legal Advisor to provide on call legal services External Announcement Brief introduction REACH Ethiopia is a non-political, non-religious, non-racial, and non-profit-making development Organization that has been registered by Charities and Societies Agency as Ethiopian Residents Charity bearing certificate No. 3020. REACH Ethiopia envisions contributing the development and wellbeing of humanity through innovation and maximizing the utilization of opportunity available for the generation.

The major goal of REACH Ethiopia is health service delivery commitment and contributing its part to improve the general health service and wellbeing of the disadvantaged community in move towards the sustainable development goal. REACH Ethiopia is currently implementing USAID Urban TB LON and Eliminate TB Projects in 2 City Administration (Addis Ababa and Dire Dawa) and 3 Regional States (Harari, Sidama and SNNPR) to contribute toward ending Tuberculosis through finding missing people with TB to access early diagnosis, care and treatment services. There is a project funded by Stop TB Partnership - TB REACH WAVE 9 Grant - on improving the treatment outcome of DR-TB Patients in the two TICs (Alert and St. Peter’s Hospitals) in Addis Ababa.
REACH Ethiopia invites qualified and experienced applicants for Legal Advisor post who will advise and represent the organization on all legal matters on part -time basis.
Job Summary In consultation with the REACH Ethiopia, the Legal Advisor shall provide call/parttime based legal advisory services, including writing proceedings and representing the organization on legal cases as legal cases emerge. Responsibilities Give accurate and timely counseling to REACH Ethiopia management on a variety of legal topics (labor law, ChSA proclamations, partnerships, international ventures, etc.); Review and give advice on internal governance policies and regularly monitor compliance; Review, evaluate and advise on different risk factors regarding business decisions and operations; Provide advice to REACH Ethiopia on effective risk management techniques and offer proactive advice on possible/emerging legal issues. Communicate and negotiate with external parties, regarding legal issues, (regulators, external counsel, public authority etc.), creating relations of trust; Draft and solidify agreements, contracts and other legal documents to ensure the REACH Ethiopia’s full legal rights; Provide clarification on legal language or specifications to REACH Ethiopia Staff; Maintain current knowledge of alterations in legislation. Other related activity assigned by the immediate supervisor Number of positions : One Educational Requirements: Requirements Licensed and proven experience as a Legal Advisor in business environment; Demonstrated ability to create legal response with defensive or proactive strategies; High degree of professional ethics and integrity; Sound judgement and ability to analyze situations and information; LLM from accredited Law school; Minimum of 5 years of practical experience in providing consultancy services in the legal...
Required Experience:
Senior Level (5+ years experience
https://t.me/lawsocieties
የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ/ ለፌዴራል ጠበቆች በሙሉ
የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ/ ለፌዴራል ጠበቆች በሙሉ

በፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 መሰረት የጠበቆች ማህበር የተቋቋመ ሲሆን፣ ማህበሩን ስራ ከማስጀመር አንፃር የማህበሩን የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራው ፍትሀ ሚኒስቴር መሆኑን በአዋጁ አንቀፅ 59 (1) ላይ ተመልክቷል፡፡

በዚሁ መሰረት ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተካተቱባቸው አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው የማህበሩን የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድና ማህበሩን ስራ ለማስጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በዚሁ አግባብ የማህበሩ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔው ጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ 24 ቀበሌ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ ይካሂዳል፡፡

በአዋጁ አንቀፅ 52(3) መሰረት ማኅበሩ ሁሉንም የፈዴራል ጥብቅና ፍቃድ የተሰጣቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በአባልነት ያቀፈ በመሆኑ ማናቸውም የፌዴራል ጥብቅና ፈቃድ ያላችሁ ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ ይህ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን፣ ጉባኤው የተሳታፊዎች ቁጥር ግምት ውስጥ ሳይገባ በጉባኤው ላይ በተገኙ አባላት የሚካሄድና የተለያዩ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍ በመሆኑና ይህም ውሳኔ በሁሉም የፌዴራል ጥበቅና ፈቃድ ባላቸው የህግ ባለሙያዎችና የጥብቅና ድርጀቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን በመሆኑ፣ ይህንን ተገንዝባችሁ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ ፍትህ ሚኒስቴር ጥሪውን ያቀርባል::

በዚህ ጉባዔ ላይ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የማህበሩ ፕሬዘዳንት እና ምክትል ፕሬዘዳንት የሚመረጡ ሲሆን ሌሎችም ክንውኖች የሚካሄዱ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
“አስገድዶ ደፍሮኛል” ስትል በሐሰት የወነጀለችው ተከሳሽ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ነተቀጣች

ተከሳሽ ዘማ ደባሽ የተባለችው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 447/ለ/ ላይ የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀመችው በሐሰት መወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባታል፡፡

