አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
SER'ATA MANGEST.pdf
1.2 MB
SER'ATA MANGEST: An early Ethiopian Constitution
Author(s): Bairu Tafla and Heinrich Scholler
Law and Politics in Africa, Asia and Latin America, Vol. 9, No. 4 (1976), pp. 487-499
ከአስተዳደራዊ ውሳኔ ቅሬታ ማቅረቢያ የአስራ አምስት ቀን የጊዜ ገደቦች
በተለያዩ ህጎች ላይ አቤቱታ ለማቅረብ ወይም ሌላ ህጋዊ ተግባር ለመፈጸም የተለያዩ የጊዜ ገደቦች ተቀምጠዋል። ከእነዚህ ውስጥ በአምስራ አምስት ቀን የተወሰኑ የጊዜ ገደቦች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
የኅብረ ት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁ. 985-2009
1. አንቀጽ 12/3/
የማንኛውም ኅብረት ሥራ ማህበር የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሻሻል በጠቅላላ ጉባዔው ሲወሰን የተደረገው ማሻሻያ እና በዚህ አዋጅ መሠረት የተላለፈ የኅብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ በሦስት ቅጅ ተደርጎ ውሳኔ በተላላፈ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አግባብ ላለው ባለሥልጣን መቅረብ አለበት፡፡
2. አንቀጽ 33/2/
የኅብረት ሥራ ማህበር የሥራ አመራር ኮሚቴ በድምጽ ብልጫ ሲወስን ወይም ከጠቅላላ አባላቱ መካከል አንድ ሶስተኛው ስብሰባ እንዲጠራ ሲጠይቁ የ15 ቀን ቅድሚያ ማስታወቂያ በማውጣት አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡
የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1048-2009ዓ.ም
3. አንቀጽ 37/2/
በኦዲትና ኢንስፔክሽን መኮንን ወይም በሌላ የባቡር ትራንስፖርትን እንዲያስተዳድር በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የሥራ ኃላፊ በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ቅሬታ የሚቀርብበት ጊዜ
ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ውሳኔው በተሰጠ ወይም አቤቱታ አቅራቢው ውሳኔ መሰጠቱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
4. አንቀጽ 37/3/
የባቡር ትራንስፖርትን እንዲያስተዳድር በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የበላይ ኃላፊ ቅሬታ ሲቀርብለት በቅሬታው ላይ ውሳኔ ለመስጠት በህግ የተቀመጠለት ጊዜ
የጂኦተርማል ሀብት ልማት አዋጅ ቁጥር 981-2008
5. አንቀጽ 10/2/
የጂኦተርማል ጉድጓድ መስክ የማልማትና የመጠቀም ፈቃድ እንዳይሠጥ ተቃውሞ የሚያቀርብ ሰው በአንቀጽ 10/1/ መሰረት ጥያቄ የቀረበበት ቦታ በመገናኛ ብዙሃን እንዲታወቅ በተደረገ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ያቀረበ እንደሆነ ፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን በጉዳዩ ላይ በሚመለከታቸው ወገኖች መካከል ድርድር እንዲጀመር ያደርጋል።
የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923-2008
6. አንቀጽ 38/2/
ወደ ውጭ አገር ለሥራ የላከውን ሠራተኛ በሚሄድበት አገር ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በ፲፭ ቀናት ውስጥ አሳውቆ የማስመዝገብ፣ የሥራ ፈቃድና የመኖሪያ ፈቃድ ስለማግኘቱ የማረጋገጥና ይህንኑ መረጃ አሟልቶ ለሚኒስቴሩ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
7. አንቀጽ 50/2/
ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን በአንቀጽ 50 አንቀጽ 1 መሠረት የሰጠውን ትዕዛዝ /አስተዳደራዊ ጥፋት በፈጸመ ኤጀንሲ ላይ የሚወስደው እርምጃ/ አቤቱታ የቀረበበት ኤጀንሲ በ፲፭ ቀናት ውስጥ የመፈፀም ግዴታ አለበት፣፡
8. አንቀጽ 59/1/
ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን የዚህን አዋጅ ድንጋጌ ወይም በአዋጁ መሠረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ በሚፈፀመው ጥፋት ላይ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው በደረሰው በ፲፭ ቀናት ውስጥ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም በክልል ሥልጣን ለተሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
9. አንቀጽ 69/1/ ለ የኤጀንሲ ግዴታ
ሠራተኛው ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስበት ወይም ሲሞት ጉዳት የደረሰበትን ሠራተኛ ወይም አስከሬን የሚቆይበት በቂ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ከግል ንብረቶቹ ጋር የአየር ትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን ሠራተኛው ስለደረሰበት ጉዳት ወይም ሞት ከሚገልጽ ሕጋዊ የህክምና ማስረጃ ጋር በማያያዝ በ፲፭ ቀናት ውስጥ ወደ አገሩ የመመለስ እና ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ወጪዎችን የመሸፈን፤
10. አንቀጽ 67/1/
ሚኒስቴሩ ወይም አግባብነት ያለው ባለሥልጣን አቤቱታን በተቀበለ በሦስት የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ለቀረበበት አካል በማሳወቅ ሁለቱ ወገኖች ቀርበው ጉዳዩን በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ በስምምነት እንዲጨርሱ ጥረት ያደርጋል፡፡
የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922-2008
11. አንቀጽ 33/1/
ሰነድ አረጋጋጭ በዚህ አዋጅ መሠረት መስጠት ያለበትን አገልግሎት ቢከለክል ወይም አዋጁን በመተላለፍ አገልግሎት ቢሰጥ ማንኛውም ቅሬታ ያለው ሰው ለሰነድ አረጋጋጩ የበላይ ኃላፊ በ፲፭ የሥራ ቀን ውስጥ አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859-2006
12. አንቀጽ 154/1/
ለጉምሩክ ኮሚሽን የአቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍል የሚቀርብ አቤቱታ ወይም ይግባኝ ቅሬታውን ያስከተለው ውሳኔ በፅሑፍ በተሰጠ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በፅሑፍ መቅረብ አለበት፡፡
የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 840-2006
13. አንቀጽ 15/6/
ወንጀል ሰርቶ ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ሰው ይቅርታ እንዲደረግለት ሲጠየቅለት ይቅርታውን ለመቀበል የማይፈልግ መሆኑን የይቅርታ መጠየቅያ ደብዳቤ ቅጅ በደረሰው በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ለቦርዱ ካላስታወቀ በይቅርታ ጥያቄው እንደተስማመ ይቆጠራል፡፡
14. አንቀጽ 23/7/
በሀሰተኛ ወይም በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ይቅርታ እንዲሁም በሁኔታ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ይቅርታ ሁኔታው ሲጣስ ይቅርታው ዋጋ እንዲያጣ የይቅርታ ቦርድ በሰጠው የውሳኔ ሀሳብ መነሻነት የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ይቅርታው ዋጋ እንዲጣ ትዕዛዝ ከሰጡ ይቅርታ ተደርጎለት የነበረው ሰው ትዕዛዙ እንደገና እንዲታይ ትዕዛዙ በደረሰው በ15 ቀናት ውስጥ ለይቅርታ ቦርድ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818-2006
15. አንቀጽ 17/2/
በመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሰፈር ውስጥ በሚከናወኑ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያደረበት ሰው የማረጋገጥ ሂደቱ መጠናቀቁ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ቅሬታ ሰሚ ጉባዔ ማቅረብ ይችላል፡፡
Ethiopian Legal Brief
41-27 tax frr vehicle for the disabled.pdf
2.4 MB
አካል ጉዳተኞች ለግል አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ ከቀረጥና ታክስ ነጻ የሚያስገቡበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 41-2007