አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
December 4, 2021
የኢትዯጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1183/2012)ን
1. በአፋርኛ፣
2. በትግርኛ፣
3. በሶማሊኛ፣
4. በሲዳምኛ እና
5. በአፋን ኦሮሞ

ቋንቋዎች በመተርጎም ለተጠቃሚዎች አዘጋጅቷል። ለኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ምስጋናችን ይደረሳቸው፤

አዋጁን በየቋንቋዎቹ ከዚህ ያግኙ

https://www.abyssinialaw.com/dds/latest-laws
December 6, 2021
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የደንበኞች ትምህርት ቡድን አባል አቶ ምትኩ አበባዉ ለኢትዮጵያ ቼክ ከተናገሩት ፦

- ደብዳቤዎቹ ከኛ ነዉ የወጡት፤ ትክክለኛ ናቸዉ።

- የክልከላው ምክንያት ለንግድ ማይዉሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ዝርዝር ለመወሰን የወጣዉን መመሪያ 51/2010ን በመጠቀም በተመላላሽ መንገደኞች ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ነገር ግን ለንግድ አላማ እየዋሉ የሚገኙ ዕቃዎች በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ጫና በመፍጠራቸዉ ነው።

- አንድ መንገደኛ ሁሌ የሚመላለስ ከሆነ ያለቀረጥ ሁሌም እየተመላለሰ የሚያመጣ ከሆነ በህጋዊ መልኩ በኮንቴነር የሚያስጭኑና ግብር የሚከፍሉ ነጋዴዎችን ኪሳራ ዉስጥ የሚያስገባና ተጽዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ ይህ ደብዳቤ ወጥቷል።

- ማንኛዉም መንገደኛ ማንኛዉንም አልባሳት ሆነ የንግድ ባህሪ ያለዉ ዕቃ ይዞ ከመጣ ቀረጥና ታክስ መክፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀል ምርመራ ህግም እስከ ማስጠየቅ ድረስ የሚደርስ ነዉ።

- ከአንድ ወር በላይ የቆዩና ተመላላሽ ያልሆኑ የመጀመሪያ መንገደኞች፤ ቱሪስቶች እና ዲፕሎማቶች ፓስፖርታቸዉና ማህደራቸዉ ታይቶ የንግድ ባህሪ የሌለዉ ዕቃ የያዙ ከሆነ ለጊዜዉ በመመሪያ 51/2010 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል።

- ጠቅልለዉ ወደ ሀገር የሚመለሱ መንገደኞች ጓዞቻቸዉን ይዘዉ ቢመጡም ሆነ በካርጎ ቢልኩ በመመሪያ 51/2010 የተፈቀደና ሲገለገሉበት የቆየ ዕቃ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ይችላሉ። ይሁን እንጂ በመመሪያዉ ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የተፈቀዱ ቢሆኑም ዕቃዎቹ አዳዲስ እስከሆኑ ድረስ ቀረጥና ታክስ ይከፈልባቸዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-12-06

@tikvahethiopia
December 6, 2021
December 6, 2021
December 6, 2021
December 6, 2021
December 7, 2021
December 7, 2021
Forwarded from All African/Andinet
December 8, 2021
December 9, 2021
December 9, 2021
December 9, 2021
December 9, 2021
December 10, 2021
December 10, 2021
Hence, pre-employment background checks will be conducted, and employees are required to read, understand, sign and implement different polices including safeguarding and child protection policy, Protection from Sexual Exploitation and abuse policy, sexual harassment policy, code of conducts and any other policy, rules and regulation of the organization. 

Job Requirements:

JOIN US

Do you want to join an exciting organization that brings high level impact to the community and add value to your professional advancement?  Then join us if you have:

·          Bachelor's/Master’s degree in law-related field

·         7 years’ experience as a Legal Counsel /lawyer and able to attend to routine administrative labour law among other related litigation tasks

·         Must be prepared to make ethical and moral decisions

·         Previous working experience as a Legal Counsel/ lawyer   in business/INGO sector

·         In-depth knowledge of administrative law and procedures

·         Good organisational, prioritization and time-management skills

·         Arbitration and mediation skills

·         Exemplary writing and editing skills, with proficiency in Microsoft Office: - Word, PowerPoint, Excel, Outlook etc.

·         Excellent communication, presentation, and interpersonal skills and analytical skills in both written and spoken; English, Amharic, and Afaan Oromo

·         Working well under pressure

·         Attention to detail

·         Ability to use your initiative.

·         Discretion in handling confidential matters and proactive approach to problem solving.

·         Excellent judgment and ability to anticipate legal issues or risks

·         High degree of professional ethics, integrity, and responsibility

Note: This description is not an exhaustive list of the skill, effort, duties and responsibilities associated with the position.

REMUNERATION and BENEFITS:

GOAL will pay a competitive basic salary based on the salary grading with addition benefits.

A chance to develop tangible experience.

Being part of a team who continue to make a real difference to the lives of the most vulnerable people.   

How To Apply:

APPLICATION PROCEEDURE:

Interested and qualified applicants need to submit ONLY once their non - returnable application with CV for one vacancy. The vacancy reference number along with the title & Duty station need to be written in the application letter and/or subject of the email. Applicants can apply using the following option.

Applicants can directly apply online usingwww.ethiojobs.net  orgoaljobs@et.goal.ie

GOAL strongly encourages female candidates to apply!

Only short-listed candidates will be contacted for an interview and exam.

Shortlisted candidates will need to submit other supporting documents upon request at later stage.

GOAL is not able to contribute towards any costs incurred by candidates during the recruitment process

Posted: 12.09.2021

Deadline: 12.19.2021

Job Category:
Human Resource and Recruitment, Legal, Management
Employment:

Location: GOAL Ethiopia

http://www.goal.ie/Ethiopia/159
December 10, 2021
December 10, 2021
በአዲሱ የንግድ ሕግ የተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች

1. መግቢያ
በሥራ ላይ የነበረዉ የንግድ ሕግ (1952 ዓ.ም) አገሪቷ ከደረሰችበት የንግድ እንቅስቃሴና ዘርፉ ከሚፈለገዉ ዕድገት አንፃር ብዙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ እና የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የንግድ ሕጉን መፈተሽ እና ማሻሻያዎችን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2014 ሆኖ ታትሞ ሥራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፡፡ አዲሱ የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር በርካታ ለውጦች ተደርገዉበታል። የሕጉ መውጣት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን በአወንታዊ መንገድ ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ አለዉ። በዚህ አጭር ጽሁፍ የንግድ ሕጉን ዓላማዎች፣የንግድ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት፣የንግድ ሕጉ ማሻሻል ያለዉ ጠቀሜታ እና አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች የምንመለከት ይሆናል፡፡

2. የንግድ ሕግ ዓላማዎች
አንድ ግለሰብ ነጋዴ ወይም የንግድ ማኅበር በዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴው ከተለያዩ አካላት ጋር የውል እና ከውል ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ይፈጥራል።

ለምሳሌ፦ አንድ የንግድ ድርጅት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ከሚያቀርቡ ድርጅቶች፣ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን ከሚገዙት ደንበኞች ወይም ሸማቾች፣ ለድርጅቱ ብድር ከሰጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከድርጅቱ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ካላቸው ሰዎች፣ ከንግድ ተወዳዳሪዎቹ፣ ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ከድርጅቱ ሠራተኞችና ሥራ አመራሮች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል፤ ድርጅቱ ከባለሀብቶቹ የተለየ የራሱ የሕግ ሰውነት ያለው የንግድ ማኅበር ሲሆን ደግሞ ከማኅበርተኞቹ ጭምር ግንኙነት ይኖረዋል። ከላይ ከተገለጹት የንግድ ድርጅት ከሚፈጥራቸው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አኳያ የንግድ ሕጎች ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች አሏቸው፦ አንደኛው ዓላማ አንድ የንግድ ድርጅት ከላይ በተመለከትናቸው ውስብስብ ግንኙነቶች ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሀብት እንዲያፈራ እና አትራፊ እንዲሆን የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከላይ ለተጠቀሱት ከአንድ የንግድ ድርጅት ጋር የተለያዩ ግንኙነቶች ለሚፈጥሩት አካላት መብቶች እና ቅቡልነት ያላቸው ፍላጎቶች ተገቢውን የሕግ ጥበቃ ማድረግ ነው። የንግድ ሕግ መድብል (ኮድ) እነዚህን ሁለት አንኳር ዓላማዎች ይጋራል። ይህ ሲባል ግን የንግድ ሕግ መድብል (ኮድ) ሁሉንም ከላይ የተመለከትናቸውን ግንኙነቶች አሟልቶ ይገዛል ማለት አይደለም።

3. የንግድ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት እና ጠቀሜታ
የንግድ ህጉ አሁን ያለውን ዘመናዊውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሊመልስ በሚችል መልኩ ካልተቀረፀ ወይም ካልተዘጋጀ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና የሚኖረው በመሆኑ የንግድ ህግ ዘመናዊ መሆን ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም አሁን የሚመጡ አዳዲስ ዕድገቶችን ታሳቢ ተደርጎ መረቀቅ እና በተጨባጭ ያንን ሊመልስ በሚችል መልኩ መሰራት አለበት፡፡ የእኛ ሀገር የንግድ ህግ ከብዙ ዓመታት በፊት የተዘጋጀ በመሆኑ አሁን ያለውን አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በንግድ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ሊመልስ የማይችልባቸው ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዛ መካከል አንዱ በንግድ ህጉ የተካተቱ በርካታ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ባለመሆናቸው፣የሚፈፀሙትም ቢሆን አሁን ካለው አጠቃላይ የንግድ እና ኢኮኖሚ እንቅሳሴ ጋር የማይሄዱ በመሆናቸው፣ በተለይም በሀገራችን ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ያለው ከማህበራት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው የንግድ ህግ ሊመልሳቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን መመለስ ባለመቻሉ የመጣ ችግር ነው፡፡ በመሆኑም ክፍተቶቹን በመፈተሽ አሁን ካለው እና ዘመኑ ከሚጠይቀው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ዘመናዊ የንግድ ህግ ማደራጀት በማስፈለጉ የንግድ ህጉ እንደገና እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

በዚህ ሕግ መሰረት የትኛውም እንቅስቃሴ ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለምሳሌ የንግድ ማህበራት የሚቆጣጠራቸው ሕጉ ነው፡፡ የንግድ ምዝገባ ለማድረግም መነሻ ህጋቸው ይህ ህግ ነው፡፡ የዚህ ሕግ ዘመናዊ ሆኖ መደራጀቱ ለነጋዴው፣ ለንግድ ማህበራት፣ ለ3ኛ ወገኖች እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ መደራጀታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘመኑ የሚጠይቀው ሕግ ተደንግጎ የወጣ፣ አሁን ካለው የስራ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚሄድ እና ለነጋዴው ግልፅ የሆነ የንግድ ሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ለልማታዊ ባለሀብቶች የሚያመች ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

4. አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች
ነባሩ የንግድ ህግ ጥራዝ በስድስት መጽሀፍት የተደራጀ ሲሆን፣ በአንደኛ መጽሀፍ ስለንግድ ስራና ነጋዴዎች፣ በሁለተኛ መጽሁፍ ስለንግድ ማኅበራት፣በሶስተኛ መጽሀፍ ስለኢንሹራንስና የማጓጓዣ አገልግሎት፣በአራተኛ መጽሀፍ ስለባንክና ተላላፊ ሰነዶች (የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች)፣በአምስተኛ መጽሀፉ ስለኪሳራ ህግ ፣ በስድስተኛ መጽሀፍ መሸጋገሪያ ድንጋጌዎች ሆኖ ዝርዝር ጉዳዮችን አካትቶ የተሰነደ ነው። በተደረገዉ ጥናት መጽሐፍት 3 እና 4 የንግድ ሕግ አካል ሳይሆኑ ራሳቸዉን ችለዉ የፋይናንስ አገልግሎት መድብል / Code / እንዲሆኑ እና መጽሀፍ አንድ፣ሁለት እና አምስት የንግድ ሕግ ተብሎ እንዲሻሻል ተደርጎ በአዲሱ የንግድ ሕግ ወጥቷል፡፡ በአዲሱ አዋጅ ያልተካተቱት የባንክ፣ የኢንሹራንስና፣ የማጓጓዣ ዘርፎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቀድሞው አሠራር መሠረት የሚቀጥሉ ሲሆን አዲሱ የንግድ ሕግ በርካታ ማሻሻያዎችን እና አዳዲስ አሰራሮችን የያዘ ሆኖ ወጥቷል። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እንመልከት።

 አንድ ግለሰብ ለብቻው ኩባንያ መክፈት እንዲችል ተፈቅዷል
አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 534 እንደሚያሳየዉ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያን መመስረት እንዲችል ተፈቅዷል። ይህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያግዛቸዋል ።
 የንግድ ትርጓሜን መቀየር
በተሻረው ሕግ የተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች 21 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውጪ ያሉት ንግድ አይደሉም ተብለው እንደሚገመቱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። አሁን ግን በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 5 መሰረት የንግድ አይነቶችን ወደ 37 አድገዋል። በዚሁ ሕግ የንግድ ትርጉም ክፍት ነው። በግልፅ ካልተከለከለ በስተቀር ያተርፋል ብሎ እንደሙያ የያዘውን ሥራ አስመዝገቦ መቀጠል ይችላል። ይህ መሆኑ ደግሞ አዳዲስ የንግድ አይነቶችንና የፈጠራ ሐሳቦችን ያበርታታል ።
 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የሙያ ሽርክና ማኅበራት (አንቀፅ 221)
በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ከተካተቱ ጉልህ ለውጦች መካከል አንዱ የሆነው ይህ አዲስ የሽርክና ማህበር አይነት፣ ሰዎች በተለይም የሙያ ስራዎችን ለመስራት በሙያ ከሚመስሏቸው ሌሎች ሰዎችና ለሙያው ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ሊሰጡ ከሚችሉ አጋሮቻቸው ጋር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው የሚያቋቁሙት፣ ኃላፊነቱም በሽርክና ማኅበሩ ሃብት ላይ ብቻ የተወሰነ የንግድ ማኅበር ነው በሚል በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 221 ላይ ተደንግጓል። ከቀደመው ሕግ በተቃራኒው አዲስ የጸደቀው አዋጅ ግለሰቦች በሙያቸው ተደራጅተው እንዲሠሩ በግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል።

https://t.me/lawsocieties
December 11, 2021
በሌላ በኩል የቀድሞው ሕግ የአክስዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሁሉም የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ ግዴታ የጣለ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ ባለድርሻ መሆን ሳይጠበቅባቸው፤ ባለ ድርሻ ያልሆኑ ሰዎች በሙያቸው እስከ አንድ ሦስተኛ ድረስ የሚሆነውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታን እንዲይዙ ይፈቃዳል። ይህ አይነቱ የሽርክና ማኅበር የህግ አገልግሎትን፣ የሂሳብ መዝጋትና ኦዲት ወይም ሌላ አይነት ቴክኒካዊ እውቀትን በሚጠይቁና የሙያ ፈቃድ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የስራ ዘርፎች ላይ በቅንጅት መስራት ለሚሹ ሙያተኞች አይነተኛ ምርጫ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም።
 የሆልዲንግ ካምፓኒ ስለ መፈቀዱ
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 5 ስር በተመለከቱት ሥራዎች ላይ በመሰማራት በቀጥታ ራሱ ምርትና አገልግሎት ባያቀርብም በዚህ ተግባር በተሰማሩ ሌሎች የንግድ ማኅበራት ዉስጥ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ድርሻ የሚይዝ ኩባንያ ወይም ሆልዲንግ ካምፓኒ እንደ ነጋዴ እንደሚቆጥር አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 9 ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም ሆልዲንግ ካምፓኒ በቀጥታ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ ይችላል፡፡

 ተራ የሽርክና ማህበርን የሚመለከተው የህጉ ክፍል ስለመቅረቱ፦
ነባሩ የንግድ ህግ ስለንግድ ተቋማት በሚዘረዝርበት ሁለተኛ መጽሀፉ ተራ የሽርክና ማህበርን ሰፊ ሽፋን የሰጠው ሲሆን በትንታኔው ግን ይህ አይነቱ ማኅበር በንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ እንደማይችል በግልፅ አስቀምጧል። እንግዲህ የንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ አይችልም የተባለ የሰዎች ስብስብ፣ በንግድ ህግ ጥራዝ ውስጥ እንደ ንግድ ተቋም መቀመጡ የህግ አመክንዮ የማይገኝለት በመሆኑ ውሳኔው ትክክለኛነቱ አያጠያይቅም።

 አክስዮን ማኅበርን በሚመለከተው የህጉ ክፍል አክሲዮኑ ለህዝብ ክፍት ስለሚሆን ማሕበር ሰፊ ሽፋን ስለመሰጠቱ፦
ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚሰራባቸው የንግድ ተቋማት አይነቶች ውስጥ ዋናውን ስፍራ የሚወስደው አክስዮን ማኅበር መሆኑ ይታወቃል። የባንክ እና የኢንሹራንስ ስራን የመሳሰሉ የፋይናንስ አገልግሎት ስራዎችን ለመስራት የተፈቀደለት ብቸኛው የንግድ ተቋም ፎርም አክስዮን ማኅበር ነው። በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 248 ላይ እንደተመለከተዉ የአክስዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት በሆነ የአክስዮን ሽያጭ የሚመሰረትበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህን መሰሉን ማህበር ለማቋቋም በሚሰሩት አደራጆች መብትና ግዴታ እንዲሁም ሀላፊነት ዙሪያ የተብራሩ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡

 በንግድ ድርጅቶች መካከል የሚፈጠርን ዝምድና (Affiliation) ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር የሚሆን የህግ ክፍል ስለመካተቱ
የንግድ ማኅበራትን በሚመለከተው መጽሀፍ ሁለት ውስጥ በርዕስ ዘጠኝ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተካተተው የኩባንያዎች መዛመድ ጽንሰ-ሀሳብ ሰፋ ያለ ዳሰሳና ጥናት የሚጠይቅ ጉዳይ ቢሆንም በዚህ የንግድ ህግ መካተቱ ምን አይነት ለውጦች ሊያስከትል እንደሚችል ልናነሳ ይገባል። አንድ ኩባንያ የሌላኛውን ኩባንያ አክስዮን የገዛ ከሆነ፣ ወይም እርስ በእርስ አክስዮኖች የተገዛዙ ከሆነ፣ ወይም በኩባንያዎቹ መካከል የሆልዲንግና ሰብሲዲየሪ (ተቀጽላ) ግንኙነት ካለ ወይም የአንድ ቡድን ኩባንያ (Group Company) አባላት ከሆኑ የተዛመዱ (Affiliated) ኩባንያዎች ይባላሉ። አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 550 የኩባንያዎችን ዝምድና በመተንተን ሂደትም አንድን ኩባንያ የሆልዲንግ ኩባንያ አቋም የሚያሰጡት ሁኔታዎችና የአክሲዮንና የድምጽ መብቶች መጠን፣ ሆልዲንግ ኩባንያ በተቀጥላ (Subsidiary) ላይ ስለሚኖረው ልዩ ልዩ መብትና ስልጣን እንዲሁም ሆልዲንግ ኩባንያ ከዘጠና በመቶ በላይ የድምጽ መብት በሚኖረው ጊዜ ሌሎች የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ስለሚኖራቸው አማራጭ እና በተቀጥላ ኩባንያ ውስጥ ስላሉት የስራ አመራር አባላት ተጠያቂነት በዝርዝር ያስቀምጣል።

 የኪሳራ ህግን በሚመለከተው መጽሀፍ ውስጥ ዕዳን እንደገና ስለማደራጀት የሚመለከት ተጨማሪ ጽንሰ-ሀሳብ ስለመካተቱ፦
ማንኛውም ነጋዴ ይብዛም ይነስም በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ሲሰማራና ገንዘብና ጊዜውን ሲመድብ ይሳካልኛል የሚል ብርቱ እምነት ቢኖረውም ቅሉ፣ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች ግን እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ይቀርና ወደኪሳራ ያመራሉ። ነባሩ የኪሳራ ህግ፣ አንድ ነጋዴ ያሉበትን ዕዳዎች መክፈል ማቋረጡን እንደዋና ምክንያት በመያዝ፣ የአበዳሪዎችንና ሌሎች መብት ጠያቂዎችን ጥቅም ለማስከበር ሲባል የመክሰር ውሳኔ ሊተላለፍ እንደሚችል ያትታል። አዲሱ የንግድ ህግ በዚህ ረገድ አዲስና እጅግ ጠቃሚ የሚባል ዕዳን እንደገና ስለማደራጀት የሚገልፅ ክፍል በመክሰር ሂደት ውስጥ እንዲካተት አድርጓል። ለማሻሻያው ዋና መነሻ የሚሆነው የህጉ አላማ በጊዜያዊ የገንዘብ ችግር ምክንያት ዕዳ መክፈል ያቋረጡ ወይም ለማቋረጥ የተቃረቡ ነጋዴዎች እንደገና ተደራጅተው እንዲያገግሙ እድል መስጠት ነው። እዳን እንደገና ማደራጀት የሚባለው ባለዕዳው ያለበትን የዕዳ መጠን፣ አይነት እና የአከፋፈል ሁኔታዎች በሌላ የዕዳ ወይም የመብት አይነት፣ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታዎች በፍርድ ሲለወጡ ነው። እዚህ ላይ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ዕዳን እንደገና የማደራጀት ተግባር የመክሰር ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ወይም ከተሰጠ በኋላ ሊከናወን የሚችል ሲሆን በዋነኝነትም የገንዘብ መብት ጠያቂዎች ፍላጎትና የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደቅድመሁኔታ የሚጠቀሱ ተግባራት ናቸው።

በአጠቃላይ አዲሱ የንግድ ህግ በይዘትም ሆነ በቅርፅ መሰረታዊ የሚባሉ ለውጦችን የያዘ ሰነድ ሲሆን አንዳንድ ማሻሻያዎቹ የሌሎች ሀገራት የንግድ ህግጋትን መነሻ ተጨማሪ ጽንሰ ሀሳቦችን ያካተተ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪም ከተሻረው ሕግ በተቃራኒ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚከስሩ የንግድ ሰዎች ነጻ የሚሆኑበትን መንገድ አመቻችቷል፡፡ እነዚህን ጨምሮ ለንግድ እንቅስቃሴው የማይመቹ ሕጎችን ያሻሻለው የአዲሱ አዋጅ መውጣት በሀገር ውስጥ ያለውን የንግድ እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳልጣል።

ፍትህ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
December 11, 2021
Legal Officer job at Center for African Leadership Studies (CALS) & xHub Addis
Legal Officer
Center for African Leadersh...

Addis Ababa
Full–time
JOB DETAILS:
Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble.
Summary
Date Posted: Friday, December 10, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble

Job Requirements
• Bachelor of Laws (LL.B.) or Master of Laws (LL.M.)
• 3 - 5 years of experience in a law firm or multinational organization (private sector or NGO).

Work Hours: 8

Experience in Months: 36

Level of Education: Bachelor Degree

Job application procedure
Attach the following documents in one folder to the mentioned email
Tempo of degree
Well detailed Resume and cover letter
With the subject line "Legal Officer Dec 2021" email your application to ephratag.xhubaddis@gmail.com 

Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble. Duties and Responsibilities In order to ensure that the best legal action is taken for the organization, Legal Officers perform a variety of important tasks; Provide Legal Advice- Using oral or written platforms, Legal Officer will be expected to brief a team of staff members on legal issues, potential liabilities, and possible courses of action. This involves translating complicated legal jargon (gibberish) into a language that everyone can understand, as well as taking all possible legal problems into consideration before making any recommendations. All recommendations which the Legal Officer makes must be in complete compliance with the law, and must also strive to minimize risk for their organization. Process Documents- Any sort of legal work involves a great deal of paperwork. Legal Officers will frequently need to write and review settlement documents, contracts, agreements, stock certificates, and more. This task makes up a significant portion of the day-to-day work of Legal Officers and requires both focus and precision. Perform Research- Since laws and regulations are always changing and being modified, it’s up to the Legal Officer to continuously research legal resources such as articles, codes, statutes, judicial decisions, and more. Doing so will allow the Legal Officer to stay up to date on all current laws and make well-educated legal recommendations. Identify Risks- Ideally, legal issues should be gripped in the bud before they even begin. This is why it’s essential for Legal Officers to regularly analyze the actions and decisions of the company in order to identify problem areas, suggest alternative courses of action and mitigate risk as much as possible. Review and provide legal advice on MOUs, Contracts, and tender documents. Liaise with relevant departments to ensure that where legal risks have been identified, appropriate courses of action have been taken. Provide legal protection and risk management advice to management especially on contract management.

https://t.me/lawsocieties
December 11, 2021