አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች በሕክምና ሥህተት ያለባቸው ተጠያቂነት
=======================
መግቢያ
በህክምና ተቋማት ወይም በጤና ባለሙያ እና በታካሚ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት መሠረቱ የህክምና አገልግሎት ውል ነው፡፡ ሆኖም ግን የህክምና አገልግሎት በሚሰጡት ወቅት አንዳንድ ጊዜ የሙያ ስህተት በመፈፀሙ ምክንያት ታካሚው ላይ ጉዳት ሊደርስ ወይም የሚጠበቀውን መልካም ውጤት ላያመጣ ይችላል፡፡ በመሆኑም በመርህ ደረጃ ጉዳት የደረሰበት ታካሚ ከህክምና ተቋሙ ወይም ከጤና ባለሙያው ጋር ባለው የግንኙነት ዓይነት ተቋማትን ወይም ባለሙያው ካሣ እንዲከፍለው ሊጠይቅ ይችላል፡፡
የህክምና ተቋማትን ወይም የጤና ባለሙያን የህክምና ስህተት ተጠያቂነትን በተመለከተ የታሪክ መዛግብትን በምናይበት ወቅት የህክምና ተቋማት የሚሰጡት የጤና አገልግሎት ያለክፍያ የሚሰጥ የበጎ አድራጐት ተግባር ነበር፡፡ አገልግሎቱ ለትርፍ ዓላማነት የማይሰጥ በመሆኑ አብዛኛዎቹ የህግ ሥርዓቶች በሙያ ስህተት ለሚፈጠር ጉዳት አገልግሎት ሰጪው የጤና ተቋም ወይም ባለሙያ ያለመከሰስ መብት /Immunity/ እንዳለው በመግለፅ በሕጐቻቸው ደንግገው ነበር፡፡ ያለመከሰስ መብቱ መከበሩ ዋነኛ ዓላማው ያለ ክፍያ የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋሙ ወይም ባለሙያው የሚመጣ ሰው አገልግሎቱን በሚያገኝበት ወቅት ለሚደርስበት ጉዳት ካሣ የመጠየቅ መብቱን መተው አለበት ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ሆኖም በጊዜ ሂደት የሕክምና ተቋማት ለሚሰጡት የጤና አገልግሎት ክፍያ ማስከፈል ሲጀምሩ ኀብረተሰቡ ለጤና አገልግሎት እንዱስትሪው ከዚ ቀደም የነበረውን አመለካከት በመቀየር ከተቋሙ ወይም ከጤና ባለሙያው ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት የንግድ /consumerism/ መሆኑን በመገንዘብ አገልግሎቱን መክፍያ በሚያገኙበት ወቅት በሙያ ስህተት ወይም ደረጃውን ባልጠበቀ የጤና አገልግሎት ምክንያት ለሚደርሱበት ጉዳት ተቋሙ ወይም የጤና ባለሙያው ተጠያቂ መሆን አለበት የሚለውን ሃሣብ ማንፀባረቅ ጀመሩ፡፡ በዚህም ምክንያት የጤና ባለሙያዎች ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በሙያ ስህተት ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ መሆን አለባቸው የሚለው አስተምሮ የበላይነቱን በመያዙ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች በአስተዳደር፣ በፍትሐብሔር እና በወንጀል ተጠያቂ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
ወደሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ብንመለከት መንግሥት ደረጃውን ባልጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ብቃትና የሙያ ሥነ-ምግባር በጎደለው የጤና ባለሙያና ተቋም ምክንያት በዜጐች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጤና ችግር ለመከላከል ይቻል ዘንድ የጤና አገልግሎቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ሕጐችን በማውጣትና ተግባር ላይ በማዋል የቁጥጥር ሥርዓት ዘርግቷል፡፡
በዚህ የግንዛቤ መፍጠሪያ ፅሑፍ የሕክምና ስህተት ምን ማለት እንደሆነ፣ በሕክምና ስህተት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የጤና ችግር ለማስቀረት የሀገራችን ሕጐች መከላከልን እና ቅጣትን መሠረት ያደረረ የቁጥጥር ሥርዓት የሚደነግጉ በመሆኑ በነዚህ ሁለት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡
2. የሕክምና የሙያ ስሕተት (medical malpractice)
የሕክምና የሙያ ስህተት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉም ከመስጠታችን በፊት የሙያ ስህተትን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የሙያ ስህተት ማለት በአንድ የሙያ ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ሊከተላቸው ወይም ሊመራባቸው የሚገባውን የሙያ ደንቦችና መመሪያዎች አውቆ ወይም በቸልተኝነት ሣያከብር መቅረት ወይም የሙያ ደንቦችን ባለማክበሩ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሕጋችን ከአንቀፅ 2031 እና 2035 መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ ትርጉም የምንረዳው ቁምነገር አንድ ባለሙያ ምንም እንኳ የሙያ ደንቦችን እና መመሪያዎችን ባለማክበሩ ምክንያት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም የሙያ ደንቦችን አለማክበሩ እራሱን ችሎ የሙያ ስህተት መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፡፡