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሿ የሌላውን ሰው ንጽህና እያወቀች ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በአራዳ ክፍለ ከተማ ጋንዲ ሆስፒታል ምርመራ ክፍል በመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 አካባቢ ቴዎድሮስ አበበ የተባለ ግለሰብ ቤት ውስጥ በሰራተኝነት ተቀጥራ ስትኖር “አልጋ አንጥፊ ብሎ ጠርቶኝ አስገድዶ ደፍሮኛል” በማለት ቃል ሰጥታ ተጠርጣሪው ተይዞ ጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀበት በኋላ ታህሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ለኮልፌ ቀራኒዮ ፖሊስ መምሪያ ሴቶችና ህፃናት ምርመራ ክፍል ከቤቱ መውጣት ፈልጌ እንጂ አልደፈረኝም በማለት በድጋሜ ቃል የሰጠች በመሆኑ በፈፀመችው በሐሰት መወንጀል ወይም መክሰስ ወንጀል ተከሳለች፡፡

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ተከሳሿ የተከሰሰችበትን የወንጀል ድርጊት እንደ ክሱ ሙሉ በሙሉ ያመነች በመሆኑ ባመነችው መሰረት በተከሳሿ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ይሰጥልኝ ሲል አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሿ በተከሰሰችበት ድንጋጌ ስር በዝርዝር ያመነች በመሆኑ ባመነችው መሰረት ጥፋተኛ ነሽ ብሏታል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ምድብ ፈጣን የወንጀል ችሎትም ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ1 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና አምስት መቶ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡
የሰልጣኞችን ስም ዝርዝር ለማየት የሚከተለዉን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://rb.gy/dyc6oy
የኢኮኖሚ አሻጥር ምንነት እና ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ህጋዊ አንድምታዎቹ
*
የአንድ ሀገር እሴት መገለጫ መገኛው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ናቸው፡፡ አንድ አገር አገር ሆኖ እንዲቀጥል ሶስቱ ዋና ዋና አምዶች ተጣጥመው እና ተመጋግበው መቀጠላቸው የግድ እና አስፈላጊ ነው፡፡ የኢኮኖሚ መዛባት ፖለቲካውን በእጅጉ የሚጫነው ሲሆን ፖለቲካው የተረጋጋ ባልሆነ ጊዜ ሁሉ ኢኮኖሚው ተፈጥሯዊ ዑደቱ ተስተጓጉሎ በማህበራዊ ዘርፉ ትርምስ ይፈጠራል፡፡ ስለሆነም የሀገር ምሰሶ የሆኑትን እነዚህ ሶስት እሴቶች መጠበቅ ማጎልበት እና ማሳደግ ትልቁ የመንግስታት ሚና ነው፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች መነሻ ኢኮኖሚው ሲፈተን መንግስትም ፈተናውን ለማለፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ማስተዋሉ የተለመደ ነው፡፡ በተለይም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ሀይሎች አሁን ያወጁትን የቃታ ጦርነት ከማወጃቸው በፊት የኢኮኖሚ ጦርነት በማወጅ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮችን በመንደፍ እና በመተግበር መንግስትን ሲገዳደሩ የተስተዋለ ሲሆን የዚህ ውጤት ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት፣ መሰረታዊ የሆኑትን ጨምሮ የእቃና አገልግሎት ዋጋ ንረት እና እጥረት፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የስራአጥ ቁጥር መጨመር፣ የኑሮ ውድነት እና የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አስከትሏል፡፡ እነዚህ ችግሮች በምላሹ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በህዝቡ ላይ ቅሬታ እና ጉርምርምታን በመፍጠር መንግስቱ ደካማ ነው በአግባቡ እየመራ አይደለም ለሚሉ የውጪ እና የውስጥ ሃይሎች ፖለቲካዊ ትርፍ አስገኝቷል፡፡ ለመሆኑ ኢኮኖሚ ማለት ምን ማለት ነው፣ የኢኮኖሚ አሻጥርስ ምንድነው እንዴት ይፈፀማል ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል የሚለው በዚህ አጭር ፅሁፍ ይዳሰሳል፡፡

ኢኮኖሚ ምንድነው?
ኢኮኖሚ /ምጣኔ ሃብት/ ማለት የአንድ ሃገር የምርት እና ፍጆታን በማመጣጠን ሀብት የሚተዳደርበት ስርአት ሲሆን ይህን ስርዓት የሚያጠናው ዘርፍ ደግሞ ኢኮኖሚክስ ይባላል፡፡ ኢኮኖሚክስ ከማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የሚመደብ የእቃዎችን አመራረት ክፍፍል እና አጠቃቀም የግለሰቦች፣ መንግስት እና ድርጅቶች ምርጫ፣ ሀብታቸውን የሚያወጡበት እና የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ወዘተ--- የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ በተፈጥሮ የሰዎች ፍላጎት ገደብ አልባ ሲሆን ያሉ ሀብቶች ደግሞ ውስን ናቸው ኢኮኖሚክስ እነዚህ ውስን ሃብቶች ፍትሀዊነት ባለው መልኩ እንዴት ሊከፋፈሉ እንደሚችሉ ያጠናል፡፡ ዘርፉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን microeconomics እና macroeconomics በመባል ይታወቃሉ፡፡ የመጀመሪያው ስለውስን ነገሮች ለአብነት ስለ ግለሰቦች የንግድ ተቋማት የመሳሰሉትን በመለየት ስለምርታቸው ምርጫቸው ለገበያው የሚሰጡትን ምላሽ እና ውሳኔ አሰጣጣቸውን የመሳሰሉትን ያጠናል፡፡ ሁለተኛው የኢኮኖሚ ክፍል ዋና ዋና የኢኮኖሚ መመዘኛ ነጥቦችን መሰረት በማድረግ ጠቅላላ ኢኮኖሚውን ይገመግማል ያጠናል፡፡ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የሁለቱ ኢኮኖሚ ክፍሎች ውቅር ነው፡፡

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጤነኛ ነው የሚባለው ፍላጎት እና አቅርቦት የተጣጣመ ወይም በእንግሊዘኛው demand = supply ሲሆን ነው፡፡ ፍላጎቱ በዝቶ አቅርቦቱ ካነሰ ወይም አቅርቦቱ እያለ ከዋጋ አንፃር ተደራሽ ካልሆነ እንዲሁም አቅርቦቱ እያለ ፈላጊ ከሌለም ኢኮኖሚው ተፈጥሮአዊ ዑደቱን ጠብቆ በአግባቡ እየሄደ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡
ሰዎች ተሰባስበው በአንድ አገዛዝ ስር መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ጊዜ ድረስ የመንግስታት አንዱና ዋናው ሃላፊነት የሚያስተዳድሯቸውን ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማስጠበቅ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ መንግስታት ህግ ከማውጣት አንስቶ እጥረት በሚስተዋልበት አጋጣሚ ሁሉ እቃዎችን በማቅረብ አገልግሎቶችን በመስጠት የህዝቡን ፍላጎት ለመሙላት እና ቅቡልነት ለማግኘት ሲጥሩ ይስተዋላል፡፡ የኢኮኖሚው ጤነኛ መሆን አለመሆን ለህዝቡ አስተዳዳሪ /መንግስታት/ በህብረተሰቡ ተቀባይነት ለማግኘት ወይም ላለማግኘት አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ኢኮኖሚ አገር እንደሀገር መንግስት እንደመንግስት እንዲቀጥል ያለው ሚና የጎላ ከመሆኑ አንፃር ስልጣን ላይ ባለ መንግስት ቅሬታ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከውስጥም ከውጪም ያሉ የመንግስቱ ተቃዋሚዎች ኢኮኖሚውን በመረበሽ መንግስትን ተቀባይነት ለማሳጣት እንደ አንድ የፖለቲካ መታገያ ስልት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ በሌላም በኩል ገንዘብ መሰብሰብ እና ብልፅግናን አላማ ያደረጉ በየደረጃው ያሉ ነጋዴዎች ያላግባብ ሀብት ለመሰብሰብ እና ይበልጥ ለመበልፀግ በማሰብ ኢኮኖሚው ጤነኛ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉ ተግባራቶችን የሚከወኑ ሲሆን ይህ በሙያው አጠራር የኢኮኖሚ አሻጥር /economic sabotage/ በመባል ይታወቃል፡፡

የኢኮኖሚ አሻር /Economic sabotage/ ምንድነው፡- ዳንኤል ፕሮቶር የተባሉ ኢኮኖሚስት ሲተረጉሙት Economic sabotage is the practice of undermining the economy of a nation. It is a tactic used to pressure governments. በማለት ይተረጉሙታል ወደ አማርኛው ሲመለስ የኢኮኖሚ አሻጥር የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እንዳያድግ፣ ውጤታማ እንዳይሆን፣ አቅም እንዲያንሰው እና እንዲረበሽ የማድረግ ተግባር ነው፡፡
ይህ ተግባር መንግስት ላይ ጫና መፍጠሪያ ዘዴ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል እንደማለት ነው፡፡ አጥቂዎች ትኩረት አድርገው የሚነሱት ገበያውን ነው ዋናው ተግባራቸውም በገበያው ላይ የአቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር ማድረግ ወይም የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም እንዲዳካም ማድረግ ወይም ከሚፈለገው በላይ አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ወይም ፍላጎት እንዳይኖር ወይም እንዲቀንስ ማድረግ ወዘተ----ነው፡፡ ይህ ሁነት ገበያው ላይ እንዲገለፅ ከጀርባ አይነተ ብዙ አሻጥሮች ይሰራሉ፡፡ ገበያ በአግባቡ ካልተመራ የአንድን አገርን ኢኮኖሚ ለመጉዳት እና መንግስትን ለማዳከም አይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር በሀገር ውስጥ ያለን መንግስት ከመጫን ባለፈ አንድ አገር የሌላኛውን አገር መንግስት በማጥቃት እጅ ለመጠምዘዝ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥር እንደፖለቲካ መታገያ ጥቅም ላይ ከዋለ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በአለማቀፍ ደረጃ በሁሉም ሀገሮች ተግባራዊ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተለይም ኃያላን አገሮች ከነሱ ጥቅም ተቃራኒ ሆኖ በሚቆም መንግስት ላይ የመጀመሪያው የሚወስዱት እርምጃ በኢኮኖሚ አሻጥር መንግስቱን ማዳከም ሲሆን አሻጥር የሚፈፀምበት መንግስት አሻጥሩን መቋቋም ሲያቅተው ታዛዥ መንግስት ሆኖ ይቀጥላል አልያም በህዝባዊ አመፅ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ አገራት የታየው እና ብዙውን የአካባቢው አገራት የፖለቲካ ስርዓት የቀየረው አረብ ስፕሪንግ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መነሻ በኃያላኑ አገራት ተደርሶ ስፖንሰር የተደረገ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል የለም ሰፊው ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አይደለም የሚል አጀንዳ የተሸከሙ ወጣቶች ያነሱት ተቃውሞ ነው፡፡
በተለይም መንግስት ተዳክሞ በሚገኝበት ወቅት ወይም ትኩረቱን በሌላ ስራ ላይ አድርጎ በሚገኝበት ወቅት የኢኮኖሚ አሻጥር ከውስጥም ከውጪም ዘርፉን አብዝቶ፣ ይበልጥ ጠንክሮ ጎልቶ እና ተደጋግሞ ይስተዋላል፡፡ ለመሆኑ ኢኮኖሚው መንግስት በሚፈልገው አቅጣጫ እንዳይሄድ የሚያደርጉ የኢኮኖሚ አሻጥር /economic sabotage/ መፈፀሚያ ስልቶች ምን ምንድናቸው? ተግባራቶቹ እጅግ ሰፊ እና ውስብስብ ሲሆኑ ተደጋግመው በስፋት የሚፈፀሙት እንደሚከተለው በወፍበረር ተቃኝተዋል፡፡

