አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የገዛ ባሏን በመርዝ የገደለችው ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ዋቁማ ጡሪ እንዳስታወቁት በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ ውስጥ በምትኖረው ተከሳሽ ወይዘሮ እልፍነሽ በቀለ ጅራታ ላይውሳኔው የተላለፈው ባሏን አቶ አዳነ አሰፋውን በመርዝ መግደሏ በመረጋገጡ ነው።

ሟች ከኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ከተበደሩት 86ሺህ ብር ውስጥ 10ሺህ ብር እንዲሰጣት ጠይቃ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ቂም ይዛ መርዝና አይብ በማደባለቅ መጋቢት 01/2011ዓ.ም ከምሽቱ በግምት አራት ሰዓት አካባቢ እንዲመገብ አድርጋለች።

ወደ መኝታ ክፍል እንደገባም በሩን በውጭ በኩል ዘግታ መሞቱን ካረጋገጠች በኋላ ራሱን በራሱ የገደለ ለማስመሰል ’’ፀፀት’’ ተብሎ የተፃፈና ሁለት ገጽ ያለው ወረቀት በደረቱ ላይ አስቀምጣ መኖሪያ ቤቱን በመዝጋት ንብረት ስታሸሽ መያዟን አመልክተዋል።

የተከሳሿ ድርጊት በዞኑ ዓቃቤ ሕግየሕግ ምሥክሮች በመረጋገጡ፣ ራሷም የፈጸመችውን ድርጊት ማመኗንና የመከላከያ ማስረጃም የለኝም ማለቷን አቶ ዋቁማ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግንቦት 21/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ ሆን ብላ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት ተዘጋጅታ የፈጸመችው ድርጊት በመሆኑ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

Via #ENA
🛑🛑🛑🛑🛑ውድ የህግ ቤተሰቦች
እንኳን አደረሳችሁ🔴🔴🔴🔴
2012......ዓ.ም
🤔ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ 1 ነጥብ 75 ግራም የጆሮ ጌጥ ወርቅ የዋጠው ዶሮ!

ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ወርቅ ይውጣል። ነገሩ የተከሰተው ጳጉሜ 03 ቀን 2011 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡ ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።

ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤትና የወርቋ ባለቤት ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው ወዲያው ታርዶ ወርቃቸው እንዲሰጣቸው ቢሹም የዶሮው ባለቤት ደግሞ በጉዳዩ አልተስማሙም።

ነገሩ መክረሩን ያዩት ገቢያተኞች ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ በማድረግ በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡ ጉዳዩ እንግዳ የሆነበት የወሊሶ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጣቢያም ጉዳያቸውን በመስማማት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል።

የዶሮው ባላቤትም ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው የሚያወጣውን ዋጋ ከፍለው ዶሮውን ይረከቡኝ ሲሉ ይስማማሉ። አቶ ደነቅም የወርቁ ባለቤት 250 ብር እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ባለ ወርቋ የተጠየቀውን ብር የለኝም በማለታቸው 150 ብር ሰጥተዋቸው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ነው የወሊሶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ከበደ በዳዳ የተናገሩት።

Via #ENA

https://telegram.me/lawsocieties
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ!

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ጀስቲስ ፎር ኦል የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት ናቸው።

መዝገበ ቃላቱን ለማዘጋጀት አራት ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ሲሆን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የሚዘጋጀው መዝገበ ቃላት በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች የአገሪቱ ቋንቋዎች የሚዘጋጅ መሆኑም ተጠቁሟል።

#ENA|📸FBC