አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የወንጀል ፍትህ አስተዳደር እና የሕግ የበላይነት በህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ እውን ይሆናል!
____________

መንግሥት የአገርን ብሔራዊ ደህንነትና የሕዝቡን ሰላም ማረጋገጥ ተቀዳሚ ኃላፊነት ቢሆንም ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚፈለገውን ውጤት ማረጋገጥ እና እውን ማደረግ አይቻልም፡፡

ህዝብ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም የወንጀል ፍትህ ሥርዓቱ አፈፃፀም ብቃት ለማሳደግ የሰላ ጫፍ ነው፡፡

ውድ እንባቢያን! የአገራችን ህዝብ ብሂል መሰረት መሬት እና ጎጆ በአንድ በሬ ብሎም በላ እይቆምም እንደሚባለው ሁሉ ወንጀልን ለመከላከል፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ፍትህ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ የፍትህ አካላት በሚሰሩት ሕግ የማስከበር የለውጥ እንቅስቃሴ በህዝብ ተሳትፎ የተደገፈ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

በአገራችን የረጋና ሰላማዊ ሁኔታ ለመፍጠር ህብረተሰቡ ስለሕግ፣ ፍትህ እና ወንጀል ያለው በጎ አመለካከት መያዝ ሕግና ሥርዓት ለማስከበር እና ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል መሆኑን ለማረጋገጥ የእድል የሚፈጥር ነው፡፡

ህዝብ ዋነኛ የፍትህ ተጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር፣ በሂደቱ ለሚፈለጉ መረጃዎች ዋነኛው ምንጭም ሲሆን በፍትህ ሥርዓቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማመላከት የማይተካ ሚና አለው፡፡

ቀልጠፋና ውጤታማ የሆነ የፍትህ ሥርዓት መኖር የተፋጠነ ልማትን ለማምጣት ሰላምንና መረጋጋትን ለመፍጠር ህግና ስርዓት በአስተማማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡

ስለሆነም ህብረተሰቡ ከወንጀል ስጋት እና ከማህበረሰባዊ ጠንቆች ነፃ ሆኖ በልማት ተግባሩ ላይ ብቻ እንዲሳተፍ አስተማማኝ ደህንነት እንዲሰማው ማድረግ ለአንድ ወገን የተሰጠ ተግባራ ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት ነው፡፡

በመሆኑም መንግስት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ሕጋዊ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር የህዝብ እና የመንግስትን ጥቅም ብሎም ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ እየተወሰደ ያለው ሕጋዊ እርምጃ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሕግን አክብሮ መሥራት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሕግን አክብረው መስራታቸውን መከታተልና ሕግን ጥሰው የሚገኙትን በቅንጅት ለፍርድ ማቅረብ ከመልካም እና አገር ወዳድ ዜጋ የሚጠበቅ በመሆኑ ለአገር ሰላም እና ለሕግ የበላይነት በአንድነት እንቁም መልዕክታችን ነው፡፡
በወንጀል ጉዳዮች ይርጋ በኢትዮጵያ ህግ

የይርጋ ምንነት
ይርጋ ማለት አንድ ሰው በጉዳዩ ላይ መብት ያለው ቢሆንም ይህንን መብቱን ለመጠየቅ የማይችልበትን ገደብ የሚመለከት ሲሆን ይህም በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ በአንድ ጉዳይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከልበት የህግ ፅንሰ-ሃሳብ ነው፡፡ ይርጋ በወንጀል እና በፍትሀ ብሄር ህጎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በወንጀል ጉዳይ ላይ ይርጋን በመቃወሚያነት አንስቶ ለመከራከር የሚችለው ተከሳሽ፣ ዐቃቤ ሕግና ፍርድ ቤቶች ስለመሆናቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 130/1/ሐ እና በወንጀል ሕግ 216(2) ላይ ተመልክቷል፡: በወንጀል ጉዳዮች ላይ ተከሳሹ ባያነሳውም ዳኞች በይርጋ የታገደ የወንጀል ክስ ሲቀርብላቸው ማየት አይችሉም፡፡ስለሆነም ክሱ በይርጋ ስለመታገዱና ክሱን ለመቀበል የማይገባ ስለመሆኑ ተከሳሽ ባያመለክትም ዐቃቤ ሕጉ ወይም ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡

በተመሳሳይ ቅጣቱ ሳይፈፀም የይርጋው ጊዜ ካለፈ አጥፊው ራሱ ባያነሳውም እንኳ አስፈፃሚው አካል ሊያነሳው እንደሚገባ በወንጀል ህግ አንቀፅ 216(2) እና 223 (2) ተገልጿል፡፡ለይርጋ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወይም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ሊወሰን አይችልም፡፡በፍትሀ ብሄር ጉዳዮች ግን ይርጋን እንደመቃወሚያነት ማንሳት የሚችለው ተከሳሽ ብቻ ሲሆን ይህንንም ማድረግ የሚችለው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክሱ መሰማት ከመጀመሩ እና ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር በተከሳሽ በኩል ተፈፅሟል አልተፈፀመም የሚለው ላይ ክርክር ከመደረጉ በፊት ነው፡፡ይርጋ በተከሳሹ ካልተነሳ ለማንሳት እንዳልፈለገ ስለሚቆጠር ዳኛው በራሱ ተነሳሽነት እንዲያነሳ ሕጉ አይፈቅድም፡፡

በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች
በመርህ ደረጃ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ ያለ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ህግ ከተደነገገ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎች እንዳሉ ከወንጀል ህጉ እንቀፅ 216/1 መገንዘብ ይቻላል፡፡በይርጋ የማይታገዱ የወንጀል ድርጊቶችን ከሚያስቀምጡ የህግ ድንጋጌዎች የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት ቀዳሚው ነው፡፡በህገ መንግስቱ አንቀፅ 28/1 ስር እንደተደነገገው ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች ሕጎች የሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑ ወንጀሎች ፣የሰው ዘር ማጥፋት፣ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡

በዓለም አቀፍ ሕግና ልምድ መሠረት በተለይም ይርጋ በጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ እንዳይፈፀም ለማስቀረት በተደረገው ስምምነት እና በሮም የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ መሰረት የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲሁም የጦር ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚቀርቡ ክሶች በይርጋ የማይታገዱ ናቸው::

ይርጋ ያስፈለገባቸው ምክንያቶች
የይርጋ ፅንሰ ሃሳብ እንዲኖር ያስፈለገባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች ከሳሽ በተገቢ ትጋትና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል፣ተከሳሽ በጣም ዘግይተው ለሚመጡ ክሶች የመከላከያ ማስረጃዎች እንዳያጣ ለማድረግ እና ሰዎች መብታቸውን የሚጠቀሙበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ህብረተሰቡን ከስጋት በማዳን የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ማስቻል ናቸው፡፡ይርጋ በዋናነት ጠቀሜታ የሚኖረው ለተከሳሽ መሆኑን ከህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሆኑም ተከሳሽ በይርጋ በታገደ ጉዳይ ላይ ክስ ከቀረበበት በመቃወሚያ በማንሳት ክሱ ቀሪ እንዲሆንለት መጠየቅ ይችላል፡፡

በወንጀል ህግ ውስጥ የወንጀል ይርጋ በሁለት የተከፈለ ነው፡፡ ይኸውም የክስ ይርጋና የቅጣት ይርጋ ናቸው፡፡የክስ ይርጋ ዐቃቤ ህግም ሆነ የግል ተበዳይ (ወንጀል የተፈፀመበት ሰው) ወንጀል ፈጽሟል በተባለው ሰው ላይ ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚያስቀምጥ ሲሆን ዝርዝር አሰራሩ በወንጀል ህግ አንቀጾች 216-222 ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል የቅጣት ይርጋ ከቅጣት አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ሰው ጥፋተኛ ነው ተብሎ ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ ቅጣቱ ሳይፈፀም ቢቀር በሕግ የተመለከተው ጊዜ ካለፈ ቅጣቱን የማስፈፀም መብት እንደሚቀር የወንጀል ህግ አንቀፅ 223 ስር ተቀምጧል፡፡እንዲሁም የዋነኛው ቅጣት የይርጋ ዘመን የተጨማሪ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እር

ምጃዎች መፈፀምንም ያስቀራል፡፡እንደ ወንጀሉ ክብደትና ቀላልነት የቅጣት ይርጋ በስላሳ ፣ በሃያ፣ በአስርና በአምስት ዓመት ሊወሰን እንደሚችል የወንጀል ህግ አንቀፅ 224(1) ዘርዝሮ ያስቀምጣል፡፡
ይርጋን አስመልክቶ በህግ ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎች በዋናነት የሚያመላክቱት ክስ ለማቅረብ ወይም መብት ለመጠየቅ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ እንደመሆኑ ይህን ለማድረግ እንዲቻል በህግ የሚጠየቀው የጊዜ ገደብም እንደ ጉዳዩ ክብደት፣ባህሪይና ሁኔታ የተለያየ ሲሆን ለሁሉም ጉዳዮች የተቀመጠ ተመሳሳይ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ የለም፡፡በመሆኑም ህግ አውጪው እንደ ጉዳዩ ዓይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ክስ ለማቅረብ እንደሚቻል የተለያዩ የክስ ማቅረብያ ጊዜያት በህጎች ውስጥ አካቷል፡፡
መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ወንጀሎች በሚያስቀጡት የቅጣት አይነት ላይ በመመስረት በስድስት ተከፍለው ይገኛሉ፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/1 ስር እንደተደነገገው መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በወንጀል ተግባር ክስ የማቅረብ የይርጋ ዘመን የሚፀናው ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ነው፡-
1. የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ሃያ አምስት ዓመት፣
2. ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ሃያ አመት፣
3. ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ አስራ አምስት አመት፣
4. ከአምስት አመት ለማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አስር ዓመት፣
5. ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት ዓመት፣
6. እስከ አንድ ዓመት በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሦስት ዓመት፡፡”
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/2 ስር ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ፡- የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ በሚሆንበት ጊዜ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ስለዚህ በመደበኛ የወንጀል ክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ጊዜ ቢያንስ 3 ዓመት ቢበዛ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ 25 ዓመት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡

ይሁንና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 213 ድንጋጌ መሰረት የግል ተበዳይ ሆኖ የግል አቤቱታ ማቅረብ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበት ወይም የወንጀል አድራጊውን ማንነት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካላቀረበ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ወይም የህግ ግምት ተወስዶ አቤቱታው ቀሪ ይሆናል፡፡ የግል አቤቱታ ማቅረብ ያልቻለው በበቂ ምክንያት ከሆነ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ያጋጠመው ችግር ከተወገ
ደበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ይህ እንዳለ ሆኖ ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 218 ስር እንደተደነገገው ሁለት ዓመት ነው፡፡ ማንኛዉም የግል አቤቱታ ጉዳዩ ከተፈፀመ ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የማይቀርብና ቀርቦም ከሆነ ጉዳዩን ፍርድ ቤት በዳኝነት ማየት አይችልም፡፡

የይርጋ ዘመን አቆጣጠር
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 219 /1 የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት በሚኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጡ ሲሆኑ የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡

የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀሉን ድርጊት ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ እንዲሁም የወንጀሉ ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ድርጊት ካቆመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ወንጀሉ ተደርጓል ለማለት የሚቻለው ከፀባዮቹ አንዱ የወንጀሉ ውጤት የሆነ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ውጤት ከተገኘበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡

የይርጋ ዘመን መታገድ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 220/1 በሕጉ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል እስካለ ድረስ የይርጋ ዘመን መቆጠሩ ታግዶ ይቆያል፡፡ እንዲሁም ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ እንደሆነ ወይም በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ታግዶ ይቆያል፡፡ መስናከሉም እንደተወገደ ወዲያውኑ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ይቀጥላል፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ስለክሱ መከታተል አቤቱታ እንዲቀርብ ማስፈለጉ በሕግ ተመልክቶ በተገኘ ጊዜ አቤቱታ አለማቅረብ የይርጋውን መቆጠር አያግድም፡፡ እንዲሁም ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል ጥፋተኛው በራሱ ፍላጎት የሚፈፀመው ተግባር የይርጋ ጊዜውን መቆጠር አያግደውም፡፡

የይርጋ ዘመን መቋረጥ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 221 የይርጋ ዘመን መቋረጥ ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ ፣ብርበራ እንዲደረግ ፣መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ የይርጋ ዘመን በተቋረጠ ቁጥር እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት አለው፡፡ በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆናቸው ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልታወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አስመልክቶ ሊኖረው የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡

ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን፣ በማናቸውም ምክንያት መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን /አንቀጽ 217/ አጠፌታ ጊዜ (እጥፍ) ካለፈ ወይም ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ሲሆን /አንቀጽ 218/ ከዚሁ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ አልፎ እንደሆነ በወንጀሉ ላይ የሚቀርበው ክስ ወይም የሚደረገው መከታተል በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡እንዲሁም ሕጋዊ ቅጣት ከተወሰነው የይርጋ ዘመን/224/በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ ጥፋተኛው በዚህ ጊዜ ውስጥ ቢያብስ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል አስቦ በመፈፀም አደገኛ መሆኑን ካላሳየ በቀር የቅጣት ወይም የጥንቃቄ ተግባር አፈፃፀም ውሳኔ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ቀሪ ይሆናል፡፡
አለሕግAleHig ️
what your short answer 🔴Refresh your mind‼️ you can send us you answer via @Alemwaza or share to group @ALE_lawsocieties please, indicate the relevant law that you used to answer.
XZY Plc has the right to sue.
B/c of......
- Since they were two Plc's (XYZ &ABC) Plc's that signed contract from the beginning.
- the managers also signed the contract on behalf of the Plc' s and not for their own interests.
- The manager of the XYZ Plc testified that at the time of the
Lawsuit the libres of the excavator belonged to XYZ Plc in the contract.
#therefore it is XYZ Plc that can sue for the reason i mentioned above and b/c the matter is directly related to the XYZ Plc & affects its interests.‼️‼️
via Mebratu G.
1. Who is entitled to sue? The manager or XYZ PLC?
XYZ PLC is entitled to sue.
2. Why?
This will take us to attributes of personality. One of the attributes of legal personality is to sue or be sued. Because according to what we have learned in class, PLC is one of the business organization which has its own legal personality, has the attribute to sue or be sues. Therefore, the XYZ PLC is entitled to sue ABC PLC.
1. Who is entitled to sue? The manager or XYZ PLC?
XYZ PLC is entitled to sue.
2. Why?
This will take us to attributes of personality. One of the attributes of legal personality is to sue or be sued. Because according to what we have learned in class, PLC is one of the business organization which has its own legal personality, has the attribute to sue or be sues. Therefore, the XYZ PLC is entitled to sue ABC PLC.
For the fact that the evidence (the title deed/libre) presented by the General Manager of XYZ PLC shows the excavator belongs to the XYZ PLC but not to the manager. The manager has no right to sue the ABC PLC as a separate person from XYZ PLC, in his own name, which will lead us to a conflict of interest since he is claimed that the excavator is his own excavator. But, again for the fact that the general manager represents the XYZ PLC, the manager will continue to sue the ABC PLC in the name of XYZ PLC but not in his own name.
Furthermore, one of the controversial issue in this case is, We do not have a ground how the court ordered the release of the attached excavator. But, one thing is clear for us the contract concluded concerning 264,000.00birr was between the XYZ PLC and DEF PLC but not between the manager as a person and DEF PLC. This is also another ground which will support our answer; the XYZ PLC is entitled to sue as a PLC which has a legal personality.
Our group has tried his best to answer the question based on the case, according to its scope of business law understanding.
ያለ ህጋዊ ፈቃድ ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር ሲልክ የነበረው ግለስብ ተቀጣ
___________

በህገ ወጥ መንገድ ኢትዮዽውያንን ወደ ውጭ አገር በመላክ ወንጀል የተከሰሰዉ ተከሳሽ ሀሰን ሙሀመድ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ::

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 598/1/ የተመለከተዉን በመተላለፍ ወደ ዉጭ አገር ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው የግል ተበዳይን ሙስጠፋ ጣሂርን የባለቤቴ ወንድም ዱባይ ሀገር ስላለ እልክሀለሁ ብሎ በማግባባት መጀመሪያ ለሂደት (ለፕሮስስ) ማስጀመሪያ በሚል 20 ሺ ብር ከተቀበለ በኃላ በተለያዩ ጊዚያት ለጉዳይ ማስፈጸሚያ እና ለቪዛ ማሰሪያ በሚል በአጠቃላይ 83 ሺ ብር ተቀብሎ ወደ ዱባይ እንዲሄድና እንግልት እንዲደርስበት በማድረጉ በፈጸመው ህጋዊ የስራ ፈቃድ ሳይኖር ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡ ያስረዳል ፡፡

ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎች በማደረጀት ለችሎቱ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽ የቀረበበት ክሱ ግልጽ ነው፤መቃወሚያ የለኝም በማለቱ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከደመጠና መዝገቡን ከመረመረ በኃላ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ባለመከላከሉ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እና 2000 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኗል::
Forwarded from Esmael Seid
Please send ye wul hig meserete hasaboch by professor tilahun teshome Amharic version
Forwarded from MuleZ One
Hi Dear! Anyone who have this Soft of this Catalog? Help!🙏🙏🙏
የፍትሀብሔርና ስነ-ስርአት ህግን አለመከተል የሚያስከትለው ውጤት
****
የፍትሀብሔር ስነ ስርአት በአጠቃላይ የፍትሀብሔር ክርክሮች በምን መልኩ ወይም ሂደት እንደሚካሄዱና ጉዳዮች እንዴት እልባት እንደሚሰጣቸው የሚያመለክት ነው፡፡ የህጎች አንደኛው መከፋፈያ መንገድ የፍሬ ነገር እና የስነ ስርአት ህጎች የሚል አይነት ነው፡፡ የፍሬ ነገር ህጎች መብቶችን እና ግዴታዎችን የሚደነግጉ ሲሆን የስነ ስርአት ህጎች ደግሞ እኒዚህ መብትና ግዴታዎች እንዴት እንደሚፈፀሙና እንደሚተገበሩ የሚደነግጉ ናቸው፡፡ የፍሬ ነገር ህጎች ውጤትን ወይም ግብን የሚያመለክቱ ሲሆን የስነ ስርአት ህጎች ደግሞ እዚህ ግብ ወይም ውጤት ላይ እንዴት እንደሚደረስ የሚያመለክቱ መንገዶች ወይም ዘዴዎች ተብለው ይወሰዳሉ፡፡ በስነ ስርአት ህግ አይነቶች ውስጥ ደግሞ በዋናነት በሶስት ተከፍለው የፍትሀብሔር፣ የወንጀል እና የአስተዳደር ስነ ስርአት በሚል ይታወቃሉ፡፡

በዚህ አጭር ፅሁፍ ስለ ፍትሀብሔር ስነ ስርአት እና ውጤቱ ለማሳየት እንሞክራለን፡፡ የስነ ስርአት ህጎች በዋናነት ሰዎች መሰረታዊ የሆኑ የመብት ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የሚዳኙበትን ልዩ የሆኑ መብቶች፣ ጥቅሞችና ግዴታዎች በሚመለከታቸው የህግ አካላት የሚወሰኑበትን እና ተፈፀሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን ዘዴ የሚያሳይ ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ የፍትሀብሔር ስነ ስርአት ማለት ደግሞ የፍትሀብሔር ክርክሮችን በተመለከተ የምንከተለውን ስርአት የሚያመልክት ነው፡፡

በሀገራችን ያለው የፍትሀብሔር ስነ ስርአት ህግ ማእቀፍ ስንመለከት በዋነኛነት የምናገኘው የፍትሀብሔር ስነ ስርአት ህግ የሚባለውን ኮድ ነው፡፡ ይህ ህግ በ1958 ዓ/ም በድንጋጌ ቁጥር 52/1958 የወጣ ነው፡፡ ይህ የህግ ኮድ #483 ቁጥሮች እና ሰንጠረዥና ፎርሞች ያሉት ሰፊ ህግ ነው፡፡ ሁለተኛው የስነ ስርአት ህግ ማእቀፍ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጆች ከነማሻሻያዎቻቸው አዋጅ ቁጥሮች 25/1988፣ 138/1991፣ 188/1992፣ 254/1993፣ 321/1995፣ 322/1995፣ 454/1997፣ ስለ ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን፣ ለሰበር አቤቱታ አቀራረብ ስርአት ወዘተ የሚደነግጉ ናቸው፡፡ ሶስተኛው የፍትሀብሔር ስነ ስርአት የህግ ማእቀፍ በአዋጀ ቁጥ 454/1997 አንቀፅ 10/4/ የተመለከተው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል በሚለው መሰረት የፍትሀብሔር ስነ ስርአትን በተመለከተ በሰበር የሚሰጥ አስገዳጅ ትርጉም ነው፡፡ ምናልባት በአራተኛነት ሊጠቀስ የሚችለው የፍትሀብሔር ስነ ስርአት ድንጋጌ በፍሬ ነገር ህጎች ውስጥ ተካቶ የሚገኘው ነው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ ይርጋን በተመለከተና የማስረጃ አግባብነትና ተቀባይነትን በተመለከተ በፍሬ ነገር ህጎች ውስጥ ተካተው ይገኛሉ፡፡

አንድ ሰው የፍትሀብሔር ስነ ስርአት ህግን ተጠቅሞ በፍርድ ቤት መብቱ እንዲከበርለት ወይም ጥቅሙ እንዲረጋገጥለት ሊጠይቃቸው የሚችሉ ጉዳዮች ውስጥ የሚከተሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ አንድ ሰው በውል የፈጠረውን መብትና ግዴታ ለማስከበር፣ በሽያጭ ውል ለሸጠው እቃ ዋጋውን ለመጠየቅ ወይም እቃው እንዲቀርብለት ለመጠየቅ፣ የቤት ኪራይ ለማስከፈል፣ በውርስ ያገኘውን ንብረት ክፍፍል እንዲደረግለት ወይም ወራሽነቱ እንዲረጋገጥለት፣ በጋብቻ ስለተፈራ የጋራ ንብረት ክፍፍል ለመጠየቅ፣ የፍቺ ማመልከቻ ለማቅረብ፣ ከአሰሪው የሚጠይቀውን መብት ለመጠየቅ ወይም ሌሎች በህግ ያሉትን መብቶች በፍርድ ለማስከበር በፍርድ ቤት የፍትሀብሔር ክስ ለማቅረብ ከላይ የተመለከቱትን የፍትሀብሔር ስነ ስርአት የህግ ማእቀፎች በዝርዝር መመልከት ግንዛቤ ይሰጣል፡፡

በህጎቹ ይዘት ውስጥም ስለ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ማለትም ምን አይነት ጉዳይ በየትኛው የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት፣ በየትኛው የፍርድ ቤት ደረጃ የመጀመሪያ፣ ከፍተኛ ወይም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሱን ማቅረብ እንዳለበት ይገልፃሉ፡፡ በከሳሽነት ወይም ተከሳሽነት በክርክር ተካፋይ ስለመሆን፣ ከሳሽ ስለመሆን ችሎታና ስለውክልና፣ ስለተከራካሪ ወገኖች ስለመቅረብና ስላለመቅረብ፣ ስለመጥሪያ አደራረስ፣ ስለምስክሮች አቀራረብና አመሰካከር፣ ስለሰነድ ማስረጃ አቀራረብ፣ ለጊዜው ስለሚሰጡ የእግድ ትእዛዞች፣ ስለፍርድና ትእዛዝ አሰጣጥ፣ ስለክስና መልስ አፃፃፍ፣ ስለ ክስ አሰማም፣ ስለ ክስ ማቋረጥ፣ ስለተፋጠነ ስነ ስርአት፣ በግልግል ወይም በስምምነት ክርክርን ስለመቋጨት፣ ስለይግበኝ፣ ስለመቃወም፣ ፍርድን ስለማጣራት፣ ስለፍርድ አፈፃፀም፣ ስለ ሀራጅ ሽያጭ ወዘተ የሚመለከቱ ዝርዝር ድንጋጌዎች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ስነ ስርአቶች ሙግት ወይም ክርክር በታወቀ ስርአት እንዲመራ ከማድረግ ባለፈ የተከራካሪ ወገኖች እኩል የመሰማት እድል በመስጠት ፍርድ ቤት በእውነት ላይ ለመድረስ እና በህግ የተመለከተው መብትና ግዴታ እንዲከበርና እንዲረጋገጥ ብሎም እንዲፈፀም ለማድረግ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተጨማሪም ክርክሮች ስርአት ባለው፣ በሰለጠነና በመከባበር ሙግት ለማካሄድ፣ የተከራካሪዎችንና የፍርድ ቤትን ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ ክርክር ለመምራት፣ ውጤታማና ቀልጣፋ ፍትህ ለማስገኘት የተደራጁ ናቸው፡፡
@lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties
ምክር ቤቱ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ
———————————————————-
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።
ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ኒውክለርን አማራጭ የሃይል አቅርቦት ለማድረግ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችውን የስምምነት ረቂቅም በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።
በዚህም የፌዴራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
ከሶስት ዓመታት በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው ረቂቅ አዋጅ በምክር ቤቱ የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና በሚመለከታቸው አካላት በጥንቃቄ ሲታይ እንደነበር ተገልጿል።
የፌዴራልና የክልል መንግስታት ያላቸውን አቅም በማቀናጀት ህጋዊ በሆነ መንገድ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ የግንኙነት ስርዓቱ ወሳኝ መሆኑ ተብራርቷል።
ረቂቅ አዋጁ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አልዘገየም ወይ? የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልል መንግስታት በረቂቅ አዋጁ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ ምን ይመስላል? የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት ተነስተዋል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የፌዴራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት ህጋዊ ዕውቅና ሊኖረው ይገባል ብለዋል።
በተናጠልና በጋራ የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር በግልጽ በማስቀመጥ አገራዊ የልማት ስራዎችን በተናበበ መልኩ መስራት እንደሚገባቸውም ነው ያነሱት።
በስራ ውል የሠራተኛ መብቶች እና ከስራ የመቀነስ አሰራር
---------------------------

በመንግስት ወይም በግል መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች በተለያዩ ህጎች የሚተዳደሩ ሲሆን ከነዚህ ህጎች የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1054/10 እና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/11(የግል ሰራተኞችን የሚመለከት) ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡የአሰሪ እና ሰራተኛ ግንኙነት የሚጀምረው በመካከላቸው በሚደረገው የስራ ውል ነው፡፡የስራ ውል በውስጡ በአሰሪው እና በሰራተኛው መካከል ባለ ግንኙነት ሊኖሩ የሚችሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡

እነዚህ ዝርዝር ጉዳዮች በዋናነት የተዋዋዮቹን ስምምነት የያዙ ቢሆኑም በስራ ውል የሚደረግ ስምምነት ህግን መሰረት ያደረገ እና ህግን የማይቃረን መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም የሥራ ውል በሕግ፣ በኅብረት ስምምነት ወይም በሥራ ደንብ ለሠራተኛው ከተሰጡት ጥቅሞች ያነሰ ጥቅም የሚሰጥ መሆን የለበትም፡፡

በዚህ በራሪ ፅሁፍ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/11 በስራ ውል የሠራተኛ መብቶች እና ከስራ የመቀነስ አሰራርን የተመለከቱ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡
የሥራ ውል ይዘት
ማንኛውም ግለሰብ ደመወዝ እየተከፈለው በአሠሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ሥራ ለአሠሪው ለመሥራት ሲስማማ በሁለቱ መካከል የሥራ ውል ይመሠረታል፡፡ስለሆነም የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ሊደረግ ይችላል ማለት ነው፡፡

ውሉ በፅሁፍ ወይም በቃል ሊደረግ የሚችል ሲሆን በቃል ለተደረገ ውል አሰሪው ለሰራተኛው በ15 ቀን ውስጥ የሥራውን ዓይነትና ቦታ፣ ለሥራ የሚከፈለውን ደመወዝ መጠን፣ የስሌቱን ዘዴ፣ የአከፋፈሉን ሁኔታና ጊዜ እና ውሉ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ ፣ የአሠሪውን ስምና አድራሻ እና የሠራተኛውን ስም፣ እድሜ፣ አድራሻና የሥራ ካርድ ቁጥር ካለ የያዘ ሰነድ ፈርሞ ለሰራተኛው መስጠት አለበት፡፡

የሥራ ውል ተዋዋይ ወገኖች በውሉ መሠረት የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ በማያጠራጥር አኳኋን በሚያውቁበት ሁኔታና በግልጽ መደረግ ይኖርበታል፡፡በመሆኑም የስር ውል ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ጉዳዮች ያካተተ መሆን አለበት፡፡ይሁንና የእነዚህ ሁኔታዎች አለመሟላት ሠራተኛው በአዋጁ መሠረት የሚያገኛቸውን መብቶች አያሳጣውም፡፡
አሠሪና ሠራተኛ የአሠሪንና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ድንጋጌዎችን፣ የኅብረት ስምምነትን፣ የሥራ ደንብንና በሕግ መሠረት የሚተላለፉ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ከአዋጁ መገንዘብ የምንችል ሲሆን አሠሪውም ሆነ ሠራተኛው በሥራ ግንኙነታቸው ሂደት የተለያዩ መብቶችና ግዴታዎች ይኖራቸዋል፡፡ በአብዛኛው ለአንደኛው ግዴታ የሆነው ለሌላኛው መብት ሆኖ የሚያገለግልበት ሁኔታዎች ስላሉ የአንዱን ግዴታ በምንመለከትበት ጊዜ በተዘዋዋሪ የሌላኛውን መብት እናያለን ማለት ይቻላል፡፡
የሠራተኛ መብቶች
አሠሪ በሥራ ውሉ ከተመለከቱት ልዩ ግዴታዎች በተጨማሪ በአዋጁ አንቀፅ 12 ስር የተዘረዘሩ ግዴታዎች አሉበት፡፡ ከነዚህ ግዴታዎች አብዛህኛዎቹ በተዘዋዋሪ የሰራተኛው መብት ሆነው እናገኛለን፡፡እነዚህም፡-
 በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር ለሥራ የሚያስፈልገውን መሣሪያና ጥሬ ዕቃ የማግኘት፣
 ለሰራው ስራ ደመወዙንና ሌሎች ክፍያዎችን በአዋጁ ወይም በኅብረት ስምምነት መሠረት የመከፈል፣
 ተገቢውን ሰብዓዊ ክብር የማግኘት መብት ፤
 ከስራው ጋራ በተያያዘ ሊደርስ ከሚችል አደጋ የመጠበቅ እና በአሰሪው ለጤንነቱን የጥንቃቄ እርምጃዎች የማግኘት፡
 ጤንነቱ እንዲመረመር በሕግ ወይም አግባብ ባለው አካል ግዴታ ሲጣል ከክፍያ ነፃ ምርመራ የማግኘት፤
 የሥራ ውል በሚቋረጥበት ወይም ሠራተኛው ሲፈልግ በማናቸውም ጊዜ ሠራተኛው ሲሰራ የነበረውን የሥራ ዓይነት፣ የአገልግሎት ዘመኑንና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ያለክፍያ የማግኘት ፣
 በሥራ ላይ ያሉ የአስተዳደር ደንቦችን የማወቅ መብት፣
 በህግ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት(አንቀፅ 39)
 የሳምንት እረፍት፣የዓመት ፍቃድ ወይም የወሊድ ፍቃድ ከክፍያ ጋር የማግኘት (አንቀፅ 69፣76፣88) የሰራተኛው ተጠቃሽ መብቶች ናቸው፡፡

የሰራተኛ ቅነሳ እና ከስራ የመቀነስ አሰራር
የስራ ውል በተለያዩ ምክንያቶች እና ሁኔታዎች ሊቋረጥ ይላል፡፡ በአሰሪ አነሳሽነት፣ በሰራተኛው አነሳሽነት፣በማስጠንቀቂያ እና ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ሊቋረጥ እንደሚችል እና በነዚህ ሁኔታዎች ውሉ እንዴት እንደሚቋረጥ አዋጁ ዝርዝር ጉዳዮችን አካቶ ይገኛል፡፡በተያያዘ ጉዳይ የሰራተኛ ቅነሳ በአዋጁ የተካተተ እራሱን የቻለ አሰራራ ያለው የስር ውል ሊቋረጥ የሚችልበት ምክንያት ነው፡፡

የሰራተኛ ቅናሳ ማለት የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚተከሉት ምክንያቶች የሥራ ውልን በማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ሲሆን ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሠራተኞች ቢያንስ ከመቶ አሥር የሚያህለውን ወይም የሠራተኞች ቁጥር ከ20 እስከ 50 በሆነበት ድርጅት ቢያንስ 5 ሠራተኞችን የሚመለከት ከአሥር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ውል መቋረጥ ነው፡፡

የሠራተኞች ቁጥር ማለት ሠራተኞች ለመቀነስ አሠሪው እርምጃ ከወሰደበት ቀን በፊት ባለው 12 ወራት ውስጥ በአሠሪው ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች አማካይ ቁጥር ነው፡፡ ምክንያቶቹም፡-

 ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
 ከስራ ለማገድ ምክንያት ተብለው የተጠቀሱት ከ10 ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የድርጅቱን ሥራ በሙሉም ሆነ በከፊል የሚያቋርጥ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት እና የአሠሪው ጥፋት ባልሆነ ምክንያት ከ10 ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የድርጅቱን ሥራ የሚያቋርጥ ያልታሰበ የገንዘብ ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤

 የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸው፡፡

የስራ ቅነሳ አሰራር
ከላይ በተጠቀሰው መሠረት የሠራተኞች ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው ከሠራተኞች ማኅበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የሥራ ችሎታ ያላቸውና ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ተመሳሳይ የሥራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት የሚያመርቱ ሠራተኞች ሲኖሩ ቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ሠራተኞች በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናሉ:-
በመጀመሪያ ደረጃ ቅነሳው የሚመለከታቸው
 በድርጅቱ ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች፤
 አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ጥገኞች ያሏቸው ሠራተኞች፤
በመቀጠል
 አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሠራተኞች፤
 በድርጅቱ ሳሉ በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች፤
 የሠራተኞች ተጠሪዎች፤
 ነፍሰጡር ሠራተኞች ወይም ከወለዱ እስከ 4 ወር ድረስ የሆናቸው ሴት ሠራተኞች፡፡

በመጨረሻም በልዩ ሁኔታ ቅነሳው የሚመለከታቸው ሠራተኞች የተቀጠሩበት ሥራ ከማለቁ በፊት ካልሆነ በቀር የኮንስትራክሽን ሥራው በተከታታይ እያለቀ ሲሄድ የሥራው መ
ጠን በመቀነሱ ምክንያት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች ላይ ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው በአዋጁ የተመለከቱትን የሠራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይኖርበትም፡፡የኮንስትራክሽን ሥራ ማለት ሕንጻ፣ መንገድ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የባሕር ወደብ፣ የውሃ ግድብ፣ ድልድይ፣ የመሣሪያ ተከላና ሌላም ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት የመለወጥ፣ የማስፋፋት፣ የማደስና የመጠገን ሥራን ይጨምራል፡፡
https://t.me/lawsocieties
Law societies: why you should join‼️