አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአፍሪካ ህብረት ዛሬ "የአፍሪካ ሴቶች ቀን" አስመልክቶ በርካታ ሴት አፍሪካውያንን እያስታወሰ ይገኛል!

ከዚህ መሀል ሁለት ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ: ጣይቱ ብጡል (እቴጌ ጣይቱ) እና አትሌት ደራርቱ ቱሉ (ኮ/ል)።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'One Voice for Our Dam'

ለግድባችን ያለንን ድጋፍ ነገ እሁድ ሐምሌ 26/2012 ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሁላችንም በአንድ ላይ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በያለንበት ሆነን በዓለም አቀፍ ደረጃ ድምፃችንን እናሰማለን!

via tikvahethiopia
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
የፌዴራል ፍ/ቤቶች ዳኞች የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች ግንባታ ስራ ተጠነቆ ተመረቁ

የፌዴራል መንግስት ዳኞች በተመቻቸ ቦታ እንዲኖሩ በማድረግ የፍትህ ዘርፉን በተለይም የዳኝነት አካሉን ለማሻሻል ያስገነባቸው የዳኞች የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች ተገባደው አገልግሎት መስጠት የሚችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው የምረቃ ስነ ስርዓት ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

የዳኝነት አካሉን ነጻነት ለማረጋገጥ መንግስት እየወሰዳቸው ካሉ ተጨባጭ ተግባራት መካከል የዳኞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን ማሻሻል ሲሆን ለዚህም ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው ዳኞች በመኖሪያ ቤት ኪራይ የሚደርስባቸውን እንግልትና ተጽእኖ ለመቀነስ ደረጃውን የጠበቀ የጋራ መኖሪያ ቤት ገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉ ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ምንስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ሃገራችን የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል፤ የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደረጋገጡ በምታደርገው ከፍተኛ ጥረት ውስጥ ትልቁ ኃላፊነትና ሸክም የተጣለባችሁ የፌዴራል ዳኞች ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍናን ለማሻሻል፤ ጥራትን ለማሳደግ እና ነጻነትን ለማስጠበቅ ብሎም ዳኞች በሙሉ አቅማቸው በዳኝነት ሰራ ላይ እንዲያውሉ በማድረግ በኩል የዛሬው ፕሮጀክት መጠናቀቅ ያለው ትርጉም እጅግ ታላቅ ነው ብለዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አመነው ዳኞችን በመወከል ባስተላለፉት መልዕክት የዳኝነት ነጻነት መነሻና መድረሻው የህብረተሰቡን የፍትህ ጥያቄ መመለስ ነው፡፡ የዳኝነት ነጻነት በተቋም እና በግለሰብ ደረጃ ሊገለጽ የሚችል ነው ካሉ በኋላ በህገመንግስት የተረጋገጠውን የዳኝነት ነጻነት ተግባራዊ ለማድረግ በመንግስት በተወሰዱ እርምጃዎቸ ውስጥ ምቹ የስራ ቦታ እና ሁኔታ መፍጠር ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ዳኛ ብርሃኑ መንግስት በቅርብ ዓመታት የዳኞች ግለሰባዊ ነጻነትን ለማረጋገጥ ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ምስክርነት ሲሰጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ከታክሲና ከከተማ አውቶቡስ ሰልፍ ተላቀው በየግላቸው መኪና የተመደበላቸው መሆኑ፤ በየደረጃው ፍርድ ቤት ያሉ ዳኞች በተቋሙ የትራንስፖርት አገልግሎ እንዲጠቀሙ መደረጉ እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ፍ/ቤቶች ላሉት ዳኞች የደሞዝና የጥቅማጥቅም ማሻሻያ መደረጉ እና ዛሬ ደግሞ የዳኞች የመኖሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ ተጠናቆ በመረከባችን የዳኞች ዘርፈብዙ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ መሆናቸውን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በስነስዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለህንጻዎቹ ግንባታ መጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለተጫወቱና ሃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ አካላት ምስጋናቸውን ገልጸው መንግስት የዳኝነት ዘርፉን ለመደገፍ እየወሰደ ያለው እርምጃ ትልቅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዳኞች ቤታቸው መኖሪያ ብቻ ሳይሆን ከስራ መብዛት የተነሳ መዝገብ የሚመረምሩበት እና ውሳኔ የሚሰጡበት ቢሮም ነው፡፡ እንዲህ ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶች የዳኞችን የስራ አቅም የሚያጎለብቱና የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ብርታት የሚሰጧቸው ናቸው ብለዋል፡፡