1/ ምርቶችን ማከማቸት ፡-
ማከማቸት ማለት እቃዎች ከተመረቱበት አላማ ውጪ ምክንያታዊ ከሆነ ጊዜ በላይ ይዞ የማቆየት ተግባር ነው፡፡ ይህ ተግባር አንዱ የንግድ ባህሪ እንደመሆኑ እቃዎቹ የተከማቹበትን ጊዜ መጠን እና አላማ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢ ነው የሚባልበት አጋጣሚዎች ያሉ ሲሆን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ተገቢ ያልሆነ የማከማቸት ተግባር ይስተዋላል፡፡ የእቃዎች ከተገቢው መጠን እና ጊዜ በላይ መከማቸት በገበያ ላይ የእቃዎችን እጥረት በመፍጠር የኢኮኖሚውን ጤነኛ እንቅስቃሴ ያስተጓጉላል በተለይም ማከማቸቱ ለንሮ አስፈላጊ በመሆኑ እቃዎች ላይ ከሆነ ከኢኮኖሚ መናጋት ባለፈ የሚያመጣው ማህበራዊ ምስቅልቅል እና ፖለቲካዊ ቅሬታ ከፍተኛ ነው፡፡ ማከማቸት ለተለያየ አላማ ሊፈፀም ይችላል የመጀመሪያው ዋጋ በመጨመር የተሻለ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ሲሆን ሌላው እና ውስን የፖለቲካ አላማ ያላቸው ግለሰቦች ተናበው የሚሰሩት ሰው ሰራሽ የእቃዎች እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ቅሬታ በማሳደር መንግስትን እንዲቃወም በማድረግ የመንግስት ለውጥ እንዲመጣ አላማን ይዞ የሚፈፀም ነው፡፡

2/ ጥቁር ገበያ፡-
ይህ ተግባር ገንዘቦችን በተለይም የውጪ ሀገር ገንዘቦችን ከባንኮች ቁጥጥር ውጪ በማድረግ የፋይናንስ ስርዓቱን የመረበሽ ተግባር ነወ፡፡ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አብዛኛው የፍጆታ እቃዎች ከውጪ በሚያስገቡ እና የውጪ ንግድ ሚዛናቸው ያልተመጣጠነ በሆነ ሀገራት የውጪ ምንዛሪ ያለው ሚና እጅጉን የጎላ ነው፡፡ መንግስት የህብረተሰቡን ፍላጎት ከመድሃኒት ጀምሮ እስከ አልባሳት እና ጥቃቅን እቃዎች ጭምር አብዛኛውን የሚያሟላው ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ሲሆን እነዚህ ምርቶች የሚገዙት ደግሞ በውጪ ምንዛሪ ነው፡፡ ጥቁር ገበያ መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን የውጪ ምንዛሪ እንዳያገኝ ያለውንም በአግባቡ እንዳይጠቀም ህጋዊ ነጋዴዎች ደግሞ ከባንኮች ማግኘት የሚገባቸውን የውጪ ምንዛሪ እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡ በምላሹ ህጋዊ ነጋዴዎች ዶላር ፍለጋ ጥቁር ገበያውን ይቀላቀላሉ የጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ ከባንኮች ይልቅ ከፍተኛ በመሆኑ በውጪ ምንዛሪው የሚመጣው እቃ ዋጋም በዚያው ልክ ከፍ ይላል ወይም ከውጪ የሚገቡ እቃዎች እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል በሀገር ውስጥ የሚመረቱት ደግሞ ዋጋቸው እንዲጨምር ያደርጋል ሁኔታው በሰፋ እና ከተደጋገመ ሁሉን አቀፍ የዋጋ ግሽበት በማስከተል ኢኮኖሚውን ሊገዳደር ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ህዝቡ ከመንግስት ሊያገኝ የሚጠብቀውን መሰረታዊ አገልግሎት እና አቅርቦት እንዳያገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዲያቀርብ ይሆናል፡፡ ጥቁር ገበያ በኢኮኖሚው ላይ ከሚያደርሰው ጫና ባለፈ በተለያየ መንገድ ሽብርተኝነትን ለመደገፍ ሊውል ይችላል፡፡

3/ የአገልግሎት ወይም የምርት ማቋረጥ፡-
አንዳንድ የምርት ወይም የአገልግሎት አይነቶች በባህሪያቸው በሚወስዱት ካፒታል፣ በሚጠቀሙት የተማረ የሰው ሀይል የተነሳ በውስን ሰዎች የሚሰሩበት አጋጣሚ ይኖራል የእነዚህ ምርቶች ወይም አገልግሎቶት ሰጪ ተቋማት ባለቤቶች ለግል ወይም ፖለቲካዊ አላማቸው መሳካት ሲሉ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን በማቋረጥ የእቃዎች እና አገልግሎቶች እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲከሰት የሚያደርጉበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ለአብነት በሀገራችን ከለውጡ ማግስት ከጅቡቲ አዲስ አበባ ፈሳሽ እና ደረቅ እቃ አጓጓዥ አገር አቋጭ ተሸርካሪ ማህበራት ስራ በማቆም በሀገር ውስጥ የእቃዎች እጥረት እንዲከሰት እንዲሁም መንግስት አላስፈላጊ የወደብ ኪራይ እንዲከፍል በማድረግ የፈጠሩት ተግዳሮት በመንግስት ደረጃ እውቅና ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡

4/ ኮንትሮባንድ፡-
ኮንትሮባንድ እቃዎች መንግስት ያስቀመጠው የቁጥጥር ስርዓትን ሳያልፉ እና ተገቢው ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸው በድብቅ ወደሀገር ውስጥ የማስገባት ተግባር ነው፡፡ ይህ ተግባር የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው መንግስት በቀረጥና ታክስ መልክ ሊያገኝ የሚገባውን ገንዘብ እንዳያገኝ ያደርጋል፣ በመቀጠል የእቃዎች ዋጋ እንዲረክስ በማድረግ ህጋዊ ነጋዴዎች ከገበያ እንዲወጡ ያደርጋል አለፍ ሲልም ጥራታቸውን ያልጠበቁ እቃዎች መንግስት የማያውቃቸው ገንዘቦች፣ ጦር መሳሪያዎች እና የመሳሰሉት ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ያስከትላል፡፡

5. ህገወጥ ሃዋላ
ወደ አንድ ሃገር የሚገባ ወይም ከአንድ ሃገር የሚወጣ ገንዘብ በተዘረጋ የፋይናንስ ስርአት ውስጥ ማለፍ እና ፈቃድ በተሰጣቸው ፋይናንሻል ተቋማት አማካኝነት ማለፍ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ በዚህ ገንዘብ የመላክ እና የመቀበል ሂደት ሃገሪቷ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እንዳታገኝ ያደርጋል፡፡ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራት በህገወጥ አስተላላፊዎች አማካኝነት ፈቃድ ከተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ውጪ ሲደረግ የሃገሪቷን ኢኮኖሚ የማዳከም እና በመንግስት ላይ ጫና የመፍጠር ውጤት ያለው ተግባር ነው፡፡

6. ህገወጥ የሆነ የከበሩ ማእድናት ንግድ
የከበሩ ማእድናት እንደ ወርቅ፣ብር፣ኦፓል የመሳሰሉት ማእድናት መንግስት ቁጥጥር የሚያደርግባቸው እና በተዘረጋላቸው የንግድ ስርአት ለገበያ መቅረብ ያለባቸው ምርቶች ናቸው፡፡ በዚህ በተዘረጋ ስርአት ውስጥ የሚደረግ ግብይት ሀገሪቷ ከማእድናቱ ግብይት የምታገኘውን ትክክለኛ ገቢ ለማወቅ እና ሃብቱን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችላት ቢሆንም ይህ ግብይት ከስርአቱ ውጪ ሲደረግ ከግብይቱ መገኘት ያለበት ገቢ እንዳይገኝ በማድረግ የሃገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅህኖ የመፍፀር አቅም ይኖረዋል፡፡

7. ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር
ገንዘብ በፋንናንሽያል ተቋማጥ ውስጥ እንዲዘዋወር ይፈለጋል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ገንዘቡ በኢኮኖሚው ውስጥ ሰርኩሌት እንዲሆን በቂ የካሽ እና የብድር አቅርቦት እንዲኖር የማድረግ ሚና ይኖረዋል፡፡ አንድ መንግስት በባንክ ውስጥ ያለ ተቀማጭ ገንዘብ እና በቂ የገንዘብ ኖት የማይኖረው ከሆነ ለኢኮኖሚው ግብአት የሚሆን የብድር አቅርቦት ሊኖረው የማይችል ከመሆኑም በላይ ኢኮኖሚውን እና የባንክ ስርአቱን በተገቢው እነዳይቆጣጠረው ያደረገዋል፡፡ የባንኮችን ብድር የማቅረብ አቅም ለማዳከም እና ስርአቱ ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ የገንዘብ ኖቶችን አከማችቶ በመያዝና ከባንክ ስርአት ውጪ እንዲሆን የማድረግ ተግባር አንዱ የኢኮኖሚ አሻጥር ተግባር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር ከህግ አንፃር
የተለያዩ ሀገራት የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀምን በግልፅ ወንጀል አድርገው የደነገጉ ሲሆን /ለአብነት አውስትራሊያ እና ፊሊፒንስ/ አንዳንድ ሀገራት ደግሞ የኢኮኖሚ አሻጥርን በጥቅሉ ሳይሆን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም የሚረዱ ተግባራቶችን በመለየት ወንጀል ሲያደርጓቸው ይስተዋላል፡፡
ከሀገራችን አንፃር ህግ አውጪው ሁለተኛውን አማራጭ የተከተለ ይመስላል፡፡ የኢፌደሪ የወንጀል ህግ ርዕስ 4 ምእራፍ አንድ ከአንቀፅ 343 ጀምሮ በተከታዮቹ ድንጋጌዎች በመንግስት የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የተዘረዘሩ ሲሆን የኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀል ሆኖ አልተደነገገም፡፡ በልዩ ህጎችም የኢኮኖሚ አሻጥርን ወንጀል አድርጎ የደነገገ ልዩ ህግ የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተግባሩ የተፈቀደ ነው ማለት አይደለም ከወንጀል ህጉ ጀምሮ በተለያዩ ልዩ ህጎች ውስጥ የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም ያስችላሉ የተባሉ ተግባራቶች ወንጀል ተደርገው ይገኛል ለአብነት፡- የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 913/2006 አንቀፅ 43/4/ በገበያ ላይ እጥረት ያለባቸውን መሰረታዊ ምርቶች ማከማቸት ወንጀል እንደሆነ ይደነግጋል፣ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 168/1/ ኮንትሮባንድ ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፣ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 446 ተከታዮቹ እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/200 መሰረት በውጪ ምንዛሪ መነገድ፣ ያለፈቃድ መያዝ እና መጠቀም ወንጀል ተደርጓል፡፡

ይህም በመሆኑ የኢኮኖሚ አሻጥር ያልተከለከለ ተግባር ነው ተብሎ ሊወሰድ የሚችል አይደለም፡፡

ሲጠቃለል ኢኮኖሚ ብቻውን የሚቆም ሳይሆን ከማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥር በግለሰቦች ላይ ከሚያመጣው ማህበራዊ ቀውስ አንስቶ በመንግስት ላይ የሚያስከትለው ፖለቲካዊ መናጋት እና አለመረጋጋት ከፍተኛ ነው ህጋዊ ነጋዴውም ነግዶ ለማትረፍ ጠንካራ የመግዛት አቅም ያለው ማህበረሰብ እና የተረጋጋ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስርዓት የሰፈነባት ሀገር ይሻል፡፡ ስለሆነም መንግስት እንደመንግስት ጥብቅ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ኢኮኖሚውን ሊጠበቅ እና አሻጥረኞችንም ለህግ ማቅረብ የግዴታዎቹ ሁሉ ዋነኛ አድርጎ ሊሰራበት ይገባል በሌላ በኩል ህዝቡ እና የንግድ ማህበረሰቡ እንደ-አንድ የድርጊቱ ሰለባ የኢኮኖሚ አሻር የሚፈፅሙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባለመተባበር እና ፈፃሚዎቹ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ተገቢውን ጥቆማ ለህግ አካላት በመስጠት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ ይገባል፡፡
Legal Advocate

Hagbes Private Limited Company

Addis Ababa
Full–time

Legal Advocate Job Description: Job Requirements: At least five(5) years of related preferable experience in labor, civil and criminal court litigation .
How To Apply:
Interested and qualified applicants can apply through until January 3,2022. Posted:12.28.2021 Deadline:01.03.2022 Job Category:Legal Employment:Full time Location:Addis Ababa, Addis Ababa
ጋብቻ በሚፈርስበት ወቅት የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ሥነ-ሥርዓት ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ

በ፡ ሙሉቀን ሰይድ

በዚህ አጭር ጽሁፍ የጋራ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ አከራካሪ ከሆኑ ጉዳዩች መካከል የትኞቹ ንብረቶች የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት ይባላሉ፤ ተጋቢዎቹስ ምን ያህል ምጣኔ ድርሻ በንብረቶቹ ላይ ይኖራቸዋል፤ የጋር ንብረት ክፍፍል ጥያቄስ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባዋል የሚሉ ነጥቦችን የፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ እና ከተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔ አንጻር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2018-procedures-of-partition-of-common-property-after-divorce
የንግድ ሥራ የመስራት መብት
----------------------------

1. መግቢያ
በኢትዮጵያ ዉስጥ ግለሰብ ነጋዴዎችም ሆኑ የንግድ ማኅበራት ማንኛዉንም የንግድ ሥራ ለማካሄድ ተመዝግበዉና የንግድ ሥራ ፈቃድ ወስደዉ መሆን እንዳለበት በህግ ተደንጓል (አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም ከነ ማሻሻያ አዋጁ 1150/2011 ዓ.ም)፡፡ በተጨማሪም የንግድ ስም ፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እና ሌሎች የንግድ የንግድ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ተሟልተዉ መሆን አለበት፡፡ ይህ አጭር ጽሁፍ የንግድ ሥራ የመስራት መብት በመያየዝ ዋና ዋና ሀሳቦችን ለማስጨበጥ የሚሞከርበት ሲሆን እነርሱም የንግድ ሥራ በጠቅላላዉ፤ የንግድ ሥራ ምንነት፣የንግድ ሥራ የመስራት መብት ከህገ መንግስቱ እና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንፃር፣የንግድ ሥራን የመስራት ነፃነትና መብት እና መሰረታዊ የንግድ ሥነ-ምግባር መርሆች ላይ ይሆናሉ፡፡

2. የንግድ ሥራ በጠቅላላዉ
ግለሰብ ወይም ግለሰቦች በተናጠልም ሆነ በመደራጀት ኑሮን ለማሸነፍ፣ ሀብት ለማካበት፣ ለመበልጸግና ደስተኛ ሆኖ ለመኖር የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን በማቋቋም የንግድ ሥራ ይሰራሉ፡፡ ስኬታማ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ የንግድ ሥራ በመጀመሩ ብቻ ሳይሆን የተፈጠረዉ ስራ የሚገዛበትን፣ የሚመራበትን መሠረታዊ የሆኑ የንግድ መስፈርቶች / Elements / የንግድ ህግንና የንግድ ሥነ-ምግባርን ማወቅ ወይም መረዳት ሲቻል ነዉ፡፡ የንግድ ሥራ ከሀገሮች ዕድገት ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነዉ፡፡ የትስስሩ ሰንሰለት የሚጀምረዉ በግለሰብ ደረጃ ንግድን ከማካሄድ ሲሆን በተደራጀ መልክ እስከ ማስኬድ ድረስ ነዉ፡፡ ይህ አሁን ላሉት በግለሰብ ብቻ ሳይሆን በንግድ ማኅበራትና ኩባንያዎችን ለመስራትም መሠረት ነዉ፡፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲሱ የንግድ ህግ ዉስጥ በርከት ያሉ ስራዎችን በማቀፍና ካፒታል በማሰባሰብ በግለሰብ ደረጃም ሆነ በባለአክስዮኖች በሚመሰረቱ የንግድ ማኅበራት የወደደዉና የፈቀደዉን የንግድ ሥራ የመስራት መብት አለዉ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ግለሰብ ወይም ድርጅት (ማኅበር) በህግ ካልተከለከለ ወይም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር ሥራ በስተቀር የመረጠዉን ሕጋዊ የሆነዉን ማንኛዉንም የንግድ ሥራ የመስራት መብት አለዉ፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀጽ 22 ላይ በተገለፀዉ መሰረት ሀሳቡን ያጠናክረዋል፡፡

3. የንግድ ሥራ ምንነት
ንግድ ማለት ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ነገሮችን አምርቶ ወይም ገዝቶ የመሸጥና የመለወጥ ሂደት ነዉ፡፡ የተለያዩ የቴክኒካል አገልገሎቶችን እና ሙያዊ አገልግሎቶችን ለአገልግሎት ፈላጊዎች የመስጠት ሂደትንም ይጨምራል፡፡ ይሁን እንጂ ማንኛዉም ግዥና ሽያጭ ንግድ አይደለም፡፡ የንግድ ስራ ተከናዉኗል ለማለት ሽያጭ እና ግዢዉ በቋሚነት እና በድግግሞሽ የሚከናወን መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ላይ ንግድ እና ነጋዴ ሚለዉን ማየቱ ተገቢ ነዉ፡፡ ንግድ ማለት የሰዉ ልጅ ፍላጎትና ምኞትን ለማሟላት፣የኑሮ ደረጃዉን ከፍ ለማድረግና ከንግድ እንቅስቀሴዉም ትርፍ ለማግኘት፣ ምርት ለማቅረብና አገልግሎት ለመስጠት የሚደረግ ማንኛዉም እንቅስቃሴ ነዉ፡፡ ከዚህ የምንረዳዉ የንግድ ሥራ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የተለያዩ ምርቶችን ወይም ዕቃዎችን የመግዛትና የመሸጥ ወይም የተለያዩ የሙያ አገልግሎቶችን የመስጠት ሂደት መሆኑን ነዉ፡፡ በመሆኑም የንግድ ሥራ ማለት ነጋዴ የሚሰራዉ ማንኛዉንም ሥራ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ለንግድ ዓላማ እየተዘጋጁ የሚሸጡ ማናቸዉም ዕቀዎችም ሆኑ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ለአገልግሎት ፈላጊዎች የሚሰጡ ቴክኒካዊ (ሙያዊ) አገልግሎቶች በሕግና በንግድ ሥነ-ምግባር መግዛት አለባቸዉ፡፡ ለዚህም ዋናዉ ነጋዴዉ ነዉ፡፡ የንግድ ምዝገባና ሥራ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ን ለማሻሻል ተደንግጎ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1150/2011 ዓ.ም ነጋዴ ማለት ንግድን የሙያ ሥራዉ አድርጎ ተገቢ ጥቅም ለማግኘት በንግድ ህጉ እና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ መደብ የተዘረዘሩትን ማንኛዉንም ስራዎች የሚሰራ የሚል ነዉ፡፡ በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243 /2013 ዓ.ም አንቀጽ 5 ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች የሚሰራ ወይም አገልግሎት የሚሰጥ የንግድ ሥራ ነዉ ተብሎ በሕግ የተደነገገዉን ሥራ የሚሰራ ማንኛዉም ሰዉ ነዉ ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ በአደጉ ሀገራት ያሉት የንግድ መህበረሰቦች ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን የመሸጥ ሥራን እንደ መሠረታዊ የንግድ እንቀስቀሴአቸዉ ያደርጉታል፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2001 ብቻ በአሜሪካ 10 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያላቸዉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ተሸጠዋል፡፡ በሌሎች ያደጉና በማደግ ላይ በሚገኙ የዓለማችን አገራትም ዕቃዎችና አገልግሎቶች እንደዚሁ ይሸጣሉ፡፡

4. የንግድ ሥራ የመስራት መብት ከህገ መንግስቱ እና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንፃር
ማንም ሰዉ ሥራ የመስራት፣ሥራዉን በነፃነት የመምረጥ፣በትክክለኛና በአመቺ የሥራ ሁኔታ ዉስጥ የመሥራትና ከሥራ አጥነት የመዳን መብት ያለዉ መሆኑን የሰብአዊ መብቶች ሁሉ አቀፍ መግለጫ (1948) አንቀጽ 23 (1) ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የኢኮኖሚ፣የማኅበራዊና የባሕላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን (1966) በክፍል ሶስት አንቀጽ 6 የመሥራት መብት ማንኛዉም ሰዉ በነፃ ፈቃዱ የመረጠዉን ወይም የተቀበለዉን ሥራ ሰርቶ ሕይወቱን ለመምራት እንዲችል ዕድል መስጠትን ይጨምራል በማለት አስፍሯል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 41 ላይ ግልጽ በሆነ በማያሻማ ሁኔታ የኢኮኖሚ የማኅበራዊና የባሕል መብቶች በሚለዉ ስር፡-
• ማንኛዉም ኢትጵያዊ በሀገሪቱ ዉስጥ በማንኛዉም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራትና ለመተዳደሪያዉ የመረጠዉን ስራ የመሥራት መብት አለዉ በሚል እና
• ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያዉን ሥራዉንና ሙያዉን የመምረጥ መብት አለዉ በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የንግድ ሥራ እንደሌሎች ሥራዎች ሁሉ የንግድ ሥራ ለመስራት የፈለገ እና ለንግድ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በማሟላት ለሕግና ለሞራል የማይቃረኑ የንግድ ሥራዎች በመሰመራት የሚሰራ ሥራ መሆኑ በዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ህጎች መሰረት ያለዉ ነዉ፡፡
5. የንግድ ሥራን የመስራት ነፃነትና መብት
በህግ ተለይተዉ የተከለከሉ ነገሮች ወይም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድርን የሚመለከቱ ክልከላዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ማንኛዉም ሰዉ ማንኛዉንም የንግድ ሥራ የመስራት ነፃነት እንዳለዉ በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ አንቀጽ 21 ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን ይህ የተሰጠዉ ለሀገር ዉስጥ ነጋዴዎች ነዉ፡፡ በዉጭ ሀገር ስለተቋቋመ ወይም በዉጭ ሀገር ስለሚሰራ ማኅበርና ሀገር ዉስጥ ተመስርቶ በዉጭ ሀገር ስለሚቋቋም ቅርንጫፍ በአዲሱ ንግድ ሕግ አንቀጽ 579 ላይ የዉጭ ሀገር የግል ድርጅት፣ የንግድ ማኅበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ቅርንጫፍ ከፍቶ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ የመሳተፍ መብት አላቸዉ፡፡ ሆኖም መጀመሪያ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም በሌላ አግባብ ያለዉ የባለስልጣን መስሪያቤት በሚያዘዉ የንግድ መዝገብ ዉስጥ መመዘገብ ያለበት መሆኑም ተገልጿል፡፡