አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 03/2011
#AddisAbaba
ከትላንት ጥቅምት 22 ጀምሮ በአዲስ አበባ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ክልከላ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ተከትሎ ለአፈፃፀም ይረዳ ዘንድ መመሪያ 03/2011 በመጫን አቅም ልክ መጠን ከባድና ቀላል ተሽከርካዎች በማለት የሰዓት ገደብ ክልከላውን ለይቶ አስቀምጧል፡፡

በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 12፡30 እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ አይችሉም።

በመመሪያው ክፍል ሁለት ስለሰዓት ገደብ እና ስለፈቃ በሚያትተው ጽሁፍ መሰረት ማናቸውም ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች ማለትም ከ25 እስከ 35 ኩንታል (ከ2.5 እስከ 3.5 ቶን) የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡30 እስከ ረፋዱ 4፡00 እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 እንቅስቃሴ የሚገደቡ ይሆናል፡፡

ይህ ማለት ከሰዓት ክልከላው ውጭ ያለው ጊዜ ከረፋዱ 4፡00 እስከ ከቀኑ 10፡00 ድረስ መንቀሳቀስ የሚችሉ ይሆናል፡፡

በተጓዳኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ማለትም ከ35 ኩንታል (ከ3.5 ቶን) በላይ የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከማለዳው 12፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይቻሉ በመመሪያው ተቀምጧል፡፡

የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 03/2011 በሰኔ 2011 ዓ.ም ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

#AATB
via tikvahethiopia

ቅጣትን በተመለከተ ፦

" የሰዓት ክልከላውን የሚጥሱ አካላት ከ5 መቶ እስ 6 ሺህ በገንዘብ እና ከ1 ወር እስከ 3 ወር መንጃ ፈቃድ በማገድ ያስቀጣል " - አአትቢ

የጭነት፣ ማሽነሪዎችና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ተከትሎ ክልከላውን በሚጥሱ አካላት ላይ ከ5 መቶ እስ 6 ሺህ በገንዘብ እና ከ1 ወር እስከ 3 ወር የመንጃ ፈቃድ እገዳ ያስጥላል።

አሽከርካሪዎች በተለይ የከባድ ጭነት፣ ማሽነሪዎችና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚነዱ በሙሉ መረጃውን በማወቅ መመሪያውን እንዲያከንሩ ተብሏል።

የህግ አስከባሪዎችም መመሪያውን በሚጥሱ አካላት ላይ በተቀመጠው የቅጣት ወሰን መሰረት እንዲፈፀም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

* ቅጣትን በተመለከተ ከላይ በዝርዝር ይመልከቱ።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