አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Tg Sador:
Some of them are for HR and AU some of them for ITL
Jos A:
Hey there...can you plz share a book by Araya Kebede on conflict of family laws
Shêwã Zêd:
Eski mekerugn beka temro endet .......
ራሴን ያጋለጥኩለት ሁኔታ ምን ይመስላል?

ራስን አጋልጦ መስጠት ማለት አንድን ሰው ወይም ሁኔታ ይመጥነኛል ብለን ስላመንንበት ራሳችንን መክፈት ማለት ነው፡፡ በሕይወትህ የምትይዛቸው ወዳጆች አመለካከትህን ይጠቁማሉ፡፡

ለምሳሌ፣ የከበረ አመለካከት እያለህ ለተራ ነገር ለመስከን ከወሰነ ሰው ጋር ጓደኝነት መያዝ ያስቸግርሃል፡፡ ሰው ከመሆን አንጻር ሁሉም ሰው እኩል ነው፡፡ በየእለቱ ከሚወስዱት ውሳኔና ምርጫ አንጻር ግን ሰዎች የተለያየ ደረጃ አላቸው፡፡

“የከበረ” ሰው አለ፣ “ተራ” ሰው ደግሞ አለ፡፡ ይህንን የሰዎችን ደረጃ የወሰነው እድል ሳይሆን የሰዎቹ ምርጫና ውሳኔ ነው፡፡ ራስን ያከበረ ሰው ወደ ሕይወቱ የሚያስገባቸውን ሰዎች በጥንቃቄ በመምረጥ የሚኖር ሰው ነው፡፡

ለማንነትህ ከሚመጥነው በታች ከሆነ ሰውና ሁኔታ ለመጠበቅ ይህንን አስብ፡-

1. ራስህን እወቅ
ይህን ጥያቄ መመለስ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፣ ምክንያቱም ማንነቴን በሚገባ እንድገነዘብ፣ ከማንነቴ ጋር የሚመጥነውንና የማይመጥነውን እንድለይ ስለሚረዳኝ ነው፡፡ ራሴን በሚገባ ሳውቅ፣ ሳሻሽልና ሳከብር ራሴን ከተራው ነገር መጠበቅ እጀምራለሁ፡፡

2. መድረስ፣ ማድረግና መሆን የምትፈልገውን እወቅ
የወደፊት ራእያችን ጥራት ለራሳችን የምንሰጠውን ግምት ከፍ እንድናደርግ ያነሳሳናል፡፡ ይህ መልካም እይታ ወደ እኛ ሲመጣ ራሳችንን ወደ ማክበር እንመጣለን፡፡ የራእይ ጥራት ማንነትን የመቅረጽ ታላቅ ተጽእኖ አለውና፡፡

3. ወዳጅህን እወቅ
ራስህን አጋልጠህ የሰጠህለት ሰውና ሁኔታ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚስብህ ሰው ነው ወይስ ወደ ታች የሚያወርድህ? ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን መልስ በማግኘት ለማንነትህና ለራእይህ ክብር ከማይመጥን ሰው መለየት የግድ ነው፡፡
ምህረት ደበበ:

ሸር ...............
share........................
🔴🔴🔴🔴🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
#አለ 🛑 #ALE
🛑“እምቢ” ማለት ለምን ያስቸግረናል?

አንዴ ያለፈ ጊዜ ለዘለአለም ላይመለስና ዳግም እድል ላይሰጥ ሄዷል፡፡ ጊዜአችንን በሚገባ ለመጠቀም ከሚያስችሉን ጥበቦች መካከል “እሺ” በምንለውና “እምቢ” በምንለው ነገር መካከል መለየት አንጋፋው ነው፡፡ አንዳንዴ ግን ለሁሉም ነገር “እሺ” ወደ ማለት የመገደድ ሕይወት ውስጥ ስንገባ ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ ውጤቱም ከአላማችንና ከፍላጎታችን ውጪ በሆኑ ነገሮች ስንባክን ጊዜን ማባከን ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ለምንድን ነው?
ሁሉን ሰው የመርዳ ዝንባሌ፡- አንዳንድ ሰዎች እርዳታ የጠየቃቸውን ሰው ሁሉ መርዳት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፡፡

ክፉ መስሎ የመታየት ፍርሃት፡- የአንዳንድ ሰዎች እምቢ ማለት ያለመቻል ምንጩ “ሰዎች ክፉ ነው ብለው ያስቡኛል” የሚል መሰረት የለሽ ፍርሃት ነው፡፡
ከቡድን የመገለል ፍርሃት፡- “የቡድን መንፈስ” ከባድ የሆነ በሰዎች ላይ የመገደድን ስሜት የሚያመጣ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው በዙሪያው ከሚገኙት ወዳጆቹ መለየትን የሚፈራ ከሆነ የቡድኑ አባላት ለሚያቀርቡለት ሃሳብ ሁሉ ወደመስማማት ዝንባሌ ሊያመራ ይችላል፡፡

ግጭትን ፍርሃት፡- አንዳንድ ሰዎች የጠየቁንን ነገር በሙሉ ፈቃደኝነት ተስማምተን ካልተገበርን የመቆጣትና የመናደድ ባህሪ ስላላቸው ግዳጅ ውስጥ ይከቱናል፡፡
እድል ያመልጠኛል የሚል ፍርሃት፡- ምናልባት ለተጠየከው ነገር ሁሉ በእሺታ የምትስማማው አንድ እድል ያመልጠኛል ብለህ የምትሰጋ ሰው ስለሆንክ ይሆናል፡፡ ይህኛው ሰው ዛሬ ለጠየቀኝ ጥያቄ እምቢ ካልኩት ነገ ከእሱ ማግኘት የምፈልገውን ለማግኘት አልችልም የሚል ጫና እንደ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች “እምቢ” የሚባልን መልስ መስማት አይፈልጉም፡፡ ስለዚህ፣ የሚችሉትን መንገድ ተጠቅመው የእነርሱን ሃሳብ እንድታስፈጽም ጫና ያሳድሩብሃል፡፡ ከዚህ በታች የምንመለከተው እንደዚህ ያሉ ሰዎችን እንዴት እንደምንለያቸውና በምን መልክ ልንቀርባቸው እንደምንችል ነው፡፡

• “ሸንጋዮች” - አንድ አንድ ሰዎች እንድታደርግላቸው የሚፈልጉትን ነገር ለማስደረግ ወይም ደግሞ እንድትሄድላቸው ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ለመውሰድ ብዙ የማሞካሻ ቃላትን ሊደረድሩልህ ይችላሉ፡፡

• “ወቃሾች” - አንዳንድ ሰዎች ለሌላው ሰው ሁሉ ጊዜ ሲኖርህ ለእነርሱ ብቻ ጊዜ እንደሌለህና ከአንተ ብዙ ጠብቀው የጠበቁትን ስላላገኙ እንዳዘኑ ይነግሩህና በጥፋተኝነት ስሜት ከመቱህ በኋላ ስለተወቀስህ ሃሳባቸውን እንድትፈጽም ግፊት ያደርጉብሃል፡፡

• “አደናቃፊዎች” - አንዳንድ ሰዎች፣ “ለዛሬ ብቻ ይህንን ብታደርግ ምን ትሆናለህ” በሚል ቃል ካወጣኸው እቅድና መስመር እንድትወጣና ወደ እነርሱ ሃሳብ ዘንበል እድትል በመጫን ከመንገድህ ያደናቅፉሃል፡፡

• “ነጭናጮች” - አንዳንድ ሰዎች ሁል ጊዜ ለሰው የሚደርሱና የሰው ነገር ግድ የሚላቸው እነሱ ብቻ እንሆኑና አንተም ሆንክ ሌላው ሰው ለእነሱ ግድ እንደሌላችሁ በመነጫነጭ ከዚያ ንጭንጫቸው ለመዳን ስትል የመገደድ ስሜት እንዲሰማህ ያደርጉሃል፡፡

• “ጉልበተኞች” - አንዳንድ ሰዎች በአጭሩ ጉልበተኞች ናቸው፡፡ ዛቻን፣ ቁጣንና የማስፈራራትን ቃላት በመጠቀም ሊያጨናንቁህና የሚሉትን ነገር አድርገህላቸው ከዛቻቸው እፎይ እንድትል መንገዱን ሊያጠቡብህ ይሞክራሉ፡፡