የጤና ሙያ አንድ የሙያ ዘርፍ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የሚፈፀሙትን የህክምና ስህተት ከላይ ከተመለከትነው የሙያ ስህተት ትርጉም አንፃር እና ደንብ ቁጥር 299/2007 በአንቀፅ 2 ንዑስ አንቀጽ 31 ሙያዊ ያልሆነ ተግባርን በተመለከተ ከሰጠው ትርጉም አንፃር እንደሚከተለው እናያለን፡፡ አንድ የጤና ባለሙያ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በአስፈፃሚ አካሉ አንድን የተወሰነ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት በህግ ከተመለከተው የአገልግሎት ደረጃና የሙያ ወሰን ወይም ሥነ-ምግባርን በሚቃረን ሁኔታ የሕክምና አገልግሎት ከሰጠ የሕክምና ስህተት እንደፈፀመ ይቆጠራል፡፡ የጤና አገልግሎት ደረጃ /standard of health care/ ማለት አንድ የሕክምና ባለሙያ አንድን የተወሰነ የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ ሊያከብራቸው ወይም ሊፈፅማቸው ይገባል ተብለው በአስፈፃሚ አካሉ ወይም በልማድ የተቀመጡ ዝቅተኛ የሕክምና አገልግሎት ደረጃን /minimum standard of care/ የሚመለከት ነው፡፡ እዚህ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የሕክምና ባለሙያው አንድን የተወሰነ የሕክምና አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት የሕክምና ሙያ ደንቦችን በማክበር ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ሰጥቷል ወይስ አልሰጠም ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠቱ ላይ ነው፡፡ ሙያውን የሚመለከቱ ደንቦች በሕግ የታወጁ እና በሕግ ያልታወጁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ደንቦቹ በሕግ የታወጁ በሆነ ጊዜ የሕክምና ባለሙያው የሙያ ወሰኑ የሚፈቅድለትን አንድን የተወሰነ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ በሕጉ የተመለከተውን የጤና አገልግሎት ደረጃ ወይም ወሰን ማክበር ሲገባው በህጉ ከተመለከተው ውጭ አገልግሎቱን ከሰጠ የሙያ ስህተት እንደፈፀመ ይቆጠራል፡፡ ለምሣሌ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና አገልግሎት አስተዳደር ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 በአንቀፅ 39 መድሃኒቶችን ማዘዝ የሚችለው አግባብ ላለው አካል የሙያ ሥራ ፈቃድ የተሰጠው የሕክምና ባለሙያ መሆኑን የሚገልፀውን ድንጋጌ በመተላለፍ መድሃኒት ያዘዘ እና የሸጠ የመድሃኒት ባሉሙያው (medicinal professional) መድሃኒቱ ለሚ.ያደርሰው ጉዳት በሙያ ስህተት ኃላፊነት ሊጠየቅ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የሕክምና ሙያ ደንቦች በሕግ የተደነገጉ ሳይሆኑ በሙያው የተሰማሩ ሰዎች አውቀው ከሚገለገሉባቸው ከተለመደ የመልካም አሠራር መመሪያዎች የሚመነጩ ሊሆኑ ይችላሉ(የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2030 ይመለከቷል)፡፡ አንድን ዓይነት አሠራር ተከትሎ እየደጋገሙ መስራት ልማድን የሚፈጥር ሲሆን (customary practice) ልማዱም የእነዚህ ደንቦች ምንጭ ይሆናል፡፡ እንዲህ ካሉት ልማዶች ዉጭ የሕክምና አገልግሎት በመሰጠቱ ጉዳት የደረሰበት ታካሚ ካሳ እንዲከፈለው ፍርድ ቤት በሚጠይቅበት ወቅት ዳኞች በቀረበው የህክምና ስህተት ውሳኔ ለመስጠት እውቀቱ ስለማይኖራቸው በሙያው የተሠማሩ ባለሙያዎችን በአዋቂ ምስክርነት /expert witness/ ሊጠይቁና የተባሉት ሰዎች ሞያቸውን የሚያስተዳድሩትን የተለመዱ የመልካም አሠራር መመሪያዎች ካስረዷቸው በኋላ የህክምና ሙያ ስህተት ተፈፅሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ጭብጥ ላይ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡
3. የጤና አገልግሎት የቁጥጥር ስርዓት /the regulation of Health care/
የሃገራችን መንግሥት የጤና ሕክምና አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን እና ህሙማን በህክምና ወቅት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለማድረግ ይቻል ዘንድ የጤና አገልግሎት አሠጣጡን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊስዎችን፣ ሕጐችን እና ደንቦችን የአሠራር ሥርዓቶችን በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ለአብነት ያህል፤-
የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ
የምግብ፣ መድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002
የምግብ፣ መድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 299/2007
መሃበራዊ የጤና መድህን አዋጅ ቁጥር 690/2001
የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ 189/2002 (ከአሁን በኋላ ባለስልጣን እየተባለ የሚጠራው)
የኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ህግ
የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ ወ.ዘ.ተ የሚጠቀሱ ናቸው
የሕክምና ባለሙያዎችን በመቆጣጠር በህግ አውጪው አካል ፀድቀው ሥራ ላይ የዋሉት ህጐች መከላከልን እና ቅጣትን /prevented and punitive approach/ መሠረት አድርገው የወጡ ናቸው፡፡
መከላከልን መሠረት ያደረገ የቁጥጥር ስርዓት