አያይዘውም የጋራ መኖሪያ ህንጻዎቹ የተለያየ ቤተሰብ ሳይሆን የዳኝነት አካሉ አንድ ትልቅ ቤተሰብ የሚኖርበት በመሆናቸው የጋራ መኖሪያ አካባቢው ደረጃውና ክብሩ ተጠብቆለት፤ ንጹህና ያማረ ሆኖ የዳኝነት ከብር መገለጫ እዲሆን የማስተዳደሩን ስራ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ኃላፊነቱን ወስዶ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊና የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለጻዲቅ ተ/አረጋይ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ እንደገለጹት የዳኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከ9 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞለት የተጀመረ ቢሆንም ከታሰበለት በታች ከ750 ሚሊዮን ብር ባልበለጠ በጀት ተጠናቋል፡፡

ለዳኞች መኖሪያነት የተገነቡት ህንጻዎች ሁለት መንትያ ሕንጻዎች ሲሆኑ እያንዳንዳቸው ባለ G+18 ፎቅ ናቸው፡፡ ህንጻዎቹ 140 ባለ ሶስት መኝታ እና 138 ባለ ሁለት መኝታ ቤቶች በድምሩ 278 ቤቶች አሉት፡፡ በምረቃ ወቅት 80 ቤቶች ማለትም 40 ባለ ሶስት አና 40 ባለ ሁለት መኝታ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለባለ ዕድለኞች ዝግጁ ሆነዋል፡፡ እንደ ፕሮጅክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሪፖርት ቀሪዎቹ 198 ቤቶች የቀራቸው የማጠናቀቂያ እቃዎች ተገጥመውላቸው እስከ ነሓሴ 30/ 2012 ዓ.ም ለሚፈለገው ዓላማ ይውላሉ፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የ80 ቤቶች ቁልፍ ርክክብ የተካሄደ ሲሆን የናሙና ቤቶች ጉብኝት ተደርጓል፡፡ የህንጻ ተቋራጭ ድርጅቱ መሃንዲስ የሆነት ኢንጂነር ቴዎድሮሰ ስለ ግንባታው ሂደትና ይዘት ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የፌራደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የህንጻ ግንባታ ተቋራጭ ድርጅት ባለሙያዎች የአረንጓዴ አሻራቸውን ለማስቀመጥ በቅጥር ጊቢው ዙሪያ ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

መገናኛ አካባቢ እየተገነባ ያለው የዳኞች የጋራ መኖሪያ ቦታ 7 ሺህ 316 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን የጋራ መኖሪያ ህንጻዎቹ የመኪና ማቆሚያ፣ የገበያ ማዕከል፣ ስፖርት መስሪያ ማዕከል፣ የህጻናት መጫወቻ ክፍል፣ ቤተ-መጽሃፍት እና ሌሎችን ያሟላ እንደሚሆን የህንጻው ንድፍ ያሳያል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም ለድህረ ምረቃ ትምህርት በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ የትምህርት አሰጣጡ የኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ እስከሚሻሻል ድረስ በቨርቹዋል እና በኢለርኒግ የመማር ማስተማር መንገድ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ በገጽ ለገጽ የሚካሄድ መሆኑን እያሳወቀ የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር 600 /ስድስት መቶ/ የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል (ክፍያ የሚፈጸምበትን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 አጭር ኮዶች ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት በዩኒቨርሰቲው ድረ ገጽ እና በፌስቡክ እናሳውቃለን)፡፡
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን$፣ እንዲሁም ለቀን መርሃ ግብር የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም አስገብተው እና ሌሎች መረጃዎችን በማከል ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
4. የSponsorship ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ (portal.aau.edu.et/ aau.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ለPhD አመልካቾች የ yBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት እና የMA/MSC ዲግሪና ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
6. በተጨማሪም ለPhD አመልካቾች ትምህርት ክፍሉ የሚጠይቀውን ማያያዝ ይኖርብዎታል፡፡
7.ለMA/MSC አመልካቾች የ yBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ
• ምዝገባው የሚከናወነው aau.edu.et ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
• የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን ማስረጃ ዋናውን በተጠየቃችሁ ግዜ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
• ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡
• የፈተና ግዜውን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (portal.aau.edu.et/aau.edu.et) መከታተል የምትችሉ ያሳውቃል፡፡
• ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
• የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የመመዝገቢያ ቀን ከነሐሴ 06 እስከ ነሐሴ 21 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
http://www.aau.edu.et/
Hello, I have just read AAU application for postgraduate and PhD programs for next year in Ale, I want to ask what about the undergraduate who will finish next year have they taken us into consideration like they have in health school to apply and learn, or is there a possibility to apply when we finish in maximum of 2 months?
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሬጂስትራር ጽ/ቤት ከነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ መዝገብ ለመክፈት የወጣ መርሃ-ግብር
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ፍ/ቤቱ በወጣው መመሪያ መሰረት አዲስ ፋይሎች የመክፈት አገልግሎት ከነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም ምክንያት ባለጉዳዮች በተመሳሳይ ቀን ወደ ፍ/ቤቱ በብዛት በመምጣት መጨናነቅ እንዳይፈጠርና ተገልጋዩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሊወሰድ የሚገባውን አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲችል ከአዲስ አበባም ሆነ ከክልል የሚመጡ ባለጉዳዮች የሚስተናገዱበት መርሃ ግብር አውጥቷል፡፡ የፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር ጽ/ቤትም ተገልጋዮች ከዚህ በታች በተዘጋጀው መርሃ ግብር መሰረት በመምጣት አገልግሎቱን ማገኘት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል፡፡
1. የሰበር አጣሪ ባለጉዳዮች
1.1. የመጨረሻ ውሳኔ ከታህሳስ 10- ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሰጠባቸው መዝገቦች ከነሐሴ 1 - 8 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
1.2. የመጨረሻ ውሳኔ ከየካቲት 1- 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሰጠባቸው መዝገቦች ከነሐሴ 11- 15 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
1.3. የመጨረሻ ውሳኔ ከሚያዚያ 1 - 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሰጠባቸው መዝገቦች ከነሐሴ 18 - 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
1.4. በመረጃ እጥረት ምክንያት በፕሮግራሙ መሰረት ቀርበው ያልተስተናገዱ ባለጉዳዮች ካሉ ከነሓሴ 25 - 29 ቀን 2012 ዓ.ም ይስተናገዳሉ፡፡
2. የወንጀል ይግባኝ ባይ ባለጉዳዮች
2.1. ከየካቲት 10 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የውሳኔ ግልባጭ የደረሳቸው ባለጉዳዮች ከነሐሴ 1- 8 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
2.2. ከሚያዚያ 1 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የውሳኔ ግልባጭ የደረሳቸው ባለጉዳዮች ከነሐሴ 11- 15 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
2.3. ከሰኔ 1 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም የውሳኔ ግልባጭ የደረሳቸው ባለጉዳዮች ከነሐሴ 18 – 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
2.4. በመረጃ እጥረት ምክንያት በፕሮግራሙ መሰረት ቀርበው ያልተስተናገዱ ባለጉዳዮች ካሉ ከነሓሴ 25 - 29 ቀን 2012 ዓ.ም ይስተናገዳሉ፡፡
3. የፍትሐብሔር ይግባኝ ባለጉዳዮች
3.1. ከጥር 10 እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የውሳኔ ግልባጭ የደረሳቸው ባለጉዳዮች ከነሐሴ 1- 8 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
3.2. ከመጋቢት 1 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም የውሳኔ ግልባጭ የደረሳቸው ባለጉዳዮች ከነሐሴ 11- 15 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
3.3. ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የውሳኔ ግልባጭ የደረሳቸው ባለጉዳዮች ከነሐሴ 18 – 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀርበው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
3.4. በመረጃ እጥረት ምክንያት በፕሮግራሙ መሰረት ቀርበው ያልተስተናገዱ ባለጉዳዮች ካሉ ከነሓሴ 25 - 29 ቀን 2012 ዓ.ም ይስተናገዳሉ፡፡
4. በኢ- ፋይሊንግ ጉዳያቸውን ለሚያቀርቡ ባለጉዳዮች
ከላይ ለሰበር አጣሪ፣ ለወንጀል እና ለፍትሐብሔት ይግባኝ ባለጉዳዮች በወጣ ው መርሃ-ግብር መሰረት በክልሎች በሚገኙ ተወካዮቻችን በኩል የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ
• የወንጀል ይግባኝ መርሃ ግብር ታሳቢ ያደረገው ይግባኝ ባዮች የውሳኔ ግልባጭ ጠይቀው መሸኛ የተሰጠበትን ቀን ነው፡፡
• አስቸኳይነት ያላቸው ጉዳዮች ተብለው በመመሪያው የተለዩ ጉዳዮች ከሓምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡
• የሰበር፤ የወንጀል እና የፍትሐብሔት ይግባን ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈባቸው ባለጉዳዮች ያለፕሮግራም ከ ሐምሌ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡
• ፋይል ለማስከፈት የሚቀርቡ ባለጉዳዮች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) መጠቀም ግዴታ ነው፡፡ እንዲሁም ፍ/ቤቱ ባዘጋጀው በንጽህና መጠበቂያ ውሃና ሳሙና እጃቸውን መታጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመግቢያ በር አካባቢ ባሉ ባለሙያዎች ሙቀታቸውን ተለክተው ወደ ግቢው እንዲገቡ ይገደዳሉ፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሬጂስትራር ጽ/ቤት
ጤና ይስጥልኝ! የዛሬ ስድስት ወር አካባቢ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የረዳት ዳኞች ምዝገባ ብንመዘገብም እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም የፌደራል አቃቢ ህግም ተመዝግበን ነበር ግን እስካሁን አልፈጠሩም። አዲስ ነገር ካለ ብታሳውቁን please.
Hello! How are you doing? Can I get the English version of the Draft Commercial Code?
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት ለ15 ሺህ 563 መዛግብት እልባት ሰጠ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት ለ19 ሺህ 981 መዛግብት እልባት ለመስጠት ከያዘው ዕቅድ ውስጥ ለ15 ሺህ 563 መዛግብት እልባት የሰጠ ሲሆን ይህም በበጀት ዓመቱ ከቀረቡለት 18 ሺህ 928 መዛግብት አንጻር አፈጻጸሙ 82.22 በመቶ መሆኑን ያሳያል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች በዳኝነት ዘርፉ የ2012 ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ነሐሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ባካሄዱት የጋራ ውይይት የመዝገብ አፈጻጸሙ ፍርድ ቤቱ በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በከፊል ዝግ ሆኖ በቆየበት ጊዜ ጭምር የተመዘገበ በመሆኑ አበረታች ውጤት የታየበት እንደነበር ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በፍርድ ቤቱ ዕልባት እንዲያገኙ በዕቅድ ከተያዙት መዛግብት መካከል ከሐምሌ 2011 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2012 ዓ.ም መጀመሪያ ማለትም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ እስከተወሰነበት ጊዜ ድረስ ዕልባት ማግኘት ከሚገባቸው 13,987 መዛግብት ውስጥ 12,085 መዛግብት ዕልባት በማግኘታቸው በተጠቀሰው ጊዜ ፍርድ ቤቱ የዕቅዱን 86.4% መፈጸም እንደቻለ በቀረበው ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

ፍ/ቤቱ ከመጋቢት 2012 ዓ.ም መጀመሪያ ሳምንት በኋላ በከፊል ዝግ ሆኖ እንዲቆይ መወሰኑን ተከትሎ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በቀጠሮ ላይ ከሚገኙ እንዲሁም አዲሰ እና እንደገና ከተከፈቱ 6 ሺህ 840 መዛግብት መካከል ለ3 ሺህ 478 መዘግብት እልባት መሰጠቱም ተነግሯል፡፡

እልባት ከተሰጣቸው 15 ሺህ 563 መዛግብት መካከል 14 ሺህ 780 ጉዳዮች ወይም 95 በመቶ ያህሉ ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ያገኙ ናቸው፡፡

በሪፖርቱ ላይ በተደረው ውይይት ከመዛግብት አፈጻጸም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ በዕቅድ ባስቀመጣቸው ግቦች ላይ በተለይም የዳኝነት ነጻነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት መርሆች አፈጻጸምን ለማሻሻል፣ የዳኝነት ጥራትን ለማሳደግ፣ የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍናን ለማጎልበት እንዲሁም የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በተሰሩ ስራዎች ላይ በሰፊው ውይይት ተካሂዷል፡፡

የሶስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሆኑት የፌዴራል ጠቅላይ፣ ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች በ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸማቸው ላይ ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም የጋራ ውይይት በማድረግ በቀጣይ ስራዎች ላይ አቅጣጫ እንዲሚያስቀምጡ ታውቋል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Hey Ale እንዴት ናችሁ?


Journal of Ethiopian Lawyers Association የሰኔ 2010 E.C የት ማግኘት እችላለሁ?
Andargachew.docx
11.3 KB
Dear sisters and Brothers,

I attached the questionnaire below. I am waiting for your genuine and timely response. Please, Pass my gratitude to those who are cooperating.


Peace and Grace be yours in abundance.
abuschharald@gmail.com
1596861400949_Revised Questionnaire for Unity Park Visitors.docx
20.4 KB
Dear sisters and Brothers,

I attached the questionnaire below. I am waiting for your genuine and timely response. Please, Pass my gratitude to those who are cooperating.


Peace and Grace be yours in abundance.
abuschharald@gmail.com
ሩሲያ ይፋ ያደረገችው ክትባት ውጤታማ ስለመሆኑ አለማረጋገጡን ዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 8/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአዲስ ተገኘ በተባለው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጉዳይ ከሩሲያ ጋር እየተወያየ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ሩሲያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኗን ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። ከ20 በላይ ሀገራት 1 ቢሊዮን ብልቃጥ ክትባት ማዘዛቸውንም ሞስኮ ገልጻለች።

የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ በክትባቱ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልገው ገልጿል። በመረጃው መሠረት የቀጣይ ሂደት እንደሚወሰንም አስታውቋል።

ከአለም ጤና ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከ 170 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች የተለያዩ የግምገማ ደረጃዎችን አልፈዋል። ከእነዚህ ውስጥ 26 የሚሆኑት በሕክምና የሙከራ ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው። ቀሪዎቹ ደግሞ በቅድመ የሕክምና ሙከራ ሂደት ላይ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ በዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛዎች ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሩሲያ ጥቅም ላይ ያዋለችው አዲስ ክትባትም በሕክምና የሙከራ ሂደት ላይ ካሉት መካከል የተካተተ ነው።

ክትባቱ ውጤታማ ስለመሆኑ በዓለም ጤና ድርጅት ያልተረጋገጠ መሆኑ ተመላክቷል። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ብሩስ ባስተላለፉት አጭር የቪዲዮ መልዕክት ስለ ክትባቱ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጠናቀር፣ የሙከራ ሂደቱ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ እና የተገኘውን ውጤት ለመረዳት ከሩሲያ መንግሥት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። ከውይይቱ በኋላም ቀጣይ መደረግ የሚገባቸው ጉዳዮች እንደሚወሰኑ ከፍተኛ አማካሪው ገልጸዋል።

ሩሲያ የመጀመሪያውን ክትባት ማግኘቷን ለመግለጽ ችኮላ እንደታየባትም አናዶሉ ዘግቧል። የኮሮናቫይረስን ስርጭት ውጤታማ በሆነ መልኩ መከላከል የሚያስችል ክትባት ከተገኘ የዓለም ጤና ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አመላክቷል።

እንደ አናዶሉ ዘገባ ውጤታማ የምርምር ሥራዎችን ለማፋጠን የዓለም ጤና ድርጅት የማበረታቻ መርሃ ግብር አለው፤ ነገር ግን የክትባቱ ምቹነት እና ውጤታማነት እንዲታወቅ የሚጠበቅበትን ሂደት ማለፍ ይኖርበታል።

በደጀኔ በቀለ
ጤና ይስጥልኝ! የዛሬ ስድስት ወር አካባቢ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የረዳት ዳኞች ምዝገባ ብንመዘገብም እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም የፌደራል አቃቢ ህግም ተመዝግበን ነበር ግን እስካሁን አልፈጠሩም። አዲስ ነገር ካለ ብታሳውቁን please.!?
#Ethiopia : የፓርቲ አባል ያልሆነ ሰው የጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆኖ ሲሾም በሀገራችን የመጀመሪያው ሰው መሆናቸው ነው ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ:: ዶ/ር ጌዲዮን ጥሩ እውቀት እና መልካም ጠባይን በአንድነት ከያዙ ሰዎች መካከል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ከፊት ተሰላፊ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። እነሆ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በመሆን በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ መሾማቸውን ሰምተናል:: እኛም "ይበል ያሰኛል" ብለናል።

እንኳን ደስ አለህ!! መልካም የስራ ዘመን
via Natnael