አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ዳይሬክተር አቶ ይሄይስ ቦጋለ በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ትምህርት ፈተና ለተማሪዎች መስጠት ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ማቆሙንና የተጀመሩ ፈተናዎችን ለማስጨረስ አሁን ላይ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደመጡ በመጀመሪያ ሳምንታት ውስጥ ዳግም ምዝገባ በማካሄድ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ፈተና እንደሚሰጥና የሁለተኛ መንፈቅ ትምህርት በሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ተማሪዎች በሴሚስተር 16 ሳምንታት እንደሚማሩ የሚገልፁት ዳይሬክተሩ፣ አሁን በስምንት ሳምንታት ውስጥ ለማጠናቀቅ የማስተማሪያ ቁሳቁስ ለተማሪዎች በመምህራን በኩል እየተዘጋጀ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ከመማሪያ ክፍሎች ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በአንድ ክፍል ውስጥ ብዙ ተማሪዎች እንደሚማሩ እና አሁን ላይ ግን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት ከ20 ተማሪ በላይ በአንድ ክፍል ውስጥ እንደማይቀመጥ ተናግረዋል፡፡ዶርሞችም ተማሪዎችን የመያዝ አቅማቸው በግማሽ ይቀንሳል ብለዋል፡፡ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛ፣ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ የሚያስተምር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው፡፡

©Walta
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሕግ መጽሐፍ (Book Review) ዳሰሳ መድረክ አከናወን
************************************************************
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ መስከረም 30/2013 ዓ.ም በዶ/ር መሓሪ ረዳኢ ተዘጋጅቶ በ2012 ዓ.ም የታተመውን የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ ይዘቱ እና አተገባበሩ የሚለው መጽሐፍ ላይ የዳሰሳ ፕሮግራም አካሄዳል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ በማርቀቅ፣ የተለያዩ መጽሐፍትን በማዘጋጀት እና ደሰሳ የተካሄደበትን መጽሐፍ ያሰተሙት ዶ/ር መሐሪ ረዳኢ መድረኩ ላይ በመገኘት የመጽሐፉን ይዘት አብራርተዋል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የፍርድ ቤት አመራሮች፣ የየምድብ ችሎቶቹ አስተባባሪ ዳኞች፣ የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የተገኙ ሲሆን በቀረበው ማብራሪያ ላይ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አቅርበው ዶ/ር መሓሪ ረዳኢም የራሳቸውን እይታ አጋርተዋል፡፡
በዚሁ መድረክ ላይ የቤተሰብ ዳኞች ቡድን ተወካይ የሆኑት ክቡር ዳኛ ተክለሃይማኖት ዳኜ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቤተሰብ ችሎት አሰራሮች፣ መልካም ተሞክሮዎች እና ክፍተቶች የሚል ተግባራዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል፡፡
በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ ንግግር ያካሄዱት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፋአድ ኪያር ፍርድ ቤቱ በየህግ ዘርፉ የሚካሄዱ ጥናቶች እና የህትመት ውጤቶች ላይ ዳኞች እንዲወያዩ ማድረግ የፍርድ ቤት ባህል እንደሚገባ በማንሳት በቀጣይም የተለያዩ የዳኞች ቡድን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮች የሚዘጋጁ መሆኑን አውስተዋል፡፡
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
የወንጀል ክስ በባህላዊ ሥርዓት ውሳኔ የሚያገኝበትን አማራጭ የያዘ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ለፓርላማ ቀረበ
11 October 2020
ዮሐንስ አንበርብር
የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች አዲስ አበባ በሚገኙ የክልሉ ተቋማት ላይ የዳኝነት ሥልጣን ይሰጣቸዋል

በሁለት ዓመት ውስጥ ያልተፈጸመ የሞት ፍርድ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ይለወጣል

ማንኛውም በምርመራ፣ በክስ ወይም በፍርድ ሒደት ላይ የሚገኝ የወንጀል ጉዳይ በባህላዊ ሥርዓት ታይቶ ውሳኔ ወይም መፍትሔ እንዲሰጥበት የሚያስችል የፍትሕ አማራጭን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ረቂቅ ሕጉ ለስድስት አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየውን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ የሚተካና የማስረጃ ሕግ ሥርዓትንም እንደ አዲስ የሚያበጅ ነው።

‹‹የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ረቂቅ አዋጅ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ሐሙስ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው።

ረቂቁ ማንኛውም የወንጀል ጉዳይ በባህላዊ ሥርዓት የሚታይበትን አማራጭ የፍትሕ ሥርዓት ቢያስቀምጥም፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ በሰው ልጅ ክብርና በአገር ደኅንነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ግን ባህላዊ ሥርዓት ተፈጻሚ እንደማይሆን ያመለክታል።

በባህላዊ ሥርዓት የሚታይ የወንጀል ጉዳይ በዓቃቤ ሕግ አነሳሽነት ወይም በግል ተበዳይ ወይም በባህላዊ ሥርዓት ሥልጣን ባለው ሰው፣ እንዲሁም አግባብነት ባለው የመንግሥት አካል፣ ወይም ጉዳዩን በሚያየው ፍርድ ቤት ጠያቂነት ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ፈጸመ የተባለው የወንጀል ድርጊት በባህላዊ መንገድ እንዲታይ ሊቀርብ እንደሚችል የረቂቁ ድንጋጌ ያመለክታል።

ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሽ ፈጽሟቸዋል የተባሉ ተያያዥ ወይም ተደራራቢ ወንጀሎች ከፊሎቹ በባህላዊ መንገድ፣ ቀሪዎቹ በመደበኛው ሥርዓት ሊታዩ የሚችሉ በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉም ወንጀሎች በመደበኛው ሥርዓት እንዲታዩ እንደሚደረግ ረቂቁ ይደነግጋል።

በባህላዊ ሥርዓት እንዲታይ የተወሰነው ጉደይ ሳይታይ ከቀረ ወይም መፍትሔው በሙሉ ወይም በከፊል ሳይፈጸም ከቀረና ሊፈጸም የሚችልበት ሁኔታ የለም ብሎ ዓቃቤ ሕግ በበቂ ሁኔታ ካመነ፣ ጉዳዩ በመደበኛው ሥርዓት እንዲታይ ሊወሰን እንደሚችልም ያመለክታል።

ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ከተወሰነም ፍርድ ቤት የዘጋውን መዝገብ፣ በዓቃቤ ሕግ ጠያቂነት ዳግም እንዲከፈትና መደበኛው የፍርድ ሥርዓት እንዲቀጥል እንደሚያደርግ በረቂቅ ሕጉ ድንጋጌ ተመልክቷል።

በቅድመ ሁኔታነትም ዓቃቤ ሕግ ጉዳዩ በባህላዊ ሥርዓት መፍትሔ እንዲያገኝ ሲወስን፣ የተጠርጣሪውን ወይም የተከሳሹን ፈቃደኝነትና ጥፋተኛ ለማሰኘት የሚያስችል ማስረጃ መኖሩን ማረጋገጥ እንደሚገባው፣ ዓቃቤ ሕግ ወይም ፍርድ ቤት እንደነገሩ ሁኔታ ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ተደጋጋሚ ወንጀለኛ ሆኖ ካገኙት ጉዳዩ በባህላዊ ሥርዓት እንዳይታይ ሊወስኑ እንደሚችሉ ረቂቁ ይደነግጋል።

በባህላዊ የፍትሕ አማራጭ ሥርዓት ውስጥ ክልከላ የተጣለባቸው ተግባራትም በረቂቁ ተካተዋል። በዚህም መሠረት ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ በፈጸመው አንድ የወንጀል ጉዳይ ላይ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ባህላዊ ሥርዓቶችን ተፈጻሚ ማድረግ፣ ወይም ተከሳሹ ያልተቀበለውን ባህላዊ ሥርዓት ተፈጻሚ ማድረግ፣ ወይም ባህላዊ ሥርዓቱን ከሌላ መፍትሔ ጋር መቀላቀል የተከለከለ መሆኑን ረቂቁ ያመለክታል።

ረቂቅ ሕጉ አጠቃላይ የአገሪቱን ፍርድ ቤቶች የዳኝነት የሥልጣን ወሰን፣ ከነባራዊው የፌዴራል ሥርዓት ጋር የተጣጣመ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ይዟል።

በዚህም መሠረት የክልል ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስን በተመለከተ የሚኖራቸው የዳኝነነት ሥልጣን በክልል መንግሥት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ላይ፣ የወንጀሉ አፈጻጸም ከአንድ የአስተዳደር ክልል በላይ ያልወጣ ወይም ያልተፈጸመ ከሆነ፣ እንዲሁም አንድ ክልል ከሚያስተዳድረው የአስተዳደር ክልል በላይ በሆኑ ቀላል የወንጀል ጉዳይ ላይና ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ባልተሰጡ ጉዳዮች ላይ የመዳኘት ሥልጣን እንደሚኖራቸው የረቂቁ ድንጋጌዎች ያለመለክታሉ።

ከላይ የተቀመጡት እንዳሉ ሆነው፣ የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች በተለየ ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ተቋማት ውስጥ በተቋማት፣ በንብረቶች፣ በገንዘብና በሰነዶች ላይ በሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ላይ የመዳኘት ሥልጣን እንደሚኖራቸው ይደነግጋል።

በሌላ በኩል ረቂቅ አዋጁ ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ ላይ የሚሰጡት የቅጣት ውሳኔን አፈጻጸምን የተመለከቱ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ድንጋጌዎችን አካቷል። ከእነዚህም መካከል አንዱ ፍርድ ቤቶች የሚወስኑት የሞት ቅጣት በቀጥታ ሊፈጸም እንደማይችል የረቂቁ ድንጋጌዎች ይመለክታሉ።

በዚህም መሠረት ማንኛውም የሞት ቅጣት ውሳኔ ይግባኝ ቢቀርብበትም ባይቀርብበትም፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚሰየሙ አምስት ዳኞች የቅጣት ውሳኔው ዳግም እንደሚታይ ተደንግጓል።

ለዚህም ሲባል ማንኛውም ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ሲወስን ውሳኔውንና የመዝገቡን ግልባጭ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የማስተላለፍ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም አምስት ዳኞች በመሰየም የቀረበለትን የሞት ቅጣት ውሳኔ በመመርመር ተገቢነቱን አረጋግጦ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ረቂቁ ያመለክታል።

ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሚያሳውቅ እንደሚሆን፣ የሞት ቅጣቱን ተፈጻሚ ለማድረግም ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሞት ቅጣቱ ላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን፣ በይቅርታ ወይም በምሕረት ያልተሻረ ወይም ያልተለወጠ መሆኑን አረጋገጦ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር በማቅረብ ሲያፀድቅ እንደሚሆን ረቂቁ ይደነግጋል።

በተጨማሪም የሞት ፍርድ በማንኛውም ምክንያት ሳይፈጸም ከሁለት ዓመት በላይ የቆየ እንደሆነ፣ ወደ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንደሚቀየር ረቂቁ ይደነግጋል።

ከላይ በተቀመጡት ድንጋጌዎች ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎች፣ መንግሥት የሞት ቅጣትን በሕግ ለማስቀረት ባይፈልግም የተቀመጡት ድንጋጌዎች በአመዛኙ የሞት ቅጣት ተፈጻሚነትን ሊያስቀሩ እንደሚችሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በማከልም የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው ቅጣቱ ያልተፈጸመባቸው ከአገር ውጭ የሚገኙ ፍርደኞች ወደ አገር ተመልሰው የእስር ቅጣት እንዲፈጸምባቸው ፈቃደኛ ከሆኑ ድንጋጌው የሞት ቅጣቱን ተፈጻሚነት ሊያስቀርላቸው እንደሚችል ገልጸዋል።

የእስራት ቅጣቱን መቀበል ከጀመሩ በኋላ ደግሞ በምሕረት ወይም በይቅርታ አማራጮች ቅጣቱ ቀሪ ሊሆንላቸው እንደሚችል አስረድተዋል። የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ወይም በአገር ውስጥ የማይገኙ የደርግ ባለሥልጣናት ይህ ረቂቅ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ ተጠቃሚ ለመሆን የሚችሉት፣ እጃቸውን ሰጥተው የዕድሜ ልክ የእስራት ቅጣት አፈጻጸም ከተጀመረ በኋላ ሊሆን እንደሚችል አክለዋል።

በረቂቅ ሕጉ ከተካተቱ ቅጣትን የተመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች መካከል፣ በፍርድ ቤት የእስር ቅጣት የተወሰነበት ጥፋተኛ የቅጣቱ ተፈጻሚነት ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘምለት ለማድረግ የሚችልባቸው ሥነ ሥርዓቶች ተጠቃሽ ናቸው።

በዚህም መሠረት በፍርድ ቤት የእስራት ቅጣት የተወሰነበት ፍርደኛ በጠና በመታመሙ የተነሳ በማረሚያ ቤት ቅጣቱን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ፣ ፍርድ ቤቱ ከሕመሙ እስኪድን አስፈላጊ ነው ብሎ ሲወስን ለተወሰነው ጊዜ ያህል ቅጣቱ ሊተላለፍለት ይችላል።https://www.ethiopianreporter.com/article/20099
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
a_handbook_on_the_criminal_code.docx
522.4 KB
A Handbook on the Criminal Code of
Ethiopia
Dejene Girma Janka
(LL.B (Addis Ababa University, Ethiopia), LL.M (University of
Pretoria, South Africa), PhD (University of Alabama, USA))
Assistant Professor, School of Law, Jimma University
Visiting Professor, Law Schools of Bahir Dar and Gonder Universities
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Philippe Graven An Introduction to Ethiopian Penal Law.docx
1.2 MB
Philippe Graven
AN INTRODUCTION TO ETHIOPIAN PENAL LAW
(Arts. 1-84 Penal Code)
የገበሬው ህልውና የእኔም ነው‼️‼️
በስንቱ እንታመም‼️‼️‼️
አርሶ፤ ዘርቶ እና አርሞ ዛሬ ነገ እያለ በተስፋ ሲጠባበቀው የነበረው የእለት ጉርሱን የተነጠቀው ያገሬ ገበሬ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ሲሆን ያማል‼️‼️‼️
ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ እንሁን‼️‼️
Be Voice For The Voiceless
ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ ይሁኑ!!!
@lawsocieties
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Malcolm_N_Shaw_International_Law_Cambridge_University_Press_2008.pdf
7.8 MB
INTERNATIONAL LAW
Sixth edition
Malcolm Shaw’s engaging and authoritative International Law has become
the definitive textbook for instructors and students alike, in this increasingly popular field of academic study.
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
CASSATION OVER CASSATION.pdf
353.6 KB
የሰበር ሰበርና ተግዳሮቶቹ በIትዮጵያ

መሓሪ ረዳይ~
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Francis_Fukuyama_Identity_The_Demand_for_Dignity_and_the_Politics.pdf
1.9 MB
Description:
TheNew York Timesbestselling author ofThe Origins of Political Orderoffers a provocative examination of modern identity politics: its origins, its effects, and what it means for domestic and international affairs of state

In 2014, Francis Fukuyama wrote that American institutions were in decay, as the state was progressively captured by powerful interest groups. Two years later, his predictions were borne out by the rise to power of a series of political outsiders whose economic nationalism and authoritarian tendencies threatened to destabilize the entire international order. These populist nationalists seek direct charismatic connection to "the people," who are usually defined in narrow identity terms that offer an irresistible call to an in-group and exclude large parts of the population as a whole.
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Criminal Procedure Code Draft.pdf
1.9 MB
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዐት እና የማስረጃ ሕግ
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Ethiopian_Criminal_Procedure_pdf.pdf
1.1 MB
CRIMINAL PROCEDURE LAW
PRINCIPLES, RULES AND PRACTICES
Simeneh Kiros Assefa
(LL. B., Addis Ababa University, 1998; LL. M., University of Pretoria, 2002; LL. M., Kyushu University, 2006; LL. M., University of San Francisco, 2008)
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 700 በላይ መዝገቦች በእርቅ መቋረጣቸውን ገለጸ!

በደቡብ ክልል የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 700 በላይ መዝገቦች በእርቅ መቋረጣቸውን ገልጿል፡፡የዞኑ ህዝብ ለባህላዊ የሙግት፣ ዕርቅ እና ይቅር ባይነት ያለው እምነት የፀና ነው ያሉት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት አቶ መኩሪያ ፈለሃ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 1 ሺህ 764 የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች በእረቅ እንዲቋረጡ መደረጉን አስታውቀዋል።

@BBC amharic
የዳኝነት ነፃነት ይበልጥ እውን እንዲሆን ከተፈለገ በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ ሞያ ነጻ መሆን አለበት። ነጻ ያልሆነ የሕግ ባለሞያ ዳኛ ሆኖ በነጻነት ለመሥራት ብዙ ፈተና ይገጥመዋል። ስለዚህ ሙያውን ነጻ የሆነ የሙያ ማህበር እንዲቆጣጠረው በሕግ በአዋጅ መብት ሊሰጠው ይገባል። ዳኞችም በዋናው የሕግ ባለሞያ ማሕበር ውስጥ የሚሳተፉበት ሁኔታ ሊመቻች ይገባል። የነጻ ሙያ ማህበር አባል ያልሆነ፣ በሙያው ሥነ ምግባር ደንብ ለመገዛት ግዴታ ገብቶ ያልፈረመ፣ ለሙያው ብቻ ተገዢ ለመሆን ቃል ኪዳን ያልገባ፣ ከሙያው በላይ ሌላ አለቃ ያለው ዳኛ የግል ስብዕና ጥንካሬ ከሌለው በስተቀር ለሙያው ተገዢ ለመሆን በጣም ፈተና ያጋጥመዋል። ለሁለት ጌታ መገዛት አይቻልም። ዳኛ መገዛት ያለበት ለሙያው ብቻ ነው። በሌላ አባባል ዳኛ ለሕግ ተገዢ መሆን የሚችለው ለሙያው ብቻ ተገዢ ሲሆን ነው። ይህ ይበልጥ እውን የሚሆነው ዳኛው የነጻ ሙያ ማህበር አባል ሲሆንና ነጻው የሙያ ማህበር የዳኛውን አሿሿም፣ ስነምግባር፣ መብት፣ ጥቅም እና ስንብት መቆጣጠር እና መከታተል ሲችል ብቻ ነው። ስለዚህ ፍርድ ቤቱ፣ ዳኞች፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ፣ ጠበቆች፣ የሕግ ባለሞያዎች በሙሉ፣ መንግሥት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ህዝብ ለዚህ እውን መሆን ቢሠሩ ጥሩ ነው።
በታምራት ኪዳነማሪያም
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የድምፅ ብክለት

(ከኪዳኔ መካሻ)

አንድ እለት ከአንድ ወዳጄ ጋር አመሻሹ ላይ ሜክሲኮ አካባቢ ስናልፍ ጎን ለጎን ሆነን መደማመጥ አቃተን። የታክሲ ረዳቶች ጥሪ፣ የመኪና ጥሩንባ፣ ለእንቶኔ ህክምና እርዳታ ስጡ ብሎ በትልቅ ድምፅ ማጉያ የሚማፀን ድምፅ፣ የዘማሪት አገሊት መዝሙር በሲዲ ግዙ የሚል ጆሮ የሚበጥስ ማስታወቂያ፣ የመንገድ ላይ እቃ ነጋዴዎች እና የሌሎችም የድምፅ ውርጅብኞች ከጆሮ አልፎ ልብን ያስጨንቃሉ።

ወዳጄ ከረብሻው ድምፅ እስክንርቅ እያጣደፈኝ ጥቂት ራቅ ካልን በኋላ
‘‘በዚህ አያያዛችን ከጥቂት አመታት በኋላ በከተማችን አዋጩ ሸቀጥ ፀጥታ ይሆናል፡፡ አይገኝም እንጂ በመሀል ከተማ ፀጥ ብለህ መንፈስህን የምታረጋጋበት ቦታ ከተገኘ ላለማበድ ስትል የተጠየከውን ትከፍላለህ።’’ አለኝ።
ትንሽ አጋነንከው ብለውም የከተማችን ድምፆች ጤና አጥተው ጤና እያሳጡን መምጣታቸው ላይ ግን የወዳጄን ሀሳብ ተጋርቻለሁ፡፡

ለመሆኑ የድምፅ ብክለትን ሀይ ባይ ሕግ የለም እንዴ?

መኖርስ አለ።ያው ሕጉን ባግባቡ የሚያስከብር ነው የጠፋው።

የድምፅ ብክለት ጤናማ ህይወት ለመምራት የሚስፈልገንን ጤናማ አካባቢ በመበከል ስነልቦናዊ እና አካላዊ ጤናችን እንዲጓደል ያደርጋል።
በሕገ መንግስታችን አንቀ 44 ላይ ጤናማና ንፁህ የሆነ አካባቢ ውስጥ የመኖር መብት አለን፡፡በአንቀጽ 92 ላይም መንግስት ጤናማና ንፁህ አካባቢ እንዲኖረን የአቅሙን ጥረት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎበታል።
ሌሎች ለጉዳያቸው በሚያወጡት ድምፅ አካባቢያችን እንዳይበከል ከአካባቢው መራቅ ወይም የፀጥታ ያለህ ማለት ይጠበቅብንም በድምፅም አለመረበሽ ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው፡፡

በ1952 ዓ.ም የወጣው የፍትሀ ብሔር ሕጋችን በቁጥር 1225 ላይ ማንኛውም ሰው ጎረቤቶቹችን እንዲያስብ አስጠንቅቋል፡፡በይዞታችሁና በንብረታችሁ ስተጠቀሙ ከመጠን አልፎ የጎረቤታችሁን ጥቅም እንዳይቀንስ ወይም እንዳይጎዳ አድርጉ ብሏል፡፡ በተለይ ጢስ፣ ጥላሸት፣ጎረቤት ሊታገሰው ከሚችለው በላይ ሽታ፣ ጩኸት ፣ንውፅታ ( የድምፅ ብክለት) ጎረቤት ላይ መፍጠር እንደማይቻል ደንግጓል፡፡

የአካባቢ ብክለት መቆጣጠሪያ አዋጅ ቁጥር 300/1995 ላይ አካባቢ በካይ ከሚባሉት ነገሮች መሀል ጤናን የሚጎዱና የሚያውኩ ድምፅና ንዝረቶችን ተካተዋል። በአንቀጽ 3 ላይ ማንም ሰው የተቀመጠውን የአካባቢ ጥበቃ ደረጃ በመተላለፍ በድምፅም ሆነ በሌሎች ነገሮች አካባቢን መበከል እንደማይችል ደንግጓል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ደግሞ የዓለም የጤና ድርጅት ባስቀመጠው መለኪያ መሰረት ከፍተኛውን የሚፈቀድ የድምፅ መጠን አስቀምጧል፡፡
ለመኖሪያ አካባቢ ማታ 55 ቀን 45 ዴሲብል፤
ለንግድ አካባቢ ማታ 65 ቀን 55 ዴሲብል፤ ለኢንዱስትሪ አካባቢ ምሽት 75 ቀን 70 ዴሲብል በላይ ድምፅ ማውጣት አካባቢን ይበክላል ብሏል።

ይህ መለኪያ ምን ያህል የድምፅ መጠን ነው? የሚለውን በፅሁፍ ለማሳየት ቢያስቸግርም፤ እንደየ አካባቢው አገልግሎትና ድምፅ እንደሚወጣበት ጊዜ ከተቀመጠው የድምፅ መጠን በላይ መጠቀም በድምፅ ያለመበከል መብታችንን መጣስ መሆኑንና ለድምፅም የተቀመጠ ገደብ መኖሩን ያሳያል፡፡የድምፁ መጠን በሕግ ከተፈቀደው በላይ መሆኑንም በዘርፉ እውቀቱ ያላቸው ባለሙያዎች ልኬቱን እንዲያካሂዱ በማድረግ ማስረዳት ይቻላል። እንደ ግለሰብ ግን በአንድ አካባቢ ላይ የሚሰማው ድምፅ ጤናማ ኑሮን ለመምራት በሚፈጥርብን መታወክ የድምፅ ብክለት እንዳለ ለማወቅ አይከብድም።

በማስታወቂያ ሰበብ የድምፅ ማጉያ መሳሪያ በመጠቀም ከተቀመጠው የድምፅ መጠን ገደብ በላይ ተጠቅሞ አካባቢን መበከልም በማስታወቂያ አዋጁ 759/2004 አንቀጽ 7(7) ላይ በሕገ ወጥ ተግባርነቱ ተከልክሏል፡፡

የድምፅ ብክለትን መፈፀም በአካባቢ ብክለት መቆጣጠሪያ አዋጁ አንቀጽ 16 ከ1ሺ - 10 ሺ ብር መቀጮ ወይም ከ1-10 አመት እስር ሊያስቀጣ እንደሚችልና ለጥፋቱ የዋለው ንብረት እደሚወረስ ብክለቱን ግለሰቡ /ተቋሙ/ እንዲያቆም ወይም ተገቢውን ካሳ እንዲክስ ፍ/ቤቶች ሊወሰኑ እንደሚችሉም ተደንግጓል፡፡
ከተፈቀደው ድምፅ በላይ በመጠቀም ማስታወቂያ ያስተዋወቀም በማስታወቂያ አዋጁ አንቀጽ 34(ሐ) መሠረት ከ20ሺ-150 ሺ ብር ቅጣት ይቀጣል፡፡

ከላይ የጠቀስኳቸው ሕጎች የወጡት ከመጠን ባለፈ ድምፅ እንዳንታወክ ጥበቃ ሊያረጉልን ነው። ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች፣የመንግስትና የግል ተቋማት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ሌሎችም እነዚህን ሕጎች ችላ በማለት በሚጠቀሟቸው ድምፆች አካባቢያችንን ሲያውኩ ይስተዋላል፡፡
የሚመለከታቸው የደንብ ማስከበርና የአስተዳደር አካላት ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። የድምፅ ብክለት የሚፈፅሙ ሰዎችንም የየአካባቢው ነዋሪዎች ለሕግ አካላት ጥቆማ መስጠት ሰላማዊና ጤነኛ የመኖሪያ አካባቢ እንዲፈጠር እገዛ ማድረግ አለባቸው።

መብትን ማስከበር መብትን ከማወቅ ይጀምራልና ፅሁፉን ለወዳጆቻችሁ አጋሩት። እነዚህ ሕጎችና ገደቦች እያሉ መረን በተለቀቀ ድምፅ መረበሽና መታወክ አለብን?
🎤 ❤️በምትችለው ሁሉ ለወከለህ ህዝብ መታገል ትልቅ ጀግንነት ነው‼️‼️
ሜክሲኮ ውስጥ ነው። አንድ የፓርላማ አባል ድንገት በጦፈ ክርህር ውስጥ ልብሱን አውልቆ በመጣል ለፓርላማ አባላቱ እንዲህ ሲል በስሜት ይናገራል። "የእኔ በዚህ ቦታ ራቁቴን መታየት ያሳፍራችሁ ይሆናል፤ ነገር ግን ገንዘባቸውና ሀብታቸው የዘረፋቹሁባቸው ዜጎች ጎዳና ላይ ራቁታቸው ሆነው፣ ተስፋን ቆርጠው፣ ስራ አጥ ሆነው ተርበዋል! እናንተ ግንሲል ለፓርላማው ተናግሯል፡፡ የኛዎቹስ ትግላቸው እስከምን ድረስ ነው.
የግል ክብር ከህዝብ አደራ ቃል አይበልጥም‼️‼️
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በችሎቶች እና ጉዳዮች ድልድል ላይ የተደረገ ማስተካከያ
********************************************
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 11 ችሎቶች አደራጅቶ በይግባኝና በሰበር የሚቀርቡለትን ጉዳዮች እየተመለከተ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ እያንዳንዱ ችሎት የሚመለከታቸው የጉዳዮች ዓይነት ላይ መለስተኛ ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃው እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
በ1ኛ ሰበር ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከውርስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከንግድና ሌሎች ማህበራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከግብርና እና ከጉምሩክ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከላይ ከተመለከቱት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ2ኛ ሰበር ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከጠቅላላ ውልና ልዩ ልዩ ውሎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከውል ውጪ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከመንግስት ሰራተኛ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ለ1ኛ ሰበር ችሎት እና ለ3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ያልተደለደሉ ጉዳዮች፣
 ከላይ ከተመለከቱት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ3ኛ ሰበር ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከንብረት ጋር የተያያዙ ክርክሮች (ቤት፣ተንቀሳቃሽ ንብረትና የከተማ ቦታ ይዞታ)፣
 ከእርሻ መሬት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች (ይዞታና ሁከት ይወገድ)፣
 ከወንጀል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከጥብቅና ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከላይ ከተመለከቱት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ1ኛ አጣሪ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከእርሻ መሬት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች (ይዘትና ሁከት ይወገድ)፣
 ከውል ውጪ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከንግድና ሌሎች ማህበራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከአፈጻጸም ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ለ2ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት በግልጽ ያልተደለደሉ ጉዳዮች፣
 ከላይ ከተዘረዘሩት ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ2ኛ አጣሪ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 የወንጀል ጉዳዮች
 ከጠቅላላ ውልና ልዩ ልዩ ውሎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከባንክና ኢንሹራንስ ውል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከንብረት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከውርስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከግብርና እና ጉሙሩክ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከላይ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
 ከይዞታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ሁከት ይወገድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
በ1ኛ ፍትሐብሔር ይግባኝ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከጠቅላላና ልዩ ልዩ ውሎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከውል ውጪ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ለዚህ ችሎት ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ2ኛ ፍትሐብሔር ይግባኝ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከግንባታ ውል (ኮንስትራክሽን)ውል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከንግድና ሌሎች ማህበራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከአፈጻጸም ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ለችሎቱ ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ3ኛ ፍትሐብሔር ይግባኝ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 ከውርስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከግብርና እና ጉምሩክ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከስልጣን ይለይልኝ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣
 ከንብረት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች(ቤት፣ተንቀሳቃሽ ንብረት፣ከተማ ቦታ ይዞታ)
 ለ1ኛ እና ለ2ኛ ፍታሐብሔር ይግባኝ ሰሚ ችሎት በግልጽ ያልተደለደሉ ሌሎች ጉዳዮች፣
 ለችሎቱ ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
በ1ኛ ወንጀል ይግባኝ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 የሙስና ወንጀል(አዋጅ ቁጥር 881(2007)፣
 የእምነት ማጉደል ወንጀሎች፣
 የማታለል ወንጀሎች(ከአንቀጽ 692 እስከ 75 ድረስ የተመለከቱት)፣
 የኮምፒውተር ወንጀሎች(አዲሱ አዋጅ)፣
 በመንግስት የኢኮኖሚና የገንዘብ ጥቅሞች የሚደረጉ ወንጀሎች፣
 ከታክስና ከግብር ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣
 የጉምሩክ ወንጀሎች፣
 በታወቁ ገንዘቦች፣የግዴታ ወይም የዋስትና ሰነዶች፣ማህተሞች፣ቴምብሮች ወይም መሳሪያዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 በህዝብ ፀጥታና በማጓጓዣዎች ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 ለችሎቱ ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የዋስትናና ጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮች፣
 ለችሎቱ ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮች፣
 ለ2ኛ ወንጀል ችሎት በግልጽ ያልተደለደሉ ሌሎች የወንጀል ጉዳዮች፣
 ለሁለቱም ችሎቶች የተደለደሉ ጉዳዮች ተቀላቅለው በአንድ ላይ የቀረቡ ጉዳዮች ይመለከታል፡፡
በ2ኛ ወንጀል ይግባኝ ችሎት የሚታዩ ጉዳዮች
 በመንግስት፣በአገርና በዓለም አቀፍ ጥቅሞች ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች(ከወንጀል ህግ አንቀጽ 238 እስከ 283 ድረስ ያሉት)፣
 ሽብርን ለመከላከል የወጣ አዋጅ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣
 በሰው ህይወት የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 በሰው አካልና ጤና ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 የሰውን ህይወት፣አካል ወይም ጤንነት ለአደጋ በማጋለጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 በሰው የግል ነጻነቶች የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 በክብር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች(ስድብ፣ስም ማጥፋት)፣
 በመልክ ፀባይና በቤተዘመዳሞች የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 የውንብድና ወንጀሎች፣
 የስርቆት ወንጀሎች፣
 በፍትህ አስተዳደር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
 ለችሎቱ ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የዋስትናና ጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮች፣
 ለችሎቱ ከተደለደሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የማስፈቀጃ ጉዳዮችን ይመለከታሉ፡፡
ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሬጂስትራር ጽ/ቤት