መሰረታዊ እይታዎች
• ላላመንክበት ነገር እሺ ማለት የለብህም፡፡ ይህንን አስታውስ፣ አንድን ነገር ከልብህ ካላመንክበት ከውጪ በመጣብህ ግፊት ምክንያት ብቻ ያንን ነገር ማድረግ የለብህም፡፡

• ላላመንክበት ነገር እምቢ ማለትን ስትለምድ ራስህን ማስከበር እንደምት ጀምር አትዘንጋ፡፡ ሰዎች የሚያከብሩህ ራስህን ስታከብር ነው፡፡ ራስህን የማክበርህ አንዱ ምልክት ደግሞ ካመንክበት ነገር አንጻር የመኖር ሁኔታ ነው፡፡

• እርግጠኛ ላልሆንክበት ነገር ጊዜን መውሰድ ልመድ፡፡ ሰው ሁሉ ለሚጠይቅህ ጥያቄ እዚያው መልስ መስጠት የለብህም፡፡ ውስጥህ እርግጠኛ ላልሆነበት ነገር በቀጠሮ ማለፍን ልመድ፡፡

• የውስጥ ስሜትህን አድምጥ፡፡ ለአንድ ነገር እሺ ካልክ በኋላ በውስጥህ ግን የመገደድና የመጨቆን ስሜት ከተሰማህ፣ ቀድሞውኑ እምቢ ማለት እንደነበረብህ አስብና ከዚያ ልምምድ ተማር፡፡

• ኃይለ-ቃልን አስወግድ፡፡ ላላመንክበት ነገር እምቢ ለማለት የግድ ኃይለ-ቃል መጠቀም ወይም ክፉ መሆን የለብህም፡፡ ቀላል አቀራረብን መልመድና ከሰጠኸው ምላሽ ላለመወላወል መወሰን አለብህ፡፡

• “የሚያልቅ” ምክንያት አትስጥ፡፡ አንድን ነገር ላለማድረግ ስትፈልግ፣ “አሁን አሞኛል” ካልክ ሰውየው ነገ እስኪሻልህ ጠብቆ ይመለሳል፡፡ ይህ አላቂ ምክንያት ይባላል፡፡ በተቃራኒው ግን ነገሩን ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለህ በጥበብ ከመለስክለት ጉዳዩ እዚያ ላይ ያበቃል፡፡

• የሚቀበልህና የሚወድህ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ እሺም አልከው እምቢ አንተን ከመቀበል እንደማይከለክለው እወቅ፡፡ ይህንን ማወቅ ተቀባይነትን ላለማጣት ለመጣው ጥያቄ ሁሉ እሺ ከማለት ይጠብቅሃል፡፡

የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
በምህረት ደበበ.......

🔴(ለበለጠ እውቀት መጽሐፉን በገበያ ላይ ያገኙታል)🛑

👍
ሸር ...............
share........................
🔴🔴🔴🔴🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
#አለ 🛑 #ALE
🛑አመክሮ ማለት ምን ማለት ነው ?
🛑ለሕግ ታራሚ የሚሰጠው ጥቅ
ምን እንደሆን ስንቶቻችን እናውቃለን ?
››››››››››››››››››››››››››››››››››
ሰላም የተወደዳቹሁ እንባቢያ!! በአገራችን እንድ የሕግ
ታራሚ በአመክሮ ተለቀቀ ሲባል በሚዲያ ሁሌ
የምንሰማው ከጀሮችን ብዙ ያራቀ ግን በውል የማንረዳው
ቃል ነው፡፡ ለመሆኑ አመክሮ ማለት ምን ማለት ነው
ለሕግ እስረኛ የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው በሚል
ርዕሰ ጉዳይ ያላቹሁን ግንዛቤ ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ
ይህንን አሰረጂ ጥንቅር ይዘን ቀርበናል ተከታተሉን፡፡
አመክሮ የምንለው አንድ የሕግ እስረኛ የእስራት ቅጣት
ተወስኖበት ከእስራት ዘመኑ ሁለት ሦስተኛውን እንደፈጸመ
የጠባዩ መሻሻል በበቂ ሁኔታ ሲመሰከር ከእስር ቤት
እንዲፈታ የሚፈቀድበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህም ሲባል በሕጉ
የተወሰነው የአፈጻጸም ጊዜ ሲደርስና ጠቅላላው ሁኔታ
ተሟልቶ ሲገኝ ጥፋተኛውን በአመክሮ አስቀድሞ መልቀቅ
የሚቻል መሆኑን ያመለክታል፡፡ አመክሮ ጠባይ ማሻሻያና
ወደ ማህበራዊ ኑሮ መመለሻ መሳሪያ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ
አመክሮ የሚፈቀደው እስረኛው በጠባዩ ሆነ በጠቅላላ
ሁኔታው የሚሻል መሆኑ ሲታመንና ይህም ውጤት
የሚያስገኝ መሆኑ ሲታመን ነው፡፡
የአመክሮ ጊዜ አንድ የሕግ እስረኛ የተበየነበት ረጅም
የእስራት ጊዜ ከማለቁ በፊት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅሎ
ከአደገኛ ጥፋትና የወንጅል ድርጊት ተገትቶ የመልካም ስነ
- ምግባር ተገዥ ሆኖ ይኖር እንደሆነ የሚፈተሸበት ወቅት
ነው፡፡
በእስራት የተቀጣን የሕግ እስረኛ በአመክሮ ለመልቀቅ
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 207 የተጠቀሱትን
ቀጥለው የተመለከቱት ሁኔታዎች መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
1. የሕግ እስረኛው ከተፈረደበት የአስራት ዘመን ሁለት
ሦስተኛውን መፈጸሙን
2. እስረኛው በወኒ ቤት በነበረበት ጊዜ መልካም ጠባይ
ያሳየ
ለመሆኑ በቂና አጥጋቢ የምስክር ወረቀት ማግኘት
3. እስረኛው ከወኒ ቤት ሲወጣ ሥራ የሚያገኝ መሆኑ
መረጋገጡ
4. እስረኛው በተቀጣበት የወንጅል ክስ ከባላጋራው ጋር
ታርቆ
እንደሆነ የሚሉት ናቸው፡፡
የአመክሮ ሁኔታ ለሕግ እስረኛው ሊገለጽለት ይገባል፡፡
እስረኛው የተፈረደበት የእስራት ጊዜ ከማለቁ በፊት
የመፈታት ዕድል እንዲያጋጥመው ቢያውቀው መልካም
ነው፡፡ በእስራት ወቅት ምን አይነት ጠባይ ማሳየት
እንደሚገባው እንዲረዳ ማድረግ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
በተለይ የእስር ቤት ሹም በጠባዩ መሻሻል የሚያሳይ
እስረኛን ሁኔታ በመከታተል በአመክሮ ስለመፈታት የታዘዙት
ድንጋጌዎች የተፈጸሙ መሆናቸውን ሲረጋገጥ ራሱ ሹሙ
ስለ እስረኛው አስተያየት ለበላይ በማቅርብና የሕግ
እስረኛው አመክሮ እንዲታይለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ
ተቀብሎ የድጋፍ አስተያየቱን በማስፈር ለሚመለከተው
አካል በማስተላለፍ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
አመክሮ የጊዜ ገደብ እንዳለውም በሕጉ ተመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ አመክሮ የሚቆይበትን ጊዜ የመወሰን ሥልጣን
አለው፡፡ የዚህም ጊዜ ልክ ከሁለት አመት ያነሰ ከአምስት
አመት ሊበልጥ አይችልም፡፡ በተለይ በጽኑ እስራት ተወስኖ
እንዲኖር የተደረገና በተደጋጋሚ በወንጅል ድርጊት
የተሰማራ ግለሰብ ሲሆን የአመክሮ ጊዜው ከሁለት ዓመት
ሊያንስ አይችልም፡፡ በሌላ በኩል የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት
የተበየነበት ወንጀለኛ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ የአመክሮው ጊዜ
ከአምስት ዓመት የማይወርድ ይሆንል፡፡
በአመክሮ የተለቀቀ አጥፊ ተገቢ የሆነውን የጠባይ
አመራር ሥርዓት እንዲከተል ውሳኔ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡
በዚህ ጊዜ የእስረኛው የዕድሜ መጠን፣ የአመሉን ሁኔታ፣
ሊደርስበት የሚችለውን የአደጋ ሁኔታ፣ ከእስር ቤት ከወጣ
በኃላ ለሚኖርው የኑሮ ሁኔታ፣ የሙያ፣ ሥራውንና
የማህበራዊ ኑሮውን በተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ
ማስገባት አሰፈላጊ ይሆናል፡፡
በአመክሮ የመለቀቅ ትዕዛዝ የሚሻርበትም ሁኔታ በሕጉ
ተገልጿል፡፡ አመክሮ የመለቀቅ ትዕዛዝ በአጥገቢ ሁኔታ
ቢሻር እስረኛው መጀመሪያ ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ
ማድርግ ይቻላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ በአመክሮ
ተለቅቆ ያሳለፈውን ጊዜ ሊፈጸም የሚገባውን ቅጣት
ወይም የጥንቃቄ ተግባር መፈፀሚያ ከተወሰነበት ጊዜ
ጋር ሊታሰብበት አይችልም፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የሕግ
እስረኛው በመካከል አዲስ ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ የቅጣቱ
ወይም የጥንቃቄው ተግባር ውሳኔው የሚፈጸመው
በደንበኛው ድንጋጌ ላይ በተመለከተው መሰረት ይሆናል፡፡
በአንጻሩ የሕግ እስረኛው ለአመክሮ የተወሰነለትን ጊዜ
በመልካም ጠባይና አመራር የፈጸመ እንደሆነ፣
እስከመጨረሻው ነፃነቱን አግኝቶ ቅጣቱን በሙሉ
እንደሚቀርለት ሕጉ ለዚሁ አመች ሁኔታን ፈጥሮለታል፡፡
አንድ የሕግ እስረኛ ላይ በአንዳንድ ሥፍራ ከመድረሱ
የመከላከል፣ በአንድ የተወሰነ ሥፍራ ተገዶ የመኖርና
ከአገር ያለመውጣት ውሳኔ ተላልፎበት ከሆነ በአመክሮ
ጊዜ ፍርድ ቤት ይህን ሁኔታ አግዶ የሚቆይበትም ገደብ
በሕግ ተመልክቷል፡፡ይህ በሚደረግበት ጊዜ እስረኛው
የጠባይ መሻሻል ማሳየቱን፣ አደገኛ አዝማሚው
መለወጡን… ወዘተ.ከግምት ውስጥ ማስገባት
ያስፈልጋል፡፡ ፍርድ ቤት ይህን ሲያደርግ የሚመለከታቸውን
አስታዳዳሪዎች አስተያየት ይጠይቃል፡፡ እስረኛው በአመክሮ
ከተለቀቀ በኋላ ያሳየው ጠባይ አጥጋቢ ከሆነ ከአገር
እንዳይወጣ የሚከለክለውና ነፃነቱን የሚያሳጣውን ቅጣት
ጥፋቱን ሁለተኛ አይሰራውም ተብሎ ከተገመተ ሊነሳ
ይችላል፡፡
አንድ የሕግ እስረኛ የረጅም ጊዜ የእስራት ቅጣት
ቢበየንበት መደናገጡ የማይቀር ነው፡፡ መደናገጡ
አይበዛበትም፣ ምክንያቱም አስከፊ በሆነ ወንጀል ድርጊት
ባይዘፈቅ ኖሮ ይህ ዓይነቱ እጣ አይገጥመውም ነበርና፡፡
እስረኛው አሁን የረጅም ጊዜ እስራት ሲበየንበት አንድ
ሊያደርገው የሚችለው ነገር ይኖራል፡፡ይህም በጥፋት
ተጸጽቶ መልካም ዜጋ ለመሆን መጣር ነው፡፡ ዳግመኛ
በወንጀል ድርጊት እንዳይዘፈቅ ህብረተሰቡ የተቀበለውን
ሕግ እንዳይጥስ ጥንቃቄ ማድርግ ይኖርበታል፡፤ በእስር
ቤት ቆይታው ለዲሲፕሊን ተገዥ የመልካም ጠባይ
ባለቤት ሆኖ መታየት ይኖርበታል፡፡
በመልካም ዲሲፕሊን የታነጸ ዜጋ መሆን እንደሚችል
ማስመስከር ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ካደረገ ይቅርታ
ሊያገኝ፣ የሕግና የመንግስትን እንዲሁም የሕዝብን
ምህረት ሊጉናጸፍ ይችላል እያልን የኢትዮጵያ ተስፋ
በልጆቿ እጅ በመሆኑ የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ
ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ሰላም፣ ዕድገት፣ ዴሞክራሲ
በአንድነት መቆም ይጠበቅባቸዋል፡፡ከአገር የሚበልጥ
ምንም ዓይነት ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ጥቅም የለም፡፡
ለሕግ የበላይነት ክብደትና ክብር የማይሰጥ ሕገ-ወጥ
ብቻ ነው፡፡ መልካም ዜጋ የመልካም ፀባይ ባለቤት ነው፡፡

ALE (አለ) 👍
ሸር ...............
share........................
🔴🔴🔴🔴🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
#አለ 🛑 #ALE
ህግን በማክበር የህብረተሰቡን ጤና ከአደጋ፣ የሀገርን ኢኮኖሚ ከጉዳት እንጠብቅ፡፡
+....................🛑🔴🛑🔴
በተለምዶዉ ኮንትሮባንድ በመባል የሚታወቀው ህገወጥ
ንግድ ለመንግስት ግብር ወይም ቀረጥ ሊከፈልባቸው
ሲገባ ነገር ግን በተለያየ መንገድ ሸቀጦች ወይም
ንብረቶች በድብቅ ከሀገር የሚወጡበት እና የተለያዩ
ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚዘዋወሩበትን
ሁኔታ የሚገልፅ ነው፡፡ እንግዲህ ይህን ያህል የሚያወጣ
ወይንም የሚገመት የኮንትሮ ባንድ እቃ በቁጥጥር ስር
ዋለ ሲባል ስለምንሰማ ሁኔታው ለብዙዎቻችን አዲስ
አይሆንም፡፡ አንድ ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ እቃ ዝውውር
ሲደረግ መንግስት ማግኘት የሚገባውን የኢኮኖሚ ጥቅም
የሚያስቀር ከመሆኑ ሌላ፤ በህጋዊ መንገድ የንግድ ፍቃድ
አውጥተው ግብር ከፍለው በሚያስመጡ፣ በሚያከፋፍሉ
እንዲሁም ተመሳሳይ ምርቶችን ወደ ውጭ በህጋዊ
መንገድ በመላክ በንግድ የተሰማሩ ዜጎች ላይ ከፍተኛ
ኪሳራን በማስከተል ከንግድ ውድድሩ ተሸንፈዉ
እንዲወጡ ያደርጋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ንግድ በባህሪዉ ከቦታ
ቦታ የሚዘዋወርበት መንገድ ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ
ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለይ የምግብና መዳኒት ምርቶች
ጥራትና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ከማድረጉም በላይ
የአገልግሎት ጊዜያቸው በአብዛኛው ያለፈ ስለሚሆን
በህብረተሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግርን
የሚያስከትሉ ናቸዉ፡፡
ስለዚህ ይህን በሀገርና በህዝብ ህይወት ላይ ከፍተኛ
ጉዳት የሚያስከትለውን የኮንትሮባንድ ተግባር
በማስመልከት በ1997ዓ.ም የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ
በመንግስት የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ጥቅሞች ላይ
የሚፈፀሙ ወንጀሎች በሚለው ርዕስ ስር፤ በአንቀፅ 352
ላይ ኬላ መስበር ወይም ኮንትሮባንድ የሚያስከትለውን
የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡፡
የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 352(1)፣(ሀ) መሰረት
ማንም ሰው አስቦ በህግ የተወሰነ ግብር ወይም ቀረጥ
ያልተከፈለበትን ማናቸውንም አይነት የንግድ እቃ፣ ንብረት፣
ልዩ ልዩ እቃ የፋብሪካ ወይም የእጅ ጥበብ ስራ
የሚያፈራውን ማናቸውም አይነት ነገር ከኢትዮጵያ ወደ
ውጭ አገር ያስወጣ ወይም ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ
ያስገባ እንደሆነ፤ በአንቀፅ 352(1)፣(ለ) መሰረት ማንም
ሰው አስቦ ከላይ በፊደል (ሀ) የተመለከተው በህገ ወጥ
መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን እያወቀ፤ ይህንኑ
እቃ ወይም ንብረት ያከማቸ፣ ለሽያጭ ያቀረበ ወይም
የገዛ እንደሆነ፤ በአንቀፅ 352(1)፣(ሐ) መሰረት ደግሞ
ማንም ሰው አስቦ በአገር ዉስጥ ተመስርተው ቀረጥ
ሳይከፈልባቸው እንዳይዘዋወሩ የተከለከሉ እቃዎችን
ወይም ምርቶችን ያዘዋወረ እንደሆነ፤
በቅን ልቦና ለወንጀሉ ባዕድ የሆኑት ሰዎች መብት ሳይነካ፣
ወንጀሉ የተፈፀመበትን እቃ፣ መሳሪያና የወንጀሉን ፍሬ
ስለመውረስ የተደነገገዉ ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አስር
ሺ ብር (10,000) በማይበልጥ መቀጮ ወይም በቀላል
እስራት ይቀጣል በሚል ተመልክቷል፡፡
በዚሁ አንቀፅ 352 (2) መሰረት ደግሞ የኬላ መስበር
ወይም ኮንትሮባንድ ወንጀሉ የተፈፀመው በሀይል፣ በዛቻ፣
በማጭበርበር ወይም በቡድን ከሆነ፤ እቃዉ ውርስ ተደርጎ
ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ያስቀጣል
በመሆኑም ህግን በማክበር የህብረተሰቡን ህይወት
ከአደጋ እንጠብቅ፡፡

ALE (አለ)
🛑🛑🛑 ሼር share.......🛑🛑🛑
🔴🔴🔴🔴🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
ALE (አለ)
የራሱን ማንነት
በራሱ ጭንቅላት
ተሸክሞ መምራት
ያልተቻለው አንገት …
የቀኙን ከግራ
የፊቱን ከኋላ
አዙሮ መመልከት
አጢኖ መረዳት
እንዴት ሊሆንለት?
የራሱ ራስ ከብዶት
አወይ ጉድ ' #እኔነት

በዶ/ር ምህረት ደበበ
ALE (አለ) 👍
ሸር ...............
share........................
🔴🔴🔴🔴🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
#አለ 🛑 #ALE
Hu No One Is Parfect:
Please share if you have law succession ppt and logic ppt and law person ppt
Delil Ahmed:
Hi, labour note, kalachihu lakulign
ወንጀል‼️

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ኢትዮዽያዊንን ወደ ዉጭ ሀገር በመላክ ወንጅል የተከሰሰችው ረሂማ መህዲ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተባት ክስ በእስራት ተቀጣች፡፡

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሽ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 598/2/ እና /3/ የተመለከተውን በመተላለፍ የግል ተበዳይን ወደ ኳታር እንድልክህ 45 ሺ ብር ትከፍለኛለህ በማለት የፓስፖርትና የጤና ምርመራ ውጤቱን የተቀበለችው ሲሆን ከኳታር የመጣለትን ቪዛና ትኬት በመስጠት ጥቅምት 03 ቀን 2008 ዓ.ም በቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ በዱባይ በኩል በማድረግ ወደ ኳታር እንዲሄድ አድርጋለች፡፡

የግል ተበዳይ ኳታር ከደረሰ በኋላ አብዱራህማን ከድር የተባለው ግብረ አበሯ ተቀብሎት ከሌሎች ቁጥራቸው 40 ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ምግብና መኝታ በሌለበት በስቃይና በእንግልት ለሁለት ወር ያህል እንዲቆይ በማድረግ እና ተጨማሪ ገንዘብ በማስከፈል፣ ያለደሞዝ ስራ እንዲሰራ በማድረግ እንዲሁም በኳታር ፖሊስ ተይዞ ለ3 ወር ያለበቂ ምግብና መኝታ ታስሮ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲደርስበት በማድረጓ በፈጸመችው ወንጀል ተከሳለች፡፡

የክስ መዝገቡን የተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎትም ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ምስክር እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማየት ተከሳሽ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንድትቀጣ በማለት ሚያዚያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ወስኗል፡፡

ምንጭ፦የፌዳራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