አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Transparency International Ethiopia is Looking Volunteers for Social media administration and moderators.‼️‼️‼️‼️

Share to your best friends and families‼️

volunteering program opportunities ......

Civics students
Political students
Psychology
Sociology
Law
Journalism.......E.T.C.....

ባሉበት ሁነው የሚያከናውኗቸው ቀላል የበጎ አድራጎት ስራዎች ውጭውን ሸፍነን ባሉበት በሚሰሩበት በሚማሩበት በሚኖሩበት ቦታ የሙስናን አስከፊነት ይናገሩ‼️
የመልካም ዜጋን ስብዕና ያካፍሉ‼️
ይህ መልካም አጋጣሚ ነው።

በቀኑ መጨረሻ የምስክር ወረቀት እናዘጋጃለን።
እንደ አሳዩት የስራ እንቅስቃሴ የስራ እድል እናመቻቻለን።
https://t.me/TransparencyEthiopia
ቀለብ የመስጠት ግዴታ በተሸሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ
-------------------------------
በማህበራዊ ህይወት ውስጥ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ መረዳዳት ያለ እና በህግ የሚጣሉ ግዴታዎች እንዳሉ ሆነው በዋናነት ከሞራል የሚመነጭ ተግባር ነው፡፡በችግር ጊዜ ከሚደጋገፉ እና ከሚረዳዱ ሰዎች ውስጥ ደግሞ በዝምድና ወይም በጓደኝነት የሚተዋወቁ ሰዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ቀለብ መስጠት ዝምድና ያለቸው ሰዎች ካለባቸው ህጋዊ ግዴታ ውስጥ አንዱ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት ህጎች በተለይ በቤተሰብ ህጋቸው ውስጥ ቀለብ የማግኘት መብት የእነማን አንደሆነ፣ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለባቸውን ሰዎች እንዲሁም ቀለብ የሚሰጥበትን ዝርዝር ሁኔታዎች አካተው ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያም የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቀለብ የመስጠት ግዴታን ዝርዝር ሁኔታዎች የሚደነግጉ አንቀፆችን ይዟል፡፡ቀለብ የመስጠት ግዴታ የሚኖረው በህግ ቀለብ የማግኘት መብት ያለው ሰው ለመስራት እና ለኑሮው አስፈላጊውን ገቢ ለማግኘት አቅም የሌለውና በችግር ላይ የወደቀ ሲሆን ብቻ ነው፡፡በመሆኑም ቀለብ የመጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች እነማን ናቸው የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ከወላጆቻቸው ወይም በእድሜ ወይም በጤና ችግር ምክንያት እራሳቸውን ማስተዳደር ያልቻሉ ሰዎች ቀለብ የመስጠት ግዴታ ከተጣለባቸው ዘመዶቻቸው ቀለብ መጠየቅ እንደሚችሉ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡ እንዲሁም ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ሰው ቀለብ ለማቅረብ የሚችል መሆኑ ለቀለብ መስጠት ግዴታ ተፈፃሚነት ጠቃሚ ነው፡፡

በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 197 መሰረት ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ሰው እንደ ባለጉዳዮቹ ሁኔታ እና እንደ አካባቢው ልማድ የሚስማማውን በመከተል ለቀለብ ተቀባዩ ምግብ፣መኖሪያ፣ልብስ፣ጤናውን የሚጠብቅበትና እንደሁኔታው ለትምህርት አስፈላጊ የሆነውን ነገር መስጠት አለበት፡፡ይህም የሚያመለክተው ቀለብ የሚሰጠው ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ብቻ ለማሟላት እንጂ የቅንጦት ፍላጎቶችን እንደማያካትት ነው፡፡

ቀለብ የማቅብ ግዴታ በቀጥታ የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ያለ ሲሆን በባል ወይም በሚስት፣በቀጥታ ወላጆችና ተወላጆች እንዲሁም በወንድማማቾች እና በእህትማማቾች መካከል ግዴታ አለ(አንቀፅ 49 እና 198/1/2 )፡፡ በተያያዘም አንቀጽ 199 በጋብቻ ለሚፈጠር ቀለብ የመስጠት ግዴታ የሚቀርበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ይህም ጋብቻው የፈረሰው በሞት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር፤ በጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ያለው ቀለብ የመስጠት ግዴታ ቀሪ ይሆናል፡፡

ምንም እንኳን እንቀፅ 198/1/2 ስር በግልፅ ባይደነገግም አንደ ሁኔታው በጉዳፈቻ አድራጊ እና ተደራጊ መካከል ግዴታው ይኖራል፡፡ምክንይቱም በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ እንቀፅ 181 መሰረት የጉዲፈቻ ልጅ በማናቸውም ረገድ ቢሆን እንደ ጉዲፈቻ አድራጊው ልጅ ስለሚቆጠር በወላጅ እና በተወላጅ መካከል የሚኖረው ቀለብ የማቅረብ ግዴታ በጉዲፈቻ ቤተሰብም ተፋፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡

የጉዲፈቻ ግንኙነት በሚኖር ጊዜ በመሰረቱ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 212(1) እንደሚያትተው የጉዲፈቻ ልጅ፣ ባል ወይም ሚስትና የቀጥታ ጋብቻ ተወላጆች የጉዲፈቻ አድራጊው ቤተዘመዶች ቀለቡን መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ካልተገኙ በስተቀር፤ የሥር ወላጆቹን ቤተዘመዶች ቀለብ መጠየቅ አይችሉም፡፡ እንዲሁም ንዑስ አንቀጽ ሁለት የቀደምት ቤተሰቦቹ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ቀለብ ለማግኘት ከዘመዶቻቸው አንዱን ለመጠየቅ የማይችሉ ካልሆነ በስተቀር በጉዲፈቻ የሰጡትን ልጅ ቀለብ ሊጠይቁት አይችሉም በማለት ያትታል፡፡

በአጠቃላይ በህጉ ቀለብ የማስጠት ግዴታ የተጣለባቸው ዘመዳማቾች ከላይ የተገለፁት ብቻ ስለሆኑ ሰዎች ከአጎት ፣ከአክስት፣ከአጎት ልጅ ወይም ከሌላ ዘመዶቻቸው ቀለብ መጠየቅ አይችሉም ማለት ነው፡፡
በመሰረቱ(as a rule) ቀለብ የመስጠት ግዴታ የሚፈፀመው ቀለብ ሰጪው ለቀለብ ተቀባዩ ገንዘብ በመስጠት ሲሆን የቀለቡ መጠን የሚወሰነው ቀለብ ጠያቂው ያለበትን ችግር እና የቀለብ ሰጪውን አቅም በማመዛዘን ነው፡፡እንዲሁም ቀለብ ሰጪው ቀለብ ተቀባዩን በመኖሪያ ቤቱ በማኖር ግዴታውን ሊፈፅም የሚችል ሲሆን የቀለቡ መጠን ወይም ስለ ቀለብ ተቀባዩ መኖሪያ የተሰጠው ውሳኔ በቀለብ ሰጪው ወይም ቀለብ ተቀባዩ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት ሊሻሻል (ሊቀነስ ወይም ሊጨመር) ይችላል(አንቀፅ 202 እና 203)፡፡

ለቀለብ የሚከፈል ገንዘብ የቀለብ ተቀባዩ ህይወት መቀጠል እጅግ አስፈላጊ ነው ተብሎ ስለሚታመን ገንዘቡ ሊተላለፍ ወይም ሊያዝ አይችልም፡፡ይሁንና ይህ መርህ ለቀለብ ተቀባዩ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ያበደሩ ሌሎች ሰዎችን በተመለከት ተፈፃሚነት አይኖረውም(አንቀፅ 205)፡፡ በተጨማሪም ቀለብ ተቀባዩ ለኑሮው አስፈላጊ መሆኑን ካላረጋገጠ በስተቀር የቀለቡን ገንዘብ መቀበል ካለበት ቀን ጀምሮ በተከታዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ያልተቀበለው ወይም ሳይጠይቀው የቀረ እንደሆነ የተጠራቀመውን ቀለብ እንዲሰጠው መጠየቅ አይችልም፡፡

ለቀለብ ተቀባዩ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ የሆኑ እንደሆነ ቀለብ ተቀባዩ ከእነርሱ መካከል አንዱ ቀለቡን እንዲሰጠው ሊጠይቀው ይችላል፡፡ ነገር ግን ቀለብ የመስጠት ግዴታ ካለባቸው ሰዎች አንዱ ሙሉውን የከፈለ እንደሆነ፤ ከፋዩ ራሱን በቀለብ ተቀባዩ ቦታ በመተካት ቀሪ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለባቸውን ሰዎች ወጪውን እንዲተኩለት መጠየቅ ይችላል ሲል የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 208 እና 209 ደንግጓል፡፡

ምንም እንኳን ተገላቢጦሽ(reciprocal) ቀለብ የመስጠት ግዴታ (ልጅ ያሳደጉትን ወላጆቹን በእርጅና ወራት የመጦር፣ባል ሚስቱን ሚስት ባሏን የመንከባከብ ሀላፊነት ወ.ዘ.ተ.) ቢኖርም አንቀጽ 210 የቀለብ ሰጪዎች ተራ ቅደም ተከተል አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ቅደም ተከተል፤
1. ባል ወይም ሚስት
2. ተወላጆች እንደየደረጃቸው(ልጅ፣የልጅ ልጅ፣….)
3. ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደረጃቸው(አባት ወይም እናት፣አያት፣ቅድመ አያት…..)
4. ወንድማማችና እህትማማቾች
5. የጋብቻ ተወላጆች እንደየደረጃቸው(የባል ወይም የሚስት ልጆች፣የልጅ ልጆች…)
6. የጋብቻ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደረጃቸው ናቸው፡፡(የባለ ወይም የሚስት እናት ወይም አባት፣አያት ቅድመ አያት…)
በተጨማሪም በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 213 ንዑስ አንቅጽ/1 እና 2/ ስር እንደተደነገገው ቀለብ ሰጪው ለቀለብ ተቀባዩ ቀብር ማስፈፀሚያ ወጪ እንዲከፍል የሚገደድ ሲሆን እንዲሁም ይህን የቀብር ማስፈፀሚያ ወጪ ሌላ ሦስተኛ ወገን ከከፈለ ደግሞ በአበዳሪው ቦታ ራሱን በመተካት ባለዕዳው ወጪውን እንዲተካለት መጠየቅ ይችላል፡፡

በመጨረሻም በቀለብ ሰጪ እና ቀለብ ተቀባይ መካከል በሚደረግ ስምምነት፣ቀለብ ሰጪው እራሱን የሚያስተዳድርበት ገቢ ማግኘቱ፣ቀለብ ሰጪው ግዴታውን መወጣት አለመቻሉ፣ጋብቻው በፍቺ ምክንያት ከፈረሰ እና ቀለብ ተቀባዩ በቀለብ ሰጪው ወይም በዚህ ሰው ወደ ላይና ወደታች በሚቆጠሩ ወላጆች ወይም ተወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት ሕይወት ወይም ንብረት ላይ የወንጀል ድርጊት ከፈፀመ ወይም ለመፈፀም ከሞከረ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ቀሪ ይሆናል፡፡
Forwarded from Deleted Account
ዛሬ የህግ ኮንሰርቲም ተሰብስቦ exit ፈተናን ለማራዘም መወሰኑ ለህግ ተማሪዎች ምንም አይነት ርህራሄና የኛን ጉዳይ እንደራሱ አድርጎ የሚያስብ ሳይሆን በ exit እና reexit የሚሰበሰበውን ገንዘብ ብቻ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ውሳኔ ነው ።
አሁን በሁሉም ቦታ ያለ የህግ ተማሪ በምን አይነት የሞራል ውድቀት ላይ እንዳለን ብቻ ሳይሆን ወደ አልፈለግነው ነገር ውስጥ እየገባን ነው....13 የሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የጀመሩ ሲሆን በቅርቡ ተማሪዎችን ያስመርቃሉ የህግ ተመራቂ ተማሪ ግን ህግ መማር ሀጢያት በሚመስል መልኩ የበይ ተመልካች ነው...
ስለዚህ የህግ ኮንሰርቲም ተብየዎቹ ለእውነት የቆማችሁ ከሆናችሁ ወሳኔያችሁን ከእንደገና እንድታጤኑት በፍትህና በርትዕ ስም እንለምናችኋለን!!
በአሁን ሰአት ኤግዚት የሚባል ነገር አንፈልግም ቴምፗችንን ስጡን እና በቀጣይ የምንፈተንበት ሁኔታ ካለ ይመቻች....
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
https://t.me/lawsocieties
share‼️‼️‼️‼️
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ
______________

በቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ በእስራት ተቀጣ፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በቦሌ ክፍል ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር 03-2421 ኦሮ የሆነ በተለመዶ አባዱላ ተብሎ የሚጠራውን መኪና እያሽከረከረ ግብረ አበሮቹን ይዞ ወደ ግል ተበዳይ ሽኩር የሱፍ ሱቅ በመሄድ አንደኛው ያልተያዘው ግብረ አበሩ ባለሱቁን የ50 ብር ካርድ አልህ ወይ ብሎ በመጠቅ ካርዱን ሊሰጠው ወደ ውስጥ ሲገባ ያልተያዙት ሁለቱ ግብረ አበሮቹ ከመኪናው በመውረድ ተከትለው በመግባት አንደኛው ግብረ አበሩ በጩቤ አንገቱን ይዞ በማስፈራራት ሁለተኛው ግበረ አበሩ በስቁ ውስጥ የነበረውን 30‚000 ብር እና አጠቀላይ ከ51ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶችን ከወሰዱ በኋላ ተከሳሽ ይዞ በመሰወሩ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው የከባድ ውንብድና ወንጀል ተከሷል ዐቃቤ ህግም እንደ ክሱ አቀራረብ የሰውን እና የሰነድ ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ የቤተስብ አስተዳዳሪ እና ሪከርድ የሌለበት መሆን ማቅለያ በመያዝ ጥቅምት 24 ቀን 3013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎል፡፡
share ‼️🔴

https://t.me/lawsocieties
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ
______________

በልደታ ክፍለ ከተማ የ12 ዓመቷን ታዳጊ አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ አቶ ግርማዬ ገ/ስላሴ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1)ን በመተላለፍ የ12 ዓመት ታዳጊና የልጁ ጓደኛ በሆነችው የግል ተበዳይ ላይ ሚያዚያ 08 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ልማት ምንጭ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙን ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

የዐቃቤ ሕግ ክስ በችሎቱ የተነበበለት ተከሳሽ በበኩሉ የቀረበበትን ክስ የማይቃወም መሆኑን ጥቅሶ የወንጀል ድርጊቱን ግን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ሲል ክዶ የተከራከረ ሲሆን የመከላከያ ምስክሮቹንም ቃል አስደምጧል፡፡

ዐቃቤ ሕግም ተከሳሹ ወንጀሉን ሰለመፈጸሙ ያሰረዱልኛል ያልኳቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ ያቀረብኩ በመሆኔና የተከሳሽ ምስክሮችም የቀረበውን የወንጀል ድርጊት ማስረጃ የላስተባበሉ በመሆኑ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ወሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኃላ ተከሳሽን በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

ክሱን የተመለከተው የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎትም መዝገቡን መርምሮ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት፣የቤተሰብ አስተዳዳሪና ማህበራዊ ተሳትፎ ያለው መሆኑን እንዲሁም የአስም ህመምተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተከሳሽ በ12 ዓመት ጽኑ እስራ እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
https://t.me/lawsocieties
በኢትዮጵያ ስላሉ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች አንዳንድ ጉዳዮች
BY አብዱሰላም ሳዲቅ ሙክታር

በመከላከያ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀፅ 28 (3) ስለወታደራዊ ፍትህ አካላት ሲዘረዝር በወታደራዊ ሰራዊት ውስጥ የወታደራዊ ፍትህ ስራን የሚያከናውኑ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች መቋቋማቸውን ይደነግጋል፡፡ በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እነዚህ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በህግ ስላላቸው ስልጣንና ተያያዥ ጉዳዬች በአጭሩ በዚህ ጽሑፍ ተዳስሷል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1965-some-notes-on-military-courts-of-ethiopia
ስድብ ተሰድቤያለሁ በሚል ምክንያት ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ።
------------------------------------------------

ተከሳሽ ሀይሉ ዳዲ ሳይና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 (ሐ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሹ በሰው አካል ወይም ጤንነት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ጥቅምት 20/2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 11፡15 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው “ዕውቀትአምባ ትምህርት ቤት” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ ወ/ሮ መስታውት ሀይሉን ብሄርን መሰረት ያደረገ ስድብ ሰድባኛለች በሚል ድንጋይ በመወርወር እና አፏን በመምታት የላይኛው የፊት ለፊት ጥርሷ እንዲሰበር እና የታችኛው ከንፈሯ እንዲሰነጠቅ በማድረግ በፈፀመው ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል ።

ለፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት ህዳር 08/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለበት መሆኑ ፣ዝቅተኛ የትምህርት እና የኑሮ ደረጃ ከግምት ውስጥ በማስግባት እና ሶሰት የቅጣት ማቅለያዎች በመያዝ ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል በሚል በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ።
https://t.me/lawsocieties
የኢትዮ-ቴሌኮምን ንብረት የሰረቁት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡
--------------------------------

ሸሽጉ ካሰዉ እና ሲሳይ ጌትነት የተባሉት 1ኛ እና 2ኛ የዐቃቤ ህግ ተከሳሾች የተከሰሱበትን ወንጀል የፈጸሙት የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ሲሆን ቦታዉም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 011 ልዩ ቦታዉ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ነዉ፡፡

ሁለቱም ተከሳሽ ግለሰቦች የማይገባቸዉን ብልጽግና ለራሳቸዉ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት አስበዉ ንብረትነቱ የኢትዮ-ቴሌኮም የሆነና የህዝብ ስልክ ቋሚ መጠለያ /ቡዝ/ ሆኖ ሲያገለግል የነበረዉን ግምቱ 20000/ሀያ ሺህ ብር/ የሚገመት ብረት ካልተያዙት ግብረአበሮቻቸዉ በመቀናጀት እያንከባለሉ ሲወስዱ በአካባቢዉ ህብረተሰብ ተደርሶባቸዉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ ወንጀሉን በዋና አድራጊነት በመፈጸማቸዉም በከባድ የስርቆት ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 669/1/ለ ስር የተደነገገዉን በመተላለፋቸዉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዉ መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ችሎት ቀርበዉ የእምነት ክህደት ቃላቸዉን ሲጠየቁ ሁለቱም ተከሳሾች ወንጀሉን እንዳልፈጸሙና ጥፋተኛም እንዳልሆኑ ክደዉ ተከራክረዋል፡፡

ሆኖም የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ የካ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡለትን የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ የወንጀሉን መፈጸም ካረጋገጠ በኋላ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈባቸዉ ሲሆን ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባስቻለዉ 1ኛ ወንጀል ችሎት በ5 (አምስት) ዓመት ከ6 (ስድስት) ወራት እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from Deleted Account
Administrative agancies rule making power at federal and oromia regional state research kalachuh bitilikulign ?
Forwarded from Biniam Ayalew
የደቡብ የሊዝ መመሪያ 08/07 ያለው
አለም አቀፍ የፍልሰት ስምምነት ሀገራዊ አፈጻጸም በተመለከተ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት ተካሄደ
___________

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ብሔራዊ እና አለም አቀፍ መደበኛ የፍልሰት ቃል- ኪዳን ስምምነት አፈጻጸም ረቂቅ ሪፖርትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካለት ጋር ግብዓት የማሰባሰብ ውይይት ተካሄደ፡፡

በመድረኩ የብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትህያ ሰዒድ እንደተናገሩት አገራችን ደህንነቱና ሥርዓቱ የተጠበቀ አለም አቀፍ መደበኛ የፍልሰት ቃል- ኪዳን ስምምነት አፈጻጸም ሰነዱን ከፈረሙ አገራት መካከል እንዷ መሆኗን እና ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማስገባት መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ፣ አለም አቀፍና አገር ውስጥ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተሳተፉት ዘርፍ ብዙ ተግባራት ተከናውናል ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ አያይዘውም አገራት በእንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን መብት ለመጠበቅ፣ ክብር፣ ደህንነትና ጥቅም የሚያስከብር አገልግሎቶችን የተሻለ ለማድረግ አለም አቀፍ የቃልኪዳን ስምምነት (GCM) በ2018 በሞሮኮ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት በተቋማቸው የተከናወኑ እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተግባራት ሪፖርት የሚያቀርቡበት የአሰራርና አደረጃጀት ሥርዓት የተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ፈትህያ ሰዒድ አክለውም አገራቸን ስምምነት ሰነዱን ከፈረመች ጀምሮ የሕግ ማዕቀፎችን በመፈተሸና በማሻሻል የዜጎችን መብትና ደህንነት የሚያረጋግጡ እንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ የገቡ ዜጎቻችን ሆነ ሌሎችን መብቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ሆነው እንዲገኙ የተለያዩ አዋጆችን በማውጣት፣ አደረጃጀቶችንና አሰራሮች በመዘርጋት፤ የተግባር ክንውን ሪፖርት ጉዳዩ የሚመለከታቸው መረጃ የሚሰጡ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ የተዘጋጀ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባስብ የውይይት መድረኩ አላማ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ሰላም ሚኒስቴር፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ፣ የፌ/የከተሞች ስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ፣ ሴቶችን፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዜጎች ከተለያዩ አገራት ሲመለሱ የምክር፣ የመጠለያ አገልግሎት የሚሰጡ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅቶችና የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ ተጨማሪ ግብዓት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ለሁለት ቀን በሚደረገው የውይይት መድረክ በሀገር ደረጃ በመሪዎች የሚፈረሙ ስምምነቶች ከመፈረም ውጭ ምን ውጤት አመጡ የሚለውን በማየትና የአገራችን ዜጎች መብት፣ ደህንነታቸውን እና እንቅስቃሴያቸውን በተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰሩ ያሉ ውጤታማ ስራዎችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ከሌሎች የአለም አገራት ጋር በመቀናጀት፣ ትብብር እና ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል የተሟላ የሰነድ በማዘጋጀት ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል እንደሚላክ ወ/ሮ ፈትህያ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
https://t.me/lawsocieties