አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
567..:
Please share me tax legislations....abush HU
ራስን እንዴት መቀየር ይቻላል
ሕይወት በድንገተኛ አጋጣሚዎች ታጅባ መጓዟ የተፈጥሮ ግዴታ በመሆኑ በድንገት ሁሉም ነገር ቦታውን ሊለቅ ይችላል። በአጋጣሚዎች ሕይወት የመመሳቀሏን ያህል ቀን ጠብቆ ነገሮች የሚለወጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል።
ዘመኑን ሙሉ የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ኑሮ ሲመራ የነበረ ሰው ድንገት ሕይወቱ ተዘበራርቆ የማያውቀው ዓለም ውስጥ ሊገባ ይችላል። ታዲያ ከገባበት የችግር አዘቅት ለመውጣት የሚፈልግ ሰው ችግሩ በተከሰተባ ቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ማሰብና መፍትሔ ማፈላለግ ሰላማዊው ኑሮውን ለመመለስ ይጣጣራል።

ከገባበት ችግር ለመውጣት ቀዳዳውን ማግኘት የተሳነው ሰው ደግሞ በሚወስዳቸው የተሳሳቱ እርምጃዎች ከዕለት ዕለት ችግሩን እያወሳሰበው ይሄዳል።

«ዊኪ ሃው» የተባለ ድረ ገጽ በሕይወት አጋጣሚ ከገቡበት ጥሩ ያልሆነ መስመር ለመውጣትና ራስን ለመቀየር የሚረዱ ነጥቦች ብሎ ያስቀመጣቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል።

• ችግሮችን መለየት
ችግሮችን መለየት እራስን ለመለወጥ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል። ችግሩ ከታወቀ በኋላ «ለምን ሆነ፣ መቼ ሆነ፣ እንዴት ሆነ?» ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይቻላል። የመፍትሔ ሰበብ ተገኝቶ ለውጥ እስኪመጣ የተፈጠሩ ችግሮችን መለየት ወሳኝ ነው። የችግሮቹ ምክንያት በግልፅ ከታወቀ መፍትሔ ይገኝለታል።

• ለራስ ሃሳብ ቅድሚያ መስጠት
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ችግር በሚያጋጥማ ቸው ወቅት ራሳቸው የሚያፈልቁትን ሃሳብ ከመከተል ይልቅ በሰዎች ሃሳብ መመራት ያዘወትራሉ። ራስን በመቀየር ሂደት ውስጥ ግን ከሰው ሃሳብ ይልቅ የራስን አእምሮ ተጠቅሞ የለውጥ መንገድ መፈለግ ይደገፋል።
• ሁኔታዎች መቀያየር እንደሚችሉ ማመን
እራሱን መለወጥ የሚፈልግ ሰው በነገሮች ቦታቸውን መልቀቅና መያዝ ያምናል። አሁን የተረጋጋ የሚመስል ነገር ከቀናት በኋላ እንዳልነበር ሊሆን ይችላል። ሁሉም ነገር ሊመጣ እንደሚችል፣ እንደሚያጋጥም የሚያምን ሰው ጊዜው ሲደርስ በሚከሰተው ነገር ካለመሸበሩ በተጨማሪ ሕይወቱ አይናጋም። ምክንያቱም ቀድሞ ሊመጣ እንደሚችል ያውቅ ነበርና።

• ታጋሽ መሆን
የታጋሽነት ጥበብ እራስን ለመቀየር ከሚያስፈልጉ ጥበቦች አንዱ ነው። ራሱን መለወጥ የሚፈልግ ሰው ሁሉንም እንዳመጣጡ መመለስና ሁሉንም መቻል አለበት። የሚያጋጥ ሙትን ችግሮች በፊት ከሚፈታበት በተሻለና ማስተዋል በተሞላበት መንገድ መፍታት ይጠበቅበታል። ለዚህ ደግሞ ትዕግስተኛ መሆን የግድ ነው ።
ምህረት ደበበ:
የሕግ ተገዥ ነኝ የሚል መሪ ሃሳብ ያለው የፍትሕ ወር ከጋዜጠኞ ጋር በተደረገ ኮንፍረንስ ተጀመሯል::
Meaza Ashenafi
በፍትሕ ወሩ ከሚደረጉ ተግባራት መሐል በሽግግር ወቅት የመደበኛ ፍትህ ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ የሚደረግ ውይይት ሲሆን የዕርቅና የሽግግር ፍትሕ ደጋፊ ሚናም ላይ ዳሰሳ ይደረጋል።
በተጨማሪም በፍትሕና የሕግ የበላይነት ላይ የሚያተኩር ሕዝባዊ መድረክ፣ አሳታፊ የጥበብ ክዋኔዎች የሚደረጉ ይሆናል።
Meaza Ashenafi
The #Federal Justice Sector Steering Committee launches the #Justice Month with a press conference.
#Meaza Ashenafi
President of the supreme court of Federal Democratic republic of Ethiopia‼️
A+ for euta. hahaha... euta:
Hello admin pls sle judicial training meche registration endemijemr info kalachu post btaderguln beteley ye dire dawa ena ye adis abeba ketema newari yehonen temerakiwoch geragebtonal😒😳😔☺️ please please info.
dialogue platform on the draft administrative procedure proclamation. 
FDRE Attorney General Legal and Justice Affairs Advisory Council Secretariat.
one day stakeholders discussion on the
🔴 "Draft Administrative Procedure Proclamation". 
ተሳታፊዎች
ፖለቲካ ፓርቲዎች
የህግ ባለማያዎች
CSO organizations
government body's
special guests
የፌደራል የአስተዳደር ተቋሞች
የአሠራር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ
(ረቂቅ)
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
🔴በሌላ አለ ዜና ዛሬ......

