አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
@lawsocieties @lawsocieties
በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ሲቂ ማሪያም አካባቢ የአስገድዶ #መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ #በእስራት ተቀጣ፡፡

የክሱ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ጫኔ ተሾመ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/2/ሀ/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ለአካለ መጠን ያልደረሰች የባለቤቱን እህት በቢላዋ እገልሻለሁ በማለት አስፈራርቶ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ዐቃቤ ሕግ የግል ተበዳይን ጉዳት የሚያስረዳ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተከሳሹ በሰራው ወንጀል ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 09 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት መዝገቡን መርመሮ ተከሳሹ ምንም አይነት ወንጀል ሰርቶ እንደማያውቅና የቤተሰብ አስተዳደሪ መሆኑን በማቅለያነት በመያዝ ተከሳሹን ያርማል በማለት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@lawsocieties @lawsocieties