ህግ በተለያዩ ዓይነቶች ሊከፈል የሚችል ቢሆንም በቀላሉ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
ለአሁን ትኩረት የምንሰጠው በሰዎች ህግ ላይ ነው፡፡
በቀላል ትርጉም ሕግ ማለት የህብረተሰብ ሰላምና ኑሮ ጸጥታ ለመጠበቅ ከአንድ መንግሥት የወጣ መተዳደሪያ ደንብ ነው።
ህግ ማድረግ የሚገባንና ማድረግ የሌለብንን ይነግረናል፡፡ ማድርግ የሚገባንን ሳናደርግ ስንቀር ወይም ማድረግ የሌለብንን ፈጽመን ስንገኝ የሚፈጸምብን ቅጣት በህግ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ህግ የሚያስፈልገው ማድረግ ያለብንን ሳይፈጽሙ ወይም ማድረግ የሌለብንን የሚፈጽሙ ሰዎች ስላሉ ሰዎች በህግ መመራት ያለባቸው በመሆኑ ነው። የህግ መሠረታዊ መርህ - ህግን ማስከበር ህግን ይዞ ነው፡፡ ህግን ለማስከበር ከህግ ዉጪ መሆን አይፈቀድም፡፡ ከህግ ውጪ ሆኖ ህግን ለማስከበር የሚደረግ ጥረት ሁሉ ህገ ወጥ ነው፡፡
የተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ የማውጣት ስልጣን የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ ነው፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የማውጣት ስልጣን የሚመነጨው በተወካዮች ምክር ቤት ከሚወጣ አዋጅ ነው፡፡ መመሪያ የማውጣት ስልጣን የሚመነጨው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሚወጣ ደንብ ወይም በተወካዮች ምክር ቤት ከሚወጣ አዋጅ ነው፡፡ በህግ ስልጣን የተሰጣቸው የሚኒስትር መ/ቤቶችና ተቋማት መመሪያ የሚያወጡት በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 የተደነገገውን የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅን መሠረት በማድረግ ብቻ ነው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል እንደሆኑ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ ተደንግጓል፡፡
ለተቋማት በህግ የተከለከሉና ጨርሶ የማይፈቀዱ ድርጊቶች
1. የተወካዮች ምክር ቤት በህገ መንግሥቱ ስልጣን ባልተሰጠው ጉዳይ ላይ አዋጅ ማውጣት፣
2. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተወካዮች ምክር ቤት ከሚወጣ አዋጅ ውጪ ስልጣን ባልተሰጠው ጉዳይ ላይ ደንብ ማውጣት፣
3. የሚኒስትር መ/ቤቶችና ተቋማት መመሪያ ለማውጣት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሚወጣ ደንብ ወይም በተወካዮች ምክር ቤት ከሚወጣ አዋጅ ውጪ ስልጣን ባልተሰጣቸው ጉዳይ ላይ መመሪያ ማውጣት፣ መመሪያ ሲያወጡም በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 ከተደነገገውን የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ውጪ መመሪያ ማውጣት
አዋጅ ቁጥር 3/1987
የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ
አንቀጽ 2 የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ መቋቋም
1. የፌዴራል የህግ ጋዜጣ የሆነ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የሚወጣ የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡
2. ማናቸውም የፌዴራል መንግሥት ህግ የሚወጣው በፌዴራሉ ነጋሪት ጋዜጣ ይሆናል፡፡
3. ማናቸውም የፌዴራል ወይም የክልል ህግ አውጪ፣ አስፈፃሚና ተርጓሚ እንዲሁም ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የሚወጣ ህግን የመቀበል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
4. የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የሚታተመው በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይሆናል፣ በሁለቱ ቋንቋዎች መካከል ልዩነት በሚፈጠርበት ጊዜ የአማርኛው የበላይነት ይኖረዋል ፡፡
ህግ ሲጣስ ህግ የሚሰጠው ህጋዊ መፍትሄ “ህግን ማስከበር ህግን ይዞ ነው” የሚል ብቻ ነው፡፡
ከህግ ውጪ በሆነ መንገድ” ህግን ለማስከበር” መሞከር ከህግ ውጪ ነው፡፡ ህግን ማስከበር ህግን ይዞ ነው የሚለው አባባል ሲተነተን ህግ ተጥሶብኛል የሚለው ወገን ህግ በሚፈቅደው መንገድ ለሚመለከተው ፍትህ ሰጪ አካል አቤቱታውን ማቅረብ፣ ማስረጃዎቹን ማሰማት፣ በየደረጃው በተቀመጡ የፍትህ አካላት የተሰጠው ውሳኔ ፍትህ አላረጋገጠልኝም ብሎ ካመነ ህጉ ለሚፈቅደው የበላይ አካል እያመለከተ ህጉ እስከሚፈቅደው ጣሪያ ድረስ ይግባኝ እየጠየቀ መጓዝን ያካትታል፡፡
#Awoke_Asfaw_Authorized_Accountant_&_Tax_Consultant
https://www.linkedin.com/in/mikias-melak?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app
1. የተፈጥሮ ህግ - ምሳሌ ፡ the law of gravity
2. የሰዎች ህግ
ለአሁን ትኩረት የምንሰጠው በሰዎች ህግ ላይ ነው፡፡
በቀላል ትርጉም ሕግ ማለት የህብረተሰብ ሰላምና ኑሮ ጸጥታ ለመጠበቅ ከአንድ መንግሥት የወጣ መተዳደሪያ ደንብ ነው።
ህግ ማድረግ የሚገባንና ማድረግ የሌለብንን ይነግረናል፡፡ ማድርግ የሚገባንን ሳናደርግ ስንቀር ወይም ማድረግ የሌለብንን ፈጽመን ስንገኝ የሚፈጸምብን ቅጣት በህግ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ህግ የሚያስፈልገው ማድረግ ያለብንን ሳይፈጽሙ ወይም ማድረግ የሌለብንን የሚፈጽሙ ሰዎች ስላሉ ሰዎች በህግ መመራት ያለባቸው በመሆኑ ነው። የህግ መሠረታዊ መርህ - ህግን ማስከበር ህግን ይዞ ነው፡፡ ህግን ለማስከበር ከህግ ዉጪ መሆን አይፈቀድም፡፡ ከህግ ውጪ ሆኖ ህግን ለማስከበር የሚደረግ ጥረት ሁሉ ህገ ወጥ ነው፡፡
የህግ ደረጃዎች - በኢትዮጵያ ሁኔታ
1. ህገ መንግስት
2. በተወካዮች ምክር ቤት የሚወጣ ህግ - አዋጅ
3. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጣ ደንብ - ደንብ
4. በህግ ስልጣን በተሰጣቸው የሚኒስትር መ/ቤቶችና ተቋማት የሚወጣ መመሪያ - መመሪያ

👍21😁2❤1