የፍትሕ ወር በተለያዩ ፍትሕ ነክ ክንውኖች እንደሚከበር ተገለጸ

የፍትሕ ወር "የሕግ ተገዥ ነኝ!" በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ፍትሕ ነክ ዝግጅቶች እንደሚከበር የፌዴራል ፍትህ አካላት ጥምረት አብይ ኮሚቴ ሐምሌ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገለጹ፡፡

አምስቱ የፍትሕ አካላት በመባል የሚታወቁት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በመሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ "የፍትሕ ሳምንት" በማዘጋጀት ሕብረተሰቡ ስለፍትሕ አስፈላጊነት ግንዛቤ እንዲኖረውና ለፍትሕ መስፈን የድርሻውን እንዲወጣ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ሲካሄዱ መቆታቸውን አስታውሰው ዘንድሮ በሚከበረው የፍትሕ ወር ደግሞ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የሚሆኑባቸው የውይይት መድረኮችና አሳታፊ የሥነጥበብ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ በመግጫቸው ጠቁመዋል፡፡

አገራችን በለውጥ ሒደት ላይ መሆንዋን የገለጹትና ይህም በአንድ በኩል ተስፋ በሌላ በኩል ደግሞ ተግዳሮቶችን ይዞ እንደሚመጣ የገለጹት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በአገራዊ ለውጡ አማካኝነት በፍትሕ ዘርፉ የሚኖረውን መልካም አጋጣሚዎች ለማጠናከር እንዲሁም በዘርፉ ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ትክክለኛ መስመር አስይዞ ሕብረተሰቡ የፍትሕ ተጠቃሚ እንዲሆን በቅርበት ማወያየት እንደሚገባ አስምረውበታል፡፡

በፍትሕ ወር ከሚካሄዱ የተለያዩ ፕሮግራሞች የመጀመሪያው ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄደውና 300 ያህል ተጋባዦች የሚሳተፉበት ሃገር አቀፍ ፎረም እደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡ ፎረሙ በሽግግር ወቅት በመደበኛ የፍትሕ ስርዓቱ ላይ በሚያጋጥሙ ችግሮችና የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲሁም የሕብረተሰቡ ሚና የሚዳሰስበት መድረክ እንደሚሆነም አስገንዝበዋልዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ፍትህ ነክ የተውኔት፣ የዶክመንተሪ ፊልም የስዕል ኤግዚቢሽን እንደሚኖር በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተጠቀሰ ሲሆን የፍትሕ ወር ከመጠቃለሉ በፊት ደግሞ ከፍትሕና ከባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚወከሉ 3000 ያህል ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እንደሚኖርም ተገልጽዋል፡፡

የፍትሕ ወር በሚጀመርበትና በስካይ ላይት ሆቴል የሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በሚካሄደው መድረክ ላይ የክልል ርዕሰ-መስተዳድሮች፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችና ም/ፕሬዜዳንቶች፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የፌደራል ፍትሕ አካላት፣ የሲቪክ ማሕበረሰብ አባላትና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡

ዓብይ ኮሚቴው የአምስቱን የፍትህ ተቋማት ሃላፊዎች በአባልነት በመያዘ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሰብሳቢነት በ2002 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን የፍትህ ተቋማቱ ነጻነትና ገለልተኝነት እንደተጠበቀ በፍትህ ስርዓቱ በተለይም በወንጀል ፍትህ አስተዳደር የየራሳቸውን ሃላፊነት ሲወጡ በጋራ በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የአሰራርና የአደረጃጀት ማስተካከያዎች ለማድረግ የሚያስችሉ ሃሳቦችንም ያመነጫል፡፡

የፍትህ አካላት የሃገርን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥና ፍትህን ለማስፈን ወንጀልን የመከላከል፤ ተፈጽሞ ሲገኝ ተጠርጣሪዎችን በህግ ተጠያቂ የማድረግ፤ ዳኝነት የመስጠት በመጨረሻም አጥፊዎችን የማረም እና የማነጽ የተሳሰሩ ተግባራት የማከናወን ሃላፊነቶች ያለባቸው ናቸው፡፡

የፌዴራል የፍትህ አካላቱ ዓብይ ኮሚቴ የፍትህ ሳምንትን ለ8 ተከታታይ ዓመታት ያከበሩ ሲሆን ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ የፍትህ ወር በሚል ስያሜ እና የህግ ተገዢ ነኝ በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 26 ቀን ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች የሚከበር ይሆናል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት