አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Hence, pre-employment background checks will be conducted, and employees are required to read, understand, sign and implement different polices including safeguarding and child protection policy, Protection from Sexual Exploitation and abuse policy, sexual harassment policy, code of conducts and any other policy, rules and regulation of the organization. 

Job Requirements:

JOIN US

Do you want to join an exciting organization that brings high level impact to the community and add value to your professional advancement?  Then join us if you have:

·          Bachelor's/Master’s degree in law-related field

·         7 years’ experience as a Legal Counsel /lawyer and able to attend to routine administrative labour law among other related litigation tasks

·         Must be prepared to make ethical and moral decisions

·         Previous working experience as a Legal Counsel/ lawyer   in business/INGO sector

·         In-depth knowledge of administrative law and procedures

·         Good organisational, prioritization and time-management skills

·         Arbitration and mediation skills

·         Exemplary writing and editing skills, with proficiency in Microsoft Office: - Word, PowerPoint, Excel, Outlook etc.

·         Excellent communication, presentation, and interpersonal skills and analytical skills in both written and spoken; English, Amharic, and Afaan Oromo

·         Working well under pressure

·         Attention to detail

·         Ability to use your initiative.

·         Discretion in handling confidential matters and proactive approach to problem solving.

·         Excellent judgment and ability to anticipate legal issues or risks

·         High degree of professional ethics, integrity, and responsibility

Note: This description is not an exhaustive list of the skill, effort, duties and responsibilities associated with the position.

REMUNERATION and BENEFITS:

GOAL will pay a competitive basic salary based on the salary grading with addition benefits.

A chance to develop tangible experience.

Being part of a team who continue to make a real difference to the lives of the most vulnerable people.   

How To Apply:

APPLICATION PROCEEDURE:

Interested and qualified applicants need to submit ONLY once their non - returnable application with CV for one vacancy. The vacancy reference number along with the title & Duty station need to be written in the application letter and/or subject of the email. Applicants can apply using the following option.

Applicants can directly apply online usingwww.ethiojobs.net  orgoaljobs@et.goal.ie

GOAL strongly encourages female candidates to apply!

Only short-listed candidates will be contacted for an interview and exam.

Shortlisted candidates will need to submit other supporting documents upon request at later stage.

GOAL is not able to contribute towards any costs incurred by candidates during the recruitment process

Posted: 12.09.2021

Deadline: 12.19.2021

Job Category:
Human Resource and Recruitment, Legal, Management
Employment:

Location: GOAL Ethiopia

http://www.goal.ie/Ethiopia/159
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ
Federal Document Authentication And Registration Agency


ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት

ቅርንጫፍ 1-ላንቻ
ቅርንጫፍ 2-መሳለሚያ
ቅርንጫፍ 3-መገናኛ
ቅርንጫፍ 4-ስድስት ኪሎ
ቅርንጫፍ 5-ጉለሌ
ቅርንጫፍ 6-አየር ጤና
ቅርንጫፍ 7-ቃሊቲ ቅርንጫፍ 8-ካሳንቺስ
ቅርንጫፍ 9-ንፋስ ስልክ ላፍቶ
ቅርንጫፍ 10-ልደታ
ቅርንጫፍ 11-ሲኤምሲ
ቅርንጫፍ 12-ቦሌ
ቅርንጫፍ 13-ጎጃም በረንዳ (መርካቶ)
ቅርንጫፍ 14 – ጀሞ

ተራ በመጠበቅ እና በወረፋ ጊዜዎን እንዳያጠፉ ቤትዎ እና ስራ ቦታዎ ሁነው
online ማንኛውም አይነት ጉዳይ እንሞላለን print አድርገው ብቻ የሚገለገሉበት ሲስተም ላይ አስገብተን በሚመችዎት መንገድ እንልክልዎታለን።
በቴሌግራም ብቻ ጉዳዮን ይጨርሳሉ።
https://t.me/GudayAsfetsami
@GudayAsfetsami
@GudayAsfetsami
በአዲሱ የንግድ ሕግ የተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች

1. መግቢያ
በሥራ ላይ የነበረዉ የንግድ ሕግ (1952 ዓ.ም) አገሪቷ ከደረሰችበት የንግድ እንቅስቃሴና ዘርፉ ከሚፈለገዉ ዕድገት አንፃር ብዙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ እና የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የንግድ ሕጉን መፈተሽ እና ማሻሻያዎችን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2014 ሆኖ ታትሞ ሥራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፡፡ አዲሱ የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር በርካታ ለውጦች ተደርገዉበታል። የሕጉ መውጣት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን በአወንታዊ መንገድ ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ አለዉ። በዚህ አጭር ጽሁፍ የንግድ ሕጉን ዓላማዎች፣የንግድ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት፣የንግድ ሕጉ ማሻሻል ያለዉ ጠቀሜታ እና አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች የምንመለከት ይሆናል፡፡

2. የንግድ ሕግ ዓላማዎች
አንድ ግለሰብ ነጋዴ ወይም የንግድ ማኅበር በዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴው ከተለያዩ አካላት ጋር የውል እና ከውል ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ይፈጥራል።

ለምሳሌ፦ አንድ የንግድ ድርጅት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ከሚያቀርቡ ድርጅቶች፣ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን ከሚገዙት ደንበኞች ወይም ሸማቾች፣ ለድርጅቱ ብድር ከሰጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከድርጅቱ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ካላቸው ሰዎች፣ ከንግድ ተወዳዳሪዎቹ፣ ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ከድርጅቱ ሠራተኞችና ሥራ አመራሮች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል፤ ድርጅቱ ከባለሀብቶቹ የተለየ የራሱ የሕግ ሰውነት ያለው የንግድ ማኅበር ሲሆን ደግሞ ከማኅበርተኞቹ ጭምር ግንኙነት ይኖረዋል። ከላይ ከተገለጹት የንግድ ድርጅት ከሚፈጥራቸው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አኳያ የንግድ ሕጎች ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች አሏቸው፦ አንደኛው ዓላማ አንድ የንግድ ድርጅት ከላይ በተመለከትናቸው ውስብስብ ግንኙነቶች ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሀብት እንዲያፈራ እና አትራፊ እንዲሆን የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከላይ ለተጠቀሱት ከአንድ የንግድ ድርጅት ጋር የተለያዩ ግንኙነቶች ለሚፈጥሩት አካላት መብቶች እና ቅቡልነት ያላቸው ፍላጎቶች ተገቢውን የሕግ ጥበቃ ማድረግ ነው። የንግድ ሕግ መድብል (ኮድ) እነዚህን ሁለት አንኳር ዓላማዎች ይጋራል። ይህ ሲባል ግን የንግድ ሕግ መድብል (ኮድ) ሁሉንም ከላይ የተመለከትናቸውን ግንኙነቶች አሟልቶ ይገዛል ማለት አይደለም።

3. የንግድ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት እና ጠቀሜታ
የንግድ ህጉ አሁን ያለውን ዘመናዊውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሊመልስ በሚችል መልኩ ካልተቀረፀ ወይም ካልተዘጋጀ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና የሚኖረው በመሆኑ የንግድ ህግ ዘመናዊ መሆን ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም አሁን የሚመጡ አዳዲስ ዕድገቶችን ታሳቢ ተደርጎ መረቀቅ እና በተጨባጭ ያንን ሊመልስ በሚችል መልኩ መሰራት አለበት፡፡ የእኛ ሀገር የንግድ ህግ ከብዙ ዓመታት በፊት የተዘጋጀ በመሆኑ አሁን ያለውን አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በንግድ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ሊመልስ የማይችልባቸው ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዛ መካከል አንዱ በንግድ ህጉ የተካተቱ በርካታ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ባለመሆናቸው፣የሚፈፀሙትም ቢሆን አሁን ካለው አጠቃላይ የንግድ እና ኢኮኖሚ እንቅሳሴ ጋር የማይሄዱ በመሆናቸው፣ በተለይም በሀገራችን ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ያለው ከማህበራት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው የንግድ ህግ ሊመልሳቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን መመለስ ባለመቻሉ የመጣ ችግር ነው፡፡ በመሆኑም ክፍተቶቹን በመፈተሽ አሁን ካለው እና ዘመኑ ከሚጠይቀው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ዘመናዊ የንግድ ህግ ማደራጀት በማስፈለጉ የንግድ ህጉ እንደገና እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

በዚህ ሕግ መሰረት የትኛውም እንቅስቃሴ ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለምሳሌ የንግድ ማህበራት የሚቆጣጠራቸው ሕጉ ነው፡፡ የንግድ ምዝገባ ለማድረግም መነሻ ህጋቸው ይህ ህግ ነው፡፡ የዚህ ሕግ ዘመናዊ ሆኖ መደራጀቱ ለነጋዴው፣ ለንግድ ማህበራት፣ ለ3ኛ ወገኖች እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ መደራጀታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘመኑ የሚጠይቀው ሕግ ተደንግጎ የወጣ፣ አሁን ካለው የስራ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚሄድ እና ለነጋዴው ግልፅ የሆነ የንግድ ሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ለልማታዊ ባለሀብቶች የሚያመች ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

4. አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች
ነባሩ የንግድ ህግ ጥራዝ በስድስት መጽሀፍት የተደራጀ ሲሆን፣ በአንደኛ መጽሀፍ ስለንግድ ስራና ነጋዴዎች፣ በሁለተኛ መጽሁፍ ስለንግድ ማኅበራት፣በሶስተኛ መጽሀፍ ስለኢንሹራንስና የማጓጓዣ አገልግሎት፣በአራተኛ መጽሀፍ ስለባንክና ተላላፊ ሰነዶች (የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች)፣በአምስተኛ መጽሀፉ ስለኪሳራ ህግ ፣ በስድስተኛ መጽሀፍ መሸጋገሪያ ድንጋጌዎች ሆኖ ዝርዝር ጉዳዮችን አካትቶ የተሰነደ ነው። በተደረገዉ ጥናት መጽሐፍት 3 እና 4 የንግድ ሕግ አካል ሳይሆኑ ራሳቸዉን ችለዉ የፋይናንስ አገልግሎት መድብል / Code / እንዲሆኑ እና መጽሀፍ አንድ፣ሁለት እና አምስት የንግድ ሕግ ተብሎ እንዲሻሻል ተደርጎ በአዲሱ የንግድ ሕግ ወጥቷል፡፡ በአዲሱ አዋጅ ያልተካተቱት የባንክ፣ የኢንሹራንስና፣ የማጓጓዣ ዘርፎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቀድሞው አሠራር መሠረት የሚቀጥሉ ሲሆን አዲሱ የንግድ ሕግ በርካታ ማሻሻያዎችን እና አዳዲስ አሰራሮችን የያዘ ሆኖ ወጥቷል። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እንመልከት።

 አንድ ግለሰብ ለብቻው ኩባንያ መክፈት እንዲችል ተፈቅዷል
አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 534 እንደሚያሳየዉ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያን መመስረት እንዲችል ተፈቅዷል። ይህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያግዛቸዋል ።
 የንግድ ትርጓሜን መቀየር
በተሻረው ሕግ የተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች 21 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውጪ ያሉት ንግድ አይደሉም ተብለው እንደሚገመቱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። አሁን ግን በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 5 መሰረት የንግድ አይነቶችን ወደ 37 አድገዋል። በዚሁ ሕግ የንግድ ትርጉም ክፍት ነው። በግልፅ ካልተከለከለ በስተቀር ያተርፋል ብሎ እንደሙያ የያዘውን ሥራ አስመዝገቦ መቀጠል ይችላል። ይህ መሆኑ ደግሞ አዳዲስ የንግድ አይነቶችንና የፈጠራ ሐሳቦችን ያበርታታል ።
 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የሙያ ሽርክና ማኅበራት (አንቀፅ 221)
በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ከተካተቱ ጉልህ ለውጦች መካከል አንዱ የሆነው ይህ አዲስ የሽርክና ማህበር አይነት፣ ሰዎች በተለይም የሙያ ስራዎችን ለመስራት በሙያ ከሚመስሏቸው ሌሎች ሰዎችና ለሙያው ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ሊሰጡ ከሚችሉ አጋሮቻቸው ጋር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው የሚያቋቁሙት፣ ኃላፊነቱም በሽርክና ማኅበሩ ሃብት ላይ ብቻ የተወሰነ የንግድ ማኅበር ነው በሚል በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 221 ላይ ተደንግጓል። ከቀደመው ሕግ በተቃራኒው አዲስ የጸደቀው አዋጅ ግለሰቦች በሙያቸው ተደራጅተው እንዲሠሩ በግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል።

https://t.me/lawsocieties
በሌላ በኩል የቀድሞው ሕግ የአክስዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሁሉም የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ ግዴታ የጣለ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ ባለድርሻ መሆን ሳይጠበቅባቸው፤ ባለ ድርሻ ያልሆኑ ሰዎች በሙያቸው እስከ አንድ ሦስተኛ ድረስ የሚሆነውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታን እንዲይዙ ይፈቃዳል። ይህ አይነቱ የሽርክና ማኅበር የህግ አገልግሎትን፣ የሂሳብ መዝጋትና ኦዲት ወይም ሌላ አይነት ቴክኒካዊ እውቀትን በሚጠይቁና የሙያ ፈቃድ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የስራ ዘርፎች ላይ በቅንጅት መስራት ለሚሹ ሙያተኞች አይነተኛ ምርጫ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም።
 የሆልዲንግ ካምፓኒ ስለ መፈቀዱ
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 5 ስር በተመለከቱት ሥራዎች ላይ በመሰማራት በቀጥታ ራሱ ምርትና አገልግሎት ባያቀርብም በዚህ ተግባር በተሰማሩ ሌሎች የንግድ ማኅበራት ዉስጥ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ድርሻ የሚይዝ ኩባንያ ወይም ሆልዲንግ ካምፓኒ እንደ ነጋዴ እንደሚቆጥር አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 9 ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም ሆልዲንግ ካምፓኒ በቀጥታ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ ይችላል፡፡

 ተራ የሽርክና ማህበርን የሚመለከተው የህጉ ክፍል ስለመቅረቱ፦
ነባሩ የንግድ ህግ ስለንግድ ተቋማት በሚዘረዝርበት ሁለተኛ መጽሀፉ ተራ የሽርክና ማህበርን ሰፊ ሽፋን የሰጠው ሲሆን በትንታኔው ግን ይህ አይነቱ ማኅበር በንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ እንደማይችል በግልፅ አስቀምጧል። እንግዲህ የንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ አይችልም የተባለ የሰዎች ስብስብ፣ በንግድ ህግ ጥራዝ ውስጥ እንደ ንግድ ተቋም መቀመጡ የህግ አመክንዮ የማይገኝለት በመሆኑ ውሳኔው ትክክለኛነቱ አያጠያይቅም።

 አክስዮን ማኅበርን በሚመለከተው የህጉ ክፍል አክሲዮኑ ለህዝብ ክፍት ስለሚሆን ማሕበር ሰፊ ሽፋን ስለመሰጠቱ፦
ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚሰራባቸው የንግድ ተቋማት አይነቶች ውስጥ ዋናውን ስፍራ የሚወስደው አክስዮን ማኅበር መሆኑ ይታወቃል። የባንክ እና የኢንሹራንስ ስራን የመሳሰሉ የፋይናንስ አገልግሎት ስራዎችን ለመስራት የተፈቀደለት ብቸኛው የንግድ ተቋም ፎርም አክስዮን ማኅበር ነው። በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 248 ላይ እንደተመለከተዉ የአክስዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት በሆነ የአክስዮን ሽያጭ የሚመሰረትበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህን መሰሉን ማህበር ለማቋቋም በሚሰሩት አደራጆች መብትና ግዴታ እንዲሁም ሀላፊነት ዙሪያ የተብራሩ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡

 በንግድ ድርጅቶች መካከል የሚፈጠርን ዝምድና (Affiliation) ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር የሚሆን የህግ ክፍል ስለመካተቱ
የንግድ ማኅበራትን በሚመለከተው መጽሀፍ ሁለት ውስጥ በርዕስ ዘጠኝ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተካተተው የኩባንያዎች መዛመድ ጽንሰ-ሀሳብ ሰፋ ያለ ዳሰሳና ጥናት የሚጠይቅ ጉዳይ ቢሆንም በዚህ የንግድ ህግ መካተቱ ምን አይነት ለውጦች ሊያስከትል እንደሚችል ልናነሳ ይገባል። አንድ ኩባንያ የሌላኛውን ኩባንያ አክስዮን የገዛ ከሆነ፣ ወይም እርስ በእርስ አክስዮኖች የተገዛዙ ከሆነ፣ ወይም በኩባንያዎቹ መካከል የሆልዲንግና ሰብሲዲየሪ (ተቀጽላ) ግንኙነት ካለ ወይም የአንድ ቡድን ኩባንያ (Group Company) አባላት ከሆኑ የተዛመዱ (Affiliated) ኩባንያዎች ይባላሉ። አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 550 የኩባንያዎችን ዝምድና በመተንተን ሂደትም አንድን ኩባንያ የሆልዲንግ ኩባንያ አቋም የሚያሰጡት ሁኔታዎችና የአክሲዮንና የድምጽ መብቶች መጠን፣ ሆልዲንግ ኩባንያ በተቀጥላ (Subsidiary) ላይ ስለሚኖረው ልዩ ልዩ መብትና ስልጣን እንዲሁም ሆልዲንግ ኩባንያ ከዘጠና በመቶ በላይ የድምጽ መብት በሚኖረው ጊዜ ሌሎች የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ስለሚኖራቸው አማራጭ እና በተቀጥላ ኩባንያ ውስጥ ስላሉት የስራ አመራር አባላት ተጠያቂነት በዝርዝር ያስቀምጣል።

 የኪሳራ ህግን በሚመለከተው መጽሀፍ ውስጥ ዕዳን እንደገና ስለማደራጀት የሚመለከት ተጨማሪ ጽንሰ-ሀሳብ ስለመካተቱ፦
ማንኛውም ነጋዴ ይብዛም ይነስም በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ሲሰማራና ገንዘብና ጊዜውን ሲመድብ ይሳካልኛል የሚል ብርቱ እምነት ቢኖረውም ቅሉ፣ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች ግን እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ይቀርና ወደኪሳራ ያመራሉ። ነባሩ የኪሳራ ህግ፣ አንድ ነጋዴ ያሉበትን ዕዳዎች መክፈል ማቋረጡን እንደዋና ምክንያት በመያዝ፣ የአበዳሪዎችንና ሌሎች መብት ጠያቂዎችን ጥቅም ለማስከበር ሲባል የመክሰር ውሳኔ ሊተላለፍ እንደሚችል ያትታል። አዲሱ የንግድ ህግ በዚህ ረገድ አዲስና እጅግ ጠቃሚ የሚባል ዕዳን እንደገና ስለማደራጀት የሚገልፅ ክፍል በመክሰር ሂደት ውስጥ እንዲካተት አድርጓል። ለማሻሻያው ዋና መነሻ የሚሆነው የህጉ አላማ በጊዜያዊ የገንዘብ ችግር ምክንያት ዕዳ መክፈል ያቋረጡ ወይም ለማቋረጥ የተቃረቡ ነጋዴዎች እንደገና ተደራጅተው እንዲያገግሙ እድል መስጠት ነው። እዳን እንደገና ማደራጀት የሚባለው ባለዕዳው ያለበትን የዕዳ መጠን፣ አይነት እና የአከፋፈል ሁኔታዎች በሌላ የዕዳ ወይም የመብት አይነት፣ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታዎች በፍርድ ሲለወጡ ነው። እዚህ ላይ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ዕዳን እንደገና የማደራጀት ተግባር የመክሰር ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ወይም ከተሰጠ በኋላ ሊከናወን የሚችል ሲሆን በዋነኝነትም የገንዘብ መብት ጠያቂዎች ፍላጎትና የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደቅድመሁኔታ የሚጠቀሱ ተግባራት ናቸው።

በአጠቃላይ አዲሱ የንግድ ህግ በይዘትም ሆነ በቅርፅ መሰረታዊ የሚባሉ ለውጦችን የያዘ ሰነድ ሲሆን አንዳንድ ማሻሻያዎቹ የሌሎች ሀገራት የንግድ ህግጋትን መነሻ ተጨማሪ ጽንሰ ሀሳቦችን ያካተተ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪም ከተሻረው ሕግ በተቃራኒ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚከስሩ የንግድ ሰዎች ነጻ የሚሆኑበትን መንገድ አመቻችቷል፡፡ እነዚህን ጨምሮ ለንግድ እንቅስቃሴው የማይመቹ ሕጎችን ያሻሻለው የአዲሱ አዋጅ መውጣት በሀገር ውስጥ ያለውን የንግድ እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳልጣል።

ፍትህ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
Legal Officer job at Center for African Leadership Studies (CALS) & xHub Addis
Legal Officer
Center for African Leadersh...

Addis Ababa
Full–time
JOB DETAILS:
Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble.
Summary
Date Posted: Friday, December 10, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble

Job Requirements
• Bachelor of Laws (LL.B.) or Master of Laws (LL.M.)
• 3 - 5 years of experience in a law firm or multinational organization (private sector or NGO).

Work Hours: 8

Experience in Months: 36

Level of Education: Bachelor Degree

Job application procedure
Attach the following documents in one folder to the mentioned email
Tempo of degree
Well detailed Resume and cover letter
With the subject line "Legal Officer Dec 2021" email your application to ephratag.xhubaddis@gmail.com 

Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble. Duties and Responsibilities In order to ensure that the best legal action is taken for the organization, Legal Officers perform a variety of important tasks; Provide Legal Advice- Using oral or written platforms, Legal Officer will be expected to brief a team of staff members on legal issues, potential liabilities, and possible courses of action. This involves translating complicated legal jargon (gibberish) into a language that everyone can understand, as well as taking all possible legal problems into consideration before making any recommendations. All recommendations which the Legal Officer makes must be in complete compliance with the law, and must also strive to minimize risk for their organization. Process Documents- Any sort of legal work involves a great deal of paperwork. Legal Officers will frequently need to write and review settlement documents, contracts, agreements, stock certificates, and more. This task makes up a significant portion of the day-to-day work of Legal Officers and requires both focus and precision. Perform Research- Since laws and regulations are always changing and being modified, it’s up to the Legal Officer to continuously research legal resources such as articles, codes, statutes, judicial decisions, and more. Doing so will allow the Legal Officer to stay up to date on all current laws and make well-educated legal recommendations. Identify Risks- Ideally, legal issues should be gripped in the bud before they even begin. This is why it’s essential for Legal Officers to regularly analyze the actions and decisions of the company in order to identify problem areas, suggest alternative courses of action and mitigate risk as much as possible. Review and provide legal advice on MOUs, Contracts, and tender documents. Liaise with relevant departments to ensure that where legal risks have been identified, appropriate courses of action have been taken. Provide legal protection and risk management advice to management especially on contract management.

https://t.me/lawsocieties
ማስታወቂያ
ጉዳይ አስፈፃሚዎችን ከሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማዎች እና ክልል ከተሞች መመዝገብ እንፈልጋለን።