መከላከልን መሠረት ያደረጉ የቁጥጥር ህጐች ዋና ዓላማቸው አንድ የህክምና ባለሙያ በሙያው ለመሰማራት ማሟላት የሚያስፈለገውን አስገዳጅ ወይም ዝቅተኛ መስፈርቶችን በመደንገግ እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ባለሙያዎች ብቻ በአንድ በተወሰነ የሕክምና ሙያ ውስጥ እንዲሰሩ የሙያ ፈቃድ በመስጠት መስፈርቱን የማያሟሉ ባለሙያዎች /unqualified professionals/ በሙያው ተሰማርተው የሚፈፅሙትን የሙያ ስህተት መከላከል ነው፡፡ መከላከልን መሠረት ያደረጉ የጤና ሙያ የቁጥጥር ህጐች የሙያ ፈቃድ መስጠትንና ማደስን የሚመለከቱ ብቻ ሳይሆኑ የሙያ ፈቃድ የወሰደ የሕክምና ባሉሙያ አንድን የተወሰነ ሕክምና አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ሊከታላቸው ወይም ሊያከብራቸው የሚገባውን የአገልግሎት ደረጃዎች (standard of health care) በግልፅ በማሳወቅ ከተቀመጠው ደረጃ በታች አገልግሎት እንዳይሰጥ ግንዛቤ መፍጠርን ያጠቃልላል፡፡ ለምሣሌ ያክል አዋጅ ቁጥር 661/2002 እና ደንብ ቁጥር 299/207 እንደቀደም ተከተላቸው በአንቀፅ 33 እና በአንቀፅ 63 ማንኛውም ሰው እንደ ጤና ባለሙያ ለመሠራት ባለስልጣኑ የክልል ወይም የፈደራል ተቆጣጣሪ አካል እንደስልጣን ወሰናቸው ለጤና ሙያ ሥራ ፈቃድ ያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልቶ ሲገኝ የጤና ሙያ ሥራ ፈቃድ ሲሰጠው ብቻ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የምንችለው አንድ የህክምና ባለሙያ በአንድ በተወሰነ የህክምና ሙያ ወሰን ለመሰማራት ባለስልጣኑ ያወጣቸውን መስፈርቶች (የትምህርት፣ ልምድ እና ክህሎት) በሟሟላት የሥራ ፈቃድ ሲወሰድ ይገባል፡፡ በተጨማሪም የጤና ሙያ በውስጡ ብዙ ዓይነት የጤና ሙያ ዘርፎችን የያዘ በመሆኑ ከአንድ በላይ የሆነ የጤና ሙያ ያለው ሰው አስፈላጊውን መስፈርት ሙያዎች ለመሥራት በሟሟላት የጤና ባለሙያ በሆነባቸው ሙያዎች ሁሉ መስራት የሚችለው በእነዚህ የሙያዎች ለመስራት የሙያ ፈቃድ ሲሰጠው ብቻ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ባለሥልጣኑ ደረጃውን ያልጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ብቃትና የሙያ ሥነ-ምግባር የጎደላቸውን የጤና ባለሙያዎችን ፈቃድ በመከልከል በዜጐች ላይ በሙያ ስህተት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መከላከል ይችላል ማለት ነው፡፡ በተመሣሣይ እንዲሁ የጤና ተቋምን ለማቋቋም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል የብቃት ማረጋገጫ የመስክር ወረቀት (certificate of competence) ማግኘት እንደሚገባው እና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በወሰደበት የአገልግሎት ዓይነት እና ደረጃ መሰረት ስራውን ማከናወን እንዳለበት በአዋጁ እና በደንቡ እንደቅደም ተከተላቸው በአንቀፅ 41 እና 90 ላይ ተደንግጓል፡፡
ቅጣትን መሠረት ያደረገ የቁጥጥር ሥርዓት
መንግሥት የጤና ባለሙያዎች በሚፈፅሙት የሙያ ስህተት ምክንያት በዜጐች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የማይተካ ጉዳት ለመከላከል ይችል ዘንድ በሙያው የሚሰማሩ ባለሙያዎች ሊያሟሏቸው የሚገባቸውን መስፈርቶች በማውጣት መስፈርቶቹን ለሚያሟሉ ባለሙያው እውቀት፣ ክህሎት እና ልምድ ላላቸው ብቻ የሙያ ሥራ ፈቃዱ በመስጠት እና በሙያው ሲሰማሩ ሊመሩባቸው የሚገባቸውን የጤና አገልግሎት ደረጃዎችና የሥነ-ምግባር መመሪያዎች በግልፅ እንዲያውቁት በማድረግ የመከላከል የቁጥጥር አቅጣጫ አንደሚከተል ተመልክተናል፡፡ ሆኖም ግን ሙያው የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው የጤና ሙያ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ባለሙያዎችና ተቋማት ደረጃውን ያልጠበቀ ወይም የሙያ ወሰናቸው መሠረት ያላደረገ የጤና አገልግሎት በመስጠት በዜጐች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም መንግሥት በሙያ ስህተት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለደረስባቸው ጉዳት ተመጣጣኝ ካሣ እንዲያገኙ፣ የሙያ ስህተት የፈፀሙትም ያጠፉትን ጥፋት አውቀው እንዲማሩ፣ እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ተመሣሣይ ስህተት እንዳይፈፅሙ ለማስተማር አስተዳደራዊ፣ ፍትሐብሔራዊ እና የወንጀል ተጠያቂነትን የሚደነግጉ ሕጐች በማውጣት ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ እነዚህን ተጠያቂነቶች እንደቅደም ተከተላቸው እንደሚከተለው እናያለን፡፡
3.1.1 አስተዳደራዊ ተጠያቂነት
አዋጅ ቁጥር 661/2002 በአንቀፅ 48 አግባብ ባለው አካል የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ወይም የሙያ ሥራ ፈቃድ የተሰጠው ማንኛውም ሰው ጤናን የተመለከቱ አዋጆችን፣ ደንቦችን ወይም መመሪያዎችን በመተላለፍ ሲሰራ የተገኘ እንደሆነ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ወይም ፍቃድ ሊታገድ ወይም ሊሰረዝ እንደሚችል በመደንገግ የሙያ ስህተት የሚፈፅሙ ባለሙያዎች ጥፋታቸው ሲረጋገጥ የጤና ሙያ የሥራ ፈቃዳቸው እንደሚሰረዝ ወይም እንደሚታገድ ይገልፃል፡፡ ይህንን አስተዳደራዊ ቅጣት (እርምጃ) በአግባቡ ለመፈፀም ይቻል ዘንድ ደንብ ቁጥር 299/2007 ዓ/ም በአንቀፅ 71 ደረጃውን ባልጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ብቃትና ሙያዊ ሥነ-ምግባር በጎደለው የጤና ባለሙያ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ የሚያጣራ፣ የሚመረምር እና ሊወሰድ ስለሚገባው አስተዳደራዊ እርምጃ የውሣኔ ሃሣብ ለባለሥልጣኑ የሚያቀርብ የጤና ባለሙያ ሥነ-ምግባር ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
3.1.2 የሕክምና ተቋማትና ባለሙያዎች የፍትሐብሄር ተጠያቂነት
የፍትሃብሔር ሕጋችን ከአንቀጽ 2639-2652 ሥለ ሕክምና ወይም ሆስፒታል ውል(contract of hospitalization) የሚደነግግ ሲሆን ታካሚው/ተገልጋዩ/ ከሕክምና ባለሙያው ወይም ከሕክምና ተቋሙ ጋር የሚኖረው የሕክምና ግንኙነት የሚመሰረተው በውል እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ የውል ግንኙነት በማይኖርበት ጊዜ ግንኙነታቸው ከውል ውጭ ኃላፊነት ሕግ መሠረት የሚታይ መሆኑን ከአንቀጽ 2037 መረዳት እንችላለን፡፡ በመሆኑም ታካሚው ከሕክምና ባለሙያው ወይም ተቋሙ ጋር ባለው የሕክምና ውል መሰረት ባለሙያው ወይም በተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ተገቢውን ክፍያ የመፈፀም ግዴታ ያለበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሕክምና ባለሙያው ወይም ተቋሙ የአገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ ወይም የሕክምና ደንቦችን ያከበረ ወይም መሠረት ያደረገ የሕክምና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ግን የሕክምና ተቋሙ ወይም ባለሙያ ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት የመስጠት የውል ግዴታውን በመተላለፍ/ የሙያ ስህተት በመፈፀም/ በታካሚው ላይ
የማይተካ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የሕክምና ተቋሙ ወይም ባለሙያው ላደረሰበት ጉዳት ተገቢውን ካሣ ለመክፈል ከውል የመነጨ ፍትሃብሔራዊ ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የሕክምና ግንኙነቱ በውል በማይመሠረትበት ወቅት ለምሳሌ ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎት ወይም በድሃ ደንብ ነፃ ህክምና በሚሰጥበት ሁኔታ ተቋሙ ወይም ባለሙያው በታካሚው ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት ከውል ውጭ ኃላፊነት ተጠያቂ ይሆናሉ (አንቀጽ 2126፣2127 እና 2130 ይመለከቷል)፡፡
የሕክምና ተቋማት የፍትሃብሔር ተጠያቂነት
በፍትሃብሔር ሕጋችን በአንቀጽ 2641 መሠረት የሆስፒታል ውል ማለት አንዱ የሆስፒታል መሥሪያ ቤት ስለ አንድ የታወቀ በሽታ ብዙ ሃኪሞች ወይም አንድ ሆኖ ለአንድ ሰው የሕክምና ሥራዎች ሊደረግለት የሚመሠረት ውል መሆኑን ይደነግጋል፡፡
በዚህ ውል መሠረት የሕክምና ተቋሙ ከታካሚው ጋር ባለሙ ግንኙነት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በታካሚው ላይ ለሚደርስበት ጉዳት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ተጠያቂ የሚሆኑት በአስተዳደራዊ እና በሕክምና መሣሪያዎች ጉድለት/ Medical equipment deficiencies /፣ በኃይል መቋረጥ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በታካሚው ላይ ጉዳት ሲደርስ ነው፡፡ ለምሣሌ፡- በአዋጅ ቁጥር 661/2ዐዐ2 በአንቀጽ 44 መሠረት ማንኛውም የጤና ተቋም በአስፈፃሚ አካሉ የወጡ የጤና አጠባበቅ ደረጃዎችን/ Standard of hygienic requirements/ በማሟላት የሕክምና አገልግሎት መሥጠት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ግን የጤና ተቋሙ የጤና አጠባበቅ ደረጃዎችን ባልጠበቀ መልኩ/ Sub-standard hygienic condition/ አገልግሎቱን በመስጠት በታካሚው ላይ ጉዳት ቢያደርስ ተቋሙ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በተመሣሣይ እንዲሁም ታካሚው ስለሕክምናው ጥቅም በማለት በሆስፒታሉ ወይም በሕክምና ተቋሙ የተቀመጠና የተመገበ እንደሆነና በምግብ ወይም በመኝታ አገልግሎት ችግር ምክንያት በታካሚው ላይ ጉዳት ቢደርስበት የሕክምና ተቋሙ ተጠያቂ ይሆናል/አንቀጽ 2652 ይመለከታል/፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ የሕክምና ተቋማት በፍትሃብሔር ተጠያቂ የሚሆኑበትን አግባብ እንመለከታለን፡፡
የሕክምና ተቋማት በሕክምና ባለሙያዎቻቸው ለሚፈፅሙት የሙያ ስህተት
ያለባቸው ተጠያቂት
