Forwarded from Transparency International Ethiopia (TIE)
አስቸኳይ ማስታወቂያ ‼️
ተመርቀው ስራ በማፈላለግ ላይ ያሉ
5 ስራ ፈላጊዎች በኢንተርን(intern) መቅጠር ይፈልጋል።
ነገ ሀሙስ መጀመር የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ነገ ሀሙስ 24/10/2013 ዓ.ም
ሳር ቤት ADAMS Pavilion ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር S14
በአካል ተገኙ እንላለን።
ለበለጠ መረጃ፤
Tel: +251 11 834 2741
or
Tel: +251 11 827 9746
............‼️ urgent ‼️.................
for tomorrow ............
We want additional 5 (five) interns.....?
only Five (5)
the person that who can work full day two (2) days per a week.
#Transparency_International_Ethiopia
via @Transparency_Ethiopia_Bot
@Transparency_Ethiopia_Bot
https://t.me/TransparencyEthiopia
@TransparencyEthiopia

Telegram
Transparency International Ethiopia (TIE)
Ethical and corruption free society that upholds integrity and accountability
Contact Us via
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
Contact Us via
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
. https://et.linkedin.com/jobs/view/associate-legal-expert-at-african-union-2581241876?refId=PSpMO1gkNPOGY7zJvcAmLg%3D%3D&trackingId=T5GzvjAlsiphTvSuMACWDQ%3D%3D&position=3&pageNum=0&trk=public_jobs_jserp-result_search-card&utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic
TENURE OF APPOINTMENT: The Appointment will be made on a fixed term contract for a period of one (1) year, of which the first three (3) months will be considered as a probationary period. Thereafter, the contract may be renewed for a similar period subject to funding availability, satisfactory performance and agreed deliverables.
GENDER MAINSTREAMING: The AU Commission is an equal opportunity employer and qualified women are strongly encouraged to apply. REMUNERATION: The salary attached to the position is an annual lump-sum of US$ 85,212.07 (P2 Step 5) inclusive of all allowances for internationally recruited staff, and US$ 66,751.81 inclusive of all allowances for locally recruited staff of the African Union Commission. Applications must be made not later than 9 July 2021. Requisition ID: 504

Linkedin
1 Legal Specialist jobs in Ethiopia
Today’s top 1 Legal Specialist jobs in Ethiopia. Leverage your professional network, and get hired. New Legal Specialist jobs added daily.
ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ
----------*****-----------
መግቢያ
ሰዎች በወንጀልም ይሁን በፍትሐብሔር ጉዳይ ክስ ቀርቦባቸዉ ወይም ክስ አቅረበዉ ወደ ፍትህ አካላት በተለይም ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሕግን እና የሕግ ሥርዓትን አካሄድ ማወቅ ጠቃሚ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን ሁሉም ሰዉ ሕግ የተማረ፣ ስለሕግ በቂ ዕውቀት እና ግንዛቤ ያለዉ ሊሆን ስለማይችል በሕግ ባለሙያ መደገፍ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት አብዛኛቹ ሀገራት ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ለሚገባቸዉ ሰዎች የሕግ ማዕቀፍ በማዉጣት አገልግሎቱን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያም ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማደረግ በተለይም ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችና የወንጀል ሰለባ ለሆኑ ሰዎች፣ ለበጎአድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት የሕግ ማዕቀፎችን ለአብነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 20 (5)፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(4) (8) (11)፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/1992 እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የሥነ- ምግባር ደንብ ቁጥር 57/1992 እንዲሁም የክልሎች ተመሳሳይ ሕጎችን በማዉጣት እና በመመሪያና በአሰራር ማንዋል በመደገፍ አገልግሎቱን እየሰጠች ትገኛለች፡:
1. ነፃ የሕግ ድጋፍ ምንነት፣ አስፈላጊነትና ዓላማ
የነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ማለት የፍትህ ስርዓቱ ፍትሐዊና ተደራሽ እንዲሆን ለጠበቃ ገንዘብ ለመክፈል ለማይችሉ፣ በኢኮኖሚ አቅም በአነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የገንዘብ አቅም ለሌላቸዉ ለበጎ አድራጎት ደርጅቶች እና ማኅበራት አገልግሎቱን በነፃ እንዲያገኙ ዓላማ አድርጎ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ በተጨማሪም የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የፍትሕ ሥርዓቱን ፍትሐዊና ሚዛናዊ የማድረግ ዓላማን ይዞ ለፍትሕ አሰጣጥ አስፈላጊ መሆኑ በተደነገገ ጊዜ እንዲሁም በክፍያ የሕግ አገልግሎት ሊገኝ በማይችልባቸዉ አካባቢዎችም ነዋሪ ለሆኑ ዜጎች ይሰጣል፡፡ ይህ አገልግሎት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ አገር በቀል ተቋማት በኩል የሚሰጥ ነዉ፡፡ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በራሱ መብት ነዉ፡፡ የሕግ ግንዛቤ መኖር ሰዎች ሊደርሱባቸው ከሚችሉ ጥቃቶች የመጠበቅ መብቶች እንዳሉዋቸው እንዲረዱ ቢያደርጓቸውም የነዚህ መብቶች ጥሰት ከደረሰ በኋላ ግን የሕግ ባለሙያዎች መግባት አለባቸው። ይህ የሚሆነዉ በጠበቃ ታግዞ ለመከራከር የገንዘብ አቅም የሌላቸዉ ሰዎች የፍትህ እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ በመሆኑ ነዉ፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ ማጣት ምክንያት ዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብታቸዉን እንዳያጡ ለማድረግ ነዉ።
የፍትሕ ተደራሽነት በዉስጡ ሶስት መሰረታዊ መብቶችን የያዘ ሲሆን እነሱም፡- የሕግ ተደራሽነት፣ በሕግ ባለሙያ የመታገዝ መብት እና የፍርድ ቤት ተደራሽነት መብት ናቸዉ፡፡በዚህ ጽሁፍ የምንመለከተዉ በሕግ ባለሙያ የመታገዝ መብትን ነዉ፡፡ በሕግ ባለሙያ የመታገዝ መብት ማለት አንድ የወንጀል ተጠርጣሪ ወይም የፍትሐብሔር ወይም የአስተዳደር ሙግት ተሳታፊ የሆነ ግለሰብ ለጉዳዩ የሚረዳዉና ብቃት ያለዉ የሕግ ምክርና በዉክልና በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር በክፍያ ወይም ያለ ክፍያ ለማግኘት የሚቻልበት አግባብ ነዉ፡፡ በዚህ ላይ ለማየት የምንሞክረዉ ግን በነፃ የሚሰጠዉን የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ነዉ፡፡
2. በነፃ የሕግ ድጋፍ የሚሸፈኑ ጉዳዮች
በሕግ ባለሙያ የመታገዝ መብት በአብዛኛዉ ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተገኛኘ መታየቱ የተለመደ ቢሆንም ወንጀል ነክ ባልሆኑ (ፍትሐብሔራዊና አስተዳደራዊ) ጉዳዮችም መብቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ምንም እንኳ እንደወንጀል ጉዳይ ሕይወትና ነፃነትን የሚያሳጡ ባይሆኑም የሀብትና ንብረት መብትን እና ማህበራዊ ጥቅሞችን አዳጋ ዉስጥ የመክትት ዉጤት ስለሚኖራቸዉ በፍትሐብሔር ጉዳይም የሕግ ባለሙያ ድጋፍ የማግኘት ጉዳይ አስፈላጊነቱ ትኩረት እያገኘ መጥቷል፡፡ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ያለዉ ዉስብስብነትና ጠበቃ መቅጠር ከሚችሉ ተሟጋቾች ጋር ያለዉን የክርክር ሚዛን ማጣትን መመልከት የመብቱን አስፈላጊነት የበለጠ ለመረዳት ያስችላል፡፡ በተጨማሪም በሕግ ፊት እኩል የመዳኘት መብት (አንቀጽ 25)፣ የሴች መብት (አንቀጽ 35)፣ የህፃናት መብት (አንቀጽ 36)፣ የተያዙ ሰዎች መብት (አንቀጽ19) እና የተከሰሱ ሰዎች መብት (አንቀጽ 20) በበለጠ በአገራችን እንዲከበሩ ለማድረግ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሆኔታ በማመቻቸት እና ሥርዓት በመዘርጋት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
3. ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚዎች
ነፃ የሕግ ድጋፍ ባለመብት ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሕግ መሰረት ከክፍያ ነፃ የሆነ የሕግ ምክር፣ የክስ አቤቱታ የማዘጋጀት እና የመከራከር አገልግሎት የሕግ ባለሙያዎች ይሰጣል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ይህን ድጋፍ የሚጠይቁት በገንዘባቸዉ ጠበቃ ማቆም የማይችሉ ቢሆኑም አልፎ አልፎም ቢሆን ሌሎች የገንዘብ አቅም ያላቸዉ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ይህን አገልግሎት ሲጠይቁ ይስተዋላል፡፡ በዚህ አግባብ ተጠቃሚነት ለመለየት የተለያዩ የመመዘኛ መስፈርቶችን በማዉጣት አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ የመመዘኛ መስፈርቶችን በተመለከተ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት የተቀመጡ መሰረታዊ መብቶችን ባማከለ መልኩ እንዲሁም የሀገራችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ባገናዘበ መንገድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች የኢኮኖሚ አቅም፣ ፆታ፣ ለመብት ጥሰት እና ለማኅበረሰቡ የሚያስገኘዉ ጠቀሜታ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች እንደመመዘኛ ነጥቦች ተወስዶ ነዉ፡፡ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቱ የሚሰጠዉ ግለሰብ የኢኮኖሚ አቅም እንደሌለዉ ለማረጋገጥ ግለሰቡ ከተለያዩ ምንጮች የሚያገኛቸዉን ገቢዎች፣ ቋሚ እና ተንቀሳቀሽ ንብረት ታይቶ ይሆናል፡፡
ስለሆነም ነፃ የሕግ ድጋፍ የሚሰጠዉ ጠበቃ አቁሞ ለመከራከር የገንዘብ አቅም ለሌላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የራሳቸዉ የሕግ ባለሙያ ለሌላቸዉ የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም የኢትዮጵያ ማኅበራት እና ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ሲባል ፍርድ ቤቶች ወደ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ጠበቆች የሚልኳቸዉ ሰዎችና ድርጅቶች ሲሆን በወንጀል ደግሞ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ (5) መሰረት የተከሰሱ ሰዎች ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣቸዉ ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግስት ጠበቃ የማግኘት መብት ያላቸዉ በመሆኑ ፍ/ቤት በነፃ በሚመድባቸዉ ተከላካይ ጠበቆች የሚወከሉ ይሆናል፡፡
4. በነፃ የሕግ ድጋፍ የሚሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶች
ነፃ የህግ አገልግሎት ከሕግ ምክር አገልግሎት ጀምሮ ተከራክሮ ማስወሰንና ማስፈፀምን ጭምር የሚያጠቃልል ሲሆን በዋናነት፡
• የሕግ ምክር አገልግሎት መስጠት፣

• ለፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚችል ክስ፣ መልስና የመልስ መልስ፣ መቃወሚያ፣ አቤቱታ፣ ቃለ መሀላ እና የመሳሰሉ ሠነዶችን ማዘጋጀት፣
• ማንኛዉንም ዓይነት የዉል ስምምነት ማዘጋጀት፣
• ማንኛዉንም የድርጅት ማቋቋሚያ ወይም ማሻሻያ ወይም ማፍረሻ ሠነድ ማዘጋጀት፣
• አለመግባባቶችን በእርቅ ወይም በድርድር ለመፍታት በሚደረጉ የድርድር ሂደቶች ዉስጥ አስፈላጊዉን ድጋፍ መስጠት እንዲሁም ለኅብረተሰቡ የንቀተሕግ ትምህርቶችን መስጠት፣
• ነፃ የሕግ ድጋፍ ተገልጋዩን ወክሎ በፍርድ ቤት (የአፈፃፀም ክርክሮችንም ይጨምራል) ወይም የዳኝነትተግባር ለመፈጸምበሕግ ስልጣን የተሰጠዉ ሌላ ተቋም ፊት ቀርቦ በዉክልና መከራከር እና ይግባኝ ማቅረብ ወዘተ… የሚያካትት እና
• ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸዉ ሕግ ነክ አገልግሎቶችን መስጠት ነዉ፡፡
5. የሕግ ድጋፍ የሚሰጡ አካላት
ነፃ የሕግ ድጋፍ የሚሰጠዉ በመንግስትና በግል ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ (በጠበቆች) ሲሆን ፡-
በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤሕግ የፍትሐብሔር ዳይሬክቶሬትና በምድብ ጽ/ቤቶች፣
በክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍትሐብሔር የሥራ ሂደቶች (በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ባሉት)፣
በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የሚገኘው የተከላካይ ጠበቃ ጽ/ቤት፣
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባቋቋማቸዉ ነፃ የሕግ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት፣
የዩኒቨርስቲዎች ሕግ ክፍል ባቋቋሟቸዉ ነፃ የሕግ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት፣
በጠበቆች ቢሮዎች ወይም የሕግ አማካሪና ጠበቃ በሆኑ የሕግ ባለሙያዎች፣
በሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ማህበር እና በመሳሰሉት
6. ነፃ የህግ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
የህግ ባለሙያዎችና የተገልጋዮች ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ እንዳይባክን በአግባቡ እንዲዉል ለማድረግ ሲባል ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው ነገሮች፡-
• ለጠበቃ መክፈል አቅም የሌላቸው ሰዎች ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን በሚኖሩበት አካባቢ የማህበራዊ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ የድህነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የነዋሪነት መታወቂያ የሌላቸው በጎዳና ላይ የሚኖሩ ህጻናትና ሴቶች የመብት ጥሰት ከደረሰባቸው ይህንኑ የሚያስረዳ የጽሁፍ ማረጋገጫ ከፖሊስ ጽ/ቤት ወይም ከማረሚያ ቤት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
• የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም የኢትዮጵያ ማህበራት ተጠቃሚ የሚሆኑት የታደሰ ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሆኖም ግን የኢኮኖሚ አቅም እና የሕግ ባለሙያ ያላቸውን ድርጅቶች ወይም ማህበራት ነፃ የጥብቅና አገልግሎቱ አይመለከታቸውም፡፡
• ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋን ለመቀልበስ ወይም በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመርዳት ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተቋቁመው የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ኮሚቴዎች ለዚህ አይነት ስራ መቋቋማቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚመለከተው ሕጋዊ አካላት ሲያቀርቡ የነጻ የጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡
• ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ሲባል ፍርድ ቤቶች ነፃ የጥብቅና አገልግሎት እንደሚያስፈልጋቸዉ በማመን ወደ ጠበቃ የሚልኳቸው ሰዎች የሚስተናገዱ ይሆናል፡
• ተገልጋዩ (ደንበኛዉ) በራሱ ላይ የደረሰበትን ጉዳይ ወይም ያጣዉን መብት ማስገኘት (ማስከበር) ያስችላሉ ያላቸዉን ማስረጃዎች አሟልቶ ማቅረብ፣
7. ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልገሎት ለማግኘት ተገልጋይ መፈፀምያለበት ተግባርና ግዴታ
• ተገልጋዩ ከአገልግሎቱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸዉን ሙያዊ ያልሆኑ ስራዎች ማለትም የፍርድ ቤት መጥሪያ፣ መልስ መስጠትና መቀበል፣ ትዕዛዝ፣ የፍርድና ዉሳኔ ግልባጭ እና ተያያዥነት ያላቸዉ ጉዳዮችን ለሚመለከተዉ ክፍል ማድረስ ወይም መቀበል፣
• ከነፃ የሕግድጋፍአገልግሎት ጋር የተያያዙ ክፍያዎች እና ወጭዎችን ማለትም የዳኝነት፣ የማኅተም፣ የቴምብር ቀረጥ የፎቶ ኮፒ እና የመሳሰሉ ወጪዎችን የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቱን በሚሰጡ ተቋማትና ጠበቆች መክፈል ካልተፈለገ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚዉ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
• ተገልጋዩ የሕግ ባለሙያዉ ከቀረበለት ማስረጃ ጋር የተያያዘ ነገር ሲጠይቀዉ የቻለዉን ያህል ማስረዳት አለበት፣
• ተገልጋዩ እዉነተኛነት የሌላቸዉን ወይም የሀሰት ጉዳይ ይዞ ለሕግ ባለሙያዉ መቅረብ የለበትም፡፡

ALE (Alternative Legal Education)
All in one, for all.🔴
አለ (አማራጭ የሕግ ትምህርት)
ሁሉም በአንድ፣ ለሁሉም።🔴
There is free legal aid.
ነፃ የሕግ ድጋፍ አለ።
For discussion @ALE_lawsocieties
For more Contact us: @LawsocietiesBot
https://t.me/lawsocieties
All in one, for all.🔴
አለ (አማራጭ የሕግ ትምህርት)
ሁሉም በአንድ፣ ለሁሉም።🔴
There is free legal aid.
ነፃ የሕግ ድጋፍ አለ።
For discussion @ALE_lawsocieties
For more Contact us: @LawsocietiesBot
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች
=======//////========
የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።
ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦
#የመፋለም ክስ ( petitory action)
~~××××××~~~~~
ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡
ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡
ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።
በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)
N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።
#ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat)
~~~×××××~~~~~~
እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው።
አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል......
ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገዱ አይደሉም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 43226)
N.B= ይህ ሲባል ግን የህጉን መስፈርት ያላሟሉ ውሎች (illegal contract) ከህገ ወጥ ውል በተለየ ሁኔታ ታይተው የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆንባቸው መሆኑን መረዳት ይገባል።
#የመንግስትን መሬት የማስመለስ ክስ
~××××××~~~~~~
ግለሰቦች በፌደራሉ እና በክልሉ መንግስት በወጡ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ በሚደነግጉት መሰረት በህጋዊ መንገድ ሳይሰጣቸው ከህግ ውጪ የወል ወይም የመንግስትን መሬት ይዘው መቆየታቸው እና የመሬቱ ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታቸው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ሊያደርጋቸው አይችልም። በወረራ የተያዘ የመንግስት መሬትም ይርጋ የሌለው መሆኑን የአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 በግልፅ ያስቀምጣል።
በመሆኑም ከህግ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን መኖራቸውን ሲረዳ መሬት አስተዳደርም ሆነ የመንግስት ወኪል የሆነ አካል መሬቶቹን ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ)
#በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ የግለሰብ ይዞ መሬት
~~××××××~~~~~~
ከላይ እንደተመለከትነው ህገ ወጥ ውልን መሰረት አድርጎ የግለሰብን መሬት በያዘ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 መሰረት ህጉ በማይፈቅድበት መንገድ በሀይልም ሆነ በህገ ወጥ አግባብ የገጠር መሬትን ይዞ የተገኘ ግለሰብ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የለውም።
N.B= በህገ ወጥ መንገድ የሚለው ሀሳብ በህግ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን የያዘን በሚመለከት እንጂ የህጉን መስፈርት ባላሟላ ውል ወይም ተግባር (illegal contrat) አማካኝነት የተያዘን መሬት የሚመለከት አይደለም። ምክንያቱም መሬቱን የያዘው በህጉ በተፈቀደ የውል ተግባር ሆኖ የሚፈለገውን ፎርማሊቲ ወይም መስፈርት አለማለቱ ብቻ አያያዙ ህገ ወጥ ነው የሚያስብል ስላልሆነ ነው።
#የአደራ ውል
~×××
አደራ ተቀባይ በአደራ የሚጠብቀውን ዕቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውል ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ ዕቃውን መመለስ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2781(1) የተመለከተ ሲሆን በውል ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከሌለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዲያውኑ እንደሚመለስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2989(1) ስር ተመላክቷል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው አደራ ተቀባይ ዕቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዲቀመጥ የሰጠው ዕቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን ነው።
#የውርስ ሀብት ክፍፍል
~~~~××××~~~~
ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም።
#የድምፅ ብክለት
~×××~~

የድምፅ ብክለት ክልከላ ባለቤቱ ስራውን የሚፈፅመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም ድርጊቱ ሌላውን ጎረቤት እንዳይረብሽ፣ እንዳያውክ፣ ወይም ችግር እንዳያስከትል በማድረግ መብቱን ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን አድማስ የሚወስን ስርዓት መሆኑን ከአንቀፅ 1226 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
Source:- The Voice of Justice page
https://t.me/lawsocieties
ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
Source:- The Voice of Justice page
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
የውርስ ፅንሰ ሀሳብ በኢትዮጵያ ሕግ (ፍ/ሕ/ቁ 826-1025)
======================
ውድ አንባብያን የዚህ ርእሰ ጉዳይ ይዘት ሰፋ ያለ በመሆኑ በዚች አጭር ፅሑፍ ለመዳሰስ ስለማይቻል በሁለት ክፍሎች ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በዚህም መሰረት በመጀመሪያው ክፍል የውርስ ምንነትና ውርስ ማስተላለፍ፣ የውርስ መከፈት፣ ስለ ውርስ ማጣራት፣ በውርስ መተላለፍ ስለሚችሉ መብትና ግዴታዎች፣ ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልግ ችሎታ እና ያለኑዛዜ ውርስን እንመለከታለን፡፡ በሁለተኛው ከፍል ደግሞ የኑዛዜ ውርስ ምንነት፣ የኑዛዜ ዓይነቶች፣ የኑዛዜ ፎርሞች፣ የኑዛዜ መሻር እና ከወራሽነት መነቀልን በተመለከተ የምንዳስስ ይሆናል፡፡
1. የውርስ ምንነት፡- ውርስ ምንድን ነው የሚለውን ትርጉም በሀገራችን የውርስ ሕግ ውስጥ በቀጥታ ተተርጉሞ ባናገኘውም የአንድ በሞት የተለየን ሰው ንብረት እና ሀብት እንዲሁም ሊተላለፉ የሚችሉ መብት እና ግዴታዎች በሕይወት ላለ ሰው የሚተላለፍበት መንገድ መሆኑን ከሕጉ ጠቅላላ መንፈስ መረዳት እንችላለን፡፡
የውርስ ሕግ ማለት ደግሞ የሟች (አውራሽ) መብቶች እና ግዴታዎች በሕይወት ወዳሉት ወራሾቹ የሚተላለፍበት ደምብ/ስርዓት ነው፡፡ የሟች ውርስ መች እና እንዴት ይከፈታል፣ ወራሾች እነማን ናቸው፣ ወራሽነትን የሚያሣጡ ነገሮች ምንድን ናቸው፣ የሟች ኑዛዜ ምን ማሟላት አለበት፣ ዉርሱ እንዴት እና በማን ይጣራል፣ የውርስ ክፍያ እንዴት እና በማን ይፈፀማል እና የመሳሰሉት ጉዳዮች የሚመሩት በውርስ ሕግ ነው፡፡
ውርስ ማለት የሟችን መብቶች እና ግዴታዎችን ወደ በሕይወት ያሉ ወራሾች ማስተላለፍ ከሆነ የማስተላለፍ ሂደት የተሟላ እንዲሆን ወራሾችን ማጣራት (መውረስ የሚችሉ እነማን እንደሆኑ ማወቅ)፣ ውርስ ማጣራት እና የውርስ ክፍፍል የሚሉትን ቅደም ተከተሎች መከተል ተገቢ ይሆናል፡፡
2. ስለ ውርስ መከፈት፡- የሟች ሀብትና ንብረት እንዲሁም ወራሾች በተለያየ ቦታ ሊገኙ ስለሚችሉ ሁሉንም በአንድ ቦታ አጠቃሎ ለማየት እንዲያመችና በውርስ ላይ ክርክር ቢነሳ ጉዳዩን የመዳኘት ስልጣን ያለውን ፍ/ቤት ለይቶ ለመወሰን እንዲቻል የሟች ውርስ የሚከፈተው ሟች በሞተበት ጊዜ ዋና መኖሪያው ስፍራ በሆነበት ቦታ ነው (ፍ/ሕ/ቁ 862/1/)፡፡
3. በውርስ መተላለፍ የሚችሉ መብትና ግዴታዎች፡- የሟች ንብረት እንዲሁም መብትና ግዴታዎቹ በውርስ ሕግ መሰረት ለወራሾች የሚተላለፉ ናቸዉ፡፡ ይህ አጠቃላይ ደንብ ሲሆን በባሕሪያቸው አንዳንድ መብቶች እና ግዴታዎች ደግሞ ግለሰባዊ በመሆናቸው ሁሉም መብትና ግዴታዎች ሊወረሱ ወይም ለወራሾች ሊተላለፉ አይችሉም፡፡ በመሆኑም በውርስ የሚተላለፉት መብትና ግዴታዎች ከሟች መሞት ጋር አብረው ቀሪ የማይሆኑ እና መተላለፍ የሚችሉት ብቻ ናቸው፡፡
4. ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልግ ችሎታ፡- ለወራሽነት ብቁ የሚያደርጉ በሕጉ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ እንዲሁም በስመ ወላጅነት ወይም ተወላጅነት ብቻ ወራሽ መሆን አይቻልም፡፡ በሕጉ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች ያላሟላ ወራሽ በኑዛዜ ስሙ ቢጠቀስም ወይም በሕግ ወራሽነቱ ቢገለፅም ከውርሱ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ለወራሽነት ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች በሕይወት መኖርና ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን ናቸው (በፍ/ሕ/ቁ 830)፡፡
በህይወት መኖር፡- አንድ ሰው ወራሽ ለመሆን አውራሹ በሚሞትበት ወቅት በህይወት ያለ መሆን አለበት፡፡ አውራሽ ሲሞት ያልነበረ ወይም እሱን ቀድሞ የሞተ መውረስ አይችልም፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ ሟች በሚሞትበት ወቅት ተፀንሶ የነበረ ህፃን ተወልዶ 48 ሰዓት በሕይወት ከቆየ ውርስ ሲከፈት እንደነበረ ተቆጥሮ የመውረስ መብቱ ይጠበቅለታል (ፍ/ሕ/ቁ 834)፡፡
ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን፡- ወራሽ ለመሆን ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች ሌላኛው ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን ነው፡፡ አንድ ወራሽ ለወራሽነት የማይገባ የሚሆነው በአውራሹ ወይም ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም ወደ ላይ የሚቀጠሩ ወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት ወይም በመግደል ሙከራ የተቀጣ ወይም በሀሰት በመወንጀል ወይም በመመስከር አንደኛውን የሞት ፍርድ ወይም ከአስር ዓመት በበለጠ የፅኑ እስራት ቅጣትን ለማስከተል የሚያሰጋ ሆኖ የተቀጣ ከሆነ ነው (ፍ/ሕ/ቁ 838)፡፡
ሌላው ለወራሽነት የማይገባ የሚያደርገው ምክንያት አውራሽ ከመሞቱ በፊት ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ የአውራሽን ሁኔታ ከግምት አስገብቶ ኑዛዜ እንዳያደርግ፣ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ እንደሆነ ወይም አስቦ ያለ ሟች ፍቃድ የመጨረሻውን ኑዛዜ ያበላሸ፣ እንዳይገኝ ያደረገ፣ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ እንደሆነ ነው (በፍ/ሕ/ቁ 840)፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንድ ሰው ከጥፋቱ መጠቀም የለበትም ከሚለው የሕግ መርህ በመነሳት ነው፡፡
5. የውርስ ዓይነቶች፡- ሁለት ዓይነት የውርስ ማስተላለፊያ መንገዶች ያሉ ሲሆን እነርሱም፡- ያለኑዛዜ ውርስ (Intestate Succession) እና የኑዛዜ ውርስ (Testate Succession) ናቸው፡፡
ያለ ኑዛዜ ውርስ፡- አውራሽ (ሟች) ኑዛዜ ሳያደርግ ሲሞት ወይም ያደረገው ኑዛዜ ፈራሽ በሚሆንበት ጊዜ የአውራሽ ንብረት ለወራሾች የሚከፋፈለው በሕጉ በተቀመጠው መሰረት ያለ ኑዛዜ ውርስ መሰረት ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ ውርስ የሚካሄደው በአውራሽ ፍላጎት ሣይሆን በሕጉ መሰረት ነው፡፡ የሟች ልጆች ለመውረስ ብቁ የሚያደርጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን እስካሟሉ ድረስ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ናቸው (በፍ/ሕ/ቁ 842)፡፡
አውራሽ ልጆች ከሌሉት ወይም ልጆቹን ተክቶ የሚወርስ ከሌለ የአውራሽ አባትና እናት 2ኛ ደረጃ ወራሽ ይሆናሉ (ፍ/ሕ/ቁ 843)፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አውራሽ ልጆችም ወላጆችም የሌሉት ከሆነ ወይም አነሱን ተክቶም የሚወርስ ከሌለ የአውራሽ አያቶች 3ኛ ደረጃ ወራሾች ይሆናሉ (በፍ/ሕ/ቁ 845)፡፡ የ3ኛ ደረጃ ወራሾች የሌሉ እንደሆነም የአውራሽ ቅድመ አያቶች 4ኛ ደረጃ ወራሾች ይሆናሉ (በፍ/ሕ/ቁ 847)
አባት ወይም እናት ወይም ሁለቱም ቀድመዉ የሞቱ እንደሆነ የነሱን ፋንታ ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆቻቸዉ ተተክተው ይወርሳሉ፡፡ በአባት ወይም በእናት መስመር /አንዱ መስመር/ የሚወርስ ከሌላ ወደ ሌላኛው መስመር ሙሉ ውርሱ ይተላለፋል፡፡
ዘመዶች እስከ አራተኛ ደረጃ ተለይቶ ያልተገኘ እንደሆነ የሟችን ንብረት ለመንግስት እንደሚተላለፍ የ/ፍ/ሕ/ቁ 852 ላይ ተደንግጓል፡፡
ያለኑዛዜ ውርስ ሲሆን ውርሱ ለሁሉም ወራሾች በእኩል የሚከፋፈል ሆኖ ከአባት ወይም ከእናት ወገን የአንደኛው መስመር ከሌለ ውርሱ ወደ ሌላኛው መስመር ይተላለፋል፡፡ ነገር ግን በልዩ ሀኔታ ንብረቱ ከመጣበት መስመር ህጋዊ ወራሽ ካለ፣ ንብረቱ የማይንቀሳቀስ ከሆነ፣ ንብረቱ በውርስ ወይም በስጦታ የመጣ ከሆነ፣ የአውራሽ ተወላጆች ወይም ወላጆች በሕይወት ካሉ ካንዱ ወደሌላው መስመር መተላለፍ አይችልም (በፍ/ሕ/ቁ 849)፡፡ ይህም የሆነው የቤተሰብ ቅርስ የሆነ ንብረት በቤተሰብ እጅ እንዲቀር ነው፡፡
ምንጭ :- ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ 0አቃቤ ህግ ገጽ

ይዞታና በፍ.ብ.ሕ.ቁ 1149 መሠረት ስለሚቀርብ የሁከት ይወገድ ክስ
=============================
1. የሁከት ይወገድ ክስ መሠረቱ
የሁከት ይወገድልኝ ክስ (Possessory Action) የፍትሐብሔሩ በሚሰጠው ድንጋጌ መሠረት የሚቀርበው አንድ ሰው በይዞታው ሥር ወይም በጥበቃው ሥር ባለው ንብረት ላይ የግፊያ ወይም የንጥቂያ ተግባር ሲፈጸም ይህ ተግባር እንዲቆም ወይም የተነጠቀው ንብረት እንዲመለስ ፍርድ ቤት እንዲያዝለት ሲጠይቅ ነው፡፡ ከዚህ የሕጉ አገባብ ላይ ለሁከት ይወገድልኝ ክስ መሠረት የሆኑትን ዋና ዋና ነጥቦች መገንዘብ ይቻላል፡፡ እነዚህም
1ኛ/ አንድ ሰው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ የሚችለው በይዞታው ሥር ባለ ንብረት ወይም መብት (ይዞታ በሌሎች ግዝፈት በሌላቸው ነገሮች ላይ ሊመሠረትም ይችላል የሚባል ከሆነ) ላይ የግፊያ ወይም የንጥቂያ ተግባር የተፈጸመበት ባለይዞታ ሲሆን ነው፡፡
2ኛ/ የሁከት ይወገድን ክስ ማቅረብ የሚችለው ባለይዞታ ብቻ ሳይሆን የሁከት ተግባር የተፈጸመበት ጠባቂም (holder) ሊሆን ይችላል፡፡ የሁከት ይወገድልኝን ክስ የሚያቀርበው ባለይዞታ ወይም ጠባቂ ነው ከተባለ ባለይዞታ ማን ነው? ጠባቂስ? ከባለቤት ጋር ያላቸውስ ልዩነት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