ከዚህ በታች ባለው ቦት ይመዝገቡ❗️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Casemanager_bot
ይመዝገቡ🔷
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/GudayAsfetsami
የውክልና ስልጣን፣ አይነት እና አተገባበሩ
--------------****---------------
1. የውክልና ምንነት እና ፋይዳው
የሀገራችን የፍታብሔር ህግ አንቀጽ 2199 እንደሚደነግገው ወክልና ወካይ የተባለው ሰው ተወካይ ለተባለው ሰው እንደርሱ በመሆን አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በእርሱ ስም እንዲያከናውን የሚሰጥ ስልጣን ነው፡፡ ተወካይ በውክልና የተሰጠውን ተግባር ሲያከናውን ሊመራባቸው የሚገባው መርሆች በህጉ የተቀመጡ ሲሆን እነዚህም፡- ተወካይ የሚያከናውነውን ተግባራት በወከለው ሰው ስም መሆን እንዳለበት፣ ተወካይ ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን እንዳለበት፣ ተወካይ ወካዩ ከሰጠው ስልጣን ውጪ በመውጣት ለሚያከናውነው ተግበር ወካይ የማይጠየቅ መሆኑ (ስልጣን ባይሰጠውም ተግባሩን ካላፀደቀለት) የተቀመጡ መርሆች ናቸው፡፡
ውክልና የተለያዩ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ በሚያስፈልገው ስራ ላይ በወኪሉ በኩል መከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸው እንደ ተፈጥሮዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆኑ በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ፣ እድሜቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ በሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስስቻል እንደ ውክልና ጥቅሞች ይጠቀሳሉ፡፡
2. የውክልና የስልጣን ምንጭ
ሶስት አይነት የውክልና ስልጣን ምንጮች ያሉ ሲሆን እነዚህም እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡
2.1. በህግ የሚገኝ የውክልና ስልጣን
ይህ አይነቱ የውክልና ስልጣን የሚመነጨው ወካይ ለተወካይ ውክልናውን በእርሱ ፍላጎት እና ፍቃድ የሚሰጠው ሳይሆን የወካዩ ፍቃድ እና ፍላጎት በህግ ድንጋጌ መሰረት የሚገኝ የውክልና ስልጣን ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ተወካይ በህግ የሚሾምለት ሰው በተለያዩ ምክኒያቶች ጥቅማቸውን ማስከበር የማይችሉ እንደ ህጻና፣፤ በእድሜ ወይም በህመም ምክንያት የመወሰን ችሎታቸውን ያጡ ሰዎች ወይም ህጋዊ ሰውነት ያለቸው ድርጅቶች ሲሆኑ ህግ የነዚህን ግለሰቦች እና ህጋዊ ድርጅቶች መብት እና ጥቅሞች ሊያስከብሩ ይችላሉ በማለት የሚገምታቸውን ሰዎች እና የድርጅት ሥራ አስኪያጆች የውክልና ስልጣን ይሰጣቸዋል፡፡ በተለይ ጥቅማቸውን ለማስከበር የማይችሉ እንደ ህጻናት፣ በእድሜ ወይም በህመም ምክንያት የመወሰን ችሎታቸውን ያጡ ሰዎች የቅርብ ዘመዶች፣ በተወላጆች ወይም በትዳር አጋሮቻቸው የሚወከሉ ይሆናል፡፡
2.2. በውል የሚገኝ ውክልና
ይህ የውክልና አይነት በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ወካይ ለተወካይ እርሱን የሚመለከቱ አንድ እና ከዛም በላይ የሆኑ ተግባራትን እንዲያከናውንለት በስምምነት የሚሰጠው የውክልና አይነት ነው፡፡ ይህ ውክልና ልዩ ውክልና ሲሆን ወካይ ለተወካይ በቀል፣ በጽሑፍ ወይም በዝምታ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ይህ ውክልና በወካይ እና ተወካይ ስምምነት ላይ የሚመሰረት ነው፡፡
2.3. በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚገኝ የውክልና ስልጣን
ይህ የውክልና ስልጣን በፍ/ሕ/ህጉ አንቀጽ 2253 እስከ 2255 መሰረት በፍ/ቤት የሚሰጥ ሲሆን አንድ የተወሰነ ስራን ወይም የተመደቡ ስራዎችን በሌላ ሰው ስም ሆኖ እንዲያከናውን ዳኞች ጠባቂ ባለአደራ ለተባለው ሰው ውክልና የሚሰጡበት የውክልና ስልጣን አይነት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው እንደራሴ ይደረግለት የተባለው ሰው በአካባቢው የሌለ ወይም በህመም ወይም በሌላ ምክንያት ወኪል ማግኘት የማይችል ከሆነ እንደራሴ እንዲደረግበት ለሚያስፈልገው ሰው ባል ወይም ሚስት የሆኑ ወይም ዘመዶች ብቻ ወኪል እንዲሾምለት ለፍ/ቤት ማመልከት የሚችሉ ሆኖ በዳኞች የተሾመውም ወኪል አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን እንዲያከናውን ብቻ የሚፈቀድለት ይሆናል፡፡
3. ውክልና ሊያሟላ የሚገባው መስፈርቶች
ውክልና ከልዩ የውል ህጎች ውስጥ አንዱ ስለሆነ አንድ ህጋዊ ውል ሊያሟላ የሚገባውን በፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 1678 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል፡፡ ይህም አንድ ውል የፀና እንዲሆን ውል ለመዋዋል ችሎታ ባለው ሰው መሆን እንዳለበት፣ ጉድለት የሌለው ስምምነት መኖር፣ የሚቻል እና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ፣ የውል ፎርም በህግ የታዘዘ ከሆነ ህጉ እንደሚያዘው ልዩ ፎርም መሆን አለበት፡፡
የፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 2200 ወካይ ለተወካይ የውከልና ስልጣኑን በቃል ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ነገር ግን ህጉ የውከልና ስልጣኑ በተለየ ፎርም መሰጠት አለበት በማለት የሚያዝ ከሆነ ይህን ማሟላት ይኖርበታል በማለት አስቀጧል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የውክልና ውል አንድ ውል ሊያሟላ የሚገባውን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ የተሰጠው የውክልና ውል ፈራሽ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የውክልና ውሉ በሚፈርስበት ጊዜ ተወካይ ከ3ኛ ወገን ጋር ያደረገው ውል እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችላል በሚለው ጥያቄ ላይ በህጉ በግልፅ ያልተቀመጠ የፍ/ህግ አንቀጽ 1816 ላይ በተቀመጠው መሰረት በቅን ልቦና የተንቀሳቀሰውን 3ኛ ወገን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ በሚሆንበት ጊዜ ውሉ ፈራሽ የማይሆን መሆኑ በዚህ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚነሳ ሲሆን በወካይ እና በተወካይ መካከል ያለው ግንኙነት ተወካይ የውክልና ስልጣን ውል መሰረት ከ3ኛ ወገን ጋር ከሚያደርገው ግንኙነት ተለይቶ መታየት ስላለበት የውክልናው ውል ቀሪ እና ፈራሽ መሆን ተወካይ እና 3ኛ ወገን ያደርጉትን ውል ቀሪ ሊያደርገው አይገባም የሚል ክርክርም ይነሳል፡፡
4. የውክልና አይነቶች
ሁለት የውክልና አይነቶች ያሉ ሲሆን እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡
4.1. ጠቅላላ ውከልና
ይህ የውክልና አይነት በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው ነው፡፡ በፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 2204 መሰረት የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት፡- የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ/መጠበቅ፣ ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት፣ በብድር የተሰጠውን ሀብት የመሰብሰብ፣ ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ የማስቀመጥ፣ ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ የመስጠት፣ ሰብሎችን መሸጥ፣ ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሸጥ ናቸው፡፡
4.2. ልዩ ውክልና
ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ወጪ የተለየ ተግባር እንዲፈጽምለት በመግለጽ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ፣ አስይዞ መበደር፣ በካፒታሎች ላይ እንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በመሃበር የመግባት፣ ስጣታን ማድረግ፣ በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር እና የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡
5. የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች
5.1. የተወካይ ግዴታዎች
ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ማሳየት- ተወካይ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ እና ግልጽ መሆን ያለበት ሲሆን ወካዩ ውክልናውን ለማስቀረት ወይም የውክልና ቃሉን ለመቀየር የሚያስችሉ ነገሮች በሚከሰቱበት ወቅት ለወካዩ የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት፡፡ እንዲሁም ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት የወካዩን ጥቅም ለማስከበር መንቀሳቀስ ያለበት ሲሆን ያለ ወካዩ ፍቃድ እና እውቅና ምንም ጥቅም መውሳድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካይ በውክልናው ምክንያት ያገኛቸውን መረጃዎች ወካዩን በሚጎዳ መልኩ
ሊጠቀምባቸው አይገበም፡፡
የውክልናው ሒሳብ አያያዝ- ተወካይ የሚያደረጋቸውን የገንዘብ እንቅሳቃሴዎችን ገቢ እና ትርፎችን፣ ወጪ እና ኪሳራዎችን የመመዝገብ እና ለወካዩ የማሳወቅና ገቢ የማድረግ ሀላፊነት ያለበት ሲሆን ተወካይ ለወካዩ ሊሰጠው የሚገባውን ገንዘብ ለራሱ አውሎት እንደሆነ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ አንድም ማስጠንቀቂያ ሳያስፈልገው ከነወለዱ እንዲከፍል የሚደረግ ይሆናል፡፡
አስፈላጊ ትጋት ማሳየት- ተወካዩ የተሰጠውን ሀላፊነት በከፍተኛ ትጋት እና ጥንቃቄ የማከናወን ሀላፊነት ያለበት ሲሆን ይህን ባለመድረጉ በወካይ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የሒሳብ ማቅረብ ግዴታ- ተወካይ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ የስራውን አካሄድ መግለጫና ሒሳብ በየጊዜው የማቅረብ ግዴታ እና የተሰጠውን ውክልና በአግባቡ መፈጸሙን በየጊዜው ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
የተወከለበትን ሥራ በእራሱ የመፈጸም ሀላፊነት- ተወካይ የተወከለበትን የስራ ተግባር እራሱ የመፈጸም ሀላፊነት አለበት፣ ነገር ግን በእርሱ ፋንታ ሌላ ሰው ወክሎ ማሰራት የሚችለው፡- የወከለው ሰው ሲፈቀደለት፣ በልማዳዊ ደንብ እና አሰራር መሰረት ሌላ ሰው ተክቶ ማሰራቱ ተወካዩ እራሱ እንደሰራው የሚያስቆጥር እንደሆነ፣ ተወካዩ ጊዜ የማይሰጥ ድንገተኛ መሰናክል የገጠመው እንደሆነ እና በወቅቱ ለወካዩ ለማሳወቅ በቂ ጊዜ የሌለው እና የወካዩን ጥቅም ለማስከበር የስራው ሁኔታ የሚያስገድደው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ ውጪ ተወካይ በራሱ ፍቃድ ወክሎ የሚያሰራው ሰው በሚያከናውነው ተግባር ለሚደርሰው ጉዳት ተወካይ እራሱ እንደፈጸመው ተቆጥሮ ሙሉ ሀላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከላይ በተገለጹት ሁኔታ ሌላ ሰው ወክሎ ተወካዩ በስራው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ተወካዩ የሚጠየቀው የወከለውን ሰው ሲመርጥ መድረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ እና ለተተኪው ተገቢውን የስራ መመሪያ እና ትዕዛዝ ሲሰጥ ለሚፈጽመው ስህተት እና ጉድለት ይሆናል፡፡
5.2. የወካይ ግዴታዎች
የድካም ዋጋ መክፈል- ወካዩ በውላቸው ላይ የተመለከተውን የድካም ዋጋ ለተወካይ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት ሲሆን በውላቸው ላይ ይህ ያልተካተተ እንደሆነ የስራ ዋጋ በተለምዶ አሰራር ለሞያው ሊከፈለው የሚገባ በቦታው የዋጋ ልክ መስታወቂያ ታሪፍ እና ልማዳዊ ህግ መሰረት ታስቦ ለተወካይ የሚከፈለው ይሆናል፡፡
ተቀዳሚ ተከፋይ እና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ- ለተወካይ ስለ ውክልናው ሥራ ማስኬጃ እና ማከናወኛ የሚሆን ተቀዳሚ ተከፋይ ወጪ ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን ተወካይ ለተወከለበት ሥራ ሲል ላወጣው ወጪ ወጪው ከወጣበት ቀን ከሚታሰብ ወለድ ጋር ተስቦ ሊከፈለው ይገባል፡፡
ግዴታ እና ኪሳራ- ተወካይ ለወካዩ የስራ ጥቅም እና ውጤት ሲል የገባውን የውል ግዴታዎች ውስጥ ነጻ ሊያወጣው እና ተወካይ የተወከለበትን ስራ በሚያከናውንበት ወቅት የራሱ ጥፋት ከሌለበት ለሚደርስበት አደጋ ኪሳራውን ሊከፍለው ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ወካይ የስራው ጉዳይ ተገቢውን ውጤት አላስገኘም በማለት ለተወካይ ሊከፍለው የሚገባውን ገንዘብ መከልከል የማይችል ሲሆን ተወካይ በስራው ወቅት ላደረሰው ጥፋት ልክ ሊከፍለው ከሚገባው ገንዘብ ጋር ማቻቻል ይችላል፡፡ ተወካይም በበኩሉ ወካይ ሊከፍለው የሚገባውን ገንዘብ ያልከፈለው እንደሆነ በስራ ምክንያት እጁ የገባውን አቃ ሊከፈለው የሚገባውን መጠን ልክ የሚያወጣ እቃ በመያዣነት ሊይዝ ይችላል፡፡
6. ስለውክልና መቅረት
6.1. ውክልናን በመሻር
ወካይ አስፈላጊ መስሎ ከታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን የመሻር እና ተወካይ የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ ነገር ግን ተወካይ የተሰጠውን የውክልና ውል ለመመለስ ፍቃደኛ በማይሆንበት ወቅት ወካዩ በምን አይነት ሁኔታ ሊያስገድደው እንደሚችል ህጉ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካላት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የውክልና ውሉን ተወካይ እንዲመልስለት በፍርድ ቤት ለመጠየቅ ይችላል፡፡
የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በሙሉ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም ፡፡
6.2. ወኪሉ የውክልና ስልጣኑን ሲተው
ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን መተው የሚችል ሲሆን የውክልናውን ሥራ መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልናውን ስራ መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍጹም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡
6.3. ውክልና ቀሪ የሚሆንባቸው ሌሎች ምክንያቶች
የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ በስፍራው ያለመኖር የተረጋገጠ እንደሆነ፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ኪሳራ ደርሶበት በንግድ ኪሳራ ላይ መውደቁእና የተረጋገጠበት እንደሆነ ውክልና ቀሪ ይሆናል፡፡
ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ ከመካከላቸው አንዱ የውክልና ስራውን ከተጠቀሱት ምክንያቶች በአንዱ መቀጠል ያልቻለ እንደሆነ እና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎችንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡
Source:- FDRE Attorney General
ክፍል ፫

ጋብቻ በንብረት በኩል ስለሚኖረው ውጤት

አንቀጽ ፶፯ የባልና ሚስት የግል ሀብት (፩) ያለግብይት የተገኙ ንብረቶች

ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኙዋቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው ይቀራሉ፡፡

አንቀጽ ፶፰ (፪) በግብይት የተገኙ ንብረቶች

፩. ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ አንዱ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሸጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ሀብቱ ይሆናል፡፡

፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ይባልልኝ ብሎ አንደኛው ወገን ጥያቄ ሲያቀርብ እና ፍርድ ቤት ሲያፀድቀው ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ ፶፱ የግል ሀብትን ስለማስተዳደር (፩) መሠረቱ

፩. እያንዳንዱ ተጋቢ የግል ሀብቱን ራሱ ለማስተዳደርና ገቢውንም ለመቀበል ይችላል፡፡

፪. እያንዳንዱ ተጋቢ የግል ሀብቱን ራሱ ሊያዝበት ነፃነት አለው፡፡

አንቀጽ ፷ (፪) የግል ሀብት አስተዳደርን በጋብቻ ውል ስለመወሰን

፩. ባልና ሚስት አንደኛው የሌላውን ተጋቢ የግል ሀብት በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድርለት እና እንደአስፈላጊነቱ እንዲያዝበት በጋብቻ ውላቸው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተመለከተው አኳኋን ንብረት የማስተዳደር ሥልጣን የተሰጠው ተጋቢ በሌላኛው ተጋቢ ሲጠየቅ ስለንብረቱ አስተዳደር ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ ፷፩ (፫) ስለውክልና ሥልጣን

ከተጋቢዎች አንዱ የግል ሀብቱን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድርለት ለሌላኛው ተጋቢ ውክልና መስጠት ይችላል፡፡

አንቀጽ ፷፪ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት

፩. ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው ይሆናሉ፡፡

፪. በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፶፰ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ነው ካልተባለ በስተቀር፣ ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁሉ የጋራ ሀብታቸው ይሆናል፡፡

፫. በስጦታው ውል ወይም በኑዛዜው ቃል በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር፣ በስጦታ ወይም በኑዛዜ ለተጋቢዎቹ የተሰጧቸው ንብረቶች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ ፷፫ የሕግ ግምት

፩. አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

፪. የግል ንብረት መሆኑን ሦስተኛ ወገኖች የሚያውቁት ወይም ሊያውቁት የሚገባ ካልሆነ በስተቀር፣ ባልና ሚስቱ ወይም ከሁለቱ አንዱ ይኸው ንብረት የግል ነው በማለት በሦስተኛ ወገን ላይ መቃወሚያ አድርገው ሊያቀርቡት አይችሉም፡፡

አንቀጽ ፷፬ ስለባልና ሚስት ገቢ (፩) መደበኛ የገቢ አስተዳደር

፩. ባልና ሚስት እያንዳንዳቸው ገቢያቸውን በየራሳቸው ይቀበላሉ፡፡

፪. ባልና ሚስት በየግላቸው የሚያገኙትን ገቢ የግል ወይም የጋራ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡

፫. ከባልና ከሚስት አንደኛው ሲጠይቅ፣ ሌላኛው ተጋቢ ያገኘውን የገቢ መጠን የማስታወቅ ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ ፷፭ (፪) ልዩ ሁኔታ

፩. ከባልና ከሚስት አንዱ፣ ገቢውን ሌላኛው ተጋቢ እንዲቀበልለት ሥልጣን ለመስጠት ሙሉ ነፃነት አለው፡፡

፪. ከባልና ከሚስት በአንደኛው ጠያቂነት የአንደኛውን ገቢ ሌላኛው ተጋቢ እንዲቀበልና ለመቀበሉም ደረሰኝ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ሊወስን ይችላል፡፡

፫. በሌላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር፣ ከባልና ከሚስት የአንደኛው ገቢ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲከበር በፍርድ ቤት ሊታዘዝ ይችላል፡፡

አንቀጽ ፷፮ የጋራ ሀብትን ስለማስተዳደር

፩. ከባልና ከሚስት አንዱ፣ የጋራ ሀብታቸውን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድር ግልጽ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ባልና ሚስቱ የጋራ ሀብታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ፡፡

፪. ከባልና ከሚስት አንዱ ችሎታ የለውም ተብሎ ሲወሰን ወይም ንብረት የማስተዳደር መብቱን ሲገፈፍ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት የጋራ ሀብታቸውን ለማስተዳደር የማይችል ሆኖ ሲገኝ ሌላኛው ተጋቢ የጋራ ሀብቱን የማስተዳደሩን ተግባር ያከናውናል፡፡

አንቀጽ ፷፯ የማስታወቅ ግዴታ
ከተጋቢዎች አንዱ ብቻ የጋራ ሀብታቸውን በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሀብቱን አስተዳደር በተመለከተ ለሌላኛው ተጋቢ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ ፷፰ (፩) የተጋቢዎች ስምምነት አስፈላጊ ስለመሆኑ
በሌላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር፣ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የተጋቢዎቹ ስምምነት አስፈላጊ ነው፤
ሀ) የጋራ የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ፣ ለመለወጥ፣ ለማከራየት በመያዣ ወይም በዋስትና ለመስጠት ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በዚሁ ንብረት ላይ ሌሎች ሰዎች መብት እንዲያገኙ ለማድረግ፤

ለ) ዋጋቸው ከብር ፭፻ (አምስት መቶ) በላይ የሆኑ የሚንቀሳቀሱ የጋራ ንብረቶችን ወይም የገንዘብ ሰነዶችን፣ ለመሸጥ፣ ለመለወጥ በመያዣ ወይም በዋስትና ለመስጠት ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ለማስተላለፍ፤

ሐ) ከብር ፻ (አንድ መቶ) በላይ ዋጋ ያለውን የጋራ ንብረት ወይም ገንዘብ ለሌላ ሰው በስጦታ ለማስተላለፍ፤

መ) ከብር ፭፻ (አምስት መቶ) በላይ ለመበደር ወይም ለማበደር ወይም ለሌላ ሰው ዋስ ለመሆን፡፡

አንቀጽ ፷ (፪) የስምምነት አለመኖር ስለሚያስከትለው ውጤት

፩. አንደኛው ተጋቢ ከዚህ በላይ የተመለከተውን ድንጋጌ ባለማክበር የውል ግዴታ ገብቶ የተገኘ እንደሆነ፣ ሌላኛው ተጋቢ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ጥያቄ ግዴታው ሊፈርስ ይችላል፡፡

፪. ግዴታው እንዲፈርስ የሚቀርበው ጥያቄ ጠያቂው ወገን ግዴታው መገባቱን ከአወቀበት ቀን ጀምሮ ከስድስት ወር በኋላ ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ግዴታው ከተገባ ከሁለት ዓመት በኋላ ሊቀርብ አይችልም፡፡

አንቀጽ ፸ የባልና ሚስት ዕዳ

፩. ከባል ወይም ከሚስት በግል የሚጠየቅ ዕዳ፣ ከባለዕዳው ተጋቢ የግል ሀብት፣ የግል ሀብቱ ዕዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከጋራ ሀብታቸው ይከፈላል፡፡

፪. ዕዳው የመጣው ለትዳራቸው ጥቅም ከሆነ ከጋራ ሀብታቸው የጋራ ሀብታቸው፣ ዕዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከባል ወይም ከሚስት የግል ሀብት ይከፈላል፡፡

አንቀጽ ፸፩ ለትዳር ጥቅም እንደተደረገ የሚቆጠር ዕዳ
የሚከተሉት ዕዳዎች ለትዳር ጥቅም እንደተደረጉ የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

ሀ) ለባልና ለሚስት እንዲሁም ለልጆቻቸው የዕለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለማሟላት የተገቡ ዕዳዎች፤

ለ) ባል ወይም ሚስት ቀለብ ለመስጠት ያለባቸውን ግዴታ ለመወጣት የተደረጉ ወጪዎች፤

ሐ) ከባልና ከሚስት በአንደኛው ወይም በዕዳ ጠያቂው አለመልካችነት ለትዳር ጥቅም ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የተቀበለው ሌላ ዕዳ፡፡
አንቀጽ ፸፪ የትዳር ወጪዎችን ስለመሸፈን
ተጋቢዎች የትዳራቸውን ወጪ ለመሸፈን እያንዳንዳቸው እንደየአቅማቸውና ችሎታቸው አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው፡፡
አንቀጽ ፸፫ በተጋቢዎች መካከል ስለሚደረጉ ውሎች
ባልና ሚስቱ ተጋብተው በሚኖሩበት ጊዜ በመካከላቸው የሚያደርጓቸው ውሎች፣ ፍርድ ቤት ካላፀደቃቸው በስተቀር ውጤት አይኖራቸውም፡፡
Vacancy title:
Legal Advisor
Type: FULL TIME , Industry: Human Services , Category: Legal 
Jobs at:
GOAL Ethiopia
Deadline of this Job:
19 December 2021  

Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Thursday, December 09, 2021 , Base Salary: Not Disclosed
Remuneration And Benefits:
• GOAL will pay a competitive basic salary based on the salary grading with addition benefits.
• A chance to develop tangible experience.
• Being part of a team who continue to make a real difference to the lives of the most vulnerable people.

Job Experience: No Requirements

Work Hours: 8

Level of Education: Bachelor Degree

Job application procedure
Interested and qualified applicants need to submit ONLY once their non - returnable application with CV for one vacancy. The vacancy reference number along with the title & Duty station need to be written in the application letter and/or subject of the email. Applicants can apply using the following option. Applicants can directly apply online using   goaljobs@et.goal.ie  
Attorney

Abay Bank S.C

Position: Attorney

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Hawassa, Dire Dawa and Gonder, Ethiopia

Posted date: 1 day ago

Application Deadline: Dec, 20/2021
Abay Bank S.C is one of the private commercial banks established to provide effective and efficient full-fledged banking services, focused on development, business growth and profitability to meet the expectation of all its stakeholders as well as the aspiration of its employees. The bank invites interested and qualified applicants to fill the following position.

 

Job Summary

The Attorney gives legal advice to the bank's concerned organs, participates in designing negotiation strategies, assists the Loan Recovery in the negotiation process by providing legal opinion and other professional advice, comments on the resolution proposal of the loan recovery task, designs and prepares loan, pledge/mortgage, and other contracts

Required Education and Experience

Minimum LLB with three (3) years of related work experience

Required No. 3 (Three)

Salary: Attractive and Per Bank's Salary Scale

Place of Work: Hawassa, Dire Dawa, and Gonder District Offices

How to apply

Interested and Qualified applicants fulfilling the above criteria can apply in person at 

Abay Bank S.C, Head Office

Zequala Complex Building, located around Bambis OR

Online via HR@abaybank.com.et

Only shortlisted candidates will be communicated for further
Attorney (#3)

ETB 15,000 - ETB 50,000 monthly

 Abay Bank S.C

 Addis Ababa, Ethiopia

 Dec 13, 2021

Full Time Banking Jobs in Ethiopia Legal Jobs in Ethiopia

JOB DESCRIPTION

Abay bank S.C

Attorney (#3)

Job Summary

The Attorney gives legal advice to the bank’s concerned organs, participates in designing negotiation strategies, assists the Loan Recovery in the negotiation process by providing legal opinion and other professional advice, comments on the resolution proposal of the loan recovery task,designs and prepares loan, pledge/mortgage and other contracts;

Required Education and Experience

Minimum LLB with three (3) years’ of  related work experience

Place of Work: Hawassa, Dire Dawa, and Gondar District Offices

NB

Salary: Attractive and per Bank’s Salary Scale

Application Deadline:       December 20, 2021

Interested and qualified applicants fulfilling the above criteria can apply IN-PERSON at ABAY BANK S.C. Head Office, Zequala Complex Building, located around Bambis; Or ONLINE via HR@abaybank.com.et . Only short listed candidates will be communicated for further.
Our Court - Give your verdict!
_______________________
Mr. A was an employee of the United Nations Development Program (UNDP) in Ethiopia. After working for a while, the office terminated Mr. A’s employment contract. However, Mr. A believes that the termination was unlawful. Therefore, he wanted to sue the organization based on the Ethiopian Labour Law. People consulted him, saying that since UNDP is a member of the United Nations, it is immune from prosecution.
👨‍⚖🧑‍⚖‍ If you were a judge for this case what would be your judgment, can Mr. A really sue the UNDP? Please give your verdict by saying yes, he can or no, he cannot?
👨‍⚖🧑‍⚖‍ If you were a judge for this case what would be your judgment, can Mr. A really sue the UNDP? Please give your verdict by saying yes, he can or no, he cannot?
Anonymous Poll
73%
YES, ☑️ HE CAN
27%
NO, 👎 HE CAE NOT
የንግድ መዝገብ በአዲሱ የንግድ ህግ
------------------------------------

የንግድ መዝገብ (commercial register) በተለያዩ አለም ሀገራት የተለመደ አሰራር ነው፡፡ በሀገራችንም በ1952 ዓ.ም በወጣው የንግድ ህግ የተካተተ ሲሆን የንግድ ህጉ ከወጣበት 1950ቹ በኋላ በሀገራችን በርካታ ነገሮች የተቀየሩ ከመሆኑ አንፃር 2008 ዓ.ም በወጣው የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እና በማሻሻያው 1150/2011 በጊዜ ሂደት መካተት የነበረባቸውን ሁኔታዎች ለማሟላት ተሞክሮ ነበር፡፡ ሆኖም የንግድ ህጉ ሀገራችን አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ማካተት እንደሚገባው ስለታመነበት የቀደመው የንግድ ህግ በአዲሱ የንግድ ህግ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የንግድ መዝገብ ምንነት፣ በውስጡ የሚያካትታቸውን ዝርዝር ነገሮች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡

የንግድ መዝገብ (commercial register) ምንነት

የንግድ መዝገብ (commercial register) በአዲሱም ሆነ በቀድሞ የንግድ ህግ ትርጉም አልተሰጠውም፡፡ በንግድ ምዝገባ እና ፋቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀፅ 2(20) ንግድ ምዝገባ ማለት በንግድ ህጉ ወይም በዚህ አዋጅ መሰረት የሚደረግ ምዝገባ ነው በሚል ትርጉም የሰጠ ቢሆንም የንግድ መዝገብን ምንነት በግልፅ አላስቀመጠም፡፡ ሆኖም በተለያዩ ሀገራት ካለው ግንዛቤ እና በእኛም ሀገር ህግ የንግድ መዝገብን አስመልከቶ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች አንፃር የንግድ መዝገብ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዝርዝር መረጃ የሚያዝበት የመረጃ መመዝገቢያ ሥርአት መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

ንግድ መዝገብን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለው ህግ

የንግድ ምዝገባን የተመለከቱ ድንጋጌዎች በንግድ መዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እንዲሁም በንግድ ህጉ ውስጥ ተካተው የሚገኙ እንደመሆኑ ተፈፃሚነት ያለው ህግ የቱ ነው የሚል ጥያቄ መነሳቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት በአዲሱ ንግድ ህግ ረቂቅ ማብራሪያ ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ ይኸውም የንግድ ምዝገባን የሚመለከቱ በየጊዜው የማይለዋወጡ መሰረታዊ መርሆዎች በንግድ ህጉ ውስጥ አንዲካተቱ የተደረጉ በመሆኑ በሁለቱም ላይ የተገለፁ ጉዳዮችን ቢሆኑ እንኳን ገዢ የሚሆነው የንግድ ህጉ ይሆናል፡፡ ሌሎች ተለዋዋጭነት ያላቸው ከዕለት ተዕለት ተግባራዊ አፈፃፀም ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች በተመለከተ ግን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጁ ከነማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 1150/2011 ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡

የንግድ መዝገብ አደረጃጀት

በአዲሱ የንግድ ህግ የንግድ መዝገብ በፌደራል ደረጃ የሚቋቋም ሲሆን ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የንግድ መዝገብ ሊያቋቁሙ ይችላሉ፡፡ በፌደራል ደረጃ የሚቋቋመውን የንግድ መዝገብ እንዲያቋቁም ሀላፊነት የተሰጠው ለንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የነበረ ሲሆን በአዲሱ የአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ዓ.ም መሰረት ይህ ተግባር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ይሆናል፡፡ ሚኒስቴሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ተፈፃሚነት ያለው ንግድ መዝገብ አቋቁሞ የማስተዳደር ሀላፊነት የተጣለበት ሲሆን በዚህ መልኩ በሚያቋቁመው መዝገብም ነጋዴዎችንና የንግድ ማህበራትን መመዝብ ይጠበቅበታል፡፡ ሚኒስቴሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የመመዝገብ ሃላፊነቱን በከፊል ለሌላ የፌደራል ተቋም በውክልና ማስተላለፍ ይችላል፡፡ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ራሳቸው በሚያወጡት ህግ የንግድ መዝገብ አቋቁመው የንግድ መዝገቡን አስተዳደርና የመመዝገብ ስልጣን ያለውን አካል እንዲሁም ሀላፊነቱን መወሰን የሚችሉ ቢሆንም ምዝገባውን ማከናወን ያለባቸው ግን የንግድ ህጉን በጥብቅ በመከተል መሆን አለበት፡፡

በሌላ በኩል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ተፈፃሚነት ያለው ማዕከላዊ የንግድ ምዝገባ ቋት ማደራጀትና ማስተዳደር ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡ ይህ ማዕከላዊ የንግድ መዝገብ መረጃ ቋት በፌደራል፣ በክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚኖሩ የንግድ መዛግብት የሚሰፍሩ መረጃዎች ተጠቃለው የሚገቡበት ቋት ነው፡፡ ሚኒስቴሩ ቋቱን ከማደራጀትና ከማስተዳደር በተጨማሪ በየክልሉ ባሉ ልዩ ልዩ መዛግብት የተፃፉትን እያንዳንዱን የተመዘገበውን ሰው የሚመለከቱ መረጃዎች በሙሉ በመቀበል ወደ ቋት ማስገባት፣ የንግድ ማህበራትን የሚመለከቱ ፅሁፎችን፣ ሰነዶችን፣ ማስታወቂያዎችን ተቀብሎ ቋት ውስጥ ማስገባት እና ስለ ንግድ መዛግብት የወጡ ህጎችና ደንቦች በትክክል መፈፀማቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በአንፃሩም የንግድ ምዝገባ ያከናወነ የፌደራልም ሆነ የክልል ተቋም የመዘገባቸውን የእያንዳንዱን ነጋዴ ወይም ንግድ ማህበር መረጃዎችና ሰነዶች ምዝገባውን እንዳከናወነ ለሚኒስቴሩ የማስተላለፍ ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በዚህ መልኩ የሚደራጀው የንግድ መዝገብም ለህዝብ ክፍት መሆን አለበት፡፡

በንግድ መዝገብ የሚገቡ ነገሮች

ተመዝጋቢው የሚያደርገው ዋና ምዝገባ፣ በተጨማሪ ወይም በማሟያ የሚደረጉ ምዝገባዎች፣
የተለወጡ ወይም የተሰረዙ ጉዳዮች በንግድ መዝገብ ሊገቡ ይገባል፡፡
ዋና ምዝገባ
ከስሙ እንደምንረዳው ዋና ምዝገባ ነጋዴው በዋናነት በመጀመሪያ የሚመዘገብበት ምዝገባ ነው፡፡ በዚህ ምዝገባ የነጋዴው ሙሉ ሥም፣ የትውልድ ቀንና ቦታ፣ ዜግነት፣ የግል አድራሻ፣ ያገባ ከሆነ ጋብቻው የተፈፀመበት ቀንና ቦታ፣ ጋብቻ ውል መኖር አለመኖሩ፣ ካለ የተቀመጠበት ቦታ ወይም የያዘው ሰው ሥም፣ ሚስት ወይም ባል ስለ ንግድ ሥራው ያቀረበው ተቃውሞ ካለ ያቀረቡት መቃወሚያ፣ መቃወሚያው ቀሪ ከሆነም ቀሪ የሆነበት፣ ጋብቻው እንዲፈርስ ተወስኖ ከሆነ የመፍረስ ውሳኔው፣ የንግዱ ሥም፣ የንግዱ ምልክት፣ የንግዱ አላማ፣ የንግድ መደብሩ አድራሻ፣ ንግዱን ያቋቋመው ወይም የገዛ ወይም የተከራየ ስለመሆኑ እና ተከራይቶ ከሆነ የአከራይ ሥምና አስፈላጊ ሰነዶች፣ በተመዘገበበት ቦታ ወይም ሌላ ቦታ ሌሎች መደብሮች፣ ቅርንጫፎች ወይም መኪሎች ያሉት ከሆነ አድራሻቸው፣ በቅርንጫፎቹ ሥራ አስኪያጅጆች ያሉ ከሆነ ሥልጣናቸው ቅርንጫፉን በማስተዳደር ብቻ የተወሰነ መሆኑ፣ ያለው ከሆነ ለመነገድ የንግድ ፈቃድ ተሰጠበት ቀን፣ አካለ መጠን ያልደረሰ ከሆነ የንግድ ሥራ እንዲሰራ ለሞግዚቱ የተፈቀደበት ቀን፣ ችሎታ የሌለው ስለመሆኑ በፍርድ ቤት የተከለከለ ከሆነ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲሁም አዲስ ሥራ አስኪያጅ ከተሾመ ስለመሾሙ የተመለከቱ መረጃዎች ይካተታሉ፡፡

ተመዝጋቢዎቹ የንግድ ማህበራት በሚሆኑ ጊዜም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የመልሶ ማደራጀት ሥነ ሥርአት፣ የመክሰር ሥነ ሥርአት፣ ቀላል የመክሰር ሥነ ሥርአት ወይም ከዕዳ ነፃ መደረግ ሥነ ሥርአት ውሳኔዎች ካሉ መመዝገብ ይገባቸዋል፡፡ ነጋዴው አካለ መጠን አለመድረስ፣ የነጋዴው ችሎታ ማጣት፣ ነጋዴው ማግባቱ ወይም ጋብቻው መፍረሱ፣ የጋብቻ ውል መኖር፣ የሥራ አስኪያጅ መሻር ወይም ከሥራ መሰናበት፣ የሥራ አስኪያጅ ስልጣን አንድ ቅርንጫፍ ወይም ወኪል ጽ/ቤት በማስተዳደር ብቻ የተወሰነ መሆኑ እንዲሁም በአንቀፅ 15 መሰረት ባለው ወይም ሚስት የንግድ ሥራው የጋራ አለመሆኑን አስመልክቶ የሚያቀርቡት መቃወሚያ በንግድ መዝገብ ካልተመዘገበ በስተቀር ቅን ልቦና ባላቸው ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳ አይችልም፡፡
ሌላው ከዋና ምዝገባ ጋር በተያዘ ልብ ሊባል የሚገባው አንድ ነጋዴ ዋና ምዝገባ ሊመዘገብ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን በተለያየ የንግድ ሥራዎች የሚሰራ እንኳን ቢሆን በዋናነት በንግድ መዝገብ መመዝገብ የሚችለው በአንድ ቦታ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ በሌሎች ክልሎች የሚነግድ ወይም የተለያዩ ቅርንጫፎች ወይም ወኪል መ/ቤቶች ካሉ ዋና መዝገቡ እየተጠቀሰ በአጭር ቃል በየክልሎቹ መመዝገብ አለበት፡፡ ከዋና ምዝገባ በኋላ የሚከሰቱ ለውጦች ካሉም ለውጦቹ በንግድ መዝገብ መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በንግድ መዝገብ የመግባት ሥነ ሥርአት
በሀገራችን ግዛት ውስጥ የንግድ ሥራ የሚሰራ ማንኛውም ሰው (ኢትዮጵያዊ ወይም የውጪ ዜጋ) ወይም የህግ ሰውነት ያለው የንግድ ማህበር የመመዝገብ ግዴታ አለበት፡፡ የሚመዘገበውም ተመዝጋቢው ዋና መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ መዝገብ ለመያዝ ስልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ በፅሁፍ በሚሰጠው መግለጫ መሰረት ነው፡፡ ነጋዴዎች ንግድ ከመጀመራቸው በፊት በነጋዴነት እንዲመዘገቡ ማመልከቻ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ማመልከቻውን ያላቀረበ በነጋዴነት ሊመዘገብ አይችልም፡፡ ማመልከቻውን ሲያቀርብም መዝጋቢው ተመዝጋቢው የሚያቀርበውን ማመልከቻ ትክክለኛነት፣ በህግ የታዘዙ ነገሮች በመግለጫው ውስጥ መካተታቸውን፣ ለመግለጫው ደጋፊ የሆኑ የፅሁፍ ማስረጃዎች ከመግለጫው ጋር መጣጣማቸውን እና አመልካቹ ምዝገባ የጠየቀበትን የንግድ ሥራ ለመስራት የሚያስችለውን ህጋዊ መመዘኛ ማሟላቱን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ መዝጋቢው አካል ተጨማሪ ሰነዶችና መረጃዎች አስፈላጊ ሆነው ባገኘ ጊዜ እንዲቀርቡ መጠየቅ ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት የተከናወነ ምዝገባ ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ከሚኖረው ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ የተመዘገቡ ነጋዴዎችም በሚሰሩባቸው ወረቀቶች ላይ ሁሉ የተመዘገቡበትን ቦታ እና የምዝገባ ቁጥራቸውን መግለፅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምዝገባውን በተመለከተ በመዝጋቢው እና በአመልካቹ መካከል የሚፈጠሩ ክርክሮች በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ ሲሆን ምዝገባውን የሚያከናውነው አካል እና ሰራተኞቹ ከምዝገባ ጋር በተያያዘ ለሚደርሱ ጉዳቶች በአንድነትና በተናጠል ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ መመዝገብ የሚገባው ሆኖ ሳይመዘገብ የቀረ ነጋዴ ደግሞ እንደ ነጋዴ ተቆጥሮ ሀላፊ ይሆናል፡፡
በመዝገብ የመግባት ውጤት
ከላይ በተገለፀው መልኩ የሚደረግ ምዝገባ በተመዝጋቢው እንዲሁም በሚመዘገበው መረጃ ረገድ የራሱ ውጤት የሚያስከትል ነው፡፡ ተመዝጋቢውን በተመለከተ ተቃራኒ ማስረጃ ካልቀረበ በስተቀር ማንኛውም በመዝብ የገባ ሰው ነጋዴ እንደሆነ ግምት ይወሰዳል፡፡ ሆኖም በነጋዴነት የተመዘገበው ሰው ወይም ማህበር ግን ነጋዴ አይደለሁም ሲል ማስረጃ እንዲያቀርብ አይፈቀድለትም፡፡ በዚህም ነጋዴ መሆኑ የሚያስከትለው ሀላፊነት ሁሉ ይኖርበታል፡፡
ከተመዘገበው ጉዳይ አንፃር ማንኛውም ሰው በመዝገብ እንዲገባ ያደረገው መረጃ ትክክል ሳይሆን ቢቀር የተመዘገበው መረጃ ትክክል እንደሆነ በመቀበል በሰሩ ሰዎች ላይ የሚፈጠረውን ስህተት በመቃወሚያነት እንዲያቀርብ አይፈቀድም፡፡ ሶስተኛ ወገኖችም በንግድ መዝገብ የገባውን ጉዳይ አላውቅም ነበር ብለው ማስረጃ እንዲያቀርቡ አይፈቀድላቸውም፡፡

ከመዝገብ መሰረዝ
በንግድ መዝገብ የተመዘገበ ነጋዴ በዋናነት በሶስት ምክንያቶች ከንግድ መዝግብ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
 ነጋዴው ከሞተ፡- የተመዘገበው ነጋዴ የሞተ እንደሆነ ከንግድ መዝገብ የሚሰረዝ ሲሆን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካልገጠማቸው በስተቀር የሟች ሚስት ወይም ባል ወይም ወራሾች ነጋዴው በሞተ በ60 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ምዝገባው እንዲሰረዝ ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 መነገድ መተው፡- በንግድ ሥራ የተሰማራ ነጋዴ በተለያየ ምክንያት የንግድ ሥራውን ሊተው ወይም መደብሩን ሊያከራይ ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሥራውን ከተወበት ወይም መደብሩን ካከራየበት ጊዜ ጀምሮ በ60 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመዝገብ እንዲሰረዝ ማመልከት ይጠበቅበታል፡፡
 በትዕዛዝ ስለመሰረዝ፡- ይህ በመዝጋቢው አካል የሚፈፀም ነው፡፡ ይኸውም ነጋዴው የንግድ ሥራውን ማቆሙን እና የንግድ ሥራውን ለመስራት ችሎታ የሌለው ስለመሆኑ በፍርድ ቤት እንደተወሰነበት ባወቀ ጊዜ ወይም በሌላ ህግ ለምዝገባ መሰረዝ በቂ ምክንያት ናቸው ተብለው የተደተደነገጉ ሁኔታዎች ከተሟሉ በራሱ አነሳሽነት ነጋዴውን ከመዝገብ መሰረዝ ሃፊነት አለበት፡፡ እዚህ ላይ በንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አዋጅ 980/2008 አንቀፅ 18 የተዘረዘሩት ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ መዝጋቢው አካል የመሰረዝ ውሳኔ ሲሰጥ ለነጋዴው ለእራሱ እና ለሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ አለበት፡፡

ከንግድ መዝገብ ጋር በተያያዘ የወንጀል ተጠያቂነት

ከንግድ መዝገብ ጋር በተያያዘ በንግድ ህጉ መሰረት መመዝገብ እያለበት ሳይመዘገብ የቀረ ወይም መመዝገብ ያለበትን ነገር ሳያስመዘግብ የቀረ እንዲሁም ስለሚመዘገበው ጉዳይ ሆነ ብሎ ትክክለኛ ያልሆነ መግለጫ የሰጠ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው ህግ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚኖርበት ተደንግጓል፡፡ አግባብነት ያለው ህግ የሚባለው በዋናነት በልዩ ሁኔታ ንግድ ነክ ተግባራትን የሚመለከተው የንግድ መዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ሲሆን በወንጀል የሚስቀጡ ተግባራትንና ቅጣታቸውን በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ለአብነት ሀሰተኛ መረጃ በማቅረብ በንግድ ምዝገባ የተመዘገበ ወይም የንግድ ሥሙን ያስመዘገበ ወይም የሞከረ ሰው ያለአግባብ ያገኘው ጥቅም መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከብር ስልሳ ሺ እስከ ብር መቶ ሀያ ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ከሰባት አመት እስክ አስራ ሁለት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ የአዋጁ አንቀፅ 49(3) ደንግጎ ይገኛል፡፡ ሌሎች ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች በአዋጁ አንቀፅ 49 ሥር የተዘረዘሩ በመሆኑ ህጉን በሚጥሱ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡

በአጠቃላይ የንግድ መዝግብ በንግድ ህጉ መሰረት በንግድ ሥራ ላይ የሚሳተፉ ነጋዴዎችና ማህበራት መረጃ የሚመዘገቡበት የመረጃ ሥርአት መሆኑ ታውቆ ሁሉም መመዝገብ ያለበት ነጋዴ ወይም ማህበር ተገቢውን የምዝገባ ስርአት እንዲከተል እንመክራለን፡፡
በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
Senior Attorney
Company: Amhara Bank S.C Location: Addis Ababa Deadline: December 20, 2021 Job Summery Education Level: Bachler Degree Field of Study: BA in Law
Required Work Experience: 5 years of related work experience.
Job Description
• Give legal advice to the bank’s concerned organs;
• Represents the Bank before a court of law, other judicial tribunals, and organs;
• Prepares 30-days legal notice and ensures the delivery of the notice to defaulters.
• Appeals on court decisions against the Bank.
• Applies to court to set aside legal attachment orders. NB:
• Salary: As per the Bank’s scale
• Only shortlisted candidates will be communicated
• Applicants for outlying Branches need to specify the location they apply for.
• Hard copy or physical applications will not be accepted.
How to Apply
Interested applicants fulfilling the above requirements are invited to send their applications and CVs with supporting credentials within five (5) working days from December 15, 2021, to December 20, 2021, via only the Bank’s recruitment Management System online at https://amarabanksc.com/recruitment/ For any inquiry contact us on +251976545447/+251984098355 Posted Date: 14-12-2021

Amhara Bank S.C
https://t.me/lawsocieties