የሕክምና ተቁማት ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ተጠያቂነት በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎች በሚፈፅሙት የሙያ ስህተት ተቋሙ በፍትሃብሔር ተጠያቂ የሚሆንበትን አግባብ የሚያመለክት ነው፡፡ እንደሚታወቀው የሕክምና ተቋማት የጤና አገልግሎት የሚሰጡት በሕክምና ባለሙያዎችና በረዳቶቻቸዉ አማካኝነት ነው፡፡ የሕክምና ተቋሙ ከታካሚው ጋር ያለው ግንኙነት ከውል ወይም ከውል ውጭ ሊመነጭ እንደሚችል ተመልክተናል፡፡ ግንኙነቱ ከውል የመነጨ ሲሆን የተቋሙ የሕክምና ባለሙያዎችና ረዳቶቻቸው የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የሙያ ስህተት በመፈፀም በታካሚው ላይ ጉዳት ካደረሱ የሕክምና ተቋሙ የውል ግዴታውን ባለመፈፀሙ በፍትሃብሔር ተጠያቂ እንደሚሆን በአንቀጽ 2651 ተመልክቷል፡፡ የዚህ ድንጋጌ መሠረቱ ታካሚው ከተቋሙ ጋር ያለው የሕክምና የውል ግንኙነት ሲሆን በዚህ ውል መሠረት ተቋሙ የሕክምና ደንቦችን በማክበር ለታካሚው ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ግን የሕክምና ተቋሙ በባለሙያዎች የሕክምና አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ባለሙያዎቹ አንድን የታወቀ በሽታ ለማከም ሊከተሏቸው ወይም ሊያከብሯቸው የሚገባቸውን የሕክምና ደንቦች ባለማክበራቸው ወይም ደረጃውን ያልጠበቀ የጤና አገልግሎት ባለመስጠታቸው በታካሚው ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ጉዳት የደረሰበት ታካሚ በሕክምና ስህተት ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በማስረዳት ተመጣጣኝ የሆነ የጉዳት ካሣ እንዲከፈለው ውሉን መሰረት በማድረግ የሕክምና ተቋሙን በፍትሃብሔር መክሰስ እንደሚችል ከአንቀጽ 2651 እና 1790 መረዳት እንችላለን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የህክምና ተቋማት የፍትሐብሄር ተጠያቂነት ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት ይመነጫል ይህም የሚከሰተው ተቋማቱ ከታካሚው ጋር የህክምና ግንኙነት ሳይኖረው የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ ነው፡፡ የህክምና ተቋሙ ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት (ለምሳሌ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ወይም መከፈል ለማይችሉ በድሀ ደንብ ) የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ ባለሙያዎቹ ላደረሱት ጉዳት ኃላፊነት (vicarious liability) ይኖርበታል (አንቀጽ 2126፣2127፣2129ና 2130 ይመለከቷል)፡፡
ከውል ውጭ በሆነ ኃላፊነት የመንግስትና የግል የጤና ተቋማት በህክምና ባለሙያዎቻቸው ጥፋት ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብ የተለያየ ስለሆነ ነጣጥለን ማየቱ ተገቢ ነው፡፡
ሀ) የመንግስት የጤና ተቋማት ከውል ውጭ ኃላፊነት
የመንግስት የጤና ተቋማት በህክምና ባለሙያዎቻቸው ከውል ውጭ ኃላፊነት የሚኖርባቸው ባለሙያው አገልግሎቱን ለታካሚው በቅን ልቦና፣ በስልጣኑና ለተቋሙ መልካም ያደረገ መስሎት በፈፀመው የህክምና የህክምና ስህተት በታካሚው ላይ ጉዳት ሲያደርስ መሆኑን ከአንቀጽ 2126(2) እና 2127(1) መረዳት እንችላለን፡፡ በተጨማሪም ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ በመንግስት የህክምና ተቋም የህክምና አገልግሎት ስራ ላይ የተፈጸመ ጥፋት እንደስራ ጥፋት ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ ውጭ በሆነ በማንኛውም ሌላ ጉዳይ ባለሙያው በታካሚው ላይ ጉዳት ቢያደርስ እንደግል ጥፋት ሆኖ እራሱ ኪሳራውን (የጉዳት ካሳውን) ለመክፈል እንደሚገደድ አንቀጽ 212612 እና 2127(2) አጣምረን ስናነብ መረዳት እንችላለን፡፡ ባለሙያው ያደረሰው ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመስጠት የተቋሙን ስራ እየሰራ ባለበት ወቅት በፈጸመው የሙያ ስህተት የሆነ እንደሆነ ታካሚው ተቋሙን ካሳ እንዲከፈለው መጠየቅ የሚችል ሲሆን የህክምና ተቋሙ የሚከፈለውን ገንዘብ ጉዳቱን ከደረሰው የህክምና ባለሙያ ለመጠየቅ መብት እንዳለው በአንቀጽ 2126(2) ተደንግጓል፡፡
ለ) ለትርፉ የተቋቋሙ የጤና ተቋማት ከውል ውጭ ኃላፊነት
ለትርፍ የተቋቋሙ የግል የጤና ተቋማት (for-profit health institution) ሰራተኛ የሆነ የህክምና ባለሙያ ስራውን የሚያከናውንበት ጊዜ የህክምና ስህተት በመፈጸም ኃላፊነት የሚያስከትል ጉዳት በታካሚው ላይ ቢያደርሱ ተቋሙ የጉዳት ከሳ የመክፈል ከውል ውጭ ኃላፊነት እንዳለበት ከፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 2129 እና 2130 መረዳት እንችላለን፡፡ ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ በስራ ቦታና ሰአት የተፈጸመ ጥፋት ስራን ለማከናወን ሲባል (in the discharge of function) እንደተፈጸመ እንደሚቆጠር በአንቀጽ 2132 የህግ ግምት ሰጥቶታል፡፡ ሆኖም የህክምና ተቋሙ ይህን ግምት ለማስተባበል ተቃዋሚ ማስረጃ በማቅረብ ኃላፊነቱን ቀሪ ማድረግ ይችላል፡፡
3.1.2.2 ከህክምና ውል የመነጨ የአንድ የሕክምና ባለሙያ የፍትሐብሄር ተጠያቂነት
የፍትሐብሄር ህጋችን በአንቀጽ 2639 የህክምና ውል ማለት አንድ ሀኪም ውለታ ገብቶ የሚገባውን ገንዘብ በመቀበል ላንድ ሰው የህክምና ስራዎችን እንዲያደርግለትና በተቻለውም በመልካም ጤና እንዲቆይ ወይም ሊያድነው የሚደረግ ውል ነው፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የምንችለው አንድ የሕክምና ባለሙያ ባለው የህክምና ሥራ ሙያ ፈቃድ ከታካሚዎች ጋር የህክምና ውል በመፈጸም የሕክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው፡፡ ይህ አይነቱ የሕክምና ውል በሁለት መንገድ ይፈፀማል፡፡ የመጀመሪያው የህክምና
ባለሙያው በባለቤትነት በሚያስተዳድራቸው የተወሰኑ የህክምና አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን በመጠቀም በሥራ ሙያ ፈቃዱ ወሰን መሰረት ለደንበኛው(ለታካሚው) ያለማንም ጣልቃ ገብነት በነፃነት የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሕክምና ለመስጠት የህክምና ውል ከታካሚው ጋር መመስረት ይችላል፡፡ ሁለተኛው ልዩ የህክምና እውቀት (medical specalist) ያለው የህክምና ባለሙያ በትርፍ ጊዜው ባለው ልዩ እውቀት አንድን የተወሰነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከሆስፒታል ወይም ከሌላ የህክምና ተቋም ጋር የተቋራጭነት ውል (independent contractor) በመመስረት የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ባለሆነ መልኩ የህክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከታካሚው ጋር የህክምና አገልግሎት ውል በመመስረት አገልግሎቱን በውሉ መሰረት መስጠት ይችላል፡፡ የህክምና ውል ከታካሚው ጋር የመሰረተ አንድ የህክምና ባለሙያ የህክምና አገልግሎቱን ለታካሚው ራሱ ብቻ መስጠት እንዳለበት በአንቀጽ 2649 የተመለከተ ቢሆንም በሱ መሪነትና ሙሉ ኃላፊነት የህክምና አገልግሎቱን በረዳቶቹ መስጠት እንደሚችል በዚሁ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 2 ስር ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን ከረዳቶቹ በአንዱ ጥፋት ህክምና የተደረገለት ሰው ለደረሰበት ጉዳት ሃኪሙ ኪሳራ እንዲከፍለው በውል ውጭ ኃላፊነት ሊጠይቅ እንደሚችል ከአንቀጽ 2649 እና 2130 መረዳት እንችላለን፡፡ በተጨማሪም ሃኪሙ በሙያው የኪነ-ጥበብ ደንቦች መሰረት አገልግሎቱን ሳይሰጥ በመቅረቱ በታካሚው ላይ ጉዳት ቢያደርስ የፍትሐብሄር ተጠያቂነት እንዳለበት በአንቀጽ 2647 ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም ታካሚው በሃኪሙ የሙያ ስህተት ምክንያት የደረሰበት ጉዳት ካለ ጉዳቱን በማስረዳት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንዲከፈለው በፍትሃብሄር መክሰስ ይችላል ማለት ነው፡፡
ውድ አንባብያን የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት በሚፈፅሙት የህክምና ስህተት ያለባቸውን የወንጀል ተጠያቂነት ዙሪያ በሚቀጥለው እትም ማብራሪያ ሚሰጥበት መሆኑን እየገለፅን አስተዳደራዊ እና ፍትሃብሄራዊ ተጠያቀነት ዙሪያ የተዘጋጀውን ማብራሪያ በዚሁ እጨርሳለሁ፡፡
By Abduljebar Husein
Via legal consulting limited
https://t.me/lawsocieties
የሙያ ጥፋት ምንድን ነዉ?
(Professional Fault)
=======================
ሙያ የሚባለዉ ልዩ ስልጠና፣ልዩ ዕዉቀትና ችሎታ የሚጠይቅ የስራ መስክ ነዉ።ሙያ በከፍተኛ የትምህህርት ተቋማት ገብቶ በመማር የሚገኘዉን አንደሕክምናምህንድስና፣ሕግመምህርነት የመሳሰለዉን ሲሆን በስራ ላይ ባለሙያዎች የሚሰሩትን እያዩ ወይም አበሮ በመስራትም የሙያ ዕዉቀት በማግኘት ባሉያ መሆን ይቻላል።
አንድ ባለሙያ ሙያ ብቻ ሳይሆን የሙያዉን የስነ ምግባር ደንብ ጨምሮ ጠንቅቆ ማወቅና ኃላፊነቱን ከሙያዉ የስነ ምግባር ደንብ አንፃር በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል።የሙያ ጥፋት ብዙን ጊዜ የሚከሰተዉ ባለሙያዉ የሙያ ተግባሩን በሚፈጽመበት ጊዜ የሙያ ደንቦች ባለማክበሩ የሚከሰተ ጥፋት ነዉ።
የሙያ ጥፋትን ፍትሐ ብሔር ሕጉ ምን ይላል?
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031 መሰረት በለዩ ሙያዉ አንድ ስራ የሚፈፅም ሰዉ የሙያ ስራዉ የሚመራበትን ደንብ መጠበቅ እንደሚገባዉ የሕግ ግዴታ ተጥሎበታል።ይህ ባለሙያ በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች ሁሉ የሚያወቋቸዉን ደንቦች እና መመሪዎች ሳያከበር ቢቀር የሙያ ጥፋት ፈፀመ ይባላል። ለመሆኑ የሙያ ደንቦች
የሚባሉት የትኞቹናቸዉ?የሙያደንቦች በሕግ የተደነገጉወይም በሙያዉ የተሰማሩ ሰዎች አዉቀዉየሚገለገሉባቸዉ ከተለመዱ የመልካም አስራር መመሪያዎች የመነጩ ሊሆን ይችላል።
አንድ ባለሙያ የሙያ ደንቦችን ጣሰ የሚባለዉ መቼ ነዉ?ደንቦች በሕግ በግልፅ የታወጁ በሆነ ጊዜ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2035 መሰረት ባለሞያዉ በግልጽ የተመለከተዉን ደንበና ስርዓት የጣሰ እንደሆን ጥፋተኛ ነዉ።
የሙያ ደንቦቹ በሕግ በግልፅ ያልተደነገጉ ሳይሆኑ ከተለመዱ የመልካም አሰራር መመሪያዎች የመነጨ በሆነ ግዜ የባለሙያዉ ተግባር ጥፋት የሚሆነዉ ሌላ ጥበብ ካለዉ አመዛዛኝ በሆነ ሰዉ አስራር የሚመራ ባለሙያ ጋር ሲነፃፀር ትክክል ሆኖ ያልተገኘ እነደሆነ ነዉ።
የሙያ ደንቦች ሁሌም ቋሚ ናቸዉን?አንዳንድ ሙያዎቸ የሚተዳደሩት አንዴ በተወሰኑና በልማድ ላይ በተመሰረቱ ደንቦች ብቻ ሳይሆን በየጊዜዉ እያደገ እየተቀያየረ በሚሄድ በስነ ጥበብ ደንቦች ጭምር ነዉ።በመሆኑም አንድ ባለሙያ በየጊዜዉ እነዚህን ደንቦች የመመለከትና በሙያዉም የሚደረገዉን ምርምርና ለዉጥ ሁሉ የማወቅ ግዴታዉን መዘንጋት የለበትም።
አንድ ባለሙያ በዉል የገባዉን ግዴታ እንዴት ይወጣዋል? በመርህ ደረጃ አንድ ሰዉ በዉለ የገባዉን ግዴታ ካለተወጣ ከአላፊነት አያመልጥም።ነገር ግን በፍትሐ ብሔረ ሕግ ቁጭር 1795 መሰረት በዉል ግንኙነት በአንድ ሙያ የሚችለዉን ያህል በቻ ለማድረግ ዉል የገባዉ በሙያዉ ደንቦች መሰረት የተቻለዉን ሁሉ በሙሉ ኃላፊነትና በጥንቃቄ ካከናወነ አላፊነት የለበትም።ይህም ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመዉ የዕዉቀት ስራን በሚመለከቱ እንደ ሕክምና ባሉ ጉዳዮቸ ላይ ነዉ። ለምሳሌ አንድ ሐኪም በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2647 ድንጋጌ መሰረት በኪነ ጥበብ ደንቦች ጥፋት ካላደረገ በቀር ለመታከም ለተዋዋለዉ ሰዉ አላፊነት የለበትም። ነገር ግን በሙያዉ ኪነ ጥበብ ደንቦች መሰረት መስራት የሚገባዉን ሳይሰራ በመቅረቱ ወይም መስራት የማይገባዉን በመስራቱ ምከንያት የሕክምና አገልገሎት በሰጠዉ ሰዉ ላይ ጉዳት የሚያመጣ ተግባር የፈፀመ እንደሆነ እንዲሁም ሕክምና ሊያደርግለት የተቀበለዉን ሰዉ በቂ ባልሆነ ምክንያት ሳይረዳዉ የቀረ እንደሆነ በሰራዉ ተጠያቂ ነዉ።
በሙያ ስራ ሰለሚደረግ ጥፋትና የፍትሐ ብሔር ኃላፊነት፡ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2030 መሰረት አንደ ሰዉ ሕሊናን ወይም መልካም ጠባይን ተቃዋሚ በሆነ ዓይነት የማየገባዉን ስራ የሰራ ወይም የሚገባዉን ሳይሰራ የቀረ እንደሆነ ጥፋት አንደፈፀመ ይቆጠራል።
በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2031 መሰረት በልዩ ሙዉ አንድ ስራ የሚፈጽም ሰዉ በስነ ጥበብ ወይም ራሱ በሚሰራዉ ኪነ ጥበብ ደንቦች መሰረት ያሉበትን ግዴታዎች አለመከተሉ ሲገለጽ ባለመጠንቀቅ ወይም በቸልተኝነት ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ አላፊ/ተጠያቂ/ ይሆናል።
እንዲሁም ለመጉዳት በማሰብ እያወቀ በሌላ ሰዉ ላየ ከፍ ያለ ጉዳት ያደረሰ ሰዉ በሰራዉ ስራ የጠያቂ ነዉ።
በሙያ ስራ ስለሚደረግ ጥፋትና የወንጀል አላፊነት፡ የወንጀል አላፊነት የሚኖረዉ በወንጀል ሕጉ እንዳይደረግ የተከለከለዉን በማድረግ ወይመ እንዲደረግ የታዘዘዉን ባለማድረግ ነዉ።
በወንጀል ሕግ ቁጥር69 መሰረት የሞያ ገዴታን ለመወጣት የተፈጸሙ ደረጊቶች ከሙያዉ ደንብና አሰራር ልማድ ዉጭ ካልሆኑና በከባደ የሙያ ጥፋት ካልተፈጸሙ በቀር አያሰቀጡም ይላል።ከድንጋጌዉ መረዳት እንደሚቻለዉ በሙያ ስራ የሚፈጸም ድርጊት ጥፋት ወይም ቸልተኝነት ከሌለበት በቀር አያስቀጣም።
በወንጀል ሕግ ቁጥር 575 መሰረት ማንም ሰዉ የሞያ ግዴታን በመተላለፍ አስቦ በሰዉ አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል። ማንም ሰዉ በሕይወቱ፤ በሰዉነቱ፤ወይም በጤንነቱ ላይ ሊደርስ በሚችል ከባድ አደጋ ላይ የሚገኘዉን ሌላ ሰዉ ለመታደግ ወይም ለመርዳት የሙያ ግዴታ እያለበት ሊረዳዉ ሲችል አሰቦ ሳይረዳዉ የቀረ እንደሆነ በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል።
ማንም ሰዉ የሌላ ሰዉን አካል ወይም ጤንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለበት በቸልተኝነት በሌላ ሰዉ አካል ወይም ጤንነት ላይ ጉዳተ ያደረሰ እንደሆነ በወንጀል ሕግ ቁጥር 559 መሰረት ተጠያቂ ይሆናል።
እንዲሁም የሌላ ሰዉን ሕይወት፤ጤንነት ወይም ደህንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለበት በቸልተኝነት ሰዉን የገደለ ሰዉ ቅጣቱ እንደሚከብድበት የወንጀል ሕግ ቁጥር 543(2) ይደነግጋል።
በሙያ ጥፋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች ምን መብት አላቸዉ? ጉዳት የደረሰበት ሰዉ የባለሙያዉን አድራጎት ጥፋት መሆኑንና በዚህም የተነሳ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በማስረዳተ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2028 መሰረት ለደረሰበት ጉዳት ካሳ እንዲከፈል ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ይቻላል። ነገር ግን ጉዳያቸዉን በራሳቸዉ ለመከታተል በአቅም ምከንያት የማይችሉ ዜጎች የአቅም ችገ ያለባቸዉ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ በመያዝ በጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ በዋናዉ መ/ቤትና በልደታ ወንጀል ዘርፍ እንዲሁም በአዲስ አበባ አሰሩም የጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ምድን ጽ/ቤቶች በመቅረብ ጉዳያቸዉን ዐቃቢ ህጎች እንዲከታተሉላቸዉ ማመልከት ይችላሉ። እንዲሁም የአቅም ሳይሆን የሕግ ዕዉቀት ችግር ያለባቸዉ ዜጎችም እንዲሁ ወደ ጽ/ቤቶች በመምጣት የምክር አገልግሎት በነጻ ማግኘት ይቻላል።
ሙያን አክበሮ መስራት የዜግነት ግዴታ ነው! ሃላፊነታችንን በያለንበት የሙያ መስክ በብቃት እንወጣ!
Source:- Federal Justice and Legal Research and Training Institute official
Via Tsegaye Demeke Lawyer
https://t.me/lawsocieties
Hard work is a must thing for success.
❤️🔴❤️
https://t.me/lawsocieties

Smart work is not a substitute for hard work, it is another wing of the bird which can take you to your success.

In short, there is no substitute for hard work! You have to be ready for it.
Put everything you have for what you want, This is the way of massive success!

Problems are going to be there always! Tackle them.
You have only two choices, one is EXCUSES and other is RESULTS. The choice is yours!

Don’t sacrifice your dreams for temporary pleasure. Neither this pleasure is going to come with you nor this pain.

Choose temporary pain for your permanent happiness. ⭐️

Give your 100% (not even 99%) for your dreams!
Don’t run away from hard work. This is going to give you your dreams! 💪
https://t.me/lawsocieties
How To Deal With Immature People?

We come across different types of people in our life. Each person has some limitations, but it entirely depends on how we react to the situation. Either we can let it affect us, or we can feel compassionate towards them.
Never let others' immaturity affect your life.
Just smile through and remind yourself "Their maturity is only so much".
https://t.me/lawsocieties
የድርጅት ስም የውሃ ልማት ኮሚሽን
ምዝገባ የሚያልቅበት ቀን: ጥር 06, 2013
ተፈላጊ ብዛት: 03 ቦታዎች የስራ ልምድ የማይጠይቁ 03 ቦታዎች የስራ ልምድ ላላቸው

የስራ መደብ: የህግ ባለሙያ
ደመወዝ: 4379 ብር
ተፈላጊ ብዛት: 01
የስራ ልምድ: 0 ዓመት
የትምህርት ደረጃ: በሕግ ባችለር ዲግሪ ያለው/ላት

ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፡ https://ayerbayer.com/water-development-commission-job-vacancy-announcement-ayerbayer/

https://t.me/lawsocieties
#Laws Update – Negari
ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ሲሠራባቸው የቆዩ የዋስተና ሕጎች፦
1. ስለንግድ ተቋም የዋስትና መያዣ የወጣ አዋጅ ቁጥር 98/1990
እና
2. በተንቀሳቃሽ ንብረት የመያዣ መብት ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የአዋጅ ቁጥር 97/1990 ድንጋጌዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት መሻራቸውን ያውቃሉ?

አዋጅ ቁጥር 1147/2011በነጋሪ መተግበሪያ አካትተናል። ይህንን አዋጅ ከዚህ ይመልከቱ፦
http://negari.abyssinialaw.com/laws?id=1846
ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ /Force majeure/
========================
1 • ከአቅም በላይ የሆነ ሊመልሱት የማይቻል ኃይል
2 • ባለእዳው በምንም መልኩ በቅድሚያ ሊያስበው ወይም ሊገምተው የማይችል ክስተት
ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ደርሷል የሚባለው ባለዕዳው ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግዴታውን እንዳይፈጽም ፍፁም መሰናክል በሆነ አይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመ ጊዜ ነው፡፡ በአእምሮ ግምት ባለዕዳው ቀደም ብሎ ሊያስብበት የሚችል መሆኑ የታወቀ አንድ ድንገተኛ ደራሽ ነገር ወይም ለውሉ አፈፃፀም ከባድ የሆነ ወጭ በባለዕዳው የሚደርስበት ቢሆን ከአቅም በላይ የሆነ ኃይል ነው ተብሎ አይገመትም፡፡ ስለሆነም ባለዕዳው ሁኔታው ሊፈጠር ወይም ሊከሰት እንደሚችል ቀድሞ ሊገመት ወይም ሊያስብና ጥንቃቄ ሊያደረግበት የሚችል ከሆነ ሁኔታው ድንገተኛ ደራሽ ነገር ቢሆን እንኳን ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ እንደተከሰተ አይቆጠርም፡፡
ሰ/መ/ቁ.14605 ቅጽ 1፣ ሰ/መ/ቁ. 26565 ቅጽ 5፣ ሰ/መ/ቁ. 85468 ቅጽ 15፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1791፣ 1792፣ 1793 (ሀ) እና (ለ)
የመኪና አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ በመንገዱ ላይ ድንገት ሰው ሊገባ ወይም ድንገተኛ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ብሎ ፈጽሞ አያስብም ተብሎ አይገመትም፡፡ በመሆኑም ድንገት ሰው ሮጦ ወደ በመንገዱ መግባቱ ብቻ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ መኖሩን አያሳይም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 14605 ቅጽ 1
የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ከአቅም በላይ የሆነ ኃይል ተብሎ ሊወሰድ የሚችል አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 85468 ቅጽ 15
በጉዞ ላይ ያለ ተሽከርካሪ የኤሌትሪክና የመካኒክ ሲስተሙ ድክመት ስለገጠመው በኤሌትሪክ መስመሩ ላይ ከፍተኛ ኃይል ያለው ኬብል ስራውን ስላቋረጠ ከብረት ጋር በመጋጨቱ ምክንያት በተነሳው እሳት ምክንያት ንብረት በቃጠሎ ቢወድም አደጋው አጓዡ ሊገምተውና ሊያስቀረው በማይችል ከአቅም በላይ በሆነ ሀይል ምክንያት የተፈጠረ ነው ሊባል አይችልም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 26565 ቅጽ 5
via legal consulting limited
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በዋስትና በማስያዝ ብድር የመስጠት የባንኮች ኃላፊነት

በ፡ ገዙ አየለ መንግሥቱ

ይህ ጽሑፍ በአዲሱ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1147/2011 - በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሠረት የዋስትና መብት አዋጅን መሠረት በማድረግ ዋና ዋና ነጥቦችን ያብራራል።

በተለይም አዋጁ የያዛቸውና የሚያተኩርባቸው ነጥቦች ለአበዳሪ ባንኮችም ጭምር አዲስ በመሆናቸው አዋጁን የሚጠቀሙት አስፈጻሚዎችም ሆኑ የባንክ ባለሙያዎች እንዲሁም ከዚህ አዋጅ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለአዋጁ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ውስብስብነት የሚታይበትን ይህንኑ አዋጅ መሰረታዊ ነጥቦቹን ለማስገንዘብ ከፍኛ ጠቀሜታ ስላለው ስለአዋጁ እና በባንኮች እንዴት ሊፈጸም እንደሚችል እንዲሁም የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሲባል ምን ምንን ያካትታል፤ በዚህ አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ምን ምን ጉዳዮችን ማማላት ያስፈልጋል፤ የአዋጁ ዋነኛ ትኩረት ምንድን ነው የሚሉና ሌሎች መሰረታዊ ነጥቦችን ጠቅለል ባለ መልኩ ዳሰሳ ተደርጎባቸዋል።

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1984-movable-property-security-right
I have one life to live.............❤️ I have a unique gift something special that only I am capable of bringing to life. I keep going and keep doing working on my dream. I give the best in my field... I enjoy the simple pleasure of life , laugh , love , explore and make a difference wherever I am. I do something everyday that reminds I am being fully alive. Yes , I determine to enjoy my life in small as well as big ways. I live a life that has meaning and value to me........🩸

https://t.me/lawsocieties

Have amezing day 💕 😊 🙏 🤗 👍
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